ቅዱሳን ንንን
መግቢያ ከአንዴ ወንዴም ጋር በመልካም መንፈስ በፊት ገጼ ፣በውስጥ መስመር "በጥያቄና መልስ ውይይት" መነጋገር ጀምርን ። ምንም እንኳን የግል ማንነት ወደ መተዋወቅ ባንሄድም መልካም ውይይት አድርገናል ።ልክ በአካል እንደሚንተዋወቅ ሰው። ብዙ ዓመት ጓደኛ እንደሆንን ሰዎች። ያለ ምንም ስድብ ፣ንቀት ፣ ሃሳብ አንሸራሽረናል።ይህ ዘመናዊነት ነው።ለዚህ ጥበባዊ ውይይት አለማመስገን አልችልም ። ለሁላችንም ምሳሌ የሚሆን ነው።ርዕሱ ላይ ብቻ ትኩረት መስጠት ፣ የምናምነው ነገርን በየዋህት መንፈስ ማቅረብ ፣የመቀበልና ያለ መቀበል መብት በማክበር ተወያይተናል ፣ይህ የዘመናዊነት ጥግ ነው። ስለ መልካም ምልልሳችን አመሰግናለሁ ።ክበርልኝ! በውይይታችን የቀረበውን ሃሳብ በሁሉም ዘንድ ማንሸራሸር ስለፈለኩ ለሁሉም አጋርቼ ነበር።ቅዱሳን ሁለንም የማወቅ ጸጋ ፣ በሁለም ቦታ የመገኘት ጸጋ አላቸው የሚለውና ፣ ጸጋ የሞላብሽ ሆይ የሚለውን ቃል ትርጓሜ ፣ የውይይታችን ቁልፍ ነጥብ ነበር። በዚህም ላይ የብዙዎች እምነት ከእግዚአብሔር ቃል የወጣ እንደሆነ ተመለከትኩ ። ስለሆነም የተቻለኝን ሰፊ ማብራሪያ ለማቅረብ ወደድኩ።ስለሆነም ከታች በተዘረዘሩት ነጥቦችን ላይ ጹሐፍ የማቀርብ ይሆናል፦ 1.አምላክነት ምንድነው !? 2.የቅደሳን ሁለንም የማወቅ ጸጋ ! 3.የቅደሳን በሁለ ቦታ የመገኘት ጸጋ ! 4. "ጸጋ የሞላብሽ ሆይ " ማለት ምን ማለት ነው !? 4.የቅደሳን ጸሎትን የመስማት ጸጋ ! 5.ያረፉ ቅደሳን ስለእኛ ምህረትን ይምናሉ !? መልካም ምንባብ ይሁን ! ብዙ የሚታተርፉበት ይሁን ! 1.አምላክነት ምንድነው !? ስለ እግዚአብሔር አምላክነት ...