ራዕይ ጥናት ከም.4-22
በዓለም ለሚከሰቱ ነገሮች ከበስተጀርባ ያለውን እውነታ ለማውቅ መጽሐፍ ቅዱስን እናጥና! እንወቀው! እንጽና !
(ራዕይ ጥናት ከም.4-22)
“ከዚያ በኋላም አየሁ፥ እነሆም በሰማይ የተከፈተ ደጅ፥ እንደ መለከትም ሆኖ ሲናገረኝ የሰማሁት ፊተኛው ድምፅ፦ ወደዚህ ውጣና ከዚህ በኋላ ሊሆን የሚያስፈልገውን ነገር አሳይሃለሁ አለ።”ራእይ 4፥1
ዮሐንስ ስለ 7ቱ አብያተክርስቲያናት በአስቸኳይ ልሆን የሚገባውን ከተመለከተ በኃላ ፣ በምዕራፍ 4 ደግሞ ሌላ ገና ልሆን የሚገባው ነገር ይመለከታል ። (ራዕይ መጽሐፍ ያለፈ ታርክ እየተረከልን አይደለም )
“ወዲያው በመንፈስ ነበርሁ፤ እነሆም፥ ዙፋን በሰማይ ቆሞአል በዙፋኑም ላይ ተቀማጭ ነበረ፤”ራእይ 4፥2
ዮሐንስ አብ በዙፋኑ ተቀምጦ እያለ ይመለከታል ፣
“በዙፋኑ ዙሪያም ሀያ አራት ዙፋኖች ነበሩ፥ በዙፋኖቹም ላይ ነጭ ልብስ ለብሰው በራሳቸውም የወርቅ አክሊል ደፍተው ሀያ አራት ሽማግሌዎች ተቀምጠው ነበር።” ራእይ 4፥4
እነዚህ 24 ሽማግሌዎች የተባሉት በብሉይና በአድስ ክዳን ያሉቱ መላው የእግዚአብሔር ቤተሰብ ቁጥር ነው ፣
“ከዙፋኑም መብረቅና ድምፅ ነጐድጓድም ይወጣል፤ በዙፋኑም ፊት ሰባት የእሳት መብራቶች ይበሩ ነበር፥ እነርሱም ሰባቱ የእግዚአብሔር መናፍስት ናቸው።”ራእይ 4፥5
ዮሐንስ ስመለከት ሰባት(በሙላት) የእግዚአብሔር መንፈስ አለበት በዙፋኑ ፊት፣
“በዙፋኑም ፊት ብርሌ የሚመስል የብርጭቆ ባሕር ነበረ። በዙፋኑም መካከል በዙፋኑም ዙሪያ፥ በፊትና በኋላ ዓይኖች የሞሉአቸው አራት እንስሶች ነበሩ።”ራእይ 4፥6
ዮሐንስ ስመለከት አራት እንስሶች (በዓለም በአራቱ አጥቃጫዎች ያሉት ፍጥረታት በሙሉ በፊቱ አሉ፣
እነዚህ የዓለም ፍጥረታት በሙሉ እይታቸው የሰፋ ነው ቁ.7
ደግሞም ፍጥረታት ሁሉ ያመሰግናሉ እንዲህ እያሉ፦
“..ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ የነበረውና ያለ የሚመጣውም ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ እያሉ ቀንና ሌሊት አያርፉም።” ራእይ 4፥8
ፍጥረታት ሁሉ ምስጋና ስያቀርቡ ሰዎቹም ወድቀው ማመስገን ጀመሩ እንዲህ እያሉ ፦
“..፦ ጌታችንና አምላካችን ሆይ፥ አንተ ሁሉን ፈጥረሃልና ስለ ፈቃድህም ሆነዋልና ተፈጥረውማልና ክብር ውዳሴ ኃይልም ልትቀበል ይገባሃል እያሉ በዙፋኑ ፊት አክሊላቸውን ያኖራሉ።” ራእይ 4፥10-11
በዓለም ለሚከወኑ ነገሮች በስተጀርባ ያሉትን ለማወቅ መጽሐፍ ቅዱስን እናጥና! እንጽና! (2 )
“በዙፋኑ ላይም በተቀመጠው በቀኝ እጁ ላይ በውስጥና በኋላ የተጻፈበት በሰባትም ማኅተም የተዘጋ መጽሐፍን አየሁ።” ራእይ 5፥1
መጽሐፉ የተዘጋ ነው።ጥቅልል ነው።በመጽሐፍ ውስጥ የተጻፉት ከዚህ በኃላ የሚሆነውን የዓለምን ሁኔታ የሚያሳይ ነው።
“ብርቱም መልአክ፦ መጽሐፉን ይዘረጋ ዘንድ ማኅተሞቹንም ይፈታ ዘንድ የሚገባው ማን ነው? ብሎ በታላቅ ድምፅ ሲያውጅ አየሁ።”ራእይ 5፥2
መጽሐፍ የዓለምን እንቆቅልሽ የያዘ ነው።ግን የሚተርከው ማን ነው!? ለሚከሰተው ሁኔታዎች ኀላፍው ማን ነው !? ልቆጣጠረው የሚችለው !?
“በሰማይም ቢሆን በምድርም ላይ ቢሆን ከምድርም በታች ቢሆን መጽሐፉን ሊዘረጋ ወይም ሊመለከተው ማንም አልተቻለውም።” ራእይ 5፥3
ዮሐንስ ራዕዩን ስመለከት ሁሉንም ልቆጣጠረው እና እንቆቅልሽ የሚፈታ አልተገኘም ! በዚህም ዮሐንስ አዘነ አለቀሰ ቁ.4 ።ዮሐንስ በማዘኑ አንዱ ሽማግሌ እንዲህ አለው ፦
“..፦ አታልቅስ፤ እነሆ፥ ከይሁዳ ነገድ የሆነው አንበሳ እርሱም የዳዊት ሥር መጽሐፉን ይዘረጋ ዘንድ ሰባቱንም ማኅተም ይፈታ ዘንድ ድል ነሥቶአል አለኝ።”ራእይ 5፥5
ከሽማግሌዎች (ከአማኞች) አንዱ ዮሐንስን "አታልቅስ እንቆቅልሽ ልፈታ የሚቻለው የዳዊት ዘር አለ" አለው።
“በዙፋኑና በአራቱ እንስሶች መካከልም በሽማግሌዎችም መካከል እንደ ታረደ በግ ቆሞ አየሁ፥ ሰባትም ቀንዶችና ሰባት ዓይኖች ነበሩት እነርሱም ወደ ምድር ሁሉ የተላኩ የእግዚአብሔር መናፍስት ናቸው።”ራእይ 5፥6
እንቆቅልሽ ልፈታ የሚቻለው የዳዊት ሥር የሆነው በግ ፥ በአብ ፥ በዓለም ፍጥረታትና በአማኞች መካከል "ቆሞ " እያለ ዮሐንስ ተመለከተ ። ሌላ ፉጡር መጽሐፉን ለመውሰድ ለመቆም የደፈረ የለም።(ቆሜ ማለት ኢየሱስ እየለመ ነው ማለት አይደለም)
በጉ የሃይልና የእይታ ሙላት አለው (ከበጉ የተሰወረ እና የማይቻለው ነገር የለውም)
“መጥቶም በዙፋን ላይ ከተቀመጠ ከዚያ ከቀኝ እጁ መጽሐፉን ወሰደው።”ራእይ 5፥7
እንቆቅልሽ ልፈታ የሚችለው ብቸኛው እንደሆነ በሁሉም ዘንድ አስመሰከረ ።ይህንን ስመለከቱ የዓለም ፍጥረታት እና አማኞች ሁሉም እንዲህ አደረጉ ፦
“.. በበጉ ፊት ወደቁ፥ እያንዳንዳቸውም በገናንና የቅዱሳን ጸሎት የሆነ ዕጣን የሞላበትን የወርቅ ዕቃ ያዙ።” ራእይ 5፥8 ።ከዛ ሁሉም ማመስገን ጀመሩ ፥ ሁሉም በአንድነት እንዲህ እያሉ ፦
“መጽሐፉን ትወስድ ዘንድ ማኅተሞቹንም ትፈታ ዘንድ ይገባሃል፥ ታርደሃልና፥ በደምህም ለእግዚአብሔር ከነገድ ሁሉ ከቋንቋም ሁሉ ከወገንም ሁሉ ከሕዝብም ሁሉ ሰዎችን ዋጅተህ ለአምላካችን መንግሥትና #ካህናት ይሆኑ ዘንድ አደረግሃቸው፥ በምድርም ላይ ይነግሣሉ እያሉ አዲስን ቅኔ ይዘምራሉ።” ራእይ 5፥9-10
ደግሞም ተቆጥረው የማያልቁቱ መላእክትም ያመስግናሉ በጉን ።እንዲህ እያሉ ፦
“በታላቅም ድምፅ፦ የታረደው በግ ኃይልና ባለ ጠግነት ጥበብም ብርታትም ክብርም ምስጋናም በረከትም ሊቀበል ይገባዋል አሉ።” ራእይ 5፥12
እንደገና ፍጥረት ሁሉ በጉን እና በዙፉኑ የተቀመጠውን አብን ጭምር ስያመሰግኑ ዮሐንስ ተመለከተ ።እንዲህ እያሉ፦
“..፦ በረከትና ክብር ምስጋናም ኃይልም ከዘላለም እስከ ዘላለም #በዙፋኑ_ላይ_ለተቀመጠው፥ #ለበጉም ይሁን ሲሉ ሰማሁ።”ራእይ 5፥13
ኢየሱስ ከአብ ጋር እኩል ምስጋና ከፍጥረታት እንደሚቀበል ተረድተናል (ትምህርተ ሦስትነት ይመለከቷል) ።የመጽሐፉን እንቆቅልሽ የሚፈታ እርሱ ብቻ ነው።አምላክ ነውና ተመለከ።
በቀጣይ በዓለም ላይ ከሚከሰቱ ችግሮች ፥በጀርባው ያለው ማን እንደሆነ እንደ መንፈሳዊ ሰው እናያለን ። ማንም የፖለቲካ ሆነ የማይበረሰብ ችግር ብሎ ስፈተፍት እኛ ደግሞ ቃሉን እያጠናን አምላካችን የተናገረው ነገር እየተፈፀመ እንዳለ እናስተውላለን ። እንቃትታለን ።
...
“በጉም ከሰባቱ ማኅተም አንዱን በፈታ ጊዜ አየሁ፥ ከአራቱም እንስሶች አንዱ ነጐድጓድ በሚመስል ድምፅ፦ መጥተህ እይ ሲል ሰማሁ።”ራእይ 6፥1
አሁን ለሚከሰቱ ነገሮች በጉ ባለሥልጣን ስለሆነ መግለጫ ይሰጣል ።አንደኛው ጥቅልል መጽሐፍ ፈታው ፥ ዙፋኑ ዙሪያ ካሉት አራት እንስሳዎች ፣ አንዱ ዮሐንስን የመጽሐፉን ምስጢር እንድመለከተው ተጣራ (ከአራቱ እንስሳዎች ምን የሚመስለው እንስሳ እንደሆነ አልተገለጸም ለእኛ፤መጽሐፉ ዝም ያለበት ዝም ብለን እንቀጥላለን )።ዮሐንስ ስመለከት ፦
“አየሁም፥ እነሆም፥ አምባላይ ፈረስ ወጣ፥ በእርሱም ላይ የተቀመጠው ቀስት ነበረው፥ አክሊልም ተሰጠው፥ ድልም እየነሣ ወጣ ድል ለመንሣት።”ራእይ 6፥2
አምባላይ (ነጭ) ፈረስ ላይ የወጣውን ተመለከተ ።በነጩ ፈረስ ላይ የተቀመጠው ቀስት ይዟል ።አክሊልም ተሰጠው (ሽልማት ወይም ክብር )።ከዚያም ድል እየነሳ (እየማረከ/እያሸነፈ ) ወጣ።
በዚህ ማህተም ላይ እንደሚንመለከተው በነጭ ፈረስ የሚቀመጠው ያሸነፈው ነው።ይህም ተዋጋ አሸንፏል ።ቀስትም አለው።ቀስቱ ምንድነው ፦
እያንዳንዱን ሰው እንዲያሸንፍ የሚያግዝ ጥበብ እውቀት ነው፣
ቀስት ሰውነትን በርብሮ ልገባ ይችላል ።እውቀትም የሰውነትን ሙሉ በሙሉ አዕምሮን በመማረክ ልቆጣጠረው ይችላል ፣
ይህ ጦርነት በቀስት (በእውቀት) የሚደረግ ብሆንም ለራሱ ልያደርግ ልቆጣጠረው እንድችል ሃሰተኛ ትምህርት ይጠቀማል ።ማቴ 24፥4-6
በሃሰተኛ ሃይማኖታዊ አስተምህሮ ወይንም ፍልስፍና ተጠቅሞ አዕምሮን ይማርካል ።ያታልላል ።ለራሱ ዓላማ ይጠቀማል ።
ይህ የአንድ ግዜ በአንድ ሰው በኩል ከተሰራጨ ሰውየው ስሞት ያበቃል ማለት አይደለም ።ምክንያቱም አዕምሮ የሚቆጣጠር ስለሆነ ይሸጋገራል ።ብዙዎችን ለራሱ ሃሰተኛ እውቀት ባሪያ ያደርጋል ።መጽሐፉ እንደሚል ድል ያደርጋል ማለት ነው።
በቀላሉ የሚነቀል አይደለም ።ስለዚህም ሃሰተኛ የሆነ እውቀት ከእግዚአብሔር ያልሆነ እውቀት ነው የሰይጣን ሥራ ነው።እንዲህ ለየትኛው ሃጥያት ጅማሬው የአዕምሮ መመረዝ ነው።
በዚህ ጥበቡ አዕምሮን የተቆጣጠረው አካል በቀጣይ ምን ለማድረግ መንገድ ከፋች እንዳደረገ እንመለከታለን ።
...
በዓለም ለሚከሰቱ ነገሮች ወይ የእግዚአብሔር እጅ አለበት ወይ ሰይጣን እጅ አለበት ።ከሁሉቱ ከማይታዩ አካላት የአንዱ ውጤት እንጂ ከሁለቱም አለመሆን የማይቻል ነው።የሁለተኛውን መጽሐፍ ጥቅልል ምስጢር ከዮሐንስ ጋር እንመልከት ፦
“ሁለተኛውንም ማኅተም በፈታ ጊዜ ሁለተኛው እንስሳ፦ መጥተህ እይ ሲል ሰማሁ።” ራእይ 6፥3
ምን የሚመስል እንስሳ እንደተጣራ ባይገለጽም ፣ ከዙፋኑ ዙሪያ ካሉት ከአራቱ እንሰሳዎች አንደኛው እንደ ተጣራ እንመለከታለን ።ከዮሐንስ ጋር ሁለተኛው ማህተም ማየታችንን እንቀጥል ፦
“ሌላም ዳማ ፈረስ ወጣ፥ በእርሱም ላይ ለተቀመጠው ሰላምን ከምድር ይወስድ ዘንድ ሰዎችም እርስ በርሳቸው እንዲተራረዱ ሥልጣን ተሰጠው፥ ታላቅም ሰይፍ ተሰጠው።”ራእይ 6፥4
ዮሐንስ ስመለከት ዳማ (ቀይ) ፈረስ ላይ ወጣ ። የእርስበርስ መገዳደል በምድር ላይ እንድሆን የሚሰራ ነው።
ለእርስ በእርስ ጦርነት የመጀመሪያው ፈረስ ጥቃት አበርክቶት አለው ፤የመጀመሪያው ፈረስ ውጤት አድርገም እወስዳለሁ ። መጀመሪያ በጭፍናምነት ፥በጥላቻ ፥ በጥንፈኝነት ፥ አዕምሮ ስለተበላሸ የእርስ በእርስ ግድያም ትክክል አድርጎ የሚያስወስድ ክፉ ሠራ ነው።(በዓለም ላይ የተከሰቱና በኀይልም እየተከሰቱ ያሉ ነገሮችን እስኪ እናስብ እናስተውል ? )
*ትክክለኛ ትምህርት እውነተኛ ፍሬ ያፈራል ። አዕምሮውን የተቆጣጠረው መርዝ ደግሞ ውጤቱ የውስጥም የውጭም ሰላም ማሳጣት ነው።
የእርስበርስ ጦርነት ማለት በቤተሰባዊ መካከል የሚደረግ ጦርነት ነው።የወንድማማቾች ጦርነት ነው። እንግዲህ እርስ በእርስ እንድጥፋፉ ሰይጣን የተጠቀመው መሳሪያ ሃሰተኛ ትምህርት ነው።(ትክክለኛ አስተሳሰብ እንድኖረን ጠናማ ትምህርት ወሳኝነት አለው)
ጥርስ ከማቀጨጭም አይን ከማጠቆርም አልፎ እስከ መገዳደል የሚያደርስ ስለሆነ ፣ የሃሰተኛ ትምህርት መርዝነት ምን ያህል አስከፊ እንደሆነ እናስተውል ።
(ይህም ደግሞ እንደሚሆን ጌታ አስቀድሞ አይቶታል፤ወዮ )
በቀጣይ በሦስተኛው ማህተም የኢኮኖሚ ጥቃት እንመለከታለን
በዓለም ለሚከወኑ ነገሮች በስተጀርባ ያሉትን ለማወቅ መጽሐፍ ቅዱስን እናጥና! እንጽና! (5 )
“ሦስተኛውንም ማኅተም በፈታ ጊዜ ሦስተኛው እንስሳ፦ መጥተህ እይ ሲል ሰማሁ። አየሁም፥ እነሆም፥ ጕራቻ ፈረስ ወጣ፥ በእርሱም ላይ የተቀመጠው በእጁ ሚዛን ያዘ።”ራእይ 6፥5
ጥቁር ፈረስ ነው።ትክክለኛ ሚዛን የሚያሳጣ ነው፤ ኢኮኖሚ የሚጎዳ ነው።ኤኮኖሚን እንዴት ነው የሚጎዳው !? የኢኮኖሚ ጉዳት እንዴት ነፍሳችንን ልጎዳ ይችላል !?
እስኪ ከዮሐንስ ጋር እንመልከት ፦
“በአራቱም እንስሶች መካከል ድምፅ፦ አንድ እርቦ ስንዴ በዲናር ሦስት እርቦ ገብስም በዲናር፥ ዘይትንና ወይንንም አትጕዳ ሲል ሰማሁ።”ራእይ 6፥6
ይህ ኢኮኖሚያዊ ጥቃት በሃሰተኛ እውቀት የሚፈጸም ነው ። ግን በዘይትና በወይን ላይ ሙሉዑ ጉዳት እንዳያስከትል እገዳ ተጥሏል ።ለእኛ የሚመስለው የነጋዴው ስግብግብነት ነው።ግን የዚህ መነሻው የግብይት ሥራ ለማቀላጠፍ እንደ መልካም ተቆጥሮ የገባው ሃሰተኛ ፊልስፍና ነው።
ይህ ችግር የአንድ ሃገር ችግር ብቻ አይደለም ። የዓለም ሁሉ ችግር ነው።በእርግጥም በአንድ ሃገር ላይ ይህ ችግር ሚዛን ልደፋ ይችላል ።ያ ማለት ሌላ ሀገራት ነፃ ናቸው ማለት አይደለም ። ችግሩም እጥረት ወይም Scarcity ይባላል ።
Scarcity ተፈጥሮአዊ የማምረቻ ንጥረ ነገሮች ሙሉዕ አለመሆንና የተፈጥሮ ሃብት በተጠቀምክ ቁጥር የሚያልቁ ንጠረ ነገሮች ስለሆኑ የሚከሰት ነው።ይህ ደግሞ የሁሉም ሀገር ችግር ነው።ለምሳሌ ሁሉም ሃገራት ወርቅ ማምረት ይፈልጋሉ ግን በቂና ከበቂ በላይ ለማምረት የንጠረ ነገሩ እጥረት አለ።ይህ ተፈጥሮአዊ ነው።
የሰው ፍላጐት ገደብ አልባ ነው።ይህንን ፍላጎት ለማሟላት የሰው ልጅ የማይሆነው የለም።ይህን አጋጣሚ ሰይጣን ይጠቀማል ።ምክንያቱም እጥረት ካለ ፣ምርቱ የለም ማለት ሳይሆን ፣ አንድ እቃ ገዝቶ ለመጠቀም ከወር ደሞዝ በላይ ልጠይቅ ስለሚችል ነው።
እየሁላችሁ አስተውሉ። ይህ ጥቃት አገደኛ ነው።የሰው ልጅ መጀመሪያ ሆዱ ስጠግብ ነው የተንቆጠቆጡ እቃዎችን የሚፈልገው ።ይህ ጥቃት ግን የእለት እንጀራም የሚከለክል ነው።ገበያ ገብተ ለአንድ ሙሉ ቤተሰብ የሚገዛው አስቤዛ ፣ለአንድ ሰው ብቻ የሚበቃ ያህል ብቻ እስኪሆን ድረስ ኢኮኖሚን የሚያጠቃ ነው። በረሃብ ወክት ከሆነ ከዚህም ጥቃቱ ይብሳል ።
ሰዎች ከዚህ ችግር " ኡፈ " ብለው ለመውጣት ወደ Lucifer እንዲሄዱ ልያደርግ የሚችል ነው።ስለዚህም እኛ ክርስቲያኖች አብዝተን የእለት እንጀራችንን ስጠን እያለን መጸለይ ይገባናል ።እግዚአብሔር ሁላችንንም ይጠብቀን ።አንባቢው ያስተውል።
"የሚበላው እንኳን ለጌታ ይበላል" መጽሐፍ ይለናል ሮሜ 14 ።ለጌታ ክብር እንኳን እንዳትበላ ኢኮኖሚውን የሚያጠቃ ፣ ወደ ማማረር እና ወደ መሳደብ ልወስድ የሚችል አደገኛ ጥቃት ነው ።
"ጌታ ለሁለት ጌቶች መገዛት አትችሉም" በማለት ገንዘብ ራሱ ጌታ ልሆን እንደሚችል አስተምሮናል ማቴ 6፥24። ይህ ጥቃት በገንዘብ እጦት የሚያጠቃ ስለሆነ ፣ "ገንዘብን በቀላሉ በማግኘት ይፈታል" በማስባል ፣ ገንዘብን የሚያገኙበት መንገድ በመዘርጋት ፣ እምነትን መሸርሸር የሚችል አደገኛ ሠራ ነው።አሁንም እየሆነ ነው።(በሃሰተኛ ነቢያቱ፣በሃሰተኛ አስተማሪዎች ፣ በዓለም ጨዋታ በሚመስሉ ቁማሮች፣በግልጽ የLucifer አምልኮ ጥር...ወዘተ እየሰራ ነው)
#ወንድሞቼ ሆይ! ሰይጣን ማንንም ደሃ የማድረግ ቀርቶ የደሃ ደሃ የማድረግ ዓላማም ሆነ እቅድ የለውም ። ሃሳቡ ኢየሱስን እንድትክዱ ፣ የቃሉ ግዜን በመሸርሸር ፣ልብን በማዳከም ፣ከመንገዱ ማውጣት ነውና አትቦዝኑ።(ከዚህ ማህተም መልእክት እንደሚንረዳው ብዙዎችን ልማርክ እንደሚችል ነው)
ንቁ።
.....
የፍጥረታት ምሳሌ የሆኑቱ አራቱ እንስሶች ከተባሉት አንደኛው እንስሳ ዮሐንስን መልእክቱን እንድመለከተው ይጣራል ።ከዮሐንስ ጋር እንቀጥል ፦
“አራተኛውንም ማኅተም በፈታ ጊዜ የአራተኛው እንስሳ ድምፅ፦ መጥተህ እይ ሲል ሰማሁ።”ራእይ 6፥7
ዮሐንስ የዓለምን እንቆቅልሽ መመልከት ጀምሯል ።እኛም ከዮሐንስ ጋር እንመልከት ፦
“አየሁም፥ እነሆም፥ ሐመር ፈረስ ወጣ፥ በእርሱም ላይ የተቀመጠው ስሙ ሞት ነበረ። ሲኦልም ተከተለው፤ በሰይፍና በራብም በሞትም በምድርም አራዊት ይገድሉ ዘንድ ከምድር በአራተኛዋ እጅ ላይ ሥልጣን ተሰጣቸው።” ራእይ 6፥8
ዮሐንስ ስመለከተው ሐመር (ግራጫ) ፈረስ ነው። ሞትን የሚያመጣ ነው።ከምድር አራተኛ (1/4) ያህልን ልያጠፋ የሚችል ነው።ሰዎችንም እንስሳትንም የሚያጠፋ ነው።
በተፈጥሮ አደጋ ፣ በራብ ፣በጦርነት በተለያዬ ግዜ በተለያየ ሃገር ላይ የሚከሰት ነው። እስኪ በአዕምሮአችሁ አሰላስሉ !? እንዲህ ያለውን ክስተት ።
ይህ ጦርነት የእርስበርስ ጦርነት አይደለም ።የዓለም ጦርነት ዓይነት ፥ ትልቅ እልቅት የሚያስከትል ነው ።
የጦርነቱ ምንጭ የመጀመሪያው ፈረስ የአዕምሮ ጥቃት በር ከፋችነት እንደሆነ እረዳለሁ ።
ጦርነት ክፋቱ መግባባት ብሎ ነገር የለም።ሁሉም ስገድሉ ከቆሙበት አቋም አንፃር 'ትክክል ነኝ' የሚያስብል እርህራሄ የሚያሳጣ ሰይጣናዊነት ነው። አዕምሮ ስለተበከለ መስማማት ብሎ ነገር የለም፤አይታሰብም ።
እስካሁን ያየናቸው ማህተሞች ስፈቱ ፣ የእንቆቅልሹ ምስጥር አማኝን ጭምር ሳይለይ የሚያጠቃ ነው። እንወቅ። እንጽና።
በቀጣይ የአምስተኛው ማህተም እንቆቅልሽ እናያለን
...
