ታቦትና ውዝግቡ!!
[[ታቦቱና ውዝግቡ!]]
ከዚህ በፊት "ነገረ ታቦት" ብዬ በጻፍኩት ላይ የአቅሜን ለመለገስ እንደተጣጣሪኩ ታውቃላችሁ ፣ይህ ጹሑፍ በዚህ ጹሑፍ ላይ ለተነሱ ጥያቄዎች የቀረበ መልስ ነው!
[["ታቦትና መሰዊያ " የቃላት ጨዋታ!]]
#በኢኦተቤክ | ድሮ ድሮ "ታቦታችን የሙሴ ታቦት ነው፣የቃል ኪዳኑ ታቦት ነው ፣ "እግዚአብሔር እንድንሰራ አዝዞን ነው የሠራነው " ይባል ነበር።ደግሞም "ለምን ይባዛል!?" ስባል እግዚአብሔር ሙሴ ከሰበረው በኃላ "እንደገና ሥራ ብሏል" በማለት ፥ ታዝዘን እንደበፊቱ ነው የሠራነው፤ያባዛነው የሚል መልስ ይሰጥ ነበር (ዓምደ ሃይማኖት app ይመልከቱ) ።አሁን አሁን ደግሞ ከኢኦተቤክ አንዳንድ ወንድሞች ታቦታችን የሙሴ ታቦት አይደለም ፥ ምክንያቱም የሙሴ ታቦት አራት ካህናት ይሸከማሉ ፥ የእኛ ታቦት የአድስ ኪዳን ታቦት ነው፤ሥጋውና ደሙ የሚቀርብበት እቃ ስለሆነ "ታቦት" ብለን እንጠራለን ፤"ጽላትም መሰዊያም" ተብሎ ይጠራል የሚል ነው።[ለውጥ ታይቷል በትንሹም ]
*ወደ ርዕሰ ከመግባቴ በፊት አንድ ሁለት ነገር ልበላችሁ ፦
እኔ ወንድማችሁ ገና በጌታ በሆንኩበት ወራት ለውይይት ተጠራው ፣ አንድ ወንድም ስለ ታቦት ጥያቄ በማቅረቤ ፣ ይመልሳል ወደሚለው ወንድም ፣ የራሱ ደቀመዛሙርት ወደሰበሰበው ወሰደኝ።እኔም " እሺ" ብዬ ሄድኩ።ወደቤቱ ከደረስን በኃላ ከሰላምታ በኃላ ቁጭ አልን።ያመጣኝ ልጅ የመጣንበትን ርዕስ ጉዳይ አበሰረ።እኔ "የኢኦተቤክ ታቦት የሙሴ ታቦት አይደለም፤ ታቦት መባልም የለበትም" ብዬ ያቀረብኩትን ሃሳብ አቀረበለት ። ይመልሳል የተባለውም ልጁም እንደ ወሰደ "እመልሳለሁ፥አሳያለሁ" አለ። እንድሁም "ይች ብቻ ናት ሌላም ጠይቅ!?" አለኝ ፣ ኮራ ብሎ።እኔም "በእውነት ከመጽሐፍ ቅዱስ ታሳያለሁ ? የናንተ ታቦት እንደ እግዚአብሔር ትዕዛዝ እንደተሰራ!?" አልኩ ፣ እሱም "አዎ" አለ።እሺ አሳየኝ! አልኩ።ቀጠለ..
ዘፀአት ም.25 ፥10 ጠቀሰ ታነባለህ ወይስ ላንብብልህ አለኝ!? እኔም "አንብብ እሰማለሁ" አልኩ።ከዛም አነበበ ፦“ከግራር እንጨትም ታቦትን ይሥሩ፤ ርዝመቱ ሁለት ክንድ ተኩል፥ ወርዱም አንድ ክንድ ተኩል፥ ቁመቱም አንድ ክንድ ተኩል ይሁን።” ዘጸአት 25፥10 አለ ፣ በቃልም 'ማስረዳት' ጀመረ ፣ "እየለካህ አሳየኝ!?" አልኩ ።እሺ አለ።በራስ መተማመኑ ፕሮፌሰርን ያስንቃል ።ከፊት ለፊት ባለው ጠረጴዛ ላይ ቀኝ እጁን አማትሮ መለካት ጀመረ።"ርዝመቱ ሁለት ክንድ ተክል ነው" ብሎ #በንዝሩ_ለካ ፥ "ወርዱም አንድ ክንድ ተኩል ነው" ብሎ #በስንዝር_ለካ ፥ ቁመቱንም #በስንዝሩ_ለካ ፤ተማሪዎች "መልስ ሰጠ" ብለው በፈገግታቸው ልባቸው እንደተነካ ያሳውቃል።ታዘብኩ።እኔም ልጁን "አንዴ ቆይ" ብዬ አስቆምኩ ጥያቄም አቀረብኩለት ፦
<< "አንተ የለካው በስንዝር ነው"አልኩ ፥ "የሙሴን ታቦት የኢኦተቤክ 'ታቦት' መጠን ጋር ለማስተካከል ጥረት አድርገሃል" አልኩ።መጽሐፍ ቅዱስ የሚለው ግን "ስንዝር ሳይሆን ክንድ ነው" አልኩ። ክንድ እና ስንዝር ሳትለይ ማ አላወራም አልኩም።>> አሁንም ቆም ብሎ ራሱን ከመፈተሽ "እሺ በሌላ ርዕስ እናውራ አለ!" የማይነካው የማይረግጠው የለም ፤ተማሪዎች በአስተማሪያቸው 'መልስ' ደስ ተሰኝተዋል።እኔም ዝም አልኩ። "እድሉን ዝም" አስባለ የሚል ሙገሳ ተቸረለት። ይገርማል ይህ የባለፈው ዓመት አጋጣሚ ነው። (እንደዚህ ላሉት "ዝም ማለት" የውስጥ ሰላሜን የመጠበቅ አካሄደ ነው።)
