የሐዋርያው የዮሐንስ መልእክት ለዛሬዋ ቤተክርስቲያን

የሐዋርያው የዮሐንስ መልእክት ለዛሬዋ ቤተክርስቲያን

የአንደኛው መልእክት ! ተጠንቀቁ !

ዮሐንስ መልእክቱን የጻፈበት ዓላማ ከስህተት ትምህርቶች ለመጠበቅ ነው።ፍጹም ደስታ የሚኖረው በትክክለኛ ትምህርት በተመሠረተ ነው 1፥4 በማለት ለትክክለኛ ትምህርቱም የዓይን እማኝ መሆኑንም ያበስራል 1፥1-3 ።ዝም ብሎ "ኢየሱስን አምኛለሁ" ብሉ
ምን ችግር አለው !? ለምን አስፈለገ የስህተት ትምህርት መቃወም !? ብሉ መልሱ ፦ 

“.፥ በእግዚአብሔር ማደሪያ ቤት መኖር እንዴት እንደሚገባ ታውቅ ዘንድ እጽፍልሃለሁ፤..።”1ኛ ጢሞ 3፥15 ፣እንደሚል በእግዚአብሔር ቤት ለመኖር እግዚአብሔርን መምሰል ያስፈልጋል ።

“እግዚአብሔርንም የመምሰል ምሥጢር ያለ ጥርጥር ታላቅ ነው፤ 1ኛ ጢሞ 3፥16

መምሰል የተባለው ቃል በግርኩ eusébeia የሚል ቃል ነው።እውነተኛ አምልኮ ማለት ነው።ስለዚህም የእውተኛ አምልኮ ሚስጥር ታላቅ ነው መጽሐፍ ይለናል ።እውነተኛ አምልኮ አምልኮችን ለመሆን ፦

“.፤ በሥጋ የተገለጠ፥ በመንፈስ የጸደቀ፥ ለመላእክት የታየ፥ በአሕዛብ የተሰበከ፥ በዓለም የታመነ፥ በክብር ያረገ።”1ኛ ጢሞ 3፥16 ፣ ይህንን በትክክል ማወቅ እና መቀበል ያስፈልጋል ።

ልክ እንደ ሐዋርያው ጳውሎስም ሐዋርያው ዮሐንስም ሙሉ ደስታ የሚኖረው " በትክክል እኛ በዐይናችን ያየነውን እና የተመለከትነውን ፣ከእርሱም የሰማነውን ስታምኑ ነው" በማለት ይህንን የመጀመሪያ መልእክት ጽፈውልናል።

ይገርማችኋል የኢየሱስ መሆን ኢየሱስ ኢየሱስ ዘወትር ማለት አይደለም።አምልኮ ዘወትር በጉባኤ መዘመርም ማሸብሸብም አይደለም ።ምክንያቱም እውነተኛ አምልኮ በትክክለኛ እውቀት የተመሠረተ ነው።በትክክለኛ እውቀት የተመሠረተ ሽብሸባም ዝማሬም የእውነተኛ አምልኮ ክፍል ነው። ስለዚህም ከዚህ ክፍል እውተኛ አምልኮ እንድኖራችሁ የስህተት ትምህርቶችን እናሳውቃለን እንቃወማለን እናስጠነቅቃለን ።