“አምስተኛውንም ማኅተም በፈታ ጊዜ፥ ስለ እግዚአብሔር ቃልና ስለ ጠበቁት ምስክር የታረዱትን የሰዎች ነፍሳት ከመሠዊያ በታች አየሁ።”ራእይ 6፥9
በዚህ ማህተም ላይ ዮሐንስን "ና መጥተህ ተመልከት" የሚል ድምጽ የለም። ኢየሱስ ራሱ ነው እየገለፀ ያለው ።ዮሐንስም ስመለከት የተሰውቱን ፥ የታረዱ ነፍሳትን ተመለከተ ። እነዚህ እኔ ማን ናቸው የታረዱቱ !?ሰማዕታት ናቸው።(ለስሙ ብቻ የተሰው)
“በታላቅ ድምፅም እየጮኹ፦ ቅዱስና እውነተኛ ጌታ ሆይ፥ እስከ መቼ ድረስ አትፈርድም ደማችንንስ በምድር በሚኖሩት ላይ እስከ መቼ አትበቀልም? አሉ።”ራእይ 6፥10
ሰማዕታት ስለኢየሱስ ስም ብለው ስለተሰው የእግዚአብሔርን ፍትህ ይጠይቃሉ።
እነዚህ ዮሐንስ የሚመለከታቸው ሰማዕታት እሳካሁንም ወደፊትም ስለስሙ ብለው የሚታረዱቱ ጭምር ናቸው ።የአንድ ግዜ ወይንም የአንድ ሃገር ብቻ አይደለም ። ዮሐንስ የወደፊቱን እያየ ነውና እናስተውል ።
የክርስቶስ ምዕመናት በችግር ውስጥ እያለፉ እንደሚቀጥሉ እና ብዙዎች ዋጋ መክፈላቸውን እንረዳለን ከዚህኛው ማህተም።
“ለእያንዳንዳቸውም ነጭ ልብስ ተሰጣቸው፥ እንደ እነርሱም ደግሞ ይገደሉ ዘንድ ያላቸው የባሪያዎች ባልንጀራዎቻቸውና የወንድሞቻቸው ቍጥር እስኪፈጸም ድረስ፥ ገና ጥቂት ዘመን #እንዲያርፉ ተባለላቸው።” ራእይ 6፥11
አሁን የሚሰው አማኞች ፍትህ ይጠይቃሉ ።ጌታ ግን እንደእናንተ "ገና የሚሰው አሉና" ታገሱ የሚል መልስ ይሰጣል ።የእግዚአብሔር ፍትህ የማይቀር ነው፤ ይዘገያል እንጂ፤አይቀርም።ግዜውን እየጠበቀ ።
ስለዚህም አሁንም በተለያየ ክፍሎች በዓለማችን ክርስቲያኖች በመከራ እያለፉ እንደሆነም እንረዳለን ። (ከኢትዮጵያ ድንኳን ወጥታችሁ አስብ)
በቀደሙት ማህተሞች ሁሉም ሰው በችግር ውስጥ ስያልፍ ፣ይህ ማህተም ግን ለአማኙ ብቻ ነው። የመጨረሻው ሰዓት እጅግ በጣም እንደቀረበ እንረዳለን ። (በክርስትና ስም ለተለያየ ነገር የተሰዋ ለምሳሌ ለቦታ.. መሰል ችግሮች የሞተ ለስሙ የተሰዋ አይደለም ።ለስሙ "መሰዋት ኢየሱስን አታምልክ" ተብለ የሚትሰዋ እንጂ በዚህ ቦታ አታምልክ ስባል የሚፈጠር ግርግር አይደለም ።ምክንያቱም ቦታው ለወንጌል የግድ አይደለም)
*የእግዚአብሔር ፍትህ እንድሆን የሚደረገው ልመና ይፈጸማል ። [ይመጣልናል ላመኑቱ።ላሳደዱት ይመጣባቸዋል ።]
ማህተሞቹን ከዮሐንስ ጋር መመልከታችንን እንቀጥል
...
ወደ ስድስተኛው ማህተም ደርሰናል ።የቁጣ ቀን ነው። ተመልከቱ ፦
“ስድስተኛውንም ማኅተም በፈታ ጊዜ አየሁ፥ ታላቅም የምድር መናወጥ ሆነ፥ ፀሐይም እንደ ማቅ ጠጕር ጥቁር ሆነ፥ ጨረቃም በሞላው እንደ ደም ሆነ፥” ራእይ 6፥12
የጌታ መምጣት እጅግ በጣም በጣምም እንደቀረበ አመልካች ነው።ማቴ 24፥9 ፣ ሐዋ 2፥20 ፣ማር 13፥25
"የተፈጥሮ አደጋ ብቻ ነው" በሳይንሳዊ ትንተና ልባል ይችላል፤ ምድርን እንዳልነበረ ስለሚያደርግ ቁ.14-16።ግን ይህንን ስትመለከቱ የጌታ ቀን እንደደረሰ አስተውሉ ።
ማንም ልያመልጥ አይችልም ።ያላቸው የተኛውም ተክኖሎጂ ልያስመልጥ አይችልም ቁ.15 ።
ምዕመናት እንዴት ይሆናሉ !?
በዚህ ግዜ በኖህ ዘመን እንደሆነው ፥መቅሰፍት እያለ ኖህ በመርከብ ተጠልለው እንዳለፈ ፥ በችግሩ ውስጥም እኛም አማኞች እናልፋለን በደሙ ተሸፍነን ።
ስድስተኛው ማህተም እንቆቅልሽ በም.7 ትም ይቀጥላል ።ከዮሐንስ ጋር እንቀጥል ፦
በዚህ ግዜ ገና ለሚድኑቱ ስባል በአራት ማዕዘን የቆሙ የነበሩ መላእክት መቅሰፍት ልያመጡ ስሉ ለግዜው ተከለከሉ ።ቁ.1
አራቱ መላእክት ምድርን በመቅሰፍት ልመቱ ስሉ ሌላ መላእክት መጥቶ የክርስቶስ የሆኑቱን ምልክት እስከምናደርግ ድረስ ለግዜ እንድታገሱ አደረገ። “የአምላካችንን ባሪያዎች ግምባራቸውን እስክናትማቸው ድረስ ምድርን ቢሆን ወይም ባሕርን ወይም ዛፎችን አትጕዱ አላቸው።”ራእይ 7፥3
ከዛም ዮሐንስ የክርስቶስ እንደሆኑ መንፈስ ቅዱስን የተቀበሉ ሰዎች ቁጥር ሰማ #144000 ነው። አስተውሉ ዮሐንስ የዳኑ ሰዎች ቁጥር በራዕይ ሰማ ።በጆሮው መስማት ነው የሰማው ።
“የታተሙትንም ቍጥር #ሰማሁ፤ ከእስራኤል ልጆች ነገድ ሁሉ የታተሙት መቶ አርባ አራት ሺህ ነበሩ።”ራእይ 7፥4
እጅግ በጣም በቁጥር ትንሽ ነገድ የሆኑትም እጅግ በጣም ብዙ የሆኑትንም በተመሳሳይ ቁጥር መጠን 12 ሺህ እንደሆነ ሰማ ቁ.5-8።አሁን እናስተውል ።(ይህ ቁጥር የሕሳብ ቁጥር አይደለም ።)
ዮሐንስ 144000 ናቸው የዳኑቱ ብሎ በጆሮው የሰማውን በዓይኑ ስመለከት ተቆጥሮ የማያልቁ ናቸው ።ምክንያቱም ዮሐንስ የሰማው ቁጥር የሕሳብ ቁጥር አይደለም ።ምሳሌ ፦
በብሉይ የእግዚአብሔር ሕዝብ ቁጥር 12 ሲሆን በዓድስም 12 ነው።የሁለቱ ድምር 144 ነው።ሺህ የተባለው እጅግ ብዙ ልቆጠር የማይችል የሚገልጽ ነው።ለዚያ ነው 12 *12*1000 =ብለው 144000 የሚል ቁጥራዊ ምሳሌ የተሰጠው ።
“ከዚህ በኋላ አየሁ፥ እነሆም፥ አንድ እንኳ ሊቆጥራቸው የማይችል ከሕዝብና ከነገድ ከወገንም ከቋንቋም ሁሉ እጅግ ብዙ ሰዎች ነበሩ፤ ነጭ ልብስም ለብሰው የዘንባባንም ዝንጣፊዎች በእጆቻቸው ይዘው በዙፋኑና በበጉ ፊት ቆሙ፤”ራእይ 7፥9
አስተውሉ እነዚህ ከላይ የእስራኤል ነገድ ስለተባለ የትውልድ እስራኤል ማለት አይደለም ።በመንፈስ እስራኤል የሆኑትን ጭምር እንጂ ሮሜ 2፥26-29።ምክንያቱም የዳኑቱ ፦
1ኛ ልቆጠሩ የማይችሉ ናቸው ፣
2ኛ ከሕዝብና ከነገድ ከቋንቋም ሁሉ ነው፤ናቸው ።
ስለዚህም ተቀጥሮ የማያልቁ የአምላካችን ሕዝብ አለ የሚድኑቱ ። "ማን ልድን ይችላል !? "አትበሉ።
እግዚአብሔር እየሰራ ነው።ከሰይጣን እስራት ነፃ እያወጣ ነው።
..........
የዳኑቱ ሁሉም በአንድነት በበጉ ፊት ቆመው(የኢየሱስ እናቱ ጭምር ከዳኑቱ ጋር ትቆማለች፤አትፈላሰፉ)። እንዲህ ይላሉ ፦
“በታላቅም ድምፅ እየጮሁ፦ በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠው ለአምላካችንና ለበጉ ማዳን ነው አሉ።”ራእይ 7፥10
በዙፋኑ ለተቀመጠው ለአብ ፣
ደግሞም ለበጉ ለኢየሱስ እኩል ምስጋና ያቀርባሉ ።
(ኢየሱስ ከአብ አያንስም እኩል ይመለካል፤ማርያምም ከሰው አትበልጥም እኩል ቆማ ታመልካለች፤እሷስ የታደለች ናት)
መላእክቱም እንደ ሰዎች በዘፋኑ ዙሪያ ቆመው እየሰገዱ ለእግዚአብሔር ምስጋና ያቀርባሉ ቁ.11።እንዲህ እያሉ ፦
“አሜን፥ በረከትና ክብር ጥበብም ምስጋናም ውዳሴም ኃይልም ብርታትም ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ለአምላካችን ይሁን፤ አሜን አሉ።” ራእይ 7፥12
ከሽማግሌዎች (ከአማኞች) አንዱ ዮሐንስን "በበጉ ፊት የቆሙ እነማንናቸው !?" ብሎ ጠየቀው ቁ.13 ። እኛስ እኔ ማን ናቸው ነው የሚንለው !? ከእነርሱ መካከል እንደሚንሆን እርግጠኞች ነን !? ዮሐንስ ግን አላውቅም አለ ቁ.14 ።(ዮሐንስም ከእነርሱ መካከል እንደሚሆን አያጠራጥርም)
ሽማግለው ራሱ መለሰ ስለስሙ መከራ የተቀበሉ እንደሆኑ አረጋገጠ “ ..፦ እነዚህ ከታላቁ መከራ የመጡ ናቸው፥ ልብሳቸውንም አጥበው በበጉ ደም አነጹ።” ራእይ 7፥14። ተመስገን ።ተባረክ ጌታ።ተስፋችን የታመነ ነው።እንጽና።
ስለዚህም ከዚህ በኃላ በ6ኛ ማህተም ምስጥር ፦
ለቅሶ የለም፣
መራብ መጠማት የለም፣
ያለጉድለት ያለድካም ምስጋና ብቻ ነው፣
የተኛውንም ችግር አያዩም ፣
ሞያተኛ እረኛና ተኩላ በመካከላቸው የለም፣
በጉ በመካከለቸው ነው። ቁ.15-17
ሃሌ ሉያ።
በስድስተኛው ማህተም በጉ እረኛ ሆኖ በፍጹምነት እንዲያመልኩ ስላደረገ የምዕመናት ስቃይ አብቅቷል ።ለቅሶ አብቅቷል።በቃ ደስታ ብቻ ነው።ሃሌ ሉያ።ሰይጣን የለም።ሠራተኛው በመካከላችን የለም።እግዚአብሔርን ብቻ እናመልካለን ።
#በሰባተኛው ማህተም በጥቅልሉ መጽሐፍ ምን ይኖር ይሁን !? ከዮሐንስ ጋር እንቀጥል ፦
“ሰባተኛውንም ማኅተም በፈታ ጊዜ እኵል ሰዓት የሚያህል ዝምታ በሰማይ ሆነ።” ራእይ 8፥1
ዮሐንስ መጽሐፉ ስፈታ ስመለከት ፦
ጸጥታ ረጭ አለ፣
እግዚአብሔርም አይናገርም፣
ዝምታ ሆነ፣
ለቅሶም አብቅቷል።
__________________
የውስጥ ሰላም ያገኛቸችሁ ፣
የመጸለይ አቅም ይስጣችሁ ፣
ተስፋችን የታመነ ነው፣
በጉ ብርሃን ነው፣
በዚህ ፍጹም ሰላም ይሰማችሁ ፣
ከዮሐንስ ጋር የተመለከታችሁትን ራዕይ አሰላስሉ፣
ዘመኑን እወቁ፣
በእውቀት ጎልምሱ ፣
ሃሌ ሉያ።
________________________________________
በመጀመሪያው በር ሰማይ ስከፈት ዮሐንስ 7 ጥቅልል መጽሐፍ እንደተመለከተና የመጽሐፉን ምስጢር ደግሞ በጉ ስፈታ አይተናል ።ይህ የዮሐንስ በሁለተኛ በር የተመለከተው ራዕይ ነው።
በመጀመሪያ በር የዓለም መጨረሻ ከተገለጸ ፥ለምን ለዮሐንስ ራዕይ መገለጡ ቀጠለ!? ምናልባትም ከመጀመሪያው ጋር የማይገናኝ ይሁን !?
ለዮሐንስ የሁለተኛው በር አይታ ከመጀመሪያው መልእክት አድስ አይደለም ።አንዷን ሁኔታን በተለያየ መንገድ እንድያስተውል ተገልጦለት ነው ።አንዷን ክስተት የተለያየ ጋዘጠኛ መዘገቡ መረዳትን እንደሚያሰፋ ሁሉ እግዚአብሔር ዮሐንስ በደንብ ራዕዩን እንድረዳ በሌላ መንገድ መግለጥ ጀመረ ።በጉ 7ቱን ጥቅልል መጽሐፍ ተርትረው ከገለጸው አሁን የሚገለጠወሰ ሌላ አድስ ነገር አይደለም ።ግን መረዳታችን ከተለያየ እይታ በመግለጽ ለማስፋት ስለወደደ ይህንን አደረገ።ስለዚህም የራዕይ መጽሐፍ መረዳታችን እንድሰፋልን ማጥናታችን መመልከታችንን ከዮሐንስ ጋር እንቀጥል ፦
“በእግዚአብሔርም ፊት የሚቆሙትን ሰባቱን መላእክት አየሁ፥ ሰባትም መለከት ተሰጣቸው።” ራእይ 8፥2
ለሰባቱ መላእክት ሰባት መለከት ተሰጣቸው ።መለከት በዚህ ክፍል ከእግዚአብሔር የሆነውን ማስጠንቀቂያ ለማመልከት እንደሚነፋ የሚገልጽ ነው።ማስጠንቀቂያ በራሱ እጅግ በጣም ልብን የሚያስጨንቅ ነው።"ንቃ ንቁ" የሚል ሲሆን ምህረትን ለማድረግ ነው።
“ሌላም መልአክ መጣና የወርቅ ጥና ይዞ በመሰዊያው አጠገብ ቆመ፤ በዙፋኑም ፊት ባለው በወርቅ መሰዊያ ላይ ለቅዱሳን ሁሉ ጸሎት እንዲጨምረው ብዙ ዕጣን ተሰጠው።”ራእይ 8፥3
ዮሐንስ ከሰባቱ መላእክት ውጪ ሌላ "መላአክ" ተመለከተ። መላአኩ የተገለጠበት ሁኔታ ፦
፩.ጥና (የዕጣን ማጠኛ) የያዘ ነው፣
፪.በመሠዊያ አጠገብ የቆሜ ነው፣
፫.ለቅዱሳን ሁሉ ጸሎት የሚያቀርብ ነው፣
፬.የቅዱሳን ጸሎት ሁሉን ለማቅረብ ዕጣን ይዟል ፣
፭.ጸሎቱም ወደ እግዚአብሔር ፊት የቀረበለት ነው፣
፮.መልአኩ ማጥኛውን እሳት ሞላበት ፣
፯.እሳት የሞላበትን ማጠኛ ወደ ምድር ጣለው ፣
፰.ምድርም ተናወጠች ።
ይህ ሊቀ ካህናት ሆኖ በፉጡር መላአክ የተገለጠው ኢየሱስ ሳይሆን አይቀርም ።ምክንያቱም ኢየሱስ ራሱን በተለያየ መንገድ በራዕይ ገልጿል ።እናጥና ፦
የሰው ልጅ ምስሎ ራዕይ 1 ፣
የታረደ በግ መስሎ ራዕይ 5፣
አሁን ደግሞ ፉጡር መልአክ ምሳሌ ሆኖ ተገልጧል ።እንደዚህ በመላአክ አረአያ በብሉይም ይገለጥ ነበር።ስለዚህም በዚህ ክፍልም ሊቀ ካህናት አገልግሎት ያለው የፉጡር መላአክ ምሳሌ ሆኖ የተገለጠው ሊቀ ካህናታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።
.....
“ፊተኛውም መልአክ ነፋ፤ ደምም የተቀላቀለበት በረዶና እሳት ሆነ፥ ወደ ምድርም ተጣለ፤ የምድርም ሲሶው ተቃጠለ የዛፎችም ሲሶው ተቃጠለ የለመለመም ሣር ሁሉ ተቃጠለ።”ራእይ 8፥7
#በመጀመሪያው_ማስጠንቀቂያ ደም የተቀላቀለበት በረዶና እሳት ወደ ምድር ተጣለ ፣
ሰው የሚኖርበትን አከባቢ የሚመታ መቅሰፍት ነው፣
የምድር 1/3 ኛው ይቃጠላል (ሌላ ምህረት ተደርጎበታል ) ፣
ይህ የንስሐ ጥሪ ማስጠንቀቂያ ነው።በመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ ክርስቶስ እመኑ ።
“ሁለተኛውም መልአክ ነፋ፤ በእሳት የሚቃጠል ታላቅ ተራራን የሚመስል ነገር በባሕር ተጣለ፤ የባሕርም ሲሶው ደም ሆነ”ራእይ 8፥8
#በሁለተኛው_ማስጠንቀቂያ የተመታው ባህር ነው።መርከቦች ንግድ በባህር ላይ የሚያቀላጥፉ ስለሆነ መርኮቦችን የሚመታ ይሆናል ፣
“በባሕርም ከሚኖሩ ሕይወት ካላቸው ፍጥረቶች ሲሶው ሞተ የመርከቦችም ሲሶው ጠፋ።”ራእይ 8፥9
የመርከቦች መመታት የሰውን የንግድ መስመር መምታት ነው(ይህ ከሦስተኛው ማህተም ኢኮኖሚያዊ ጥቃት ጋር የሚገናኝ ነው) ፣
የንግድ ዘርፉ መመታት እኛ ቀላል ጉዳት የሚያስከትል አይደለም ፣
በዚህ መቅሰፍት ሰው ሁሉ 'የበረከቱ' ተካፋይ ነው።
ተመለሱ የሚል ደወል ነው ።1/3 ኛውን የሚመታ ነው።
__________________________________
“ሦስተኛውም መልአክ ነፋ፤ እንደ ችቦም የሚቃጠል ታላቅ ኮከብ ከሰማይ ወደቀ፥ በወንዞችና በውኃም ምንጮች ሲሶ ላይ ወደቀ። የኮከቡም ስም እሬቶ ይባላል።”ራእይ 8፥10
#ሦስተኛው_ማስጠንቀቂያ የሰውን የተፈጥሮ ሃብት (የግድ ለመኖር የሚያስፈልጉትን) የሚያጠቃ ነው፣
ለምሳሌ የሚጠጣ ውሃ በመመረዝ የሚያጠቃ ነው፣
“የውኃውም ሲሶ መራራ ሆነ መራራም ስለተደረገ በውኃው ጠንቅ ብዙ ሰዎች ሞቱ።”ራእይ 8፥11
አማኙ ጭምር ያለ ልዩነት የሚጠቃ ነው።1/3ኛው ውሃው ይመታል ብዙ ሰዎች ይሞታሉ።
እንዲህ ያለውን ስትመለከቱ አስተውሉ!
“አራተኛውም መልአክ ነፋ፤ የፀሐይ ሲሶና የጨረቃ ሲሶ የከዋክብትም ሲሶ ተመታ፥ የእነዚህ ሲሶ ይጨልም ዘንድ፥ የቀንም ሲሶው እንዳያበራ፥ እንዲሁም የሌሊት።”ራእይ 8፥12
የሰውን አከባቢ በመግጉዳት በተዘዋዋሪ ሰውን የሚገዳ ነው ።ዘፀ 10፥21-23 ፣
1/3ኛው ይመታል ፣
እንዲህ ያለውን የቀን ጨለማ ስትመለከቱ ከሳይንሳዊ ትንተና ወጥታችሁ የመጽሐፉን ቃል አስቡ!
መመለስ ንሰሐ ከእኛ አይራቅ።
ወደ አምስተኛው ማስጠንቀቂያ ከመግባቱ በፊት የ3 ግዜ የወዮታ ድምጽ ይሰማል ።“አየሁም፥ አንድም ንስር በሰማይ መካከል እየበረረ በታላቅ ድምፅ፦ ሊነፉ ያላቸው የሦስቱ መላእክት መለከት ስለሚቀረው ድምፅ በምድር ላይ ለሚኖሩት ወዮላቸው፥ ወዮላቸው፥ ወዮላቸው ሲል ሰማሁ።”ራእይ 8፥13
____________________________________
“አምስተኛውም መልአክ ነፋ፤ ከሰማይም ወደ ምድር ወድቆ የነበረ ኮከብ አየሁ፥ የጥልቁም ጕድጓድ መክፈቻ ተሰጠው።” ራእይ 9፥1
በዚህ ማስጠንቀቂያ ጥቃት የሚፈጽመው ራሱ ሰይጣን ነው።ወድቆ የነበረ ኮከብ እና አብዶን (ሰይጣን) ተብሏል በቁ.11 ላይ።አምስተኛው መለከት ፊተኛው ወዮ ይባላል ቁ.12።
“የጥልቁንም ጕድጓድ ከፈተው፤ ጢስም ከታላቅ እቶን እንደሚወጣ ጢስ ሆኖ ከጕድጓዱ ወጣ ፀሐይና አየርም በጕድጓዱ ጢስ ጨለሙ።” ራእይ 9፥2
መንፈሳዊ ጨለማ የሚያመጣ መንፈሳዊ አዝም ጥቃት ሳይሆን አይቀርም፣
በዚህ መቅሰፍት ሰይጣን ጥቃት ሃይሉን አጠናክሮ ጥቃት ብፈጽምም ፣ አማኞች ላይ አንዳች ነገር ለማድረግ መፍት እና ስልጣን የለውም ቁ.4። ስለዚህም በዚህ መቅሰፍት የሚመቱት ኢ-አማኝ የሆኑትና ራሳቸውን መሃል ሰፋር አድርገው የሚቆጥሩቱ ናቸው ።መሃል ሰፋርነትም የሰይጣን ባሪያነት ነው።ምክንያቱም ከሁለቱ ከማይታዩ ሃይላት ለአንዱ ይሆናል እንጂ ፤በመሃል መሄድ ብሎ ነገር የለምና።
“ከጢሱም አንበጣዎች ወደ ምድር ወጡ፥ የምድርም ጊንጦች ሥልጣን እንዳላቸው ሥልጣን ተሰጣቸው።”ራእይ 9፥3
አደገኛ የአንበጣ መንጋ ጥቃት ይፈጸማል ።ይህ ሁሉ ጥቃት ኢ-አማኙን ብቻ ነው ቀ.4።
“አምስትም ወር ሊሣቅዩአቸው ተሰጣቸው እንጂ ሊገድሉአቸው አይደለም፤ እነርሱም የሚሣቅዩት ሥቃይ ጊንጥ ሰውን ነድፎ እንደሚሣቅይ ነው።”ራእይ 9፥5
የአንበጣ መንጋው ለ5ወር የሚያሰቃይ ጥቃት የሚፈጽም ነው(የአንበጣ ሕይወት ለ5ወር የሚቆይ ስለሆነ ነው) ።መግደል እንኳን አይገድልም ።ከስቃዩ ቃጠሎ የተነሳ ሰዎች መሞት የመኛሉ መኖርን ይጠላሉ ግን አይሞቱም ቁ.6።ሞት ራሱ ይሸሻቸዋል።ስቃይ ብቻ ነው ያለው ።
ጥቃቱ ሙሉ በሙሉ ከሰይጣን ብሆንም ጌታ ለሰይጣን አሳልፎ የሰጣቸው የማይያምኑቱ በአውረ እንጂ ወድቀው ከተሰቃዩ በንስሐ ይመለሳሉ ብሎ ነው።
የአንበጣው መልክ ም.9 ቁ.7-11 እንደተቀመጠው ፦
እንደ ሰው ፊት ያለ ነው(መሰሪይ ነው)፣
የሴት ጠጉር የሚመስል ጠጉር አለው(ረጅም አንተና)፣
እንደ አንበሳ ያለ ጥርስ አለው(ጨቃኝ ነው)፣
የብረት ጥሩር የሚመስል (በቀላል ሰውነትን የሚጎዳ፤)፣
የክንፋቸውም ድምጽ (ልብን የሚሸብር ፍርሃት የሚለቅ) ፣
እንደ ጊንጥ ያለ ጅራት (መከራ የሚያመጣ ነው)፣
የአንበጣው አዛዥ አብዶን የተባለው ሰይጣን ነው ቁ.11።
ይህንን ስትመለከቱ አስተውሉ!
____________________________________
“ስድስተኛውም መልአክ ነፋ፤ በእግዚአብሔርም ፊት ካለ በወርቅ ከተሠራ መሠዊያ ቀንዶች አንድ ድምፅ ሰማሁ፥”ራእይ 9፥13
የ6ኛው ማስጠንቀቂያ ሁለተኛው ወዮ ነው።ይህ ማስጠንቀቂያ ከወርቅ ከተሰራ ፥ከመሠዊያው ቀንዶች የወጣ መሆኑ እጅግ አስፈር ያደርገዋል ።ምክንያቱም የመሠዊያውን ቀንድ መያዝ የተኛውንም በደል ምህረት ያሰጣል በብሉይ ኪዳን።ከዚህ የወጣው ድምጽም የመጨረሻ የምህረት ጥሪ እንደሆነ አያጠራጥርም ። ወደ እግዚአብሔር አሁን ቅረቡ የሚል ነው።
“መለከትም ያለውን ስድስተኛውን መልአክ፦ በታላቁ ወንዝ #በኤፍራጥስ የታሰሩትን አራቱን መላእክት ፍታቸው አለው።”ራእይ 9፥14
ብዙ አማጽያን የሚነሱበት ቦታ የተጠቀሰው አደገኛ አመጽ እንደሚነሳ እና እልቅት እንደሚሆን ለመግለጽ ነው።1/3ኛ የሰው ልጅ ከምድር ይጠፋል ቁ.15።
“ፈረሶቹንና በእነርሱም ላይ የተቀመጡትን እንዲሁ በራእይ አየሁ፤ እሳትና ያክንት ዲንም የሚመስል ጥሩር ነበራቸው፤ የፈረሶቹም ራስ እንደ አንበሳ ራስ ነበረ፥ ከአፋቸውም እሳትና ጢስ ዲንም ወጣ።” ራእይ 9፥17
የተመደቡ መላእክት ለማጥፋት የተዘጋጁ ናቸው ። ይህንን እልቂት የሚፈጽሙ የእግዚአብሔር መላእክት ናቸው ።ከሰው ወገን 1/3 ኛውን ይገላሉ።የቀሩቱ በመልካምነታቸው ሳይሆን ንስሐ እንድገቡ ነው ቁ.20-21።
.....
