ራዕይ ጥናት ከም.4-22
በዓለም ለሚከሰቱ ነገሮች ከበስተጀርባ ያለውን እውነታ ለማውቅ መጽሐፍ ቅዱስን እናጥና! እንወቀው! እንጽና ! (ራዕይ ጥናት ከም.4-22) “ከዚያ በኋላም አየሁ፥ እነሆም በሰማይ የተከፈተ ደጅ፥ እንደ መለከትም ሆኖ ሲናገረኝ የሰማሁት ፊተኛው ድምፅ፦ ወደዚህ ውጣና ከዚህ በኋላ ሊሆን የሚያስፈልገውን ነገር አሳይሃለሁ አለ።”ራእይ 4፥1 ዮሐንስ ስለ 7ቱ አብያተክርስቲያናት በአስቸኳይ ልሆን የሚገባውን ከተመለከተ በኃላ ፣ በምዕራፍ 4 ደግሞ ሌላ ገና ልሆን የሚገባው ነገር ይመለከታል ። (ራዕይ መጽሐፍ ያለፈ ታርክ እየተረከልን አይደለም ) “ወዲያው በመንፈስ ነበርሁ፤ እነሆም፥ ዙፋን በሰማይ ቆሞአል በዙፋኑም ላይ ተቀማጭ ነበረ፤”ራእይ 4፥2 ዮሐንስ አብ በዙፋኑ ተቀምጦ እያለ ይመለከታል ፣ “በዙፋኑ ዙሪያም ሀያ አራት ዙፋኖች ነበሩ፥ በዙፋኖቹም ላይ ነጭ ልብስ ለብሰው በራሳቸውም የወርቅ አክሊል ደፍተው ሀያ አራት ሽማግሌዎች ተቀምጠው ነበር።” ራእይ 4፥4 እነዚህ 24 ሽማግሌዎች የተባሉት በብሉይና በአድስ ክዳን ያሉቱ መላው የእግዚአብሔር ቤተሰብ ቁጥር ነው ፣ “ከዙፋኑም መብረቅና ድምፅ ነጐድጓድም ይወጣል፤ በዙፋኑም ፊት ሰባት የእሳት መብራቶች ይበሩ ነበር፥ እነርሱም ሰባቱ የእግዚአብሔር መናፍስት ናቸው።”ራእይ 4፥5 ዮሐንስ ስመለከት ሰባት(በሙላት) የእግዚአብሔር መንፈስ አለበት በዙፋኑ ፊት፣ “በዙፋኑም ፊት ብርሌ የሚመስል የብርጭቆ ባሕር ነበረ። በዙፋኑም መካከል በዙፋኑም ዙሪያ፥ በፊትና በኋላ ዓይኖች የሞሉአቸው አራት እንስሶች ነበሩ።”ራእይ 4፥6 ዮሐንስ ስመለከት አራት እንስሶች (በዓለም በአራቱ አጥቃጫዎች ያሉት ፍጥረታት በሙሉ በፊቱ አሉ፣...