° "ሥጋችሁ በራሱ ሥጋ በመሆኑ ብቻ እርኩስ ነው"ማለትም ስህተት ነው ፣
° << የኢየሱስ ሥጋ የዳዊት ዘር አይደለም ሰውን የሚመስል ብቻ ነው >>ማለትም ስህተት ነው፣
° ኢየሱስ ሰው ሆኗል ።አምላክነቱን ሳይጥል። ኢየሱስ ሰው ብቻም አምላክ ብቻም አይደለም ፣
° ኢየሱስ ስጸነስም ስወለድም ስሞትም ስነሳም ስያርግም አሁንም ሙሉዕ ሰው ሙሉዑ አምላክ ነው፣
° ኢየሱስ የእውነትም ከነሥጋው ተነሳ ፣ ትንሳኤ ይህ ነው ።ትንሳኤ በመንፈስ ብቻ ነው ማለትም ስህተት ነወ፣ 
° ኢየሱስ ከሦስቱ አካላት አንዱ አካል ነው።"ወልድ የለም ፣ አብ ብቻ ነው" ማለትም ስህተት ነው፣
° ኢየሱስ ራሱ አብም ነው፣መንፈስ ቅዱስም ነው ማለትም ስህተት ነው፣ 
°ሞትን አሸንፎ የተነሳው በሥጋ የተገለጠው የመጣው ወልድ ነው።"አብ ነው፣ሚካኤል ነው በሥጋ የመጣው" ማለትም ስህተት ነው፣
° ኢየሱስ አንድያ ልጅ ነው ፣አቻ ነው ከአብ ጋር።"ሰው ራሱን አቻ ነኝ" ብል ስህተት ነው፣
° ኢየሱስ ብቻ ከአብ ተልኮ ከአብ ወጥቶ የመጣ ነው።ከፍጡራን መካከል ከአብ ወጥቶ የመጣ የለም ፣ "ከአብ ወጣው ማለት ኢየሱስ ነኝ ማለት ነው" ስህተት ነው፣
° ኢየሱስ ራሱ ክርስቶስ ነው ፣
° የዘላለም ሕይወት ሥጋን በመጨቆን ፣ በፉጡራን ልመና ፣ በፉጡራን ስም በመዘከር ፣ ..ወዘተ አይገኝም የለምም።የዘላለም ሕይወት ያለን በማመናችን ነው።

“የዘላለም ሕይወት እንዳላችሁ ታውቁ ዘንድ በእግዚአብሔር ልጅ ስም ለምታምኑ ይህን ጽፌላችኋለሁ።”1ኛ ዮሐ 5፥13

ስለዚህም ወዳጆቼ ትክክለኛ እና እውነተኛ የክርስቲና አምልኮ ፣በትክክል በቃሉ የተደገፈ የተገለጠውን እግዚአብሔርን በማወቅ ነው።ከዚህ ውጭ ያለው አምልኮተ እግዚአብሔር ሳይሆን አምልኮተ ዲያብሎስ ነው።

ዛሬም መልእክቱ ይህ ነው ፦

“ልጆች ሆይ፥ ከጣዖታት ራሳችሁን ጠብቁ።”1ኛ ዮሐንስ 5፥21 ፣(ጣኦታት የተባሉቱ ምንጩ ዲያብሎስ የሆነ ሃሰተኛ ትምህርት እንደሆነ ያውቁዋል፤ተጠበቁ፤በከንቱ እንዳትጠፉ)

ሁለተኛው መልእክት " አትቀበሉት !"

በዚህ በሁለተኛው ዮሐንስ መልእኩቱ ዮሐንስ ከሐሰተኞች ጋር በምንም ሕብረት አይኑራችሁ በማለት ያዝዛል ።

ምናልባትም እነዚህ ሃሰተኞች መጀመሪያ ትክክለኛ ወንጌል የሚሰብኩ ሳይሆኑ አይቀሩም።ምክንያቱም መጀመሪያ ከሐዋርያቱ ጋ መሆናቸውን ቃሉ ይገልጻል ፦

“ከእኛ ዘንድ ወጡ፥ ዳሩ ግን ከእኛ ወገን አልነበሩም፤ ከእኛ ወገንስ ቢሆኑ ከእኛ ጋር ጸንተው በኖሩ ነበር፤ ነገር ግን ሁሉ ከእኛ ወገን እንዳልሆኑ ይገለጡ ዘንድ ወጡ።”1ኛ ዮሐ 2፥19 

እነዚህ ሃሰተኛ አስተማሪዎች ነቀዝነታቸው መጀመሪያ ከሐዋርያት ጋር መሆናቸው ነው።ያ ደግሞ በቀላሉ ምስኪን ሕዝብ እንድስቱ የሚያደርግ ነው።ከእነርሱ ጋር "ነን" በማለታቸው ብቻ ሰዎችን የማሳት አቅማቸው የሌለ ነው ።

ዮሐንስ በዚህ በሽምግልናው እንኳን ፣በቆዳ ላይ ለመጻፍ የተነሳው ፣ጉዳዩ እጅግ አንገብጋቢ በመሆኑ ነው፤ለዚያውም ለአንዷ ለእናት ።ይገርማል ሐዋርያው እኛን አሁን ብመለከተን ምን ይለን ይሁን !? ለአንዷ ነፍስ እሱ እንድህ ከጻፈ ፣ ለሙሉ መንጋው እኛ እንዴት አብልጠን መጻፍ ይገባን ይሁን /ነበር/ !? 