ከ6ተኛው መቅሰፍት በኃላ 7ተኛው መቅሰፍት ወደሃኑ አልተነፋም።በመኃል ሌላ ማሳሰቢያ ገብቷል ። እንመልከት ፦
“ሌላም ብርቱ መልአክ ደመና ተጐናጽፎ ከሰማይ ሲወርድ አየሁ፤ በራሱም ላይ ቀስተ ደመና ነበረ፥ ፊቱም እንደ ፀሐይ እግሮቹም እንደ እሳት ዓምዶች ነበሩ፥”ራእይ 10፥1
ዮሐንስ ስመለከት ፦
፩.ደመና የተጎናጸፈ መላአክ ነው ፣
፪.ለማጥፋት ኪዳን የገባ ምልክት ያለው ነው፣
፫.የእሳት ዓምድ የሆነ እግር ያለው ነው(እስራኤላውያን በጉዞ ይከተላቸው የነበረ ነው) ፣
“የተከፈተችንም ታናሽ መጽሐፍ በእጁ ያዘ። ቀኝ እግሩንም በባሕር ላይ ግራውንም በምድር ላይ አኖረ፥ እንደሚያገሣም አንበሳ በታላቅ ድምፅ ጮኸ።”ራእይ 10፥2
፬.የሚገለጥ መጽሐፍ ሳይሆን የሚበላ ትንሽዬ ጥቅልል መጽሐፍ የያዘ መላአክ ነው፣
፭.የፍጥረታት ዕድል ፈንታ የሚሰጥ መላአክ ነው፣
፮."ጮኸ" እስካሁን ለምን መለከቱን ሰምተው ንስሐ አይገቡም የሚል ነው፣
“ሰባቱ ነጐድጓድ በተናገሩ ጊዜ ልጽፍ አሰብሁ፤ ከሰማይም፦ ሰባቱ ነጐድጓድ የተናገሩትን ነገር በማኅተም ዝጋው #አትጻፈውም የሚል ድምፅ ሰማሁ።” ራእይ 10፥4
፰.መላአኩ ስጮኽ ሰባቱ መለኮታዊ ቅጣት አምጭሆች ተናገሩ ፣
፱.ግን ምን እንዳሉ ዮሐንስ ለመጻፍ አልተፈቀደለትም፣
፲.ዮሐንስ የተመለከተው መላአክ እጁን ከፍ አድርጎ "ማሌ" ቁ.6 (በቅርቡ ከሰባተኛው መለከት በኃላ ሁሉም ነገር እንደሚያበቃ እንደሚፈጸም አስታወቀ) ፣
ዮሐንስ መጀመሪያ የተመለከተውን ትንሿን መጽሐፍ ከመላአኩ ወሰደ ቁ.9 ።ከወሰደም በኃላ በላ፣ በአፍ የሚትጣፍጥ በሆድ መራራ የሆነች ወንጌል ናት ቁ.10።ከዚህም ፦
“በብዙ ወገኖችና በአሕዛብም በቋንቋዎችም በነገሥታትም ላይ እንደ ገና #ትንቢት_ትናገር ዘንድ ይገባሃል ተባለልኝ።” ራእይ 10፥11
በዚህ ክፍል ላይ እንደሚንመለከተው ይህ ራዕይ የተገለጠው ከ6ኛው መለከት (ማስጠንቀቂያ) በኃላ ነው ፤በመኃል ነው የተገለጠው ።7 ተኛው መለከት ከመነፋቱ በፍት መላአኩ ዮሐንስን "ትንብት ተናገር" አለው።ትንብት የተባለው ነገ መኪና ፣ቤት ፣ ሱቅ ..የስከት በር..ልትበይል.. ልተወው..ልቀጥል ..ወዘተ ምናምን የሚል አይደለም ። የእግዚአብሔር ቃሉን ተናገር የሚል ነው እንጂ።(ነቢይነት የእግዚአብሔር አፍ መሆን ነው።እዚህ ላይ ለዮሐንስ የተገለጠው መላአክ እስካሁን እየጣሁ ለምን ንስሓ አትገቡም ለምን አትመመለሱም የሚል እጅግ ከባድ ጩኸት የሚያሰማ ነው።)
ስለዚህም ዮሐንስ በዚያ ሰዓት የሚናገረው ትንብት "ቃል" የመጨረሻው መለከት ብቻ ነው የቀረው ፤ሁሉም ነገር ልያበቃ ነው፤" ኢየሱስ ይመጣል" ብሎ የሚሰብክ ነው።(እኛስ!? ከ2000 ዓመት በኃላ ይልቁንም እንዴት አብልጠን እንሰብክ እንዘጋጅ ይሁን !?።)
የቤተክርስቲያን ተልዕኮ ይህ ነው።በመጨረሻው ሰዓት ላይ ነው ያለነው ።የመጨረሻው መለከት ልነፋ ነው።ኢየሱስ ልመጣ በደጅ ነው።ንስሐ ግቡ የሚትል ናት።አዎን ኢየሱስ ልመጣልን ነው።ወዮ ላልቀበሉት።ንስሐ ላልገቡት።
..
አሁንም 7ተኛ መለከት አልተነፋም ። ከመነፋቱ በፍት በመሃል የገባውን ራዕይ እየተመለከትን ነው ያለነው ።እንቀጥል ፦
“በትር የሚመስል መለኪያ ለእኔ ተሰጠኝ፥ እንዲህም ተባለልኝ፦ ተነሥተህ የእግዚአብሔርን መቅደስና መሠዊያውን በዚያም የሚሰግዱትን ለካ።”ራእይ 11፥1
የዮሐንስ መጀመሪያ ወንጌልን እንድሰብክ ታዘዘ ም.10. ፥11 ።በመቀጠል ደግሞ ፦ቤተመቅደስን እንድለካ ታዘዘ።ቤተመቅደስ የተባለው የብሉይ አምልኮ የሚደረግበት ሕንፃ ወይም ድንኳን ሳይሆን ፣ በአድስ ኪዳን ቤተመቅደስ የተባሉትን አማኞችን ነው።
ኢየሱስ ሊቀ ካህናት ሲሆን የሚድር ቤተመቅደስ አገልግሎቷ ቀርቷል።እንደሁም ፈርሳ ቀረች።
“በመቅደሱም ውጭ ያለው እድሞ ለአሕዛብ ተሰጥቶአልና ተወው አትለካውም፤ እነርሱም አርባ ሁለት ወር የተቀደሰችውን ከተማ ይረግጡአታል።” ራእይ 11፥2
አሕዛብ የማያምን በዚህ ቆጠራ ላይ አይካተቱም፣
ለ42 ወር ከተማውን ዓለማዊ አድርጎ ይቆጣጠራሉ ይገዛሉ ሉቃ 21፥24።የአማኞች መቆጠር ከአሕዛቦች ለመለየት ለመጠበቅ ነው።(ከ6ተኛው ማህተም ጋር ይገናኛል )
“ለሁለቱም ምስክሮቼ ማቅ ለብሰው ሺህ ከሁለት መቶ ስድሳ ቀን ትንቢት ሊናገሩ እሰጣለሁ።”ራእይ 11፥3
ሁለት ምስክር (ምስክርነታቸው ሁለት ሲሆን ተአማኒነት አለው) ዘዳ 17 ፣
ለ1260 ቀን /ለ42 ወር/ለ3 ዓምት ከተኩል/ ይሰብካሉ ይመሰክራሉ ፣
“እነዚህ በምድር ጌታ ፊት የሚቆሙ ሁለቱ ወይራዎችና ሁለቱ መቅረዞች ናቸው።” ራእይ 11፥4
የታመኑ ምስክሮች ወይራ ናቸው (ጠንካራ) ፣
መቅረዝ ናቸው (ብርሃን ናቸው ) ፣
“ማንምም ሊጐዳቸው ቢወድ እሳት ከአፋቸው ይወጣል ጠላቶቻቸውንም ይበላል፤ ማንም ሊጐዳቸው ቢወድም እንዲሁ ሊገደል ይገባዋል።”ራእይ 11፥5
ከእነርሱ ጋር የእግዚአብሔር ሃይል አለ።
“እነዚህ ትንቢት በሚናገሩበት ወራት ዝናብ እንዳይዘንብ ሰማይን ሊዘጉ ሥልጣን አላቸው፥ ውኃዎችንም ወደ ደም ሊለውጡ በሚፈልጉበትም ጊዜ ሁሉ በመቅሠፍት ሁሉ ምድርን ሊመቱ ሥልጣን አላቸው።” ራእይ 11፥6
ዝናብ እንዳይዘንብ እንደ ኤልያስ ያደርጋሉ ፣
ውሃውን ወደ ደም ይቀይራሉ እንደ ሙሴ፣
*እነዚህ ሁለት ምስክር የተባሉት በሙሴና በኤልያስ መንፈስ የሚያገለግሉ አማኞች ሁሉ ናቸው ።
“ምስክራቸውን ከፈጸሙ በኋላ ከጥልቁ የሚወጣው አውሬ ይዋጋቸዋል ያሸንፋቸውማል ይገድላቸውማል።” ራእይ 11፥7
ምስክርነታቸውን ስለፈጸሙ ስላሳኩ ፥ ይሞታሉ ፥ ይገደላሉ በሰይጣን ።ሰይጣን ሙሉ በሙሉ ይቆጣጠራል ፣
ስጋቸውም እንኳን አይቀበርም ቁ.9፣
አሕዛብ ይመለከታሉ በመሞታቸው ይደሰታሉ ቁ.8 ስጦታታም ይለዋወጣሉ ቀ.10፣
“ከሦስቱ ቀን ተኵልም በኋላ ከእግዚአብሔር የወጣ የሕይወት መንፈስ ገባባቸው በእግሮቻቸውም ቆሙ፥ ታላቅም ፍርሃት በሚመለከቱት ላይ ወደቀባቸው።”ራእይ 11፥11
እነዚህ የሞቱቱ የአሕዛብ መንግስት እስከሚወድቅ ድረስ መሳለቂያ ሆነዋል ፣ግን የእግዚአብሔር እስትንፋስ የፈጠራቸው ያዳናቸው አምላክ ፣የታመኑለት ጌታ ደረቅ አጥንታቸውን ያስነሳል።ሕዝ 37፥5-14
“በሰማይም፦ ወደዚህ ውጡ የሚላቸውን ታላቅ ድምፅ #ሰሙ፤ ጠላቶቻቸውም እየተመለከቱአቸው ወደ ሰማይ በደመና ወጡ።” ራእይ 11፥12
የደረቀ አጥንታቸው ፦
የትንሳኤ ጌታ የእንደገና አምላክ አስነሳቸው፣
ድምጹን ሰሙ ፤ ተነሱ፣
ወደ ሰማይ ከፍ ከፍ ብለው ተነጠቁ 1ተሰ 4፥16-17፣
ሃሌ ሉያ።
አምላካችን አስገድዶ በመጨረሳው ሰዓት ለራሱ ያስሰግዳል (አሕዛብን ይረግጣል የተባለው ቃል ይፈጸማል ዕብ 10፥13)።“በዚያም ሰዓት ታላቅ የምድር መናወጥ ሆነ፥ ከከተማይቱም አሥረኛው እጅ ወደቀ፥ በመናወጥም ሰባት ሺህ ሰዎች ተገደሉ፥ የቀሩትንም ፍርሃት ያዛቸው፥ ለሰማዩም አምላክ ክብር ሰጡ።”ራእይ 11፥13
ተስፋችን የታመነ ነው፣
ወንጌል ለሕይወት እንጀራችን ነው ...
________________________________________
“ሁለተኛው ወዮ አልፎአል፤ እነሆ፥ ሦስተኛው ወዮ በቶሎ ይመጣል።”ራእይ 11፥14
ሦስተኛው ወዮ የበጉ መምጫ ነው፣
ሁሉም ነገር ይፈጸማል ፣
“ሰባተኛው መልአክ ነፋ፤ በሰማይም፦ የዓለም መንግሥት ለጌታችንና ለእርሱ ለክርስቶስ ሆነች፥ ለዘላለምም እስከ ዘላለም ይነግሣል የሚሉ ታላላቅ ድምፆች ሆኑ።” ራእይ 11፥15
መንግሥቱ ለእርሱ ሆነች፣
የሰይጣን ታሳሪ የለም፣
ይህ የዓለማዊያን መጨረሻ የአማኞች ፍጹምነት ጅማሮ ነው፣
“በእግዚአብሔርም ፊት በዙፋኖቻቸው የተቀመጡ ሀያ አራቱ ሽማግሌዎች በግምባራቸው ተደፍተው ለእግዚአብሔር እየሰገዱ” ራእይ 11፥16
ከ24 ቱ ሽማግሌዎች ከቤተሰቡ መካከል የሆናችሁቱ አብረን ድምጻችን ከፍ አድርገን እናምብብ ፦
" ..ያለህና የነበርህ ሁሉን የምትገዛ ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፥
ትልቁን ኃይልህን ስለ ያዝህ ስለ ነገሥህም እናመሰግንሃለን፤
¹⁸ አሕዛብም ተቈጡ፥
ቍጣህም መጣ፥
በሙታንም ትፈርድ ዘንድ ዘመን መጣ፥
ለባሪያዎችህም ለነቢያትና ለቅዱሳን ስምህንም ለሚፈሩት ለታናናሾችና ለታላላቆችም ዋጋቸውን ትሰጥ ዘንድ
፥ ምድርንም የሚያጠፉትን ታጠፋ ዘንድ ዘመን መጣ።
አሜን ሃሌ ሉያ።
...
የዮሐንስ የሁለተኛው የሰማይ በር ስከፈት የተመለከተውን ራዕይ (ም.8) ከመጀመሪያው ሰማይ በር ስከፈት ከተመለከተው ራዕይ (ራዕይ 4) ጋር የአንድ ሳንትም ሁለት ገጽታዎች ናቸው ብለን ነበር።እስኪ የማህተሙን እና የመለከቱን ምስጥር በንፅፅር እንመልከት ፦
6ኛው #ማህተም ከተከፈተ በኃላ 7ኛው ማህተም ከመከፈቱ በፊት "እግዚአብሔር ገና የሚድኑት ይኖራሉ " ብሎ የሚመጣውን መቅሰፍት መከልከሉን እንመለከታለን (ም.7፥3) ፣ ደግሞም ከ6ኛው #መለከት በኃላ ያመኑቱ እንድጠበቁ ማድረጉ የሁለቱንም መልእክት የአማኞች በእግዚአብሔር ጥበቃ መሆናቸውን የሚያሳይ ነው፥
ከ6ኛው ማህተም በኃላ 7ኛው ማህተም ከመከፈቱ በፊት ዮሐንስ የሚድኑትን ቁጥር ሲሰማ ፥ከ6ኛው መለከት በኃላ ዮሐንስ የሚድኑቱን እንድለካ (እንድለያቸው) መስማቱ በሁለት መንገድ አንድ ሁኔታ መገለጡን እንረዳለን ፣
በ7ኛው ማህተም የእግዚአብሔር ዝምታ የሕዝቡ ደስታ ስንመለከት ም.8 ፥ በ7ኛው መለከት የፍጥረታት ምስጋና እንመለከታለን ፣
አምስተኛው ማህተም በአማኞች ብቻ መከራ እንደሚደርስ ስያወሳ ፣ 6ኛው መለከትም የአማኞች አሰቃቂ መከራ እና መረገጥ እና መማረክ ያወሳል ፣
በ3ኛው ማህተም ኢኮኖሚ ስመታ ፥ በ2ኛው መለከትም ንግዱ መመታቱን ያወሳል ፣
7ቱ ማህተሞቹ እስከ ክርስቶስ ዳግም ምጽአት ድረስ ያለውን ልዩ ልዩ መከራ ላይ ስያተኩር፥7ቱ መለከቶች ደግሞ እስከ ክርስቶስ ዳግም ምጽአት ድረስ ያለውን ልዩ ልዩ ማስጠንቀቂያ ላይ ያተኩራል ፣
*በ7ቱ ማህተሞችና በ7ቱ መለከቶች በተመለከትነው ራዕይ ሁሉም ክንውኖች በእግዚአብሔር ቁጥጥር ስሪ እንደሆነ እንገነዘባለን ፣
በተለያየ አቅጣጫ ራዕይን መመልከት ለመረዳት መልካም መሆኑን እንገነዘባለን ።
...
#3ኛውን የሰማይ በር መከፈት እንመለከታለን ፦
“በሰማይም ያለው የእግዚአብሔር መቅደስ ተከፈተ፥ የኪዳኑም ታቦት በመቅደሱ ታየ፥ መብረቅና ድምፅም ነጐድጓድም የምድርም መናወጥ ታላቅም በረዶ ሆነ።”ራእይ 11፥19
የእግዚአብሔር መቅደስ ፦እግዚአብሔር ከሕዝቡ ጋር እንደሆነ እንደሚገኝ ያመለክታል ፣
የኪዳኑ ታቦት መታየት ፦ ከግራር እንጨት የተሰራው ከወርቅም የተለበጠው ሳይሆን (ዘፀ 25፥10-31) ፣ እግዚአብሔር የገባውን ቃል ኪዳን እንዳላፈረሰ የሚያመለክት ነው።(ለዚያ ነው ከሕዝቡ ጋር የሚሆነው )፣
በሰማይም ፦ይህ ስፍራ በዚህ አውድ ፍጹም የእግዚአብሔር ሰላም ያለቦታን የሚያመለክት ሳይሆን እንድሁም መናወጥ ጦርነት ያለ ቦታ መሆኑን እንረዳለን ፣
ዮሐንስ ሰማይ ስከፈት ጦርነትን መመልከት ጀምሯል ።ከዮሐንስ ጋር እንመልከት ፦
“ታላቅ ምልክትም በሰማይ ታየ ፀሐይን ተጐናጽፋ ጨረቃ ከእግሮችዋ በታች ያላት በራስዋም ላይ የአሥራ ሁለት ከዋክብት አክሊል የሆነላት አንዲት ሴት ነበረች።”ራእይ 12፥1
#ታላቅ ምልክት ተመለከተ ሴትቱ ናት ፦ ፀሐይን የተጐናጸፈች ፥ ጨረቃ ከእግሮቿ በታች ያላት፥ በራሷም አስራ ሁለት ከዋክብት አክሊል የሆነላት ናት ዘፍ 37፥9 ፣
ሴትቱ የተባለችው አንድ ግለሰብ ትመስላለች ።ግን ብዙ የሆኑ አንዶችን የሚያመለክት ነው፣
ፀንሳ ነበር ለመውለድ ተጨንቃ ጮኸች ቁ.2፦ አደገኛ መከራ ላይ ነች፣
“ሌላም ምልክት በሰማይ ታየ፤ እነሆም ታላቅ ቀይ ዘንዶ፤ ሰባት ራሶችና አሥር ቀንዶችም ነበሩት በራሶቹም ላይ ሰባት ዘውዶች ነበሩ፥”ራእይ 12፥3
#ሌላ ምልክት ታየ ቀይ ዘንዶ ነው ፦ ታላቅ ቀይ ዘንዶ ዲያቢሎስ ነው ቁ.9 ፣
ሰባት ራሶች አሉት ፦ሥልጣን አለው፣
ዐሥር ቀንዶች አሉት ፦ብዙ ሃይል አለው ፣
በራስቹ ላይ ዘውዶች አሉት፦ጥበብ እና ሥልጣን አለው፣
ስሶውን ይስባል ወደ ምድር፦1/3ኛውን ያሸንፋል ቁ.4 ፣
“ ዘንዶውም ሴቲቱ በወለደች ጊዜ ሕፃንዋን እንዲበላ ልትወልድ ባላት ሴት ፊት ቆመ።”ራእይ 12፥4
ዘንዶው እና ሴትቱ ፊት ለፊት ተጋጠሙ ።ሴትቱ ለመውለድ ተጨንቃለች ፣ ዘንዶውም ሴትቱ የሚትወልደውን ልጇን ለመብላት ፊት ለፊት ቆመ፣
የዘንዶው ትኩረት መጀመሪያም ሴትቱ አይደለችም ፤ልጇ ነው።ሴትቱ ግን ዘንዶውን እና ተከታዮቹን የሚያሸንፈውን ወለደች ፣
ገና ስወለድም ወንድ ነው፣በአገልግሎቱም ወንድ ነው፣በመጨረሻም ሁሉንም አሸንፎ እርሱ ከፍ አለ፣የተሸነፉትንም ይረግጣል ፣ወንድ በመሆኑ አሸነፈ ተነጠቀ ቁ.4፣
“ሴቲቱም ሺህ ከሁለት መቶ ስድሳ ቀን በዚያ እንዲመግቡአት በእግዚአብሔር ተዘጋጅቶላት ወደ ነበረው ስፍራ ወደ በረሀ ሸሸች።”ራእይ 12፥6
ሴትቱ ግን ብቻዋን ወደ በረሃ ሸሸች ፥ ለ1260 ቀን ።ማለትም 1260 ቀን ሙሉ በሙሉ እግዚአብሔር ይጠብቃል ይመግባታል ።ልጇ ስላሸነፈ ዘንዶው በሴትቱ ላይ ስልጣን የለውም፣
1260 ቀን ባለፈው ጥናታችን መሠረት እንደተመለከትነው በ6ኛው መለከት ስነፋ ሰይጣን ይገዛል ፣ ዓለምን ይቆጣጠራል ።በሴትቱ ላይ ግን ሥልጣን የለውም።ሴትቱ የቤተክርስቲያን ምሳሌ የሆነች አማኞችን ትወክላለች።
*አንድት ሴት በተፈጥሮ መንገድ መውለድን የሚያመለክት ይመስላል ።ግን ሴትቱ መከራዋ አይሎ ፣ ሥጋዋ ደክሞ ፣እጅግ ከብዶባት ጭንቀቷ፣ በዚህ በመጨረሻ በመከራው ሰዓት ተጨንቃ ፣የሚያድናት ጌታ ፣ቤተሰቧ የሆነላት ፣እንድደርስላት ትቃትታለች። በመጨረሻም የቤተሰቧ አካል (ራስ) የሆነው ወንዱ ልጁ በዚያን ክፉ ግዜ ለ1260 ቀን ሙሉ ጥበቃ አደረገላት )
እንቀጥላለን ...
“በሰማይም ሰልፍ ሆነ፤ ሚካኤልና መላእክቱ ዘንዶውን ተዋጉ። ዘንዶውም ከመላእክቱ ጋር ተዋጋ፥ አልቻላቸውምም፥”ራእይ 12፥7
በ3ኛው የሰማይ በር መከፈት ዮሐንስ የተመለከተው የማይታዩ ኀይላት እርስ የሚያደርጉ ጦርነትን ነው።
እንግዲህ በዳንኤል 10 ላይ አጋንንቶች መላአኩ ወደ ዳንኤል መልእክቱን እንዳያደርስ እየተዋጋ እንደከለከሉት ቃሉ ይነግረናል ።የዘንዶው እና የመላእክት ውጊያ በዚህ በመጨረሻው ዘመን የሚሆን አይደለም ።መጀመሪያም ነበር።ግን በዚህ ግዜ የሚደረገው ጦርነት አደገኛ የመጨረሻ እንደሆነ እንረዳለን ።(እኛ የማናያቸው ኀይላት እርስ በእርስ ይዋጋሉ )ምንም እንኳን ብዋጉም እስከመጨረሻ ልንቋቋማቸው አልቻለም ።
“ከዚያም ወዲያ በሰማይ ስፍራ አልተገኘላቸውም።” ራእይ 12፥8 ።
የማይታዩ አካላት ውጊያ በሰማይ የሚደረግ ነው።ዘንዶውም ዲያብሎስ በሰማይ ነው ያለው ማለት ነው።ለዚያ ይሆናል አሁን በመጨረሻው ዘመን ከመላእክቱ ጋር ተዋግቶ የሰማይ ስፍራ ስላልለቀቀ ይሆናል ጳውሎስ ዘንዶው በሰማይ ስፍራ እንዳለ የተናገረው ፦ “መጋደላችን ከደምና ከሥጋ ጋር አይደለምና፥ ከአለቆችና ከሥልጣናት ጋር ከዚህም ከጨለማ ዓለም ገዦች ጋር #በሰማያዊም_ስፍራ ካለ ከክፋት መንፈሳውያን ሠራዊት ጋር ነው እንጂ።”ኤፌሶን 6፥12
“ዓለሙንም ሁሉ የሚያስተው፥ ዲያብሎስና ሰይጣን የሚባለው ታላቁ ዘንዶ እርሱም የቀደመው እባብ ተጣለ፤ ወደ ምድር ተጣለ መላእክቱም ከእርሱ ጋር ተጣሉ።”ራእይ 12፥9
ዘንዶው ወደ ምድር ስወድቅ የእግዚአብሔር መላእክትም ከዘንዶው ጋር ከሰማይ ወደ ምድር ወርደዋል ።(ዘንዶው በምድር ያሉትን ፣ የበጉ የሆኑትን እንዳይጎዳቸው ልሆን ይችላል )
ዘንዶው ወድቋል ስለተሸነፈ ።በሰማይ መላእክት ያሰሙትን ድምፅ ለእኛ የሚያስራች እና ማስጠንቀቂያ ነው።ድምጻችንን ከፍ አድርገን እናምብብ ፦
ራእይ 12
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁰ ታላቅም ድምፅ በሰማይ ሰማሁ እንዲህ ሲል፦ አሁን የአምላካችን ማዳንና ኃይል መንግሥትም የክርስቶስም ሥልጣን ሆነ፥ ቀንና ሌሊትም በአምላካችን ፊት የሚከሳቸው የወንድሞቻችን ከሳሽ ተጥሎአልና።
¹¹ እነርሱም ከበጉ ደም የተነሣ ከምስክራቸውም ቃል የተነሣ ድል ነሡት፥ ነፍሳቸውንም እስከ ሞት ድረስ አልወደዱም።
¹² ስለዚህ፥ ሰማይና በውስጡ የምታድሩ ሆይ፥ ደስ ይበላችሁ፤ ለምድርና ለባሕር ወዮላቸው፥ ዲያብሎስ ጥቂት ዘመን እንዳለው አውቆ በታላቅ ቍጣ ወደ እናንተ ወርዶአልና።
ዘንዶው ከሰማይ ወድቋል ።ስፍራውን ለቋል።“ዘንዶውም ወደ ምድር እንደ ተጣለ ባየ ጊዜ ወንድ ልጅ የወለደችውን ሴት አሳደዳት።”ራእይ 12፥13
ዘንዶው ከሰማይ ከመውረዱ በፊት ከሴትቱ ልጇ ጋር ይዋጋ ነበር።አሁን ደግሞ ከሴትቱ ጋር ይዋጋል።(በምድር ጦርነት ከመጀመሩ በፊት በሰማይ ተጀምሯል ማለት ነው)
“ከእባቡም ፊት ርቃ አንድ ዘመን፥ ዘመናትም፥ የዘመንም እኵሌታ ወደ ምትመገብበት ወደ ስፍራዋ ወደ በረሀ እንድትበር ለሴቲቱ ሁለት የታላቁ ንሥር ክንፎች ተሰጣት።” ራእይ 12፥14
ሴትቱን ዘንዶው እንዳያገኛት ለ1260 ቀን እግዚአብሔር ጥበቃ እና በራሱ መግቦት በማድረግ ጠብቆዋታል።ለሴትቱ ሁለት ታላላቅ ንሥር ክንፎች ተሰጣት ማለት የያዛት አምላክ የታመነ ፣ከእጁ ማንም ልወስድ የማይችል አስተማማኝ ዋሻ ነው ያላት ማለት ነው።ዘንዶው ይህንን መከራ ኢየሱስ ከመምጣቱ በፊት በአማኞች ላይ እንደሚያደርስ በማህቶሞቹም በመለከቶችም መከፈት ተረድተናል ።( ምዕመናንን ገና አደገኛ መከራ ይደርሳል)
“እባቡም ሴቲቱ በወንዝ እንድትወሰድ ሊያደርግ ወንዝ የሚያህልን ውኃ ከአፉ በስተ ኋላዋ አፈሰሰ።”ራእይ 12፥15
ሴቱትን ልጥል በእጁ ለማዝገባት ራሱ ሞከረ ፣ ግን ልይዛት አልቻለም ቁ.16።ልክ እስራኤላውያን እግዚአብሔር በምድር ስራዳ ግብጻውያን ስያሳድዱት ባህርን ተጠቅሞ እንዳተረፋቸው ።ሴትቱንም ከዘንዶው እንዲህ ያተርፋል ።(የዘንዶው ስራ አስፈፃሚ የሆኑቱ አቅም እግዚአብሔር ተፈጥሮን ተጠቅሞ ሳያፈርስ አይቀርም)
“ዘንዶውም በሴቲቱ ላይ ተቈጥቶ የእግዚአብሔርን ትእዛዛት የሚጠብቁትን የኢየሱስም ምስክር ያላቸውን ከዘርዋ የቀሩትን ሊዋጋ ሄደ፤”ራእይ 12፥17
ምዕመናንን የክርስቶስ ቤቱ የሆኑትን ክርስቶስ ከመምጣቱ በፊት አሳድዶ አሳድዶ መያዝ ልጥላቸው ባለመቻሉ ፣ የቀሩቱን የኢየሱስ ምስክሮችን ልዋጋ "ሄደ" ።ዘንዶው የቀሩቱ ዘሮችን ለመዋጋት ለምን ሄደ ሄት ሄደ !?
