የኢየሱስን እናት ብፅዕት ማርያምን አትሳደቡ! (2)
ማርያምን አትሳደቡ! (2) መግቢያ 1.ስሜ ማርያምና በስሜ ማርያም ፈውስ 2.ማርያም የክርስቶስ እናት መሆኗን መቼ አወቀች !? 3.የጥበብ ሰዎችና ስግደታቸው 4.አብርሃም ወደ ከነዓን ለምን ወጣ !? 5.ሎጥን ያዳነው ማን ነው !? 6.መላእክትን የሚያዘው ማን ነው !? 7.ለክርስቶስ መቃብር ጥበቃ ለምን ተቀጠረለት !? 8.ሰዎች ሁሉ ማንን ይለምናሉ !? 9.የሐዋርያት ሹመት በማርያም ነውን !? ማጠቃለያ ዋቢ መጽሐፍት መግቢያ! ከዚህ በፊት የቀረበውን ካነበባችሁ በኃላ እንደተጠቀማችሁ ተስፋ አደርጋለሁ ።የመጀመሪያ የጹሑፌ ዓላማ የኢየሱስን እናት እኔ (እኛ) እንደማል[ን]ሳደብ እና ማን እንደ ሚሳደብ በግልጽ ማሳየት ነበር።ይዚህኛው ዓላማ ግን የስህተት ትምህርት ዲቃላ ፍሬ ስለሚያፈራ በማሳየትም የበጉ የሆኑትን መለየት ነው ። ቃሉ እንደሚል “..፥ በጎቹም ድምፁን ያውቃሉና ይከተሉታል፤”— ዮሐንስ 10፥4 ፣ ስለዚህም የኢየሱስ የሆኑቱ ድምጹን ለይተው ያውቃሉ ፤ የሚከተሉትም እርሱንና እርሱን ብቻና ብቻ ነው።እረኛውን ስለሚያውቁ መጽሐፍ እንደሚል “ከሌላው ግን ይሸሻሉ እንጂ አይከተሉትም፥ የሌሎችን ድምፅ አያውቁምና።” — ዮሐንስ 10፥5 ።ስለዚህም ወዳጆቼ አንድ ሰው ሃሰተኛ ትምህርት ፦ አስተማሪ፣ነቢይ ፣ሐዋርያ .. የሚከተል ከሆነ እረኛውን የማውቅ ፣ድምጹንም የማይለይ ፣በግም ያለሆነ በመሆኑ ነው ማለት ነው።ባይሆንማ ቃሉ እንደሚል አይከተሉም።ይሸሹም ነበር ። ስለዚህም እንደ አንድ ክርስቲያን ሸክም እንደሚሰማው ሰው፣በእውነት ቃል ላይ ለዘመናት የተሸቃቀጠውን በመግልጽ እና...