ይህች ሚስኪን እናት በአዛኝ አንጀቷ እንዴትስ ተወጥታ ይሁን !? ቀላል እኮ አይደለም ። ከዚህ በፊት አብራቸው ማዕድ ቆርሳለች ፣ፍቅርን ተካፍላለች ፣ በብዙ ጠቀመዋታል ።ግን እንዴት ትጨቅን !? አይደለም በቤት መቀበል ፣ማዕድ መጋራት ቀርቶ ፥ የእግዚአብሔር ሰላምታ እንኳን እንዳትለዋወጥ ከልክሎዋታል ።(የማወራው ስለአንተ/ች ነው ።ፈቀቅ በል/ይ።)

እነዚህ ሰዎች መጀመሪያ ከሐዋርያው ጋር ሆኖ ብዙ ጠቅመዋል ።ግን አሁን ድምጻቸው ተቀይሯል ። ይህች እናት በዩንታ ውስጥ እንዳትገባ ፣ መጀመሪያም ከእኛ ጋር አልነበሩምና አትቀበያቸው አላት።በግልጽ ።

ከሃሰተኞች የሚገርመኝ ነገር ፈጣጣ እና ደረቅነታቸው ነው።ከሐዋርያት ተለይተውም እንኳን ልክ እንደ ሐዋርያት ወደ ሰዎቹ ቤት በእንግድነት እና ለጉዞ የሚሆን ስንቅ መቀበልም ያምራቸዋል ። የነቀዝ ሥራ ይህ ነው። ውንብድና ።ግን ከሐዋርያት ከተለዩ መለየት አያስፈልጋቸውምን !? የተንኮላቸው ተንኮል ፤ ተመሳስለው መኖራቸው ነው ።ይችሉበታል ።

*ለማነኛውም ስሙን ለመስበክ የሚመጡትን ተቀበሉ ቃሉ ብልም ፣ ለስሙ በሚመስል መልኩ ልያርዱ ፣ ተልዕኮ ለሳኦል ይዘው ስመጡ አለመቀበልም ጽድቅ ነው።

በእውነትም በስሙ የሚመጡትን መቀበል ጽድቅ እንደሆነ ሁሉ ፣ በስሙ የማይመጡትን አለመቀበልም ጽድቅ ነው።ምክንያቱም "ኢየሱስን እንቀበላለን" ማለት ሌላውን አንቀበልም ማለታችን እንደሆነ ሁሉ ፦በስሙ የሚመጡትን እንቀበላለን ማለት በስሙ የሚመጡትን ብቻና ብቻ እንቀበላለን ማለታችን ነው።

ዮሐንስ ከኢየሱስ ጋር በእውነተኛ ትምህርት እስከሆኑ ድረስ ከነዚህ ጋር ሕብረት እንዳደረገ ሁሉ ፣ እኛም የቀድሞ ዝምደት ፣ያኔ ያሳለፍነው ....ምናንም ብለን ከቃሉ በልጦብን አንቀጥልም ።ዮሐንስ እንደተለየ እንለያለን ።ይኸው ነው።

ዛሬም መልእክቱ ይህ ነው ፦

ሕብረትም እንደ ቃሉ ብቻ ነው፣
መተባበርም በኢየሱስ እስከ ቆሙ ብቻ ነው፣

ሦስተኛው መልእክት "ተቀበሉ!"