(እነዚህ ከሴትቱ ዘር የቀሩቱ ሴትቱን ለማስካድ ያለውን አቅም ሁሉንም ስጠቀም ፣ ማለትም እርሱ አንደኛው በአሰቃቂ መከራ ስገድል ሌላ አድስ አማኝ ሁለት ሳይወለድ አይቀርም በመጨረሻም ዘመን)
*በነገራችን ላይ ለሴትቱ ሁለት ክንፍ አለ፣ አስተማማኝ እጅ ውስጥ ናት ማለት መከራ አያገኛትም እያልን አይደለም ።መከራውን የሚታሸንፍ ናት ማለታችን ነው።
“በባሕርም አሸዋ ላይ ቆመ።”ራእይ 12፥18
ዘንዶው የቀሩቱን ለመዋጋት ወደ ባህር ወደ ዓለማዊያን መጣ።ከእነርሱ ጋር ይሰራል።ከዓለማዊያን ጋር በጥምረት የሚሰራው ጥበቡን ተጠቅሞ ፣የውጊያ አካሄዱን ቀይሮ ሳይሆን አይቀርም ።
*ይገርማል ዘንዶው በመጀመሪያ ከልጇ ጋር በመቀጠል ከመላእክት ጋር በመቀጠል ከቤተክርስቲያን ጋር በመጨረሻም ከቀሩቱ ቅሬታዎች ጋር ይዋጋል ።ማለትም ተስፋ አይቆርጥም ይጋዋል እንጂ አላሸነፈም ።እንድሁም ቅሬታዎችን ብቻ ባለመቻሉ ነው ሌላ ሃይል መሰብሰብ የጀመረው ።
*እነዚህ ሁሉ የሚንመለከተው ለአንደኛው ሰማይ በር መከፈት ዝርዝር ሃሳቦች እንጂ ለየት ያሉ ሁኔታዎች አይደለሁም ።
በቀጣይ የዘንዶውን የመጨረሻውን ጥበብ እንመለከታለን ...
_____________________________________
“አንድም አውሬ ከባሕር ሲወጣ አየሁ፤ አሥር ቀንዶችና ሰባት ራሶች ነበሩት፥ በቀንዶቹም ላይ አሥር ዘውዶች በራሶቹም ላይ የስድብ ስም ነበረ።”ራእይ 13፥1
ዘንዶው በዓለማዊያን ላይ በመቆሙ የራሱን መሳይ አውሬ ያስነሳል ።ከመጀመሪያው ከቀይ ዘንዶው ገጽታ የተለየው የስድብ ስም መኖሩ ነው።የስድብ ስም ክርስቶስ ሳይሆን በክርስቶስ ስም (ማንነት መጠራት/መመለክ የሚወድ በመሆኑ ነው) የሚጠራ ነው።ጌታችንና አምላካችን መባልን ይፈልጋል ።
“ያየሁትም አውሬ ነብር ይመስል ነበር፥ እግሮቹም እንደ ድብ እግሮች፥ አፉም እንደ አንበሳ አፍ ነበሩ። ዘንዶውም ኃይሉንና ዙፋኑን ትልቅም ሥልጣን ሰጠው።” ራእይ 13፥2
የዘንዶው መልክ ከዳንኤል ራዕይ ጋር ይመሳሰላል ዳን 7 ፥3-4 ። እነዚህ አውራዎችን መገለጫ አድረገው ወይም አርማቸው አድርገው የሚጠቀሙ ሃያላን የዓለም መንግስታትን የሚያመለክት ነው።ቀይ ዘንዶው ከሃያላን መንግስታት ጋር በጥምረት ይሰራል ማለት ነው።እንድሁም ለመንግስታቱም የሃያልነታቸው ምንጭ እርሱ ነው።(መንግታትን የሚሾመው እግዚአብሔር ብሆንም ሁሉም ግን ለእግዚአብሔር አይሰሩም ።)
“ከራሶቹም ለሞት እንደ ታረደ ሆኖ አንዱን አየሁ፥ ለሞቱ የሆነውም ቍስል ተፈወሰ። ምድርም ሁሉ አውሬውን እየተከተለ ተደነቀ፥”ራእይ 13፥3
ከዘንዶው መንግስታት አንደኛው ልወድቅ የደረሰ ስመስልም እንደገና ሃይሉን የማቋቋም እና የማንሰራራት አቅም እና ጥበብ አለው።እንድሁም ሌሎች ሁሉንም የሚገዛ የሚቆጣጠር የሚሰገድለት ይሆናል ።ይመኩበታል ቁ.4።
“ታላቅንም ነገርና ስድብን የሚናገርበት አፍ ተሰጠው፥ በአርባ ሁለት ወርም እንዲሠራ ሥልጣን ተሰጠው።” ራእይ 13፥5
ይህ በቀይ ዘንዶው የተቋቋመው መንግስት በ42 ወር ውስጥ የሚሰራ ነው። መንቀሳቀስ የሚጀምረው በሙላት በመጨረሻው ሰዓት ለ42 ወራት ነው።ምናልባትም በግልጽ የዘንዶው መንግስት እንደሆነ የሚታወቀው በዚያ ግዜ ሳይሆን አይቀርም ።(ይህ መንግስት የዘንዶው ሥራ አስፈጻሚ ነው።)
የኢየሱስ ምስክሮች ያልሆኑቱን ያሸንፋል ያስሰግዳል፣ያስቀብላል ቁ.8።“ጆሮ ያለው ቢኖር ይስማ።” ራእይ 13፥9
“ይማረክ ዘንድ ያለው ማንም ቢኖር ወደ ምርኮነት ይሄዳል፤ በሰይፍ የሚገድል ማንም ቢኖር ራሱ በሰይፍ እንዲገደል ይገባዋል። የቅዱሳን ትዕግሥትና እምነት በዚህ ነው።"ራእይ 13፥10
ቅደሳን እየተማረኩም እየተገደሉም በዚህ መከራ ያልፋሉ ።ከባህር የወጣ አውሬ የተባለው ከዘንዶው ጋር በሕብረት የሚሰራ ከዓለማችን መንግስታት ናቸው ማለት ነው።
..
“ሌላም አውሬ ከምድር ሲወጣ አየሁ፥ የበግ ቀንዶችን የሚመስሉ ሁለት ቀንዶችም ነበሩት እንደ ዘንዶም ይናገር ነበር።” ራእይ 13፥11
ቀይ ዘንዶው የቁሩትን ልዋጋ ባለመቻሉ ፣ ሃይሉን እና ጥበብን በመጠቀም በሌላ መንገድ ለመዋጋት በዓለማዊያን ጋ መሄዱን አይተናል ።በዚያ በመጀመሪያ ከባህር ከዓለም መንግታትን ስያነሳ ፣ በመቀጠልም ከምድርም (ሃሰተኛ ነቢያትና አስተማሪዎችን) በማስነሳት በልዩ ጥበብ መጫወት ጀምሯል ።
ይህኛው አውሬ ደግሞ እንደ በግ የሚጠቅም የሚመስል አስመሳይ ነው ግን በከባዱ የሚያጠቃ አሳች ነው፣
አውሬው የበግ መልክ አለው (ከኢየሱስ ይመስላል ) ግን ድምጹ የዘንዶ ነው።ድምጹ ከሆዱ ይወጣል ፣ ማንነቱን ያሳያል (የኢየሱስ የሆኑትም የኢየሱስ የሆኑትን በድምፅ ያውቃሉ ዮሐ 10)
ራእይ 13
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹² በፊተኛውም አውሬ ሥልጣን በእርሱ ፊት ሁሉን ያደርጋል። ለሞቱ የሆነውም ቍስል ተፈወሰለት ለፊተኛው አውሬ ምድርና በእርሱ የሚኖሩት እንዲሰግዱለት ያደርጋል።
¹³ እሳትንም እንኳ ከሰማይ ወደ ምድር በሰው ፊት እስኪያወርድ ድረስ ታላላቆችን ምልክቶች ያደርጋል።
ለዚህ ከምድር ለወጣው አውሬ (ለሃሰተኛ ሃይማኖት) ጉልበቱ ከባህር የወጣው አውሬው ነው(መንግታት ናቸው )
ደግሞም እውነተኛ የእግዚአብሔር ሰው በምመስል መልኩ ብዙ ተአምራትን ያደርጋል ።
*አስተውሉ የተለያየ ምልክቶች ማድረጉ የእውነተኛ መንፈስ መሆኑ ማረጋገጫ አይደለም ።ታዲያ እንዴት አድርገን ሃሰተኛ ከዲያብሎስ የሆነ ተአምር እንደሆነ እንረዳለን !? ብንል መልሱ ከምናገሩት ቃል የተነሳ ነው።መጽሐፍ ቅዱስን የእግዚአብሔር ቃል ነው ።አውሬው መጽሐፍ ቅዱስን አጣምሞ ያስተምራል ማለት ነው።ይናገራል ማለት ነው።(ስለዚህም ከተአምራት በላይ የእግዚአብሔርን ቃል ነው ብለው የሚናገሩትን በጥንቃቄ መመርመር ይገባናል )
“በአውሬውም ፊት ያደርግ ዘንድ ከተሰጡት ምልክቶች የተነሣ በምድር የሚኖሩትን ያስታል፤ የሰይፍም ቍስል ለነበረውና በሕይወት ለኖረው ለአውሬው ምስልን እንዲያደርጉ በምድር የሚኖሩትን ይናገራል።”ራእይ 13፥14
የሚናገረው ድምጹን የበጉ የኢየሱስ ይሁን አይሁን በቃሌ እግዚአብሔር መመዘን የማይችሉትን በተአምራቱ ያስከትላል ፤ያስታል ።አውሬው የራሱ ምልክት ይሰጣቸዋል ።
“የአውሬው ምስል ሊናገር እንኳ ለአውሬውም ምስል የማይሰግዱለትን ሁሉ ሊያስገድላቸው፥ #ለአውሬው_ምስል_ትንፋሽ_እንዲሰጠው_ተሰጠው።”ራእይ 13፥15
የአውሬው ምስል ያቆማል ፣ ክብሩን ይወስዳል ያስሰግዳል።ልናገርም የሚችል ነው (ስዕል ከተናገረ ከእግዚአብሔር ማለት አይደለም ፤ይልቁንም ከአውሬ እንደሆነ ማረጋገጫ ነው)
“ታናናሾችና ታላላቆችም ባለ ጠጋዎችና ድሆችም ጌታዎችና ባሪያዎችም ሁሉ በቀኝ እጃቸው ወይም በግምባራቸው ምልክትን እንዲቀበሉ፥”ራእይ 13፥16
አውሬው የራሱ የሆኑትን ለመለየት በግንባር ወይም በበቀኝ እጃቸው የራሱን ማህተም (ምልክት ) ያደርጋል ፣ግን አውሬው ለምን የራሱ የሆኑትን ለመለየት ፈለገ ?
“የአውሬውም ስም ወይም የስሙ ቍጥር ያለው ምልክት የሌለበት ማንም ሊገዛ ወይም ሊሸጥ እንዳይችል ያደርጋል። ጥበብ በዚህ አለ።” ራእይ 13፥17
ከየትኛውም አገልግሎት መስጫ ማዕከል አገልግሎት እንዳያገኙ ፣በዚህም በማስጨነቅ ወደ ራሱ ለመሳብ ፣ የራሱ የሆኑትን 'ለመጥቀም' ሌሎችን የማይከተሉትን ሰቆቃ ውስጥ ለማስገባት ይህንን ምልክት ይጠቀማል ።ደግሞም እጅግ ጥበበኛ ነው።ማንም ልረዳ በማይችሉት መንገድ ሳያጠምድ አይቀርም !
“አእምሮ ያለው የአውሬውን ቍጥር ይቍጠረው፤ ቍጥሩ የሰው ቍጥር ነውና፥ ቍጥሩም ስድስት መቶ ስድሳ ስድስት ነው።”ራእይ 13፥18
አውሬ ሃሰተኛ ነቢይ/አስተማሪ እንደሆነ አይተናል ፣
ቁጥሩ የሰው ቁጥር ነው፣
ቁጡሩም 666 ነው፣
666ም የሚነሳው ሃስተኛ ነቢይ ነው፤ሰው ነው።
...
“አየሁም፥ እነሆም፥ በጉ በጽዮን ተራራ ቆሞ ነበር፥ ከእርሱም ጋር ስሙና የአባቱ ስም በግምባራቸው የተጻፈላቸው መቶ አርባ አራት ሺህ ነበሩ።”ራእይ 14፥1
ዮሐንስ እግዚአብሔር ከሕዝቡ ጋር መኖሩን መመልከቱ ልብን ደስ የሚያሰኝ ፥ እምነትንም የሚጨምር ነው። ምክንያቱም በተከታታይ አውሬው የሚያደርሰውን መከራ ስመለከት ነበር።እነዚህ 144 ሺህ ሰዎች አማኞች ሁሉ ናቸው ። በዚያ መከራ ግዜም እግዚአብሔር ከእነሱ ጋር ነበር ።አልተዋቸውም።
“እንደ ብዙ ውኃም ድምፅና እንደ ታላቅ ነጐድጓድ ድምፅ ያለ ከሰማይ ድምፅን ሰማሁ፥ ደርዳሪዎችም በገና እንደሚደረድሩ ያለ ድምፅ ሰማሁ።” ራእይ 14፥2
ደርዳርዎች አማኞች ናቸው ።ድምጻቸው እንደበገና ያለ ነው።በገና በሰማይ አለ ማለት አይደለም ። የድምጻቸውን ታላቅነት ስገልጽ እንጂ።
“በዙፋኑም ፊት በአራቱም እንስሶችና በሽማግሌዎቹ ፊት አዲስ ቅኔ ዘመሩ፤ ከምድርም ከተዋጁት ከመቶ አርባ አራት ሺህ በቀር ያን ቅኔ ሊማር ለማንም አልተቻለውም።”ራእይ 14፥3
አማኞች ሁሉ በአንድነት በዚያን ጊዜ አራቱ እንስሶች ፊት(ፍጥረታት በሙሉ ፊት ) አድስ ቅኔ ይዘምራሉ።ይህንን አማኞች ብቻ ያውቀዋል ።እንዘምራለን ።ሃሌ ሉያ።
“ከሴቶች ጋር ያልረከሱ እነዚህ ናቸው፥ ድንግሎች ናቸውና። በጉ ወደሚሄድበት የሚከተሉት እነዚህ ናቸው። ለእግዚአብሔርና ለበጉ በኵራት እንዲሆኑ ከሰዎች የተዋጁ እነዚህ ናቸው።” ራእይ 14፥4
በዚህ አውድ በመወሰብ ምንዝራነት የተገለጠው እርኩሱነት የሚያመለክተው እግዚአብሔር ላይ ሌላ ጨምሮ ማምለክን ፦ መመንዘር ስለሆነ ነው።ስለዚህም እነዚህ አማኞች ለየትኛውም ነገርም ለገንዘብም፣ለሰውም ... ያልተገዙ ያላመለኩ ለእግዚአብሔር ብቻና ብቻ የሚገባውን አምልኮ የሰጡ ናቸው ።(በሌላው ጎን በቀጥታ ብንወስድ "አማኞች ከሴቶች ጋር አልረከሱም" ማለትም ዝሙትን አልፈጸሙም ማለት ነው። “በአፋቸውም ውሸት አልተገኘም፤ ነውር የለባቸውም።”ራእይ 14፥5
እነዚህ "በሴቶች ያልረከሱ" የተባሉት በመጀመሪያው ከባህር ከወጣውም(የዘንዶው ዓላማ አስፈጻሚ መንግስት) ፥በሁለተኛውም ከምድር ከወጣው አውሬ (ሃሰተኛ አስተማሪ) ጋር ሕብረት የሌላቸው ናቸው ።
..
“በምድርም ለሚኖሩ ለሕዝብም ለነገድም ለቋንቋም ለወገንም ሁሉ ይሰብክ ዘንድ የዘላለም ወንጌል ያለው ሌላ መልአክ ከሰማይ መካከል ሲበር አየሁ፤”ራእይ 14፥6
ዮሐንስ በዚያ ግዜም የዘላለም ወንጌል እንደሚሰበክ ተመልክቷል ።መላኩንም እንዲህ አለ ፦
“በታላቅ ድምፅም፦ የፍርዱ ሰዓት ደርሶአልና እግዚአብሔርን ፍሩ ክብርንም ስጡት፤ ሰማይንና ምድርንም ባሕርንም የውኃንም ምንጮች ለሠራው ስገዱለት አለ።”ራእይ 14፥7
ዳግም ምጽአት እንደደረሰ ፣ፈራሃ እግዚአብሔር እንድኖርና የሚገባውን ክብር ፥ፍጥረታት ሁሉ ለእግዚአብሔር እንድሰጡ ወንጌል ይሰበካል። "መፍራት" የተባለው ለቃሉ መገዛት ለፈቃዱ ራሱን አሳልፎ መስጠትን እንጂ ያጠፋኛል ይጎዳኛል የሚል "ፎቭያ" አይደለም ።በዚህያም ግዜም እግዚአብሔር ከሕዝብ ጋር ነው ።ለማንነቱ ስለማንነቱ ብቻ መገዛት እንደሚገባ ምዕመናት ይመሰክራሉ ።
“ሌላም ሁለተኛ መልአክ፦ አሕዛብን ሁሉ የዝሙትዋን ቍጣ ወይን ጠጅ ያጠጣች ታላቂቱ ባቢሎን ወደቀች፥ ወደቀች እያለ ተከተለው።”ራእይ 14፥8
ምንም እንኳን ቀይ ዘንዶው በመንግሥት እና በሃሰተኛ አስተማሪ ጋር በሕብረት በጥበብ ብሰራም #ይወድቃል ፤ይሸነፋል ።የማይቀር ነው።ምዕመናትም ይህንን በእርግጠኝነት ስለሚያውቁ ይጸናሉ።ሃሌ ሉያ።
“ሦስተኛም መልአክ ተከተላቸው፥ በታላቅ ድምፅ እንዲህ እያለ፦ ለአውሬውና ለምስሉ የሚሰግድ በግምባሩም ወይም በእጁ ምልክቱን የሚቀበል ማንም ቢኖር፥” ራእይ 14፥9
የሦስተኛው መልአክ እወጃ "ሁሉም የሚገባውን የሥራውን ያገኛል" የሚል ነው።ለአውሬው የተገዛ ፦ “እርሱ ደግሞ በቍጣው ጽዋ ሳይቀላቅል ከተዘጋጀው ከእግዚአብሔር ቍጣ ወይን ጠጅ ይጠጣል፥ በቅዱሳንም መላእክትና በበጉ ፊት በእሳትና በዲን ይሳቀያል።”ራእይ 14፥10 ።ይገርማል ለአውሬ የሰገዱ አይሞቱም ሁለም ግን እየተሰቃዩ ይኖራሉ ።የዘላለም ስቃይ አለ።“የሥቃያቸውም ጢስ ለዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ይወጣል፥ ለአውሬውና ለምስሉም የሚሰግዱ የስሙንም ምልክት የሚቀበል ሁሉ ቀንና ሌሊት ዕረፍት የላቸውም።”ራእይ 14፥11
ቅዱሳን ግን ፍሬውን ይበላሉ ።“የእግዚአብሔርን ትእዛዛት የሚጠብቁት ኢየሱስንም በማመን የሚጸኑት ቅዱሳን ትዕግሥታቸው በዚህ ነው።”ራእይ 14፥12
“ከሰማይም፦ ከእንግዲህ ወዲህ በጌታ የሚሞቱ ሙታን ብፁዓን ናቸው። መንፈስ፦ አዎን፥ ከድካማቸው ያርፉ ዘንድ፥ ሥራቸውም ይከተላቸዋል ይላል ብለህ ጻፍ የሚል ድምፅ ሰማሁ።”ራእይ 14፥13
አማኞች ብሞቱም ብፁዓን (የተባረኩ)ናቸው ፣
'ከድካማቸው ያርፋሉ' ማለትም በአውሬ ከደረሰው መከራ ለዘለዓለም ያርፋሉ ፣
"ሥራቸው ይከተላቸዋል" ለአውሬው የሰገዱለቱ ለሥራቸው የሚገባው የዘላለም ስቃይ ነው።ወንጌልን የመሰከሩ ምዕመናት ግን በመከራ ስላለፉ እረፍት ይጠብቃቸዋል።
አውሬውን በመከተል የሚከተለው፦የዘላለም ስቃይ ነው፣ኢየሱስን በመከተል የሚከተለው ፦የዘላለም እረፍት ነው።ሃሌ ሉያ።
____________________________________
“አየሁም፥ እነሆም ነጭ ደመና፥ በደመናውም ላይ የሰውን ልጅ የሚመስል ተቀምጦአል፥ በራሱም ላይ የወርቅ አክሊል በእጁም ስለታም ማጭድ ነበረው። ”ራእይ 14፥14
ይህ የሰው ልጅ የሚመስለው የተባለው ሊቀ ካህናታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።"ስለታም ማጭድ በእጁ ነበረው" የፍርድ ግዜ እንደደረሰ የሚያረጋግጥ ነው ።
“ሌላ መልአክም ከመቅደሱ ወጥቶ በደመናው ላይ ለተቀመጠው፦ የማጨድ ሰዓት ስለ ደረሰ ማጭድህን ስደድና እጨድ፥ የምድሪቱ መከር ጠውልጓልና ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኸ።”ራእይ 14፥15
መልአኩም ለሰው ልጅ ስለሚመስለው "እጨድ" አለው።የመልአኩ ንግግር ኢየሱስን ያዘዘው ወይንም ፈቃድ የሰጠ ይመስላል ።ይህንን ንግግር ለመረዳት ሌሎችን ክፍሎችን ማገናዘብ ሳይኖርብን አይቀርም ።
“አሁንስ ምሳር በዛፎች ሥር ተቀምጦአል፤ እንግዲህ መልካም ፍሬ የማያደርግ ዛፍ ሁሉ ይቈረጣል ወደ እሳትም ይጣላል።”ማቴዎስ 3፥10
በዚህ ክፍል ላይ እንደተገለጸው ዛፍን በሚቆርጥ መቁረጫ "ምሳር" ሆኖ የተገለጸው ኢየሱስ ነው።ምንም እንኳን ኢየሱስ የሚቆርጥ ብሆንም የሚቆርጠው ግን በራሱ ተላላኪዎች ነው ።(ራሱ እንዳደረገ ይቆጠራልና።)
(መንግስት አንድን ሰው በራሱ አካላት ብያስረው የመጣው ፖሊስ አሰረ አይባልም፤ያሰረው ብሆንም እንኳን ።ፈቃዱ የመንግሥት ተልእኮ ስለሆነ መንግስት አሰረ ይባላል።)። መላአኩ ኢየሱስን "እጨድ" ስል እያዘዘው ሳይሆን "እዘዘን" የሚል ነው።ምክንያቱም ጠባቂ ስለሆነ መጠውለጉን ሪፖርት እያደረገ ነውና።
መላአኩም እንደጠየቀው ኢየሱስ ፈቃዱን ሰጠ።“በደመናውም ላይ የተቀመጠው ማጭዱን ወደ ምድር ጣለው ምድርም ታጨደች።”ራእይ 14፥16
“ሌላ መልአክም በሰማይ ካለው መቅደስ ወጣ፥ እርሱም ደግሞ ስለታም ማጭድ ነበረው።”ራእይ 14፥17
“በእሳትም ላይ ሥልጣን ያለው ሌላ መልአክ ከመሠዊያው ወጥቶ ስለታም ማጭድ ያለውን፦ ዘለላዎቹ ፈጽመው በስለዋልና ስለታሙን ማጭድህን ስደድና በምድር ያለውን የወይን ዛፍ ዘለላዎች ቍረጥ ብሎ በታላቅ ድምፅ ጠራ።”ራእይ 14፥18
በስለታም ማጭድ መቆረጥ ስንዴውና አረሙ የሚለዩበት ሳይሆን አይቀርም ።ከዚህ ክፍል ጋር ብናያይዘው መልካም ነው፦ “..፤እስከ መከር ጊዜ አብረው ይደጉ፤ በመከር ጊዜም አጫጆችን፦ እንክርዳዱን አስቀድማችሁ ልቀሙ በእሳትም ለማቃጠል በየነዶው እሰሩ፥ ስንዴውን ግን በጎተራዬ ክተቱ እላለሁ አለ።”ማቴዎስ 13፥30
ስንዴው እና ስንዴውን የሚመስለው እንክርዳድ ማለትም አማኝና 'አማኝ' የሚመስለው የሚለይበት ሰዓት ደርሷል ነው፣ምክንያቱም እሳት የሚለይ መለኮታዊ ፍርድን ያመለክታል ።
“መልአኩም ማጭዱን ወደ ምድር ጣለው፥ በምድርም ካለው ከወይን ዛፍ ቈርጦ ወደ ታላቁ ወደ እግዚአብሔር ቍጣ መጥመቂያ ጣለ።”ራእይ 14፥19
የእግዚአብሔር መላእክት ስንዴውን እና ገለባውን ለመለየት በእግዚአብሔር ፍርድ ፊት ሁሉንም ማቆማቸውን ያመለክታል ።መለየት የእግዚአብሔር ነው።ይህንን ክፍል ከዚህ ክፍል ጋር በደንብ መረዳት እንችላለን ፦
“መንሹም በእጁ ነው፥ አውድማውንም ፈጽሞ ያጠራል፥ ስንዴውንም በጎተራው ይከታል፥ ገለባውን ግን በማይጠፋ እሳት ያቃጥለዋል።”ማቴ 3፥12
በዚያን ግዜ የእግዚአብሔር መላእክት የሰበሰቡትን ፥ ኢየሱስ ክርስቶስ አማኞችንና 'አማኝ' የሚመስሉትን ይለያል ።የሚለየውም ወይን እንደሚወቀጥ እንደሚረገጥ አማኞችም አማኝ ያልሆኑትም በጌታ ቁጣ በእሳት ይለያሉ።
“የወይኑም መጥመቂያ ከከተማ ውጭ ተረገጠ፥ እስከ ፈረሶች ልጓምም የሚደርስ ደም ርቀቱ ሺህ ስድስት መቶ ምዕራፍ ሆኖ ከመጥመቂያው ወጣ።”ራእይ 14፥20
ወይኑ ከከተማው ውጪ በተዘጋጀው ግንብ ይወቀጣል።ከዛም በተሰራው ገንዳ መጡጡ ይወጣል ።በሰዎች በመለኮታዊ ስራ መወቀጥ አማኝና አማኝ ያልሆነውን ይለያል ።ወይኑ የሆነው መጠጡ ተጣሪቶ እንደሚወጣ ደም ከመጥመመቂያው መውጣቱ በደሙ የተዋጁትን ሳያመለከት አይቀርም ።(ራዕይ እያጠናን ስንሄድ ከተለያየ አቅጣጫ እያየን መረዳታችንን እናሰፍናለን እንጂ ሙሉዑ አድስ ታርክ አይደለም )
______________________________________
“ሌላም ታላቅና ድንቅ ምልክት በሰማይ አየሁ፤ የእግዚአብሔር ቍጣ በእነርሱ ስለሚፈጸም ኋለኛዎቹን ሰባት መቅሠፍቶች የያዙ ሰባት መላእክት ታዩ።”ራእይ 15፥1
ይህ አድስ ትዕይንት አራተኛው ሰማይ መከፈት ነው።ከም.8 ፥6 ጋር የሚመሳሰል ይመስላል ።ግን በዚህ ክፍል አውድ ላይ መለከቶች ቁጣውን ስያመለከቱ በም.8፥6 ያለው ደግሞ ማስጠንቀቂያዎችን የሚያመለክት ነው።
___
“በእሳትም የተቀላቀለውን የብርጭቆ ባሕር የሚመስለውን አየሁ፥ በአውሬውና በምስሉም በስሙም ቍጥር ላይ ድል ነሥተው የነበሩት የእግዚአብሔርን በገና ይዘው በብርጭቆ ባሕር ላይ ሲቆሙ አየሁ።”ራእይ 15፥2
በቁ.1 የእግዚአብሔር ቁጣ አሳይቶ ወዲያውኑ ወደ እግዚአብሔር መገኘት እና የክርስቶስ ሕዝብ አብረው መኖሩን በቁ.2 ላይ የሚያሳየው በዚያ ቁጣ የክርስቶስ ሕዝብን ቁጣው እንደማያገኝ የሚያሳይ ሳይሆን አይቀርም ።(ምናልባትም ስናጠና ሰፊ እይታ የታከለበት ማብራሪያ እናገኝ ይሆናል )
“ሁሉን የምትገዛ ጌታ አምላክ ሆይ፥
ሥራህ ታላቅና ድንቅ ነው፤
የአሕዛብ ንጉሥ ሆይ፥
መንገድህ ጻድቅና እውነተኛ ነው፤
ጌታ ሆይ፥
የማይፈራህና ስምህን የማያከብር ማን ነው?
አንተ ብቻ ቅዱስ ነህና፥
#የጽድቅም_ሥራህ ስለ ተገለጠ አሕዛብ ሁሉ ይመጣሉ በፊትህም ይሰግዳሉ እያሉ የእግዚአብሔርን ባሪያ የሙሴን ቅኔና የበጉን ቅኔ ይዘምራሉ።”ራእይ 15፥3-4
እነዚህ የዳኑቱ የክርስቶስ ቤተሰቦች ስለ ነፃ መውጣታቸው እና ስለ መዳናቸው ያመሰግናሉ ።ደግሞም ነፃነታቸውን በዋጋ ስለመጣም "ጽድቅህ ተገለጠ" እያሉ በእግዚአብሔር ፍትህ መደሰታቸውን ያዘማሉ።ሃሌ ሉያ።
*ይህ የመጨረሻው የሶስተኛው ሰማይ መከፈት መዝግያ ነው።በአንደኛውም ሰማይ መከፈት (በማህተሞቹም)፣ በሁለተኛውም ሰማይ መከፈት (በመለከቶችም) እንደተመለከትነው በመጨረሻው የበጉ ሕዝብ አሸናፍነት አለ፤ዘለዓለማዊነት አለ።ሃሌ ሉያ።
*ደግሞም የ3ተኛው ሰማይ መከፈት ስናጠቃልለው በምድር ለሚፈጠረው ጦርነት መንሰኤው በሰማይ የተከፈተው ጦርነት እንደሆነና የማይታዩት አካላት እርስ በእርስም ጦርነት እንደሚያደርጉ የሚያስገነዝብ ነው።
(በራዕይ መጽሐፍ ጥናታችን በእያንዳንዷን ሰማይ መከፈት ከተለያዩ አቅጣጫዎች መመልከታችንን እንቀጥላለን )
__________________________________
“ከዚህም በኋላ አየሁ፥ የምስክርም ድንኳን መቅደስ በሰማይ ተከፈተ፥”ራእይ 15፥5
#ይህ_አራተኛው የሰማይ መከፈት ነው።መቅደሱ በሰማይ ነው።
“ሰባቱንም መቅሠፍት የያዙ ሰባቱ መላእክት ከመቅደሱ ወጡ፤ ከተልባ እግርም የተሠራ ጥሩ የጌጥ ልብስ ለበሱ ደረታቸውንም በወርቅ መታጠቂያ ታጠቁ።”ራእይ 15፥6
የመላእክት አለባበሳቸው ንጉሣዊ አለባበስ ነው።የንጉሡ ቁጣን ለማመልከት ሳይሆን አይቀርም ።
“ከአራቱም እንስሶች አንዱ ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ የሚኖር የእግዚአብሔር ቍጣ የሞላባቸውን ሰባት የወርቅ ጽዋዎች ለሰባቱ መላእክት ሰጣቸው።”ራእይ 15፥7
አራቱ እንስሶች ስባል በራዕይ መጽሐፍ ፍጥረታትን ሁሉንም ያመለክታል ፥በዚህ ክፍል ላይ ግን "አንዱ"እንደሚል ከፍጥረታት አንዱን ወካይን የሚያመለክት ነው ። (ከፍጥረታት አንዱ ተወክሎ እግዚአብሔር ቁጣውን እንድያደርግ እንደተስማሙ ያመለክታል ።)
“ከእግዚአብሔርም ክብርና ከኃይሉ ጢስ በመቅደሱ ሞላበት፥ የሰባቱ መላእክት ሰባቱ መቅሰፍት እስኪፈጸሙ ድረስ አንድ እንኳ ወደ መቅደሱ ይገባ ዘንድ አልቻለም።”ራእይ 15፥8
የእግዚአብሔር ፍትህ መደረጉ የእግዚአብሔርን ጽድቅን ያሳያል።ያ ደግሞ እግዚአብሔር መከበሩን ስሙም መቀደሱን ያመለክታል ።
“ለሰባቱም መላእክት፦ ሄዳችሁ የእግዚአብሔርን ቁጣ ጽዋዎች በምድር ውስጥ አፍስሱ የሚል ታላቅ ድምፅ ከመቅደሱ ሰማሁ።” ራእይ 16፥1
የእግዚአብሔር ቁጣው ቅጣቱን ያደርጋል።የሚገባ ነውና።
“ፊተኛውም ሄዶ ጽዋውን በምድር ውስጥ አፈሰሰ፤ የአውሬውም ምልክት ባለባቸው ለምስሉም በሚሰግዱ ሰዎች ክፉኛ የሚነዘንዝ ቍስል ሆነባቸው።” ራእይ 16፥2
#በመጀመሪያው_ቁጣ_ምድር_ተመታች!
የአውሬውን ምልክት የተቀበሉ በጌታ ያልሆኑ ሁሉም በቀጥታ ሰዎቹ ተመቱ!
* ይህ ቁጣ ከ7ቱ መለከቶች (ማስጠንቀቂያዎች )የሚለይበትን ነጥቦችን በመጨረሻ ክፍል ማጠቀላያ ስናደርግ እናያለን ።
#በሁለተኛው_ቁጣ_ባህር_ተመታች!
በ7ቱ መቅሰፍቶቹ እንደተመለከትነው ም.8 ላይ የባህር መመታት የሰዎች ንግድ (ኢኮኖሚን) የሚመታ እንደሆነ ብንመለከትም ፥በዚህ አውድ ግን ንግዱን ዘርፍ ወይም ኢኮኖሚያዊ ጥቃትን ሳይሆን አሁንም የማያምኑትን ሰዎችን የሚመታ ነው።
#በሦስተኛው_ቁጣ_ወንዞች_የውሃ_ምንጮች ተመቱ!
“ሦስተኛውም ጽዋውን በወንዞችና በውኃ ምንጮች ውስጥ አፈሰሰ፤ እነርሱም ደም ሆኑ።”ራእይ 16፥4
በተፈጥሮ ሃብት ውሃ መመረዝ የማያምኑቱ ይሞታሉ!
ጌታ እንዲህ በመፍረዱ ቅዱሳን ፍጥረታት እንዲህ ይላሉ፦
ራእይ 16
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁵ የውኃውም መልአክ፦ ያለህና የነበርህ ጌታ ሆይ፥ ቅዱስ ሆይ፥ እንዲህ ስለፈረድህ ጻድቅ ነህ፤
⁶ የቅዱሳንና የነቢያትን ደም ስላፈሰሱ ደምን ደግሞ አጠጥተሃቸዋል፥ የሚገባቸው ነውና ብሎ ሲናገር ሰማሁ።
⁷ ከመሰዊያውም፦ አዎን፥ ሁሉን የምትገዛ ጌታ አምላክ ሆይ፥ ፍርዶችህ እውነትና ጽድቅ ናቸው ብሎ ሲናገር ሰማሁ።
#4ኛው_ቁጣ_ፀሀይ_ተመታ!
“አራተኛውም ጽዋውን በፀሐይ ላይ አፈሰሰ፤ ሰዎችንም በእሳት ልታቃጥል ተሰጣት።”ራእይ 16፥8
ይህ ቁጣ በእጅጉ ሰዎችን በፀሃይ ሙቀት የሚቀቅል ነው።ከሙቀቱ ግለት የተነሳ ጌታን ያላመኑቱ ይሞታሉ።እንደሁም ከስቃያቸው የተነሳ እግዚአብሔርን ይሳደባሉ።“ሰዎችም በታላቅ ትኵሳት ተቃጠሉ፥ በነዚህም መቅሠፍቶች ላይ ሥልጣን ያለውን የእግዚአብሔርን ስም ተሳደቡ፥ ክብርንም እንዲሰጡት ንስሐ አልገቡም።”ራእይ 16፥9
እግዚአብሔር ፍትህ በማድረጉ ፣ በማያምኑቱ ላይ የሚገባቸውን በመፍረዱ ፣ሁሉም ያለ አንድ ፍጥረታት አዛኝነት (ተቃውሞ ) ፣በእግዚአብሔር ጽድቅ በመደሰት ስመሰክሩ እናያለን ።(እግዚአብሔር በኀጢአተኛው ስፈርድ ቅዱሳን ሁሉ "ይገባቸዋል" ብለው ይደሰታሉ በእግዚአብሔር ፍትህ፤የሚቃወሙ አዛኝ አዛኝ የሚጫወት የለም)
________________________________________
#5ኛው_ቁጣ_የአውሬ_ዙፋን_ተመታ!
“አምስተኛውም ጽዋውን በአውሬው ዙፋን ላይ አፈሰሰ፤ መንግሥቱም ጨለማ ሆነች ከስቃይም የተነሳ መላሶቻቸውን ያኝኩ ነበር፥” ራእይ 16፥10
ቀዩ ዘንዶው በሃሰተኛ ፖለቲካ ያቋቋመው ፥ የራሱ ዓላማ ማስፈፀሚያ መንግስቱ ይመታል! [ቀዩ ዘንዶው ማሸነፍ ባለመቻሉ ሃይሉን (ጥበብን) ሰብስቦ ያቋቋመውን መንግስት ፥ እግዚአብሔር ለፍርድ ስነሳ እንደ ቀላል ነገር ይገለብጣል።] ሃይል ሁሉ የእግዚአብሔር ነው።ሃሌ ሉያ።
*በአሁኑ ሰዓት በዘንዶው የሚሰሩቱ መንግስታት ሌሎችን መንግታትን በተለያየ ነገር እያስፈራሩ የራሳቸውን የሰይጣን ስራ ውሸት ፥ ልቅ ነፃነታቸውን በሕገመንግስት ደረጃ ለማስፈጸም ይጥራሉ፤ እያስፈጸሙም ነው ፤ግን ይወድቃሉ፤እንዲህ አይቀጥሉም።
*ይገርማል የእግዚአብሔር ቁጣ ስገለጥም የሚመለስ አንድ አይኖርም እንድሁም ይሳደባሉ፤በክፋታቸው ይቀጥላሉ ።
#በ6ኛው_ቁጣ_በጦርነት_ይመታል!
“ስድስተኛውም ጽዋውን በታላቁ ወንዝ በኤፍራጥስ ላይ አፈሰሰ፤ ከፀሐይም መውጫ ለሚመጡ ነገሥታት መንገድ እንዲሰናዳላቸው ውኃው ደረቀ።”ራእይ 16፥12
ኤፍራጥስ የአማጽያን የባቢሎን እና የአሳሮዊያን መንግስት አመልካች ነው።ስለዚህም አማጽያን ነገስታት ይነሳሉ፤ለአመጻቸው መንገዱ ጨርቅ ይሆናል ።
“ከዘንዶውም አፍና ከአውሬው አፍ ከሐሰተኛውም ነቢይ አፍ ጓጕንቸሮች የሚመስሉ ሦስት ርኵሳን መናፍስት ሲወጡ አየሁ፤”ራእይ 16፥13
በሶስተኛ ሰማይ መከፈት የተመለከትነው የቀዩ ዘንዶው የዲያብሎስ መሳሪያዎች በሃሰተኛ ፍልስፍና የተቋቋመው መንግስት እና ሃሰተኛው ነቢይ ጋር በጥምረት ጦርነቱን ያፋፍማሉ።
“ምልክት እያደረጉ የአጋንንት መናፍስት ናቸውና፥ በታላቁም ሁሉን በሚገዛ በእግዚአብሔር ቀን ወደ ሚሆነው ጦር እንዲያስከትቱአቸው ወደ ዓለም ሁሉ ነገሥታት ይወጣሉ።”ራእይ 16፥14
*እነዚህ የሃሰተኛው ነቢይ መንፈስ የሚያደርጋቸው ምልክቶች አዕምሮን አደንዝዘው ወደ ጦርነት ያመራሉ (በጌታ መንፈስ የተደረገው ምልክት ግን ወደ እግዚአብሔር ይመራል )
*ይገርማል በአሳቾች የተነሳሳው ጦርነት ለሰይጣን የራሱን መንግስት ለመገንባት ሲሆን ለእግዚአብሔር ግን ፍትህ የሚያደርግበት ነው።ጦርነቱን እግዚአብሔር ሳያቆመው ለራሱ ይጠቀማል ፣ ለሰይጣም የመጨረሻ ያደርገዋል ።ለዚህያ ነው ይህ ጦርነት "የእግዚአብሔር ቀን" የተባለው ።
በዚያ ግዜ ዓለም ለጦርነት ስትዘጋጅ እግዚአብሔርም ወደ ዓለም ለመምጣት ፍርዱን ለማድረግ እየተዘጋጀ ነው።ይመጣል ።“እነሆ፥ እንደ ሌባ ሆኜ እመጣለሁ፤ ራቁቱን እንዳይሄድ እፍረቱንም እንዳያዩ ነቅቶ ልብሱን የሚጠብቅ ብፁዕ ነው።”ራእይ 16፥15
“በዕብራይስጥም አርማጌዶን ወደሚባል ስፍራ አስከተቱአቸው።”ራእይ 16፥16
አርማጌዶን የመጊዶ ተራራ ማለት ነው መሳ 5፥19።በታርክ ከፍተኛ ታላቅ እልቅት የተደረገበት የጦርነት ስፍራ ነው።ስለዚህም ከፍተኛ ጦርነት ይደረጋል ፤እግዚአብሔርም ይመጣል ፤ለሰይጣን መንግስት እና ለሃሰተኛው አስተማሪ የመጨረሻ ያደርጋል፤ይሆናል።
*በዚህ ሰዓት በክርስቶስ ያላችሁ ብፁዓን ናችሁ ።አሜን ።ሃሌ ሉያ።
#7ኛው_ቁጣ_ተፈጽሟል!
“ሰባተኛውም ጽዋውን በአየር ውስጥ አፈሰሰ፤ ከመቅደሱም ውስጥ፦ ተፈጽሞአል የሚል ታላቅ ድምጽ ከዙፋኑ ወጣ።”ራእይ 16፥17
ሁሉም ነገር አበቃ!ሙሉዕ በሙሉ አበቃ።ያ ግዜ አለፈ።
በጦርነቱ መካከል አሸናፊ ወገን የለም! የእግዚአብሔር ቀን ስለሆነ የሚገዳደሉቱ ሁሉም ይጠፋሉ ።እንዲህ ነው ፦
ራእይ 16
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁸ መብረቅና ድምጽም ነጎድጓድም ሆኑ፥ ትልቅም የምድር መናወጥ ሆነ፤ ሰው በምድር ከተፈጠረ ጀምሮ እንዲህ ያለ ታላቅ መናውጥ ከቶ አልነበረም፤ ከሁሉ በለጠ።
¹⁹ ታላቂቱም ከተማ በሦስት ተከፋፈለች፥ የአሕዛብም ከተማዎች ወደቁ። ታላቂቱም ባቢሎን የብርቱ ቍጣው ወይን ጠጅ የሞላበትን ጽዋ እንዲሰጣት በእግዚአብሔር ፊት ታሰበች።
²⁰ ደሴቶችም ሁሉ ሸሹ ተራራዎችም አልተገኙም።
²¹ በሚዛንም አንድ ታላንት¹ የሚያህል ታላቅ በረዶ በሰዎች ላይ ከሰማይ ወረደባቸው፤ ሰዎቹም ከበረዶው መቅሰፍት የተነሳ እግዚአብሔርን ተሳደቡ፥ መቅሰፍቱ እጅግ ታላቅ ነውና።
*እግዚአብሔርን እየተሳደቡ ከመሞት ይጠብቃችሁ!
...
(በዓለም ለሚፈጸመው ነገር ሙሉ መረዳት እንድኖረን ጌታ በተለያየ መንገድ መገለጡን ቀጥሏል፤እኛም እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ለመረዳት ጥናታችንን እንቀጥላለን )
______________________________________
ወደ አምስተኛው ሰማይ መከፈት ከመግባታችን በፊት የበጉን ቁጣ (አራተኛው ሰማይ መከፈት ም.15-ም.16) እና የበጉን ማስጠንቀቂያ (የሁለተኛው ሰማይ መከፈት ም.8 -ም.11፥18) በንፅፅር እንመለከታለን ፦
ሰባቱ መላእክት እና ሰባቱ መለከቶች ማለቱ የሁለቱንም ሰማይ በር መከፈት እይታ አንድ ዓይነት የሆኑ ይመስላል ።ግን በም.15 (4ኛው ሰማይ መከፈት) ያለው መለከት #ቁጣ ሲሆን ፥ በ2ኛው ሰማይ መከፈት ያለው መለከት ደግሞ የሚያመለክተው #ማስጠንቀቂያ ነው ፣
በ2ኛው ሰማይ መከፈት በእግዚአብሔር ፈቃድ በሰይጣን በኩልም በመቅሰፍት መመታት ያለ ሲሆን (ኢ-አማኙን ብቻ) ም.9፥1-11፣ በ4ኛው ሰማይ መከፈት ቁጣው በእግዚአብሔር መላእክት ብቻ ይከናወናል ፣
በሁለተኛው ሰማይ መከፈት ማስጠንቀቂያው የሰውን አከባቢ ብቻ ሲጎዳ ፣ በአራተኛው ሰማይ መከፈት ግን የሰውን ነፍስ በቀጥታ ይጎዳል ይገድላል ፣
በሁለተኛው ሰማይ መከፈት ማስጠንቀቂያ ከመሆኑ አንፃር 1/3ኛው ሲመታ ሌላው አከባቢ ለምህረት እድል የተሰጠ ሲሆን ፣በአራተኛው ሰማይ መከፈት ግን በንስሐ ባለመመለሳቸው ሙሉ በሙሉ እልቂት ብቻ ነው፣
(የእግዚአብሔር ቁጣ ለምዕመናን ትልቅ ደስታ ነው ምክንያቱም የዲያብሎስ መጨረሻ ነው)
~~~~~~~~
“ሰባቱንም ጽዋዎች ከያዙ ከሰባቱ መላእክት አንዱ መጥቶ፦ ና በብዙም ውኃዎች ላይ የተቀመጠችውን የታላቂቱን ጋለሞታ ፍርድ አሳይሃለሁ፤”ራእይ 17፥1
ይህ የዮሐንስ አምስተኛው የሰማይ መከፈት እይታ ነው።ጌታ ምን ያሳየው ይሁን !? ትኩረቱ ምን ይሁን !?እንቀጥል ፦
በዚህ እይታው ዮሐንስ መጀመሪያ ራዕይ ይመለከት ከነበረው ቦታ መንቀሳቀሱን እንመለከታለን ።ጌታም በመላእክቱ በኩል የሚያሳየው ፍርድን ነው።ፍርዱም ስለ ታላቅቱ ጋለሞታ ነው።ከሌሎች ነጥሎ ጌታ ስለ ጋለሞታይቱ ማሳየት የወደደውን ፣ ትኩረት አድርጎ በዚህ ክፍል ላይ ስለ ታላቅቱ ጋለሞታ ባቢሎን ያሳየናል ።እንመልከት ፦
“የምድርም ነገሥታት ከእርስዋ ጋር ሴሰኑ በምድርም የሚኖሩ ከዝሙትዋ ወይን ጠጅ ሰከሩ ብሎ ተናገረኝ።”ራእይ 17፥2
የተከበሩ ፣ታላቅ ሰዎች የተባሉትን ጭምር ያሳተች ፣ ሰዎችን በራሷ አሰራር ያሰረች ፣ የተቆጣጠረች ናት ።
“በመንፈስም ወደ በረሀ ወሰደኝ፤ የስድብም ስሞች በሞሉበት፥ ሰባት ራሶችና አሥር ቀንዶችም ባሉበት በቀይ አውሬ ላይ አንዲት ሴት ተቀምጣ አየሁ።”ራእይ 17፥3
አንዱ መላአክ ዮሐንስን ይህንን ራዕይ ለመመልከት "ና" ብሎት ምንም ወደ ሌለበት በረሃ መወሰዱን እንመለከታለን ።መላአኩ ለምን ወደ በረሃ ወሰደ !?