በዚህ መልእክት ላይ ደግሞ በሐዋርያው የሚላኩትን ፣ የኢየሱስ ክርስቶስ ምስክሮችን እንድቀበሉ የሚያበረታታ ነው።ያ ማለት ግን ጥቅስ ተጠቅሶ "በደቀመዝሙሩ ስም መቀበል" የተባለው በሞቱ ሰዎች ስም እና በመላእክት ስም ዝክር መዘከር እና ቡድን ፈጥረው የምግብ አድማ ማካሄድ ማለት አይደለም ።

ይገርማችኋል ።ጌታ ደቀመዛሙርቱን ወደ መንደሩ ስልካቸው  ፦

<<ማቴዎስ 10 ፥ ¹² ወደ ቤትም ስትገቡ ሰላምታ ስጡ፤ …   ⁴⁰ እናንተን የሚቀበል እኔን ይቀበላል፥ እኔንም የሚቀበል የላከኝን ይቀበላል።>> አላቸው ።

ስለዚህም ደቀመዛሙርቱ ለመስበክ ወደየቤቶቻቸው ይገባሉ ።ተቀብለው አብልቶአቸው የሸኛቸው ፥ዋጋ አለው፤ምክንያቱም እነሱን መቀበል የያዙትን ኢየሱስንም መቀበል ስለሆነ።ቃሉ የሚለው ይህ ነው እንጂ ጭራሽ በአውዱ ውስጥ የሌለውን መላእክት ስም እና ቀን ሰጥተው ፣ከቤት ለቤት እየዞሩ የምግብ አድማ ስለማድረግ በፍጹም አይደለም ። በሞቱ ሰዎች ስም ለራሳቸው የሚያደርጉት ፣ የእርስ በእርስ ግብዣ ማለት አይደለም ። (ማብላትም ከሆነ እኮ የተራበውን ነው።)

ወደ ርዕሰ ስገባ ዮሐንስ እውነተኛ ወንጌልን የሚሰብኩትን በመቀበልን አብልጦ ያበረታታል ።“እንግዲህ ከእውነት ጋር አብረን እንድንሠራ እኛ እንዲህ ያሉትን በእንግድነት ልንቀበል ይገባናል።”3ኛ ዮሐንስ 1፥8

*በዚህ ዘመን ምዕመናንን ለመጠበቅ ተልዕኮ ወስደው የሚሄዱትን ሌሎች ቅዱሳን እንድተባበሩአቸው ሕጋዊ  ማህተም ማረፍ አለበት እንላለን ።"ከእነርሱ ጋር ነን" ብለው እየተሾለክለኩ እንዳያውኩ።የመበለቲቱን ቤት እንዳይዘርፉ።

የተኛውም አገልጋይ "ያለ ሽማግሌዎች በግሉ ብቻ እንቀሳቀሳለሁ" ብል ፣ ለግል ምኞት እና ተልዕኮ ነው።ለዝርፍያ አልመች ብሎት ነው።እንዲህ ያለውን የመጣበትን አጥቢያ የማይናገር እና ሕጋዊ ማህተም ያላረፈ ከሆነ አትቀበሉት ።ልበሉአችሁ የመጣ ነው።የተኛውም ቤተክርስቲያን ቤተክርስቲያን እስከሆነች ድረስ ለወንጌል ትተባበራለች እንጅ አትከለክልም።እነዚህ ያለፍቃድ ፣ያለ ሽማግሌዎች ፣ያለአጥቢያ በግላችን "እኔ ብቻ እኔ ብቻ" የሚሉቱ ለግል ጥቅማቸው ነውና ሕጋዊ ደብዳቤ ጠይቁ።ከሌላቸው ወደቤታቸው አታስገቡ።

በግል ወንጌል መስበክ ችግር አለ እያልኩ አይደለም ።በግል ብዙዎች እንጸልያለን እያሉ እየዘረፉ ፣ ክፍያ እየጠየቁ ስለሚበዘብዙ ፣ በግል ብያገለግሉም ለቤተክርስቲያን ማሳወቅ አለበት ። አለበለዚያ ለአሳችነቱ እና ለግል ዓላማው ነውና አትተባበሩ።አትቀበሉ።

ዛሬም መልእክቱ ይህ ነው ፦

ግን በሕጋዊ መንገድ በአጥቢዋ ማህተም የተረጋገጠ ከሆነ ተቀብላችሁ እንደአቅማችሁ አጠጥታችሁ በክብር ሸኙ።


Comments

Popular posts from this blog

"ደብተራ ማን ነው?" ጸረ ደብተራ ንቅናቄ በሊቀ ጠበብት በዶክተር ዘሪሁን ሙላቱ

ካህናት ነን

የኢየሱስን እናት ብፅዕት ማርያምን አትሳደቡ! (2)