ኢየሱስም በመንፈስ ወደ በረሃ ሄዶ ነበር ማቴ 4 ።ወደ በረሃ የተወሰደበት ምክንያት ዮሐንስ በዚህ በር የሚያየው ራዕይ የመንፈስ ጥንካሬን ስለሚያስፈልግ ነው።ምክንያቱም የስድብ ስም አላት ማለትም ክርስቶስ ነኝ ትላለችም፤ታስብላለችም።
ዮሐንስ ጋለሞታይቱን ስመለከት ፣ ሰዎችን በማታሳውቅ መንገድ የሚትሳደብ ናት።ጥበብ እና ሃይልም አላት።ስለዚህም ዮሐንስ ይህንን ለመመልከት ወደ በረሃ መወሰድ ግድ ከሆነ ለእኛስ እንዴታ !? የዓለም ብልጭልጭልታ ሳያሸነፈው ኢየሱስ በመንፈስ ወደ በረሃ በመሄዱ ፣ሳይሸነፍ ፣ሳይታለል ፣አሸንፎ ተመለሰ።ለእኛም ሃይልን እንድንቀበል !? ይህንን ራዕይ ለመመልከት ዓለም በብልጭልጭታዋ እንዳታሸንፈን የሁለት ቀን ጾም ጸሎት እንይዛለን ።
(ልሆን ያለውን እንደ ባለ አዕምሮ ሰው ፣ሳንታለል፣ ለመረዳት ፣ለመጽናት ፣ከጾመ ከጸሎት በኃላ እንቀጥላለን ።ግዜው አሁን ነው።ባላችሁበት ጸልዩ፤ በኢየሱስ ስም ስልጣን፤ጌታ ይሰማል፤የቅርብ ቅርብ ነው፤ወደ እግዚአብሔር በኢየሱስ ስም እንቅረብ ፤በርቱ]]
______________________________________
ጌታ መልካም ነው።ከዚህ በኃላ የምንመለከተው ስለ ጋለሞታይቱ ባቢሎን ፍርድ ነው።በቀድሞ ክፍል ራዕይ 16 ፥19 ይህች ጋለሞታይቱ ባቢሎን እንደምትወድቅ ተመልክቷል ።ስለዚህም አያስፈራንም።ጌታ ይጥላታል፤ ጥሏልም።በመንፈስ መጠንከር ፥ መመልከት ፥ ያስፈለገው ሰዎችን እንዴት እንደሚታስት ለመረዳት ፥ለመንቃት ነው።ሥራዋን እናውቃለን በጌታ መንፈስ ፤አንዳች የሚያስፈራን ነገር የለንናም። እንቀጥል ፦
“ሴቲቱም በቀይና በሐምራዊ ልብስ ተጐናጽፋ በወርቅና በከበሩ ድንጋዮች በዕንቈችም ተሸልማ ነበር፥ በእጅዋም የሚያስጸይፍ ነገር የዝሙትዋም ርኵሰት የሞላባትን የወርቅ ጽዋ ያዘች፤” ራእይ 17፥4
ሴትቱ ቀይና ሐምራዊም ልብስ የለበሰች ናት|| በደም የተጎናጸፈች ናት።ደሙ የቅዱሳን ደም እንደሆነ አያጠራጥርም ።ደግሞም ይህ በቅዱሳን ደም መስከሯ እንዳይታወቅ በወርቅ (በእንቁ) ማለትም በብልጭልጭታ ነገር የተሸፈነች ናት።ዮሐንስ ያማረ ነገር ያላት የሚመስለውን ተመልክቶ ስመለስ ፥የራሷ ሥራዋ የወርቅ ጽዋ የሞላባት እንደሆነች ተመለከተ ።የጽዋ መሞላት በመግቢያችን እንዳልነው ፍርድ እንደተገባባት የሚያሳይ ነው።(በወርቅ መከበቧ የስህተትን እና ከእግዚአብሔር እቅፍ የሚያወጣ የሚያርቀውን ነገርን እናዳናውቅ የሚያደርግ ጥበብ ነው)
“በግምባርዋም ምስጢር የሆነ ስም፦ ታላቂቱ ባቢሎን፥ የጋለሞታዎችና የምድር ርኵሰት እናት ተብሎ ተጻፈ።” ራእይ 17፥5
ማንነቷ በግልጽ ጋለሞታ እንደሆነች የሚያሳይ ነው።ይህች "ሴት ፣ ሴትቱ" የተባለችው ባቢሎን ናት፤ የጾታ ሴት አይደለችም ።ደግሞም ጋለሞታይቱ ስባል ሴተኛ አዳሪ ማለት አይደለም ።እግዚአብሔርን አለማምለክ ምንዝርነት ስለሆነ በአመንዝራነት መስሎ እየገለጠ ነው እንጂ።ይህች ሴት በቀይ አውሬ (በዲያብሎስ ) አማካይነት ሌሎችን የሚትቆጣጠር የኃጢአተኞች እና የሰዳብዎች ምንጭ (እናት) ናት።ስለዚህም ይህች ሴት በዘንዶው የተቋቋመውን ጥበብ እና ሃይል ያለውን የምድር መንግስታት አመልካች ናት።በዚህ ሰማይ መከፈት ጌታ የሚገልጠው በሰይጣን ስለ ተመሠረተው የምድር ሃያላን መንግስታት አወዳደቅ ነው።ፍርድን ነው።እንቀጥል ፦
“ሴቲቱም በቅዱሳን ደምና በኢየሱስ ምስክሮች ደም ሰክራ አየኋት። ባየኋትም ጊዜ እጅግ ታላቅ ድንቅ አደነቅሁ።” ራእይ 17፥6
መጀመሪያ ዮሐንስ ስመለከታት የሚትሰብ ፣የተንቆጠቆጠች ናት፤ዓለም።ማንነቷ ግን ነፍሴ ገዳይነት ነው።(ዮሐንስ በመንፈስ ወደ በረሃ በመሄዱ ሳይናወጥ ሳይታለል ተመለከተ፤አልተከተላትም) እንድሁም ተደነቀ።ለምን ይሁን የተደነቀው !?
“መልአኩም አለኝ፦ የምትደነቅ ስለ ምንድር ነው? የሴቲቱን ምስጢርና የሚሸከማትን፥ ሰባት ራሶችና አስር ቀንዶች ያሉትን የአውሬውን ምስጢር እኔ እነግርሃለሁ።”ራእይ 17፥7
በዮሐንስ መደነቅ ወደበረሃ የወሰደው መላአክ ለምን እንደተደነቀ ጠየቀው ።መላአኩ ግን ዮሐንስ እስኪ መልሰውም አልጠበቀም ።ራሱ የሴትቱን ራሷን (ጥበቧን) እና ቀንዷን (ሃይሏን) "እገልጣለሁ" አለ።እስኪ እንመልከት ነገረ ሥራዋን ፦
“ያየኸው አውሬ አስቀድሞ ነበረ፥ አሁንም የለም፥ ከጥልቁም ይወጣ ዘንድ አለው፥ ወደ ጥፋትም ይሄዳል፤ ስሞቻቸውም ከዓለም ፍጥረት ጀምሮ በሕይወት መጽሐፍ ያልተጻፉ በምድር የሚኖሩ አውሬው አስቀድሞ እንደነበረ አሁንም እንደሌለ፥ ነገር ግን እንዳለ ሲያዩ ያደንቃሉ።”ራእይ 17፥8
ስለ አውሬው መላአኩ ስገልጥ እንዲህ አለ፦
መላአኩ ስለአውረው የገለጠው መጀመሪያም እንደነበረ ነው።ምድራዊያን ሰዎች ደግሞም አሁን አውሬ እንደሌለ ያስባሉ (ነገረ ሥራውን ምንጩን መረዳት አይችሉም) ፣ አውሬው ግን እንዳለ ወይም አሁንም እየሰራ እንደሆነ ስመለከቱ ይደነቃሉ ።የሚደነቁት መኖሩን ስመለከቱ ነው።
ምን መሰላችሁ "ሰይጣን የለም ፥ ሰው ራሱ ሰይጣን ነው" አትበሉ ይህንን 'ስብከት' ሰይጣን ይወዳል ። ምክንያቱም ሰይጣንን ካወቁ ይርቁታል።ስለዚህም ምድራዊያንን "አሁን የለም፣ ሰይጣን ራሱ እኮ ሰው ነው" እንደሚሉ ፣ እንደዛ እያስባለ ነው።ግን መልአኩ "አሁንም አለ" የሚል መልእክት ገለጠ።ስለዚህም ዮሐንስን ያስደነቀው ሰይጣን እንዴት በድብቅ እንደሚሰራ መረዳቱ ነው። የሰይጣንን አሰራር የማያውቁት ምድራዊያን ብቻ ናቸው ።ከአማኞች የተሰወረ አይደለም ።ነገሮችን የመመዘን አቅም ጌታ ያብዛልን ።የዓለም ተራ ጨዋታ ይሁን ብልጭልጭታ አያታልለን።
“ጥበብ ያለው አእምሮ በዚህ ነው። ሰባቱ ራሶች ሴቲቱ የተቀመጠችባቸው ሰባት ተራራዎች ናቸው፥”ራእይ 17፥9
ለጋለሞታዩቱ መንግስት 7ት ጥበቦች (ራሶች) አሏት ።ጋለሞታይቱ 7ቱን ጥበቧን በተለይ በሃያል 7ት ሃገራት በኩል ትጠቀማለች ።ምናልባትም አንዱ መንግስት አንደኛው ጥበብ ስጠቀም ሌላውም እንደዛው እንደየግዘው፤እንደየዘመኑ።ሰው የአንደኛውን ነገስት (መንግስት) ጥበብ ካወቀ በሌሎች በሌላኛው መንግሥታት ጥበብ (አካሄድ) ልስት ይችላል።
“ሰባት ነገሥታት ደግሞ ናቸው፤ አምስቱ ወድቀዋል አንዱም አለ፥ የቀረውም ገና አልመጣም፤ ሲመጣም፥ ጥቂት ጊዜ ሊቆይ ይገባዋል።”ራእይ 17፥10
ሰባቱ ተራሮች ሰባቱ ነገስታት ናቸው ።ከ7ቱ አምስቱ ቀድመው ወድቀዋል። ከአምስቱ "አንደኛው ግን ወደቀ" ስብል እንደገና አገግሞ ይነሳል።ስለዚህም የቀረው መንግስት ገና የሚመጣ ነው።ማለትም ሴትቱ በ7ት ነገስታት በኩል ጥበቧን ብትጠቀምም ፣ 7ቱም ነገስታት በአንድ ግዜ እና ዘመን የሚነግሱ አይደሉም ።ስለዚህም ዮሐንስ ራዕዩን ከተመለከተበት ግዜ አንስቶ 3ቱ ነገስታት ይነሳሉ ማለት ነው።ማለትም 3 ነገስታት ገና አሉ ማለት ነው።(ሴትቱ ምንጭ እና ማዕከል ትሆናለች ማለት ነው፤ስለዚህም የሴትቱ ሰለባ የሆኑ የየሃገሩን መንግስት እንዳታስቡ። አንዷ ሃገር ነገስት ትሆናለች ሌሎችም እንድከተሉ ታደርጋለች።)
ብዙ ግዜ ሰባቱ ነገስታት (ሃገራት ) በአንድ ዘመን አንድ ላይ የሚነሱ እና የሚሰሩ እንድሁም ገና በዳግም ምጽአት አከባቢ የሚነሱ አድርገን እናስባለን ።ግን መላአኩ እንዳለው አውሬው ከመጀመሪያውም እያቋቋመ እየሰራ ነው።ከተነሱት መንግሥታት 5ቱ ተነስተዋል ።አምስቱም ወድቀዋል ።ወይም ሰይጣንን አገልግለው አልፈዋል ።ግን ከወደቁት ከአምስቱ አንደኛው ሃገር እንደገና ይንሰራራል ፤በአቅም ይነሳል።ስለዚህም ዮሐንስ ራዕይን ከሚመለከትበት ግዜ አንስቶ እንደ መላአኩ መግለጥ የሚነሱ ነገስታት 3ቱ ብቻ ናቸው ።አሁን ስንቶች እንደቀሩ እግዚአብሔር ይግለጥልን ።
______________________________________
“የነበረውና የሌለውም አውሬ ራሱ ደግሞ ስምንተኛው ነው ከሰባቱም አንዱ ነው፥ ወደ ጥፋትም ይሄዳል።” ራእይ 17፥11
ይህ አውሬ የሌለ መስሎ የሚሰራው ነው።ግ መጀመሪያም ያለ ነው።ከ7ቱ ነገስታት ጋር የሚለይበት አካሄድ አለው።በሃሰተኛ ነቢይነት ይሰራል ም.13፥11።ለዚያ ነው "8ኛ የተባለው" ተለይቶ።ምንም እንኳን ቀይ ዘንዶው ምንጭ ብሆንም።ደግሞም ከ7ቱ አውሬዎችም አንዱም ነው ተብሏል።ምክንያቱም ይህ አውሬ ከመንግሥት ጋር በቅርበት ይሰራል ።
"የራሶችን" መገለጥ ተመልክተናል ።አሁን ደግሞ የቀንዶቹን መገለጥ እንመለከታለን ቁ.3- ።እንቀጥል ፦
“ያየሃቸውም አስሩ ቀንዶች ገና መንግሥትን ያልተቀበሉ አስር ነገሥታት ናቸው፥ ዳሩ ግን ከአውሬው ጋር ለአንድ ሰዓት እንደ ነገሥታት ሥልጣንን ይቀበላሉ።” ራእይ 17፥12
አስሩ ቀንዶች ለሚቋቋመው ለዘንዶው መንግስት ሃይል የሚሆኑ ነገስታት 10ሩ መንግስታት ናቸው ።ለግዜው ለአውሬው ሃይል ብሆኑም ግን ጥቅት ግዜ ብቻ ከአውሬው ጋር ይቆማሉ፤ይረዳሉ፤ለአንድ ሰዓት ብቻ።
“እነዚህ አንድ አሳብ አላቸው፥ ኃይላቸውንና ሥልጣናቸውንም ለአውሬው ይሰጣሉ።” ራእይ 17፥13
እነዚህ 10 ሩ መንግስታት ሃይላቸውን ለአውሬ ጥቅም ያውላሉ ።ምክንያቱም የአውሬው ዓላማ የእነሱም ነው። ምንድነው ዓላማቸው !?
“እነዚህ በጉን ይወጋሉ፤ በጉም የጌቶች ጌታና የነገሥታት ንጉሥ ስለ ሆነ እነርሱን ድል ይነሣል፥ ከእርሱም ጋር ያሉ የተጠሩና የተመረጡ የታመኑም ደግሞ ድል ይነሣሉ።”ራእይ 17፥14
ዓላማቸው ኢየሱስን መጣል ነው።ግን ይሸነፉሉ።እንድሁም የኢየሱስ ተከታዮቹም ያሸንፋሉ፤ የተጣመረውን የዘንዶውን ሃይል።ሃሌ ሉያ።
“አለኝም፦ ጋለሞታይቱ የተቀመጠችባቸው ያየሃቸው ውኃዎች፥ ወገኖችና ብዙ ሰዎች አሕዛብም ቋንቋዎችም ናቸው።”ራእይ 17፥15
ገና መላአኩ ስጀምር ".. ና በብዙም ውኃዎች ላይ የተቀመጠችውን የታላቂቱን ጋለሞታ ፍርድ አሳይሃለሁ፤”ራእይ 17፥1 ብሎ ነበረና ፣ ጋለሞታይቱ የተቀመጠችው የተለያየ ቋንቋ የሚናገሩ ወገን እና ሕዝብ ላይ ነው።እነዚህን ተቆጣጥራለች።ለራሷ ትጠቀማለችም።
~~~~~~~~~
“ያየኃቸውም አስር ቀንዶችና አውሬው ጋለሞታይቱን ይጣላሉ፤ ባዶዋንና ራቁትዋንም ያደርጓታል፥ ሥጋዋንም ይበላሉ፥ በእሳትም ያቃጥሉአታል።” ራእይ 17፥16
ለአንድ ሰዓት በጉን እና ተከታዮቹን ለመዋጋት የተጣመሩት የሰይጣን ሠራዊት እና ጋለሞታይቱ /ታላቁ የአውሬው ከተማ/ እርስ በእርስ ይጣላሉ ።ምን አስተውላችሁ !?
ባዶዋን ያስቀራሉ ።ያጠፏታል።የዘንዶውን ከተማ ምንጭ የሆነችቱን ከተማ 10ሩ የሰይጣን ሃገራት ይጥሏታል ።ምን አስተዋላችሁ!? ሰይጣንን እርስ በእርስ ብቀዋወም ምን ይፈጠራል !? ቃሉ እንደሚል፦
“ሰይጣንም ራሱን ተቃውሞ ከተለያየ፥ መጨረሻ ይሆንበታል እንጂ ሊቆም አይችልም።”ማርቆስ 3፥26
ስለዚህም በሰይጣን የተቋቋመው 10ሩ መንግስታት ዋናውን የዘንዶውን ከተማ ይቃወሟታል፤ለዚያች ከተማ ውድመት ነው፤ለሰይጣን መንግስትም የመጨረሻ ይሆናል ።በ4ኛው ሰማይ መከፈት በእግዚአብሔር ቁጣ ጦርነት ይደረጋል ብለን ነበር።ለካ ጦርነቱ የሚደረገው በሰይጣን መንግስት እርስበእርስ ነው። በ6ኛው ቁጣ እንዳልነው ሰይጣን የራሱን መንግስት "አቋቋምኩ" ብሎ ስዋጋ ፥ነገሩ የእግዚአብሔር ቁጣ ስለሆነ የመጨረሻው ይሆናል ፤ፍርድን ይቀበላል ።“ያየሃትም ሴት በምድር ነገሥታት ላይ የምትነግሥ ታላቂቱ ከተማ ናት።”ራእይ 17፥18 ።
[ከፊት ለተመለከትነው ራዕይ እንደ ዮሐንስ ዝርዝር ሃሳቡን ስንመለከት ፣በይበልጥ የተረዳነው ይመስለኛል ።ተባረኩ።ጽኑ።]
________________________________________
“ከዚህ በኋላ ታላቅ ስልጣን ያለው ሌላ መልአክ ከሰማይ ሲወርድ አየሁ፥ ከክብሩም የተነሣ ምድር በራች።”ራእይ 18፥1
ባቢሎን ስጥል ከባቢሎን የሚበልጥ ክብር ያለው ፥ ታላቅ አምላክ ስለሆነ ፥ በክብር መላአኩን ገለጠው።
በክብር የተገለጠው መላአክም ስለ ባቢሎን እንዲህ እያለ ያውጃል ፤ ድምጻችን ከፍ አድርገን እናብብ!፤ መውደቋን ለራሳችንም እናውጅ ፦
ራእይ 18
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
² በብርቱም ድምፅ፦ ታላቂቱ ባቢሎን ወደቀች፥ ወደቀች፥ የአጋንንትም ማደሪያ ሆነች፥ የርኵሳንም መናፍስት ሁሉ መጠጊያ የርኵሳንና የተጠሉም ወፎች ሁሉ መጠጊያ ሆነች፤
³ አሕዛብ ሁሉ ከዝሙትዋ ቍጣ ወይን ጠጅ የተነሳ ወድቀዋልና፥ የምድርም ነገሥታት ከእርስዋ ጋር ሴሰኑ የምድርም ነጋዴዎች ከቅምጥልነትዋ ኃይል የተነሳ ባለ ጠጋዎች ሆኑ ብሎ ጮኸ።
በሦስተኛው ሰማይ መከፈት እንደተገለጠው ም.14፥8 ወደቀች፤ሃሌ ሉያ።
~~~~~~~~
ከሰይጣን መንግስት ጦርነት በኃላ ማዕከሏ ሃያሏ መንፈሳዊ ግልሙትና መገኛ ከተማ የሆነችቱ ትወድቃለች።በውስጧ ያሉትስ ሰዎች ፦
“ከሰማይም ሌላ ድምፅ ሰማሁ እንዲህ ሲል፦ ሕዝቤ ሆይ፥ በኃጢአትዋ እንዳትተባበሩ ከመቅሠፍትዋም እንዳትቀበሉ ከእርስዋ ዘንድ ውጡ፤” ራእይ 18፥4
ባቢሎን ከተማ ከወደቀች በኃላ በውስጧ ያሉቱ ከከተማዋ እንድወጡ ጥሪ ቀርቧል።እግዚአብሔር በዚያም ግዜም ንስሐ እንድገቡ ከዓለማዊነት ትዕቢት እንድወጡ ጥር ያደርጋል ።ምክንያቱም ልፈርድ ነው፦
ራእይ 18
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁵ ኃጢአትዋ እስከ ሰማይ ድረስ ደርሶአልና፥ እግዚአብሔርም ዓመፃዋን አሰበ።
⁶ እርስዋ እንደ ሰጠች መጠን ብድራት መልሱላት፥ እንደ ሥራዋም ሁለት እጥፍ ደርቡባት፤ በቀላቀለችው ጽዋ ሁለት እጥፍ አድርጋችሁ ቀላቅሉባት፤
⁷ ራስዋን እንደ አከበረችና እንደ ተቀማጠለች ልክ ሥቃይና ኀዘን ስጡአት። በልብዋ፦ ንግሥት ሆኜ እቀመጣለሁ ባልቴትም አልሆንም ኀዘንም ከቶ አላይም ስላለች፥
⁸ ስለዚህ በአንድ ቀን ሞትና ኀዘን ራብም የሆኑ መቅሰፍቶችዋ ይመጣሉ፥ በእሳትም ትቃጠላለች፤ የሚፈርድባት እግዚአብሔር ብርቱ ነውና።
*በባቢሎን ላይ የእግዚአብሔር የፍርዱን ዝርዝር እንመልከት ፦
#ለምድር_ነገስታት ||
ራእይ 18 ÷⁹ ከእርስዋም ጋር የሴሰኑና የተቀማጠሉ የምድር ነገሥታት የመቃጠልዋን ጢስ ሲያዩ ስለ እርስዋ ዋይ ዋይ እያሉ ያለቅሳሉ፤ ¹⁰ ሥቃይዋንም ከመፍራት የተነሣ በሩቅ ቆመው፦ አንቺ ታላቂቱ ከተማ፥ ብርቱይቱ ከተማ ባቢሎን፥ ወዮልሽ፥ ወዮልሽ፥ በአንድ ሰዓት ፍርድሽ ደርሶአልና እያሉ ይናገራሉ።
#ለምድር_ነጋዴዎች ||
ራእይ 18
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹¹ የመርከባቸውንም ጭነት ከእንግዲህ ወዲህ የሚገዛ የለምና የምድር ነጋዴዎች ያለቅሱላታል ያዝኑላትማል፤
¹² ጭነትም ወርቅና ብር የከበረም ድንጋይ ዕንቁም፥ ቀጭንም ተልባ እግር ቀይም ሐርም ሐምራዊም ልብስ የሚሸትም እንጨት ሁሉ፥ ከዝሆን ጥርስም የተሰራ ዕቃ ሁሉ፥ እጅግም ከከበረ እንጨት ከናስም ከብረትም ከዕብነ በረድም የተሰራ ዕቃ ሁሉ፥
¹³ ቀረፋም ቅመምም የሚቃጠልም ሽቱ ቅባትም ዕጣንም የወይን ጠጅም ዘይትም የተሰለቀ ዱቄትም ስንዴም ከብትም በግም ፈረስም ሰረገላም ባሪያዎችም የሰዎችም ነፍሳት ነው።
¹⁴ ነፍስሽም የጎመጀችው ፍሬ ከአንቺ ዘንድ አልፎአል፥ የሚቀማጠልና የሚያጌጥም ነገር ሁሉ ጠፍቶብሻል፥ ሰዎችም ከእንግዲህ ወዲህ ከቶ አያገኙአቸውም።
#ለባህር_ላይ_መርከበኞች ||
ራእይ 18
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁵-¹⁷ እነዚህን የነገዱ በእርስዋም ባለ ጠጋዎች የሆኑት እያለቀሱና እያዘኑ፦ በቀጭን ተልባ እግርና በቀይ ሐምራዊም ልብስ ለተጐናጸፈች በወርቅና በከበረ ድንጋይም በዕንቁም ለተሸለመች ለታላቂቱ ከተማ ወዮላት፥ ወዮላት፥ ይህን የሚያህል ታላቅ ባለ ጠግነት በአንድ ሰዓት ጠፍቶአልና እያሉ ስቃይዋን ከመፍራት የተነሣ በሩቅ ይቆማሉ። የመርከብም መሪ ሁሉ በመርከብም ወደ ማናቸውም ስፍራ የሚሄድ ሁሉ መርከበኞችም ከባሕርም የሚጠቀሙ ሁሉ በሩቅ ቆሙ፥
¹⁸ የመቃጠልዋንም ጢስ ባዩ ጊዜ፦ ታላቂቱን ከተማ የምትመስላት ምን ከተማ ነበረች? እያሉ ጮኹ።
¹⁹ በራሳቸውም ላይ ትቢያ ነስንሰው እያለቀሱና እያዘኑ፦ በባሕር መርከቦች ያሉአቸውን ሁሉ ከባለ ጠግነትዋ የተነሣ ባለ ጠጋዎች ላደረገች ለታላቂቱ ከተማ ወዮላት፥ ወዮላት፥ በአንድ ሰዓት ጠፍታለችና እያሉ ጮኹ።
“ሰማይ ሆይ፥ ቅዱሳን ሐዋርያት ነቢያትም ሆይ፥ በእርስዋ ላይ ደስ ይበላችሁ፥ እግዚአብሔር ፈርዶላችኋልና።”ራእይ 18፥20
ባቢሎን ላይ ፍርዱ ቀጥሏል ...
________________________________
“አንድም ብርቱ መልአክ ትልቅን ወፍጮ የሚመስልን ድንጋይ አንስቶ ወደ ባሕር ወረወረው እንዲህ ሲል፦ ታላቂቱ ከተማ ባቢሎን እንዲህ ተገፍታ ትወድቃለች ከእንግዲህም ወዲህ ከቶ አትገኝም።”ራእይ 18፥21
ሃያል ነኝ ያለችቱ ከተማይቱ እንዳልነበረ ትጠፋለች ።ዘንዶው ያቋቋመው ከተማ ይጠፋል ።አዎን ይጠፋል ።
ከተማዋ ከዚህ በፊት የነበራት እንቅስቃሴ ባጠቃላይ በመውደሙ ትጠፋለች ።ትጨልላለች።ሃያልነቷ ያበቃል ።
ራእይ 18
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²² በገና የሚመቱና የሚዘምሩም ድምፅ እንቢልታንና መለከትንም የሚነፉ ድምፅ ከእንግዲህ ወዲህ በአንቺ ውስጥ ከቶ አይሰማም፥ የእጅ ጥበብም ሁሉ አንድ ብልሃተኛ እንኳ ከእንግዲህ ወዲህ በአንቺ ውስጥ ከቶ አይገኝም፥ የወፍጮ ድምጽም ከእንግዲህ ወዲህ በአንቺ ውስጥ ከቶ አይሰማም፥
²³ የመብራትም ብርሃን ከእንግዲህ ወዲህ በአንቺ ውስጥ ከቶ አይበራም፥ የሙሽራና የሙሽራይቱም ድምጽ ከእንግዲህ ወዲህ በአንቺ ውስጥ ከቶ አይሰማም፤ ነጋዴዎችሽ የምድር መኳንንት ነበሩና፥ በአስማትሽም አሕዛብ ሁሉ ስተዋልና።
,ጌታ ስለቅዱሳን ደም ፍትህን ሰጠ ።“በእርስዋም ውስጥ የነቢያትና የቅዱሳን ደም በምድርም የታረዱ ሁሉ ደም ተገኘባት።” ራእይ 18፥24
~~~~~~~~~~~
*በባቢሎን ላይ ለተደረገው ፍርድ 24 ሽማግሌዎች (አማኞች ሁሉ) እና 4ቱ እንስሳዎች (ፍጥረታት በሙሉ) ደስ ተሰኙ ።እግዚአብሔር ስፈርድ አዛኝ አዛኝ የሚጫወት አካል የለም።ይገርማል ።
ድምጻችን ከፍ አድርገን እያመሰገንን በመንፈስ እናምብብ ፦
ራእይ 19
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹-² ከዚህ በኋላ በሰማይ፦ ሃሌ ሉያ፤ በዝሙትዋ ምድርን ያጠፋችይቱን ታላቂቱን ጋለሞታ ስለ ፈረደባት፥ የባሪያዎቹንም ደም ከእጅዋ ስለ ተበቀለ፥ ፍርዶቹ እውነትና ጽድቅ ናቸውና ማዳንና ክብር ኃይልም የአምላካችን ነው ብሎ ሲናገር እንደ ብዙ ሕዝብ ታላቅ ድምፅ ያለ ድምፅን ሰማሁ።
³ ደግመውም፦ ሃሌ ሉያ አሉ፤ ጢስዋም ለዘላለም እስከ ዘላለም ይወጣል።
⁴ ሀያ አራቱም ሽማግሌዎችና አራቱ እንስሶች በፊታቸው ተደፍተው በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠው ለእግዚአብሔር፦ አሜን፥ ሃሌ ሉያ እያሉ ሰገዱለት።
~~~~~~~
ድምጻችን ከፍ አድርገን እናምብብ ፦
ራእይ 19
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁵ ድምፅም፦ ባሪያዎቹ ሁሉ እርሱንም የምትፈሩት ታናናሾችና ታላላቆች ሆይ፥ አምላካችንን አመስግኑ ሲል ከዙፋኑ ወጣ።
⁶ እንደ ብዙ ሕዝብም ድምፅ፥ እንደ ብዙ ውኃዎችም ድምፅ፥ እንደ ብርቱም ነጐድጓድ ድምፅ ያለ ድምፅ ሰማሁ እንዲህ ሲል፦ ሃሌ ሉያ፤ ሁሉን የሚገዛ ጌታ አምላካችን ነግሦአልና።
⁷ የበጉ ሰርግ ስለ ደረሰ ሚስቱም ራስዋን ስላዘጋጀች ደስ ይበለን ሐሤትም እናድርግ ክብርንም ለእርሱ እናቅርብ።
“ያጌጠና የተጣራ ቀጭን የተልባ እግር ልብስ እንድትጐናጸፍ ተሰጥቶአታል። ቀጭኑ የተልባ እግር የቅዱሳን ጽድቅ ሥራ ነውና።” ራእይ 19፥8
~~~~~~~
*የቅዱሳን ልብስ ቀጭን የተልባ እግር ልብስ ነው።ማለትም የኢየሱስ ማንነት ነው።በእኛ የሚገለጥ ።የክርስቶስ በመሆናችን ቀጭን የተልባ እግር ልብስ ወይም ጽድቅ እንድንለብስ ተሰቶናል።የተሰጠን እንጂ ከፍለን የወሰድነው ልብስ አይደለም ።“ማንም እንዳይመካ ከሥራ አይደለም።”ኤፌሶን 2፥9 መጽሐፍ እንደሚል።
...
“እርሱም፦ ወደ በጉ ሰርግ እራት የተጠሩ ብፁዓን ናቸው ብለህ ጻፍ አለኝ። ደግሞም፦ ይህ የእግዚአብሔር እውነተኛ ቃል ነው አለኝ።”ራእይ 19፥9
*ይህ ለዮሐንስ "ጻፍ" ብሎ ትዕዛዝ የሰጠው መልአክ በም.18 ላይ የተገለጠው መልአክ ነው።ወደ እረፍቱ የገቡ ፥ከኢየሱስ ጋር የሚሆኑ የተባረኩ ናቸው አለው።ደግሞም ምስክርነቱ የታመነ ነው አለው ።
“ልሰግድለትም በእግሩ ፊት ተደፋሁ። እርሱም፦ እንዳታደርገው ተጠንቀቅ፤ ከአንተ ጋር የኢየሱስም ምስክር ካላቸው ከወንድሞችህ ጋር አብሬ ባሪያ ነኝ፤ ለእግዚአብሔር ስገድ፤ የኢየሱስ ምስክር የትንቢት መንፈስ ነውና አለኝ።”ራእይ 19፥10
ለዮሐንስ በታላቅ ክብር ፥ምድር በሚያበራ ብርሃን ፥ መላአኩ ስገለጥለት እንኳን "ያልሰገደው" ዮሐንስ ፤በሌሎች ክፍሎች እንዳየነው ምስጋናቸውን ስሰማ እና የሚሰግዱትን ስመለከት ያልሰገደው ዮሐንስ ፣ " በበጉ ሰርግ የሚገኙ ብፁዓን ናቸው" መላአኩ ስለው ሰገደለት ።የሚገኘው ለመልአኩ በመልአኩ ፈቃድ እንደሆነ አስቦ ይሁን !?
#ለምን እንደሰገደ ግን ግልጽ አይደለም !? ምክንያቱም ዮሐንስ ዝም ብሎ "እንጂ መንሳት" ወይም ክብር ለመስጠት ሳይሆን #ልያመልከው ነው።በግርኩ ሰገደለት የሚለው ቃል የተቀመጠው proskynéō የሚል ነው።አምልኮን ይገልጻል ።
#መላአኩ በዮሐንስ መመለክን አልፈለገም! አስጠነቀቀው! የእግዚአብሔርን ክብር መጋፋት አልፈለገም ። ዮሐንስ ዓይኑን ከእግዚአብሔር አንስቶ ወደ ራሱ እንድያደርግ አልጋበዘም።እንድሁም ከአማኞች ጋር እግዚአብሔርን የማመልክ "ባሪያ ነኝ" አለው ።
#የመላአኩ ትህትና ይገርማል! "ባሪያ ነኝ" ማለቱም ይደንቃል ። " ድንቅ እና ሃያል ነን" ራሳቸውን ወንጌል በመመስከራቸው ለሚሉት ተግሳጽ ነው።
#የኢየሱስ ምስክር የትንቢት መንፈስ ነው || ማለትም የኢየሱስ መስክር እኛ መልእክተኞች ሳንሆን የቃሉ መንፈስ ነው።ስለዚህም በቃሉ በተነገረው በመልእክቱ ላይ ትኩረት እናድርግ ።ከመላአኩ መልስና ከዮሐንስ ድርግት የሚንረዳው ከመልእክተኞች አይናችንን እንድናነሳ ነው፤መልእክቱን ብቻ እንቀበል
#ዮሐንስ ለማምለክ ያደረገው ሙከራ ከደስታ የመነጨ ልሆን ይችላል ብሆንም ግን ሰው በመሆኑ ነው፤ ስህተት ነው።ይህም የሰውን ድካምን ያስረዳል ።ዮሐንስን ተሳስተሃል ያለው መልአኩ እንደሆነ ይረዷል።አምልኮ መገዛት ለእግዚአብሔር ብቻና ብቻ ስለሆነ ነው።ሃሌ ሉያ።
እንቀጥላለን ...
______________________________________
በዓለም ለሚከሰቱ ነገሮች ከበስተጀርባ ያለውን እውነታ ለማውቅ መጽሐፍ ቅዱስን እናጥና! እንወቀው! እንጽና ! (34)
“ሰማይም ተከፍቶ አየሁ፥ እነሆም አምባላይ ፈረስ፥ የተቀመጠበትም የታመነና እውነተኛ ይባላል፥ በጽድቅም ይፈርዳል ይዋጋልም።” ራእይ 19፥11
#ይህ_6ኛው_ሰማይ መከፈት ነው!
ዮሐንስ ስመለከት ነጭ ፈረስ ላይ የተቀመጠ ነው፤አሸናፊ ነው።በም.6 ላይ በማህተሞቹ መከፈት የተመለከትነው ጋር ይመሳሰላል ።ግን የም.6ቱ ነጭ ፈረስ መቀመጥ በበጉ ቁጥጥር ስሪ የሆነ የሰይጣን ሰራዊት ሥራ ሲሆን የዚህ ክፍል ነጭ ፈረስ ሃሰተኛ አስተማሪ አሳች ሳይሆን እውነተኛ ነው፤የሚፈርድም ነው።ማን ይሁን !?
“ዓይኖቹም እንደ እሳት ነበልባል ናቸው፥ በራሱ ላይም ብዙ ዘውዶች አሉ፥ ከእርሱም በቀር አንድ እንኳ የማያውቀው የተጻፈ ስም አለው፤”ራእይ 19፥12
ዓይኖቹ እንደ እሳት ነበልባል ናቸው ፤በቁጣ የተሞላ ነው ም.1፥14 ተመልከቱ ።
በራሱ ላይ ብዙ ዘውዶች አሉት ፤ሥልጣን ያለው ነው።
የማይታወቅ ስም አለው፤ገና የሚገለጥልን ማንነት አለው ።የእግዚአብሔር ስም ማንነት ነው።እንጂ እንደ እኛ ሰዎችን ከሰዎች ለመለየት የሚያገለግል አይደለም ።ስለዚህም የክርስቶስን ማንነት አውቀን አልጨረስንም።መጽሐፍ እንደሚል አሁን ኢየሱስ በሚያውቀን ልቅ እኛ ያኔ ስገለጥ ገና እናውቃለን ።“ዛሬስ በመስተዋት በድንግዝግዝ እንደምናይ ነን በዚያን ጊዜ ግን ፊት ለፊት እናያለን፤ ዛሬስ ከእውቀት ከፍዬ አውቃለሁ በዚያን ጊዜ ግን እኔ ደግሞ እንደ ታወቅሁ አውቃለሁ።”1ኛ ቆሮ 13፥12
“በደምም የተረጨ ልብስ ተጐናጽፎአል፥ ስሙም የእግዚአብሔር ቃል ተብሎአል።”ራእይ 19፥13
#በደም_የተረጨ_ልብስ|| ስለኃጥአታችን የፈሰሰውን የደማውን ያመለክታል ።ግን በአውዱ ስንተረጉመው ፍትህ ልያደርግ ነው፤ልፈርድ ነው።ዮሐንስ ወንጌላዊው በወንጌሉ ም.1፥1 ላይ መጀመሪያም የእግዚአብሔር ቃል ነበረ እንዳለው አሁንም በዚህ ማንነቱ ተገልጧል ።ስሙ ማንነቱ ነው፤ኢየሱስ ክርስቶስ ቃል የተባለው አምላክ ነው።
“በሰማይም ያሉት ጭፍራዎች ነጭና ጥሩ ቀጭን የተልባ እግር ልብስ ለብሰው በአምባላዮች ፈረሶች ተቀምጠው ይከተሉት ነበር።”ራእይ 19፥14
የሚከተሉቱ የኢየሱስን ጽድቅ ያደረጉ ሁሉ ናቸው ።በአምባ ፈረስ ላይ ተቀምጠው ማለትም እንደ በጉ ስላሸነፉ በአሸናፊነት ይከተላሉ ።
“አሕዛብንም ይመታበት ዘንድ ስለታም ሰይፍ ከአፉ ይወጣል፤ እርሱም በብረት በትር ይገዛቸዋል፤ እርሱም ሁሉን የሚገዛ የእግዚአብሔርን የብርቱ ቍጣውን ወይን መጥመቂያ ይረግጣል።” ራእይ 19፥15
"ስለታም ሰይፍ" መለኮታዊ ፍርድን ያመለክታል ፣
"አሕዛብን በብረት ብትር ይገዛል" በሃይል ይገዛል ።ይንበረከካሉ ።አሁን በፈቃዳቸው ባይገዙም በመጨረሻው ፍርድ ሰዓት ያለፈቃዳቸው ይንበረከካሉ ይገዛሉ፤ይረገጣሉ ።"የወይን መጥመቂያው መረገጥ" ከአማኞች ይለያያሉ በመለኮታዊ ፍርድ ።
“በልብሱና በጭኑም የተጻፈበት፦ የነገሥታት ንጉሥና የጌታዎች ጌታ የሚል ስም አለው።” ራእይ 19፥16
ኢየሱስ ማንነቱ በራሱ አሸናፊ ነው።አምላክ ነው።የበላይ ነው።ሃሌ ሉያ።
...
“አንድም መልአክ በፀሐይ ውስጥ ቆሞ አየሁ፥ በሰማይም መካከል ለሚበሩ ወፎች ሁሉ፦ መጥታችሁ የነገሥታትን ሥጋና የሻለቃዎችን ሥጋ የብርቱዎችንም ሥጋ የፈረሶችንም በእነርሱም የተቀመጡትን ሥጋ የጌታዎችንና የባሪያዎችንም የታናናሾችንና የታላላቆችንም ሁሉ ሥጋ እንድትበሉ ወደ ታላቁ ወደ እግዚአብሔር እራት ተከማቹ ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኸ።”ራእይ 19፥17-18
ይህ ሁለተኛው የበጉ ጥሪ ነው።1ኛው የበጉ ጥሪ ቤተክርስቲያን ሙሽሪት ራሷን ስላዘጋጀች ደስ ትሰኛለች ም.19፥7 ምክንያቱም በፍርዱ ፍትህን ታገኛለች።በሁለተኛው በበጉ ጥሪ ደግሞ ቅዱሳንም የሚገባቸውን ስበሉ ፣ አውሬውን የተከተሉትም በቁማቸው የሚገባቸውን ይበላሉ።
ራእይ 19
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁹ በፈረሱም የተቀመጠውን ጭፍራዎቹንም ይወጉ ዘንድ አውሬውና የምድር ነገሥታት ጭፍራዎቻቸውም ተከማችተው አየሁ።
²⁰ አውሬውም ተያዘ በእርሱም ፊት ተአምራትን እያደረገ የአውሬውን ምልክት የተቀበሉትን ለምስሉም የሰገዱትን ያሳተ ሐሰተኛው ነቢይ ከእርሱ ጋር ተያዘ፤ ሁለቱም በሕይወት ሳሉ በዲን ወደሚቃጠል ወደ እሳት ባሕር ተጣሉ።
²¹ የቀሩትም በፈረስ ላይ ከተቀመጠው ከአፉ በሚወጣው ሰይፍ ተገደሉ፤ ወፎችም ሁሉ ከሥጋቸው ጠገቡ።
~~~~~~~~~~~~
“የጥልቁንም መክፈቻና ታላቁን ሰንሰለት በእጁ የያዘ መልአክ ከሰማይ ሲወርድ አየሁ።” ራእይ 20፥1
እየተመለከትን ያለነው የ6ኛውን ሰማይ መከፈት ነው።በዚህ ሰማይ መከፈት በሌሎች ሰማይ መከፈት የታዩ ትዕይንቶች ጠቅላላ ሃሳቡን እናገኛለን ።
በዚህ ሰማይ መከፈት የተገለጠው መላአክ ለዲያብሎስ ፈቃድ የሚሰጥ እና የሚከለክል ነው።ይህ መልአክ ማን ነው!? ዲያብሎስን ምን ያደርጋል !?
“የቀደመውንም እባብ ዘንዶውን እርሱም ዲያብሎስና ሰይጣን የተባለውን ያዘው፥”ራእይ 20፥2
መልአኩም ዲያብሎስን ያዘው ።ለምን ያዘው !?
“ሺህ ዓመትም አሰረው፥ ወደ ጥልቅም ጣለው አሕዛብንም ወደ ፊት እንዳያስት ሺህ ዓመት እስኪፈጸም ድረስ በእርሱ ላይ ዘግቶ ማኅተም አደረገበት፤ ከዚያም በኋላ ለጥቂት ጊዜ ይፈታ ዘንድ ይገባዋል።”ራእይ 20፥3
መልአኩ ዲያቢሎስን የያዘው ሺህ ዓመት ለማሰር ነው። አሕዛብን እንዳያስት ለማድረግ ነው።
*በሰይጣን ሺህ ዓመት መታሰር ብዙ ሃሳቦች አሉት ።"መቼ ነው !?" በሚለው ሃሳብ ላይ።ይህ መታሰር ግን የዘላለም የስቃይ ፍርድን የሚያመለክት አይደለም ።ሰይጣን በሕይወቱ የሚሰቃይበት መታሰር አይደለም ።ግን ሌሎችን እንዳያስት እንቅስቃሴውን ዋጋ ቢስ የሚያደርግ ነው።ሰይጣን የታሰረው አሕዛብ እንዳይስቱ ለማድረግ ነው።አስተውሉ።
ሰይጣን የታሰራው የእግዚአብሔር ልጅ በእኛ መካከል ከተገለጠበት ግዜ አንስቶ ነው።ሙሉ በሙሉ የራሱን ግብር እንዳያከናውን እግዚአብሔር አድርጎታል ።ምክንያቱም መጽሐፍ “እኔ ግን በእግዚአብሔር መንፈስ አጋንንትን የማወጣ ከሆንሁ፥ እንግዲህ የእግዚአብሔር መንግሥት ወደ እናንተ ደርሳለች።”ማቴዎስ 12፥28 እንደሚል ነው።ኢየሱስ በእግዚአብሔር መንፈስ ሰይጣንን እንዳይሰራ እያስወጣ ገብቷል ።ሰይጣንን በሙላት መስራት አሁንም አይችልም ።መጽሐፍ ፦
“ወይስ ሰው አስቀድሞ ኃይለኛውን ሳያስር ወደ ኃይለኛው ቤት ገብቶ እቃውን ሊነጥቀው እንዴት ይችላል? ከዚያም ወዲያ ቤቱን ይበዘብዛል።”ማቴ 12፥29 እንደሚል ፣ አሁንም አሕዛብንም እንዳያስት እግዚአብሔር ጣልቃ ገብቷል ።ደግሞም በሌላ ክፍል ኢየሱስ ራሱ አሕዛብን ከሰይጣን እንደማረከ እንረዳለን ፦
“ኢየሱስም በምኩራቦቻቸው እያስተማረ፥ የመንግሥትንም ወንጌል እየሰበከ፥ በሕዝብም ያለውን ደዌና ሕማም ሁሉ እየፈወሰ፥ በከተማዎችና በመንደሮች ሁሉ ይዞር ነበር።”ማቴ 9፥35
ታዲያ ሺህ ዓመት የሰይጣን መታሰር ምንድነው !? ደግሞም ለጥቅት ግዜ መፈታትስ ምን ማለት ነው!?
“ወንድሞች ሆይ፥ ልባሞች የሆናችሁ እንዳይመስላችሁ ይህን ምሥጢር ታውቁ ዘንድ እወዳለሁ፤ #የአሕዛብ_ሙላት_እስኪገባ_ድረስ ድንዛዜ በእስራኤል በአንዳንድ በኩል ሆነባቸው፤”ሮሜ 11፥25
ከዚህ ክፍል እንደሚንረዳው ወንጌል ይሰበካል ፣ አሕዛቦች ሁሉ እንዳይስቱ ጌታ በመከልከሉ ፣ የሚድኑቱ አሕዛብ ሙሉዕ በሙሉ ይድናሉ ፣ ከዚያም እስራኤላውያን ከድንዛዘአቸው ይወጣሉ ።የሰይጣን ሺህ ዓመት መታሰር #ያለ_የሚኖር_ነው፤የአሕዛብ ሙላት እስኪፈጸም ድረስ።ሰይጣንን ሙሉ በሙሉ በነፃነት ብሰራ አሕዛብ አይድኑም ማለት ነው።እናም የአሕዛብ ሙላት ስፈጸም እስራኤላውያን ከእንቅልፋቸው ወጥተው በጌታ ማመን ይጀምራሉ ።የሰይጣን ለጥቅት ግዜ መፈታት በእስራኤላውያን መንቃት ጋር ሳይገናኝ አይቀርም ።(በእስራኤላውያን ላይ መከራ ሳይበረታ አይቀርም ፤መላአኩ ሚካኤልም ይረዳቸዋል የተባለው በዚህ ግዜ ሳይሆን አይቀርም ዳን 12 )
*በዚህ ክፍል ሺህ አመት የተባለው ብዙ ብዙ ዓመታትን ለመግለጽ እንጂ 1000 ዓመት ማለት አይደለም ።ደግሞም ከኢየሱስ ጋር በምድር 1000 ዓመት እንኖራለን ማለት አይደለም ።ሃገራችን በሰማይ ነው።ይህ የሚያልፍ ዓለም ነው።
*የሰይጣን የጥቅት ግዜ መፈታቱ የ3ዓመት ከተኩል ቤተክርስቲያን ላይ የሚያደርሰው መከራ ሳይሆን አይቀርም ።
(በዚህ ሰማይ መከፈት በፊት ስላየናቸው መገለጦች ጠቅለል ያለ ሃሳቡን እያየን ነው፤እንቀጥላለን.. )
______________________________________
“ዙፋኖችንም አየሁ፥ በእነርሱም ላይ ለተቀመጡት ዳኝነት ተሰጣቸው፤ ስለ ኢየሱስም ምስክርና ስለ እግዚአብሔር ቃል ራሶቻቸው የተቈረጡባቸውን ሰዎች ነፍሳት፥ ለአውሬውና ለምስሉም ያልሰገዱትን ምልክቱንም በግምባራቸው በእጆቻቸውም ላይ ያልተቀበሉትን አየሁ፤ ከክርስቶስም ጋር ሺህ ዓመት ኖሩና ነገሡ።” ራእይ 20፥4
ዮሐንስ ዙፋኖቾኖም አየሁ አለ።የዙፋን አገላለጽ የአንድ አካል የብዛ ነው።አብን ፣ ኢየሱስ ክርስቶስን፣መንፈስ ቅዱስን ይገልጻል ብለን መረዳት እንችላለን ።ደግሞም ዮሐንስ በሌሎች ክፍሎች እንደገለፀው ዙፋኑንም የከበቡትን ቅዱሳንን ተመለከተ።(24 ሽማግሌዎች የተባሉትን።)
እነዚህ ቅዱሳን መዳኘት ይችላሉ።ለእያንዳንዱ ሰው የሚገባውን ይሰጣሉ ማለት ነውን !? አይደለም ።እንደዛ አንረዳውም።ምክንያቱም ፍርድ ለእግዚአብሔር የሚለው ሕግ መጠበቅ አለብን።ታዲያ ምን ማለት ነው !? ፍርድ ማለት እውነትን ከሃሰት መለየት ማለት ነው።(መጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት)
*ይህንን የመፍረድ ስልጣን በይበልጥ ለመረዳት የቆሮንቶስ መልእክት እንመልከት ፦
“የትዳር ጉዳይ ይቅርና በመላእክት እንኳ እንድንፈርድ አታውቁምን?”1ኛ ቆሮ 6፥3 ።
በዚህ ክፍል ላይ ሐዋርያው ጳውሎስ አማኞች በትዳራቸው ጉዳይ ስካሰሱ ወደ በዓለማዊያን ፍርድ በቶች አትሂዱ ፣በቤተክርስቲያን ጭረሱ በማለት ስገስጻቸው የተጠቀመው ሃይሌ ቃል ነው።በትዳር ጉዳይ ላይ እውነትን እውነት ነው ፣ሃሰተኛውን ሃሰተኛ ነው በማለት የመፍረድ ሙሉዕ ስልጣን ለቤተክርስቲያን እንደተሰጠ ያስገነዝባል ።
እንደዚሁም በራዕይ ጥናታችን ከዚህ ጋር ትዩዩ በሆነ መንገድ አማኞች እውነትን እውነት ነው፤ሃሰትን ሃሰት ነው የማለት ስልጣን እንዳላቸው እንገነዘባለን ።(ያ ማለት ግን የዘላለም ስቃይ ወይንም እረፍት የሚሰጡት አማኞች ናቸው ማለት አይደለም )
*እነዚህ ቅዱሳኖች ከክርስቶስ ጋር ለሺህ ዓመት የኖሩ ናቸው ።ከክርስቶስ ጋር መኖር የጀመሩት ካመኑበት ቅጽበት ጀምረው ነው።አማኞች በምድር እያሉ እንኳን በሰማይ ስፍራ ከክርስቶስ ጋር ናቸው የሚኖሩት ።ኤፌ2፥7።
ስለዚህም የእግዚአብሔር መንግስት "ትምጣ" ብለን እንደጸልይን መንግሥቱ ትመጣለች ።እኛም ከኢየሱስ ጋር እንነግሳለን።ለዘላለም ።በእረፍት ።
“ሺሁም ዓመት ሲፈጸም ሰይጣን ከእስራቱ ይፈታል፥” ራእይ 20፥7
ሰይጣን በሙላት እንዳይሰራ የከለከለው የእግዚአብሔር መንፈስ የአሕዛብ ሙላት ስፈጽም ፣ ለጥቅት ግዜ ሰይጣን ሃይሉን አጠናክሮ መስራት ይጀምራል ። ከዛዝ ምን ይከሰታል !?
“በአራቱም በምድር ማዕዘን ያሉትን አሕዛብ፥ ጎግንና ማጎግን፥ እንዲያስታቸው ለሰልፍም እንዲያስከትታቸው ይወጣል፤ ቍጥራቸውም እንደ ባሕር አሸዋ የሚያህል ነው።”ራእይ 20፥8
ቅዱሳንን ለመዋጋት ሰይጣን ሙሉዕ ሃይሉን አጠራቅሞ አቋቁሞ ልዋጋ ይመጣል።(ይህ ክስተት በሌሎች መገለጦች ያየነውን ይዘክራል) ። ሰይጣን በዓለም ነገስታት እና በ10 ሩ መንግስታት በኩል በጉን ልዋጋ ስወጣ እንደተሸነፈ ፥ እግዚአብሔርም ፍርዱን እንዳደረገ ተምረናል ።ም.18።ከላይ እንዳልነው የሰይጣን ለጥቅት ግዜ መፈታት 1260 ቀን የቤተክርስቲያን ፈተና ያመለክታል ።
“ወደ ምድርም ስፋት ወጡ የቅዱሳንንም ሰፈርና የተወደደችውን ከተማ ከበቡ፤ እሳትም ከሰማይ ከእግዚአብሔር ዘንድ ወርዳ በላቻቸው።”ራእይ 20፥9
፥ በአርማጌዶን ጦርነት እግዚአብሔር ፍርዱን እንዳደረገ ተመልክተናል ።ይህም ክፍል ሃሳብ ያንን ታርክ ያብራራል ።
*እሳት ከሰማይ ይወርዳል መለኮታዊ ፍርድ ይደረጋል ።ከዚያም ፦
“ያሳታቸውም ዲያብሎስ አውሬውና ሐሰተኛው ነቢይ ወዳሉበት ወደ እሳቱና ወደ ዲኑ ባሕር ተጣለ፥ ለዘላለምም እስከ ዘላለም ቀንና ሌሊት ይሣቀያሉ።”ራእይ 20፥10
...
“ታላቅና ነጭ ዙፋንን በእርሱም ላይ የተቀመጠውን አየሁ፥ ምድርና ሰማይም ከፊቱ ሸሹ ስፍራም አልተገኘላቸውም።”ራእይ 20፥11
ይህ ቃል ማንም በጌታ ፊት በፍርድ ሰዓት መቆም እንዳልቻለ ያሳየናል ።ሸሹ።መቆም አልቻሉም ።
“ሙታንንም ታናናሾችንና ታላላቆችን በዙፋኑ ፊት ቆመው አየሁ፥ መጻሕፍትም ተከፈቱ፤ ሌላ መጽሐፍም ተከፈተ እርሱም የሕይወት መጽሐፍ ነው፤ ሙታንም በመጻሕፍት ተጽፎ እንደ ነበረ እንደ ሥራቸው መጠን ተከፈሉ።”ራእይ 20፥12
*በዚህ መገለጥ ሙታንም ከአማኞች ጋር መቆማቸው ሁሉም በእግዚአብሔር ፊት እኩል ናቸው የሚለው ቃሉን የሚገልጽ ሳይሆን አይቀርም ።
*ደግሞም ሁለተኛው ሌላ መጽሐፍ ተመለከተ ፦የሕይወት መጽሐፍ ።በሕይወት መጽሐፍ ስሙ አለ ራዕ 3፥5።ስም ያልተገኘባቸው ሁሉም ወደ ዘላለም ስቃይ ይወርዳሉ ።
“ባሕርም በእርሱ ውስጥ ያሉትን ሙታን ሰጠ፥ ሞትና ሲኦልም በእነርሱ ዘንድ ያሉትን ሙታን ሰጡ፥ እያንዳንዱም እንደ ሥራው መጠን ተከፈለ።”ራእይ 20፥13
ሞት በሞት መቅሰፍት የሞቱትን ሙታን ይሰጣል ራዕ 6፥8 ፣ ሲኦልም ወይም በመቃብር የተቀበሩትም ይወጣሉ ፦ከዚያም እንደሰራቸው የእጃቸውን ያገኛሉ ።
'' ልጁ ያለው የዘላለም ሕይወት ፣
ልጁ የሌለው የዘላለም ሞት። ''
“ሞትና ሲኦልም በእሳት ባሕር ውስጥ ተጣሉ። ይህም የእሳት ባሕር ሁለተኛው ሞት ነው።”ራእይ 20፥14
በጌታ አለመሆን የመጀመሪያው ሞት ነው፣
በጌታ ሳይሆኑ መሞት ደግሞ ሁለተኛ ዘላለማዊ ሞት ነው፣ ስለዚህም የመጨረሻ ከባድ ስቃይ ይጠብቃል ።ልገልጸው የማልችለው ።አማኞች ደስ ይበላችሁ የዘላለም ሕይወት የእኛ ነው።እረፍቱ የእኛ ነው።ሃሌ ሉያ።ስለዚህም ከዚህ ፍርድ ነፃ ነን ፦
“በሕይወትም መጽሐፍ ተጽፎ ያልተገኘው ማንኛውም በእሳት ባሕር ውስጥ ተጣለ።”ራእይ 20፥15 ፥ በሕይወት መጽሐፍ ስሜ አለ።አበቃ።ሃሌሉያ።ድኛለሁ ።
..
“አዲስ ሰማይንና አዲስ ምድርንም አየሁ፥ ፊተኛው ሰማይና ፊተኛይቱ ምድር አልፈዋልና፥ ባሕርም ወደ ፊት የለም።”ራእይ 21፥1
ሁለም የሰማይ መከፈት መዝጊያ ስንመለከት የመጨረሻው አጨራረስ እረፍት ነው።ደስታ ነው።ቅኔ ለበጉ ነው።እናም በዚህ ክፍል ዝርዝር መገለጥ እግዚአብሔር አድርጓል ።ተመልከቱ ፦
አድስ ሰማይና ምድር (ሰማይና ምድር ነው ግን አድስ ነው)፣
አሁን የሚከበርበት ምድር ከነጦሱ አልፏል ፣
“ቅድስቲቱም ከተማ አዲሲቱ ኢየሩሳሌም፥ ለባልዋ እንደ ተሸለመች ሙሽራ ተዘጋጅታ፥ ከሰማይ ከእግዚአብሔር ዘንድ ስትወርድ አየሁ።”ራእይ 21፥2
ጌታ ስመጣ እግዚአብሔር ከሰዎች ጋር የመኖር ዓላማውን ማሳካቱን ያሳያል ፦
“ታላቅም ድምፅ ከሰማይ፦ እነሆ፥ የእግዚአብሔር ድንኳን በሰዎች መካከል ነው ከእነርሱም ጋር ያድራል፥ እነርሱም ሕዝቡ ይሆናሉ እግዚአብሔርም እርሱ ራሱ ከእነርሱ ጋር ሆኖ አምላካቸው ይሆናል፤”ራእይ 21፥3
ስለዚህም ወደ እረፍቱ የገቡቱ ከጌታ ጋር ያለ ሃሳብ ይኖራሉ ፦
“እንባዎችንም ሁሉ ከዓይኖቻቸው ያብሳል፥ ሞትም ከእንግዲህ ወዲህ አይሆንም፥ ኀዘንም ቢሆን ወይም ጩኸት ወይም ሥቃይ ከእንግዲህ ወዲህ አይሆንም፥ የቀደመው ሥርዓት አልፎአልና ብሎ ሲናገር ሰማሁ።”ራእይ 21፥4
ስለዚህም ጌታ የመጀመሪያውን ያለው አድስ አደረገ፥አድስ ነገር አልፈጠረም ።እግዚአብሔር አደሰ ያለውን ።ተሃድሶ የእግዚአብሔር ሥራ ነው።ተመልከቱ ፦
“በዙፋንም የተቀመጠው፦ እነሆ፥ ሁሉን አዲስ አደርጋለሁ አለ። ለእኔም፦ እነዚህ ቃሎች የታመኑና እውነተኛዎች ናቸውና ጻፍ አለኝ።”ራእይ 21፥5
ስለዚህም ተፈጽሟል ፦
“አለኝም፦ ተፈጽሞአል። አልፋና ዖሜጋ፥ መጀመሪያውና መጨረሻው እኔ ነኝ። ለተጠማ ከሕይወት ውኃ ምንጭ እንዲያው እኔ እሰጣለሁ።” ራእይ 21፥6 አለ።
ተፈጽሟል ብሎም የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ አስተላልፏል ጌታ፤አቤት ፍለጋ።ተመልከቱ ፦
“ዳሩ ግን የሚፈሩና የማያምኑ የርኵሳንም የነፍሰ ገዳዮችም የሴሰኛዎችም የአስማተኛዎችም ጣዖትንም የሚያመልኩ የሐሰተኛዎችም ሁሉ ዕድላቸው በዲንና በእሳት በሚቃጠል ባሕር ነው፤ ይኸውም ሁለተኛው ሞት ነው።”ራእይ 21፥8
______________________________________
“ሰባቱም ኋለኛዎች መቅሠፍቶች የሞሉባቸውን ሰባቱን ጽዋዎች ከያዙት ከሰባቱ መላእክት አንዱ መጥቶ፦ ወደዚህ ና፥ የበጉንም ሚስት ሙሽራይቱን አሳይሃለሁ ብሎ ተናገረኝ።”ራእይ 21፥9
እስካሁን በሰማይ መከፈት የተመለከትነው ፦
1ኛው.የዓለምን እንቆቅልሽ የያዘው መጽሐፍ ፣
2ኛው.ለዓለም የተተላለፈውን ማስጠንቀቂያ ፣
3ኛው.በሰማይ የነበረውን ጦርነት ፣
4ኛው.የእግዚአብሔር ቁጣ፣
5ኛው.ባቢሎን ላይ የተደረገውን ፍርድ፣
6ኛው.የራዕይ ጥቅልል መልእክት ፣
7ኛው.ስለምዕመናት(ቤተክርስቲያን )፣
*ሌሎች መገለጦች በእያንዳንዱ ሰማይ መከፈት ስሪ የተገለጡ ናቸው ።እነዚህ ሰባቱ የሰማይ መከፈቶች በውስጥ የያዙትን ዝርዝር ሃሳብ እንድንረዳ ይረዱናል ።በዚህ መገለጥ ትኩረት የተደረገችው የእግዚአብሔር ድምፅ የሰማች የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ናት፦
እነዚህ ቤተክርስቲያናት ግን በም.2-3 ባለው ራዕይ መልእክት ላይ አስቸኳይ የተሃድሶ ጥሪ የቀረበላቸው ናቸው ።እናም ጥሪውን ተቀበለው የታደሱቱ ሁሉ ይህንን ክብር ያያሉ ።
*በዚህ መስኮት በኩል ያለው መገለጥ ስንመለከት ሁላችንም የተዘጋጀውን በማሰብ ለመታደስ እንደሚንነሳሳ አያጠራጥርም ። የታደሱቱን የክርስቶስ ቤተክርስቲያንን እንመልከት ፦
ቤተክርስቲያን የበጉ ሚስት ተብላለች እርሱን ብቻ ለማምለክ ቃል ኪዳን ስላደረገች ፣ ሙሽራ ተብላለች ባልዋን ለመቀበል ፍክት ንፅት ብላ ስለምትጠብቅ።
“በመንፈስም ወደ ታላቅና ወደ ረጅም ተራራ ወሰደኝ፥ የእግዚአብሔርም ክብር ያለባትን ቅድስቲቱን ከተማ ኢየሩሳሌምን ከሰማይ ከእግዚአብሔር ዘንድ ስትወርድ አሳየኝ፤ ብርሃንዋም እጅግ እንደ ከበረ ድንጋይ እንደ ኢያሰጲድ ድንጋይ ሆኖ እንደ ብርሌ የጠራ ነበረ፤”ራእይ 21፥10-11
ጋለሞታይቱን ለማሳየት ወደበረሃ ነበር የወረደው እንዳይታለል ፣ ቤተክርስቲያንን ለማሳየት ግን ወደ ተራራ ዮሐንስ ተወሰደ ፣ ክብሯን በሙላት እንድመለከት ።የእግዚአብሔር መገኘት አለና።
“ታላቅና ረጅም ቅጥር ነበራት፥ አሥራ ሁለትም ደጆች ነበሩአት በደጆቹም አሥራ ሁለት መላእክት ቆሙ፥ የአሥራ ሁለቱም የእስራኤል ልጆች ነገዶች ስሞች ተጽፈውባቸው ነበር።”ራእይ 21፥12
*12 የብሉይ የእግዚአብሔር ሕዝብነት በአድስ ኪዳንም በ12 ሐዋርያት ቤተሰብነት እንደቀጠለ የሚያመለክት ነው።ስለዚህም የብሉይም የአድስም ቅዱሳን ከየአጥቃጨው መጥተው ገብተዋል ፤ቁ.13 ፣ ሉቃ 13፥29
“ለከተማይቱም ቅጥር አሥራ ሁለት መሠረቶች ነበሩአት፥ በእነርሱም ውስጥ የአሥራ ሁለቱ የበጉ ሐዋርያት ስሞች ተጽፈው ነበር።”ራእይ 21፥14
*ቤተክርስቲያን ከሐዋርያት ትምህርት ሌላ ትምህርት ፣ "መገለጥ ነው" ብሎ ያመነ የማይገኝባት ናት ፣
“የተናገረኝም ከተማይቱንና ደጆችዋን ቅጥርዋንም ይለካ ዘንድ የወርቅ ዘንግ ነበረው።”ራእይ 21፥15
በቤተክርስቲያን በም.11 ልዩ ጥበቃ እንድደረግላት ተለክታ ነበር፣ አሁን ግን የዘላለም መኖሪ ስፍራ ነው የሚለካው ።ደግሞም ለመለካት የተሰጣት በወርቅ ነው በብትር አይደለም ።
ራእይ 21
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁶ ከተማይቱም አራት ማዕዘን ነበራት፥ ርዝመትዋም እንደ ስፋትዋ ልክ ነበረ። ከተማይቱንም በዘንግ ለካት #አሥራ_ሁለትም_ሺህ ምዕራፍ ሆነች፤ ርዝመትዋና ስፋትዋ ከፍታዋም ትክክል ነው።
¹⁷ ቅጥርዋንም ለካ፥ #መቶ_አርባ_አራት ክንድ በሰው ልክ፥ እርሱም በመልአክ ልክ።
*የከተማዋ መጠን ተቆጥረው ከማያልቁ ከቅዱስ ቁጥር ጋር ይመሳሰላል ።
የከተማዋን ውበት ደግሞ ፦
ራእይ 21
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁸ ቅጥርዋም ከኢያሰጲድ የተሠራ ነበረ፥ ከተማይቱም ጥሩ ብርጭቆ የሚመስል ጥሩ ወርቅ ነበረች።
¹⁹ የከተማይቱም ቅጥር መሠረት በከበረ ድንጋይ ሁሉ ተጌጦ ነበር፤ ፊተኛው መሠረት #ኢያሰጲድ፥ ሁለተኛው #ሰንፔር፥ ሦስተኛው #ኬልቄዶን፥ አራተኛው #መረግድ፥
²⁰ አምስተኛው #ሰርዶንክስ፥ ስድስተኛው #ሰርድዮን፥ ሰባተኛው #ክርስቲሎቤ፥ ስምንተኛው #ቢረሌ፥ ዘጠነኛው #ወራውሬ፥ አሥረኛው #ክርስጵራስስ፥ አሥራ አንደኛው #ያክንት፥ አሥራ ሁለተኛው #አሜቴስጢኖስ ነበረ።
²¹ አሥራ ሁለቱም ደጆች አሥራ ሁለት ዕንቆች ነበሩ፤ እየአንዳንዱ ደጅ ከአንድ ዕንቍ የተሠራ ነበረ። የከተማይቱም አደባባይ ጥሩ ብርጭቆ የሚመስል ጥሩ ወርቅ ነበረ።
*እነዚህ የከተማይቱ መሠረቶች እንቁዎች እያንዳንዳቸው በራሳቸው ዕንቁዎች የተሰራ መሆኑ ይደንቃል ።(12 መሠረት እና 12 የተለያዩ ዕንቁዎች መሆኑ ሁሉም አማኞች ከአንድ ቦታ እና በአንድ መንገድ አለመምጣታቸውን የሚያሳይ ሳይሆን አይቀርም )
..
(የቤተክርስቲያንን ውበት ከመገረም ውጪ መግለጽ አለመቻለ ይታወቅልኝ፤እግዚአብሔር ይረዳኝ )
______________________________________
“ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክና በጉ መቅደስዋ ናቸውና መቅደስ በእርስዋ ዘንድ አላየሁም።”ራእይ 21፥22
*መቅደስ ለእግዚአብሔር ማደሪያ ነበር ፣ ለአማኞች ከእግዚአብሔር ጋር የሚንጋገሩበት ነው።በዚያን ግዜ ግን ራሱ ጌታ በእኛ መኃል አለ።መቅደስ የለም።መቅደሱ ራሱ አምልኮ ስፍራችን አምላካችን ነው።(ጌታ አምላክ አብ ሲሆን ጌታ በጉ ኢየሱስ ነው)
“ለከተማይቱም የእግዚአብሔር ክብር ስለሚያበራላት መብራትዋም በጉ ስለ ሆነ፥ ፀሐይ ወይም ጨረቃ እንዲያበሩላት አያስፈልጓትም ነበር።” ራእይ 21፥23
*ይህች የታደሰች ከተማ የተፈጠረ ፀሃይ አልባ ከተማ ናት።ፈጣሪዋ ራሷ ፀሃዩዋ ነው።ለሁሉም የሚያበራ ብርሃን ነው።“አሕዛብም በብርሃንዋ ይመላለሳሉ፥ የምድርም ነገሥታት ክብራቸውን ወደ እርስዋ ያመጣሉ፤”ራእይ 21፥24
ለሁሉም የሚያብራ ብቻ ሳይሆን ለሁልጊዜም የሚያበራ ነው “በዚያም ሌሊት ስለሌለ ደጆችዋ በቀን ከቶ አይዘጉም፥” ራእይ 21፥25
ስለዚህም የጌታን ተግሳጽ ተቀብሎ የትንብቱን ቃል የሚጠብቁቱ ሁሉ ይገባሉ።“የአሕዛብንም ግርማና ክብር ወደ እርስዋ ያመጣሉ።”ራእይ 21፥26
ይህች ከተማ መሰዳደብ አሽሙር ሐሜት የሌለባት ንፁህ የሆኑ የፍጹማን መኖሪያ ነች።“ለበጉም በሆነው በሕይወት መጽሐፍ ከተጻፉት በቀር፥ ጸያፍ ነገር ሁሉ ርኵሰትና ውሸትም የሚያደርግ ወደ እርስዋ ከቶ አይገባም።”ራእይ 21፥27
“በአደባባይዋም መካከል ከእግዚአብሔርና ከበጉ ዙፋን የሚወጣውን እንደ ብርሌ የሚያንጸባርቀውን የሕይወትን ውኃ ወንዝ አሳየኝ።” ራእይ 22፥1
*መገረማችን_ቀጥሏል || በምናባችን ከምናስባት በላይ ፣ከሚንናፈቃት በላይ ፣ ያማረች ፣ወንጀልም ወንጀለኛም የሌለባት ፣ የሰላም ከተማ ናት፣
*ከእግዚአብሔር የተባለው አብ ሲሆን፣ከበጉ የተባለው ኢየሱስ ነው ፤ደግሞም ከአብም ከኢየሱስም ዙፋን የሚወጣ ሆኖ የተገጠው የሕይወት ውሃ መንፈስ ቅዱስ ነው። ዮሐ 4፥14፤7
*እግዚአብሔር ጅማሮም ፍጻሜም የሌለው ሥላሴ ( #ሦስት_አካል_ያለው_አንድ_አምላክ_ነው ) ነው።አስተውሉ ይህ ዓለም ሁሉ ተጠቅልሎ አልፎ አማኞች ከአምላካቸው ጋር በደስታ በሚኖሩበት ግዜም አንዱ እግዚአብሔር ሥስት አካል አለው ።
“በወንዙም ወዲያና ወዲህ በየወሩ እያፈራ አሥራ ሁለት ፍሬ የሚሰጥ የሕይወት ዛፍ ነበረ፥ የዛፉም ቅጠሎች ለሕዝብ መፈወሻ ነበሩ።”ራእይ 22፥2
*ዘወትር ፍሬ የሚሰጡ ዛፎች ያሉባት ከተማ ናት ፣
“ከእንግዲህም ወዲህ መርገም ከቶ አይሆንም። የእግዚአብሔርና የበጉም ዙፋን በእርስዋ ውስጥ ይሆናል፥ ባሪያዎቹም ያመልኩታል፥ ፊቱንም ያያሉ፥”ራእይ 22፥3
*በዔድን ገነት መርገም ደርሶብን ነቀር፣ አሁን ግን መርገም የለም።የእግዚአብሔርና (የአብና) የበጉ(የኢየሱስ ) ዙፋን አለ፣
*ይገርማል አሁንም ባሪያዎች ናቸው ፤ አማኞች ፣ መላእክት ፣ ... ያመልኩታልም ፣
*"ፊቱን ያያሉ" እናያለን እናውቃለንም፣
“ስሙም በግምባሮቻቸው ይሆናል።”ራእይ 22፥4
*የኢየሱስ ማንነት በግልጽ በባሪያዎቹ ይታያል ም.3፥12፣
“ከእንግዲህም ወዲህ ሌሊት አይሆንም፥ ጌታ አምላክም በእነርሱ ላይ ያበራላቸዋልና የመብራት ብርሃንና የፀሐይ ብርሃን አያስፈልጋቸውም፤ ለዘላለምም እስከ ዘላለም ይነግሣሉ።”ራእይ 22፥5
*መንግሥቱ ስለመጣች ሁለም እናበራለን፣
*ለዘላለም በዚህ ክብር በእረፍት እንኖራለን ፣
*መኖር የሚለው ቃል አይገልጸውም እንደ ንጉሥ እንነግሣለን ፣
“እርሱም፦ እነዚህ ቃሎች የታመኑና እውነተኛዎች ናቸው፥ የነቢያትም መናፍስት ጌታ አምላክ #በቶሎ_ሊሆን_የሚገባውን ነገር ለባሪያዎቹ እንዲያሳይ መልአኩን ሰደደ።” ራእይ 22፥6
*ይህ ሁሉ ቅዠት አይደለም ፣
*ራዕይ ሙሉ መልእክቱ ቶሎ ልሆን የሚገባ ነው (ማለትም ራዕይ መጽሐፍ ያለፈ ታረክ ትረካ አይደለም)፣
*በመላአኩ በኩል የተገለጠው የታመነ ነው፣
ስለዚህም "ይህ ክብር ቶሎ ልሆን ይገባል!" ይለናል ጌታ ፣ የእኛ መልስ ምን ይሁን ...!?
____
“እነሆም፥ በቶሎ እመጣለሁ። የዚህን መጽሐፍ ትንቢት ቃል የሚጠብቅ ብፁዕ ነው አለኝ።” ራእይ 22፥7
*የተገለጠውን የሚጠብቅ የተባረከ (ብፁዕ) ነው፣
*ስለዚህም ተስፋውን ልፈጽመው "ቶሎ እመጣለሁ "ይለናል አምላካችን ..የእኛ መልስ ምን ይሁን !?
“ይህንም ያየሁትና የሰማሁት እኔ ዮሐንስ ነኝ። በሰማሁትና ባየሁትም ጊዜ ይህን ባሳየኝ በመልአኩ እግር ፊት #እሰግድ ዘንድ ተደፋሁ።”ራእይ 22፥8
*ዮሐንስ መልአኩን እንደገና በም.19 እንዳደረገው ልያመልከው ወደደ ፣
*መላአኩ ስግደቱን ተቀብሎ ይሁን ..!?
*መላአኩ ግን አልተታለለም የእግዚአብሔርን ለእግዚአብሔር አደረገ ፦
“እርሱም፦ #እንዳታደርገው_ተጠንቀቅ፤ ከአንተ ጋር ከወንድሞችህም ከነቢያት ጋር የዚህንም መጽሐፍ ቃል ከሚጠብቁ ጋር አብሬ #ባሪያ ነኝ፤ ለእግዚአብሔር ስገድ አለኝ።”ራእይ 22፥9
“ለእኔም፦ ዘመኑ ቀርቦአልና የዚህን መጽሐፍ ትንቢት ቃል በማኅተም አትዝጋው።”ራእይ 22፥10
*ለዳንኤል ቶሎ ስለማይፈጸም " ዝጋው ብሎ" ነበር ዳን 12፥4 ፣
*ለዮሐንስ ግን ልፈጸም ስለተቃረበ " አትዝጋው" አለ፣
(ፍጻሜው ምን ያህል እንደቀረበ ያስረዳል )
“ዓመፀኛው ወደ ፊት ያምፅ፥ ርኵሱም ወደ ፊት ይርከስ፥ ጻድቁም ወደ ፊት ጽድቅ ያድርግ፥ ቅዱሱም ወደፊት ይቀደስ አለ።”ራእይ 22፥11
*ሁሉም ሰዎች ከመንገዳቸው እንደማይመለሱ እንደማይለወጡ ያሳያል ፥
“እነሆ፥ በቶሎ እመጣለሁ፥ ለእያንዳንዱም እንደ ሥራው መጠን እከፍል ዘንድ ዋጋዬ ከእኔ ጋር አለ።”ራእይ 22፥12
*ለዓመፀኞች የሚገባውን ፥ለጻድቃንም የሚገባውን ዋጋ ለመስጠት ጌታም ቸኩሏል፣
“አልፋና ዖሜጋ፥ ፊተኛውና ኋለኛው፥ መጀመሪያውና መጨረሻው እኔ ነኝ።”ራእይ 22፥13
*አሁንም በጉ ኢየሱስ ከአብ ጋር እኩል እንደሆነ ያሳያል ፣
“ወደ ሕይወት ዛፍ ለመድረስ ሥልጣን እንዲኖራቸው በደጆችዋም ወደ ከተማይቱም እንዲገቡ ልብሳቸውን የሚያጥቡ ብፁዓን ናቸው።” ራእይ 22፥14
*ልብሳቸውን በደሙ የሚያጥቡ ብፁዓን ናቸው ፣
*በደሙ ያልነፁቱ አይገቡም ፦
“ውሻዎችና አስማተኞች ሴሰኛዎችም ነፍሰ ገዳዮችም ጣዖትንም የሚያመልኩት ውሸትንም የሚወዱና የሚያደርጉ ሁሉ በውጭ አሉ።”ራእይ 22፥15
ስለዚህም ኢየሱስ እንዲሁ ይለናል ፦
“እኔ ኢየሱስ በአብያተ ክርስቲያናት ዘንድ ይህን እንዲመሰክርላችሁ መልአኬን ላክሁ። እኔ የዳዊት ሥርና ዘር ነኝ፥ የሚያበራም የንጋት ኮከብ ነኝ።” ራእይ 22፥16
ይገርማል የዳዊት ሥር ፣
የዳዊት ዘር ነኝ ይላል ኢየሱስ በሥጋው ማንነት ሳያፍር፣
(አላፈረብንም ከእኛ እኛን በመሆኑ)፣
*ኢየሱስ የንጋት ኮከብ ነው ጨለማው ማለፉን በብራኑ የሚያበስር ነው፣
“መንፈሱና ሙሽራይቱም፦ ና ይላሉ። የሚሰማም፦ ና ይበል። የተጠማም ይምጣ፥ የወደደም የሕይወትን ውኃ እንዲያው ይውሰድ።” ራእይ 22፥17
*ጌታ ኢየሱስ መምጣት ጥቅም ገብቷቸው አሁን
መንፈስ ቅዱስ ራሱ በእኛ ውስጥ ሆኖ ና ብሎ ይጸልያል ፣
*እኛም አማኞች ከመንፈስ ቅዱስ ተቀብለን "አዎን ና" ብለን እንጸልያለን ፣
የመጨረሻው ማስጠንቀቂያ ፦
“በዚህ መጽሐፍ የተጻፈውን የትንቢት ቃል ለሚሰማ ሁሉ እኔ እመሰክራለሁ፤ ማንም በዚህ ላይ አንዳች ቢጨምር እግዚአብሔር በዚህ መጽሐፍ የተጻፉትን መቅሠፍቶች ይጨምርበታል፤”ራእይ 22፥18
*ኢየሱስም ፦ “..፦ አዎን፥ በቶሎ እመጣለሁ ይላል ፤
*እኛም ፦ ".. አሜን፥ ጌታ ኢየሱስ ሆይ፥ ና።”ራእይ 22፥20 እንላለን ።ተስማምተናል ።ብመጣ ይሻለናልና ።
ይህንን መልእክት እንደጨረስን በራስሽን ፊት ገጽ "ማራናታ" እንበል ።ናፍቆታችንን ለውዳችን እንግለጽ ።
“የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከሁላችን ጋር ይሁን፤ አሜን።”ራእይ 22፥21
ማጠቃለያ
በዓለም ላይ ልሆን ያለውን እና የማይታዩቱ ሃይላት ሥራ የተረዳነው ይመስለኛል ።ራዕይ ስናጠና " የሁሉ የበላይ ማን ነው?" ስንል ፣በጉ ኢየሱስ ማህተሙን የፈታው ነው ብለን ተመልክተናል ።ደግሞም ከሁሉም በላይ የሆነው አምላክ ያቀረበውን ተገሳጽም እንዳደረገ አስተውለናል (ማስጠንቀቂያዎችን) ፣
ከዛም ስንመለስ ጦርነት ምድር ላይ ብቻ ሳይሆን እንድሁም የመጀመሪያው ጦርነት በሰማይ እንደሚጀመርም አስተውለናል ፣ በሰማይ የነበረው ጦርነት ወደ ምድር በመምጣቱም ከፍተኛ ጦርነት መከራ እንደተከሰተም አስተውለናል ።በዚህም ደግሞ ጌታ ቁጣውን እንደገለጸ ራዕይን በተለያየ ጎን ተመልክተናል ።
የእግዚአብሔርን ቁጣ ተመልክተን ስንመለስ ሙሉ መረዳት እንድኖረን በጋለሞታዩቱ ከተማ ላይ ብቻ የሚደረገውን ፍርድ ተመልክተናል ።ይህ ሁሉ ስለሚሆነው ሙሉ መረዳት እንድኖረን ነው።
ደግሞም ወደ መጨረሻው ስንጠጋ የራዕይ ጠቅለል ያለውን መልእክቱን ለመረዳት ፣ ጥቅላላ ሃሳብን ተመልክተናል ። ከዛም በመጨረሻው መገለጥ ይህ ራዕይ እንዲጻፍ ምክንያት ስለሆነቿ ቤተክርስቲያን ምዕመናት ተመልክተናል ።
ይህ ሁሉ ሃሳብ ከእግዚአብሔር ጋር የሚሆኑት እስከመጨረሻው የሚጸኑቱ እንደሚድኑ ነው።እንደሚያሸንፉ ያሳያሉ።
ተባረኩ
እድሉ ዮሐንስ ጋምሳ ( ደቀመዛሙርቱ )
Comments
Post a Comment