ሁለተኛውን ነገር ላስቃቃኛቹ! አሁን አሁን አንዳንድ ወንድሞች ከጥያቄዎች ውርጅብኝ የተነሳ ፣መልስ ለመስጠት ስባል ፣ <<እናንተ በጠረበዛ የጌታ እራት ትካፈላላችሁ ፤እኛ ደግሞ በታቦቱ እንካፈላለን >> በማለት ፤"ታቦት ማለት መሠዊያ ማለት ነው" ይሉናል ።ግን በኢኦተቤክ ላይ ያለው ፣ የታቦት አስተምህሮ #ከመሠዊያ_እቃነት የዘለለ ነው።በንግስ ወይም በጥምቀት ቀናት ታቦቱ የሚጠራበት ስም ባለቤት ፥ በታቦቱ ሆኖ እንደሚባርክ ይነገራል ።ለምሳሌ የአርሴማ ታቦት ከሆነ "አርሴማ በታቦቱ ላይ ሆና እየባረከች ነው" በማለት ይነገራል ።ይህ የሚያሳየው አንዳንድ ወንድሞች አሁን አሁን እንደሚሉት ታቦቱ መሠዊያ ብቻ ሳይሆን ፥ #ታቦቱ_ለተሰየመበት_ባለቤት_ራሱ_ማደሪያ ጭምር መሆኑን እንደሚታስተምር የሚያስገነዝብ ነው።ሌላው ደግሞ የአንዳንድ ወንድሞች ሃሳብ ለየት የሚለው የኢኦተቤክ ከሚታንጠባርቀው ትምህርት ፣ በጥምቀት ዕለት በአንድ አደባባይ ለማክበር ፥ ከየቦታው ስመጣ ፥ ስሰበሰቡ ፣ከተለያየ ቦታ የሚመጡ ታቦታት በሚገናኙበት መንገድ ፣ ሰላምታ እንደሚለዋወጡ ይታመናል ።ማለትም አንደኛው ታቦት የገብርኤል ብሆን ከሌላ ቦታ የሚመጣው ታቦት የአርሴማ ብሆን ፣ ታቦቱን የተሸከሙ ቀሶች ሰላምታ ተሰሳጡ ሳይሆን የሚባለው "ገብርኤል አርሴማን ሰላም አላት" ነው የሚሉት ።ይህ የሚያሳየው አሁን አሁን አንዳንድ ወንድሞች እንደሚሉት ታቦት መሠዊያ ብቻ ሳይሆን ታቦቱ ለተጠራበት ባለቤትም ማደሪያ መሆኑን ነው።
[[አንዳንድ ወንድሞች ታቦት ማለት መሠዊያ ማለት ነው ብሉም ታቦት ማለት ግን መሠዊያ ማለት አይደለም ።ይህ ሁሉ ጭንቅ ስህተትን ለማስቀጠል ነው።]]
*በገበዛዝቱ በኩል የሚንጸባረቀው ትምህርት "ሥጋውና ደሙ የሚቀርብበት እቃ መሰዊያ ነው"የሚል ነው፤መሠዊያ ደግሞ ታቦት ነው የሚል አስተምህሮ ነው።ታዲያ" መሠዊያው በአድስ ኪዳን እንዴት 'ታቦት' ተብሎ ተጠራ!?" ብባል መልሳቸው ፦ ታቦት ማለት መሠዊያ ማለት ነው የሚል ነው።
#አስተውሉ! መሠዊያውን 'ታቦት' ለማለት መነሻው የሙሴ ታቦት ነው ዘፀ 25፥10 ።ሙሴን እግዚአብሔር "ታቦትን ይሥሩ" ስል መሠዊያ ሥራልኝ ማለቱ ነውን !?አይደለም ።ምክንያቱም ፦
#1ኛ.የእግዚአብሔር ጥያቄ ታቦት እንድሰራ ነው።ቃሉም በእብራይስጥ [ʼârôwn ] የሚል ነው።በእንግሊዝኛው Ark,Box,Chest,Coffin የሚል ሲሆን በአማርኛችን መርከብ፣ሳጥን፣ቁም ሳጥን፣የሬሳ ሳጥን የሚል ትርጉም የሚይዝ ነው።[ሙሴ ከሠራው ታቦት ተነስተን ብንጠራው ፥ " ʼârôwn " ማለት "ሳጥን" በሚለው ቃል ፊንትው ተብሎ የሚገለጽ ነው። (ቃላትን ስንተረጉመው በመጀመሪያው መጽሐፍ ቅዱስ በተጻፈው ቃል ተነስተን እንተረጉማለን።)
*ስለዚህም ሙሴ! በእግዚአብሔር "ታቦትን ይሥሩ" ስባል ፥ የታዘዘው "ሳጥን" እንድሰራ ነው።
#2ኛ.ታቦት ማለት መሠዊያ ማለት ብሆን እግዚአብሔር ʼârôwn ይሥሩ ማለት ሳይሆን መሠዊያ [mizbêach /altar/] ይሥሩ ይለው ነበር!
#3ኛ."ታቦት" የሚለው ቃል መሠዊያ ማለት ብሆን እግዚአብሔር ሙሴን "ታቦትን ይሥሩ" አይልም ነበር።ምክንያቱም ከሙሴ በፊት ብዙዎች መሠዊያ ሠርተዋል አቅርበዋል ፤አዳም ፣ኖኅ፤አብርሃም ፣ያዕቆብ .... መሠዊያ በመሥራት የሚጠቀሱ ናቸው ዘፍ።
ስለዚህም እግዚአብሔር ከዚህ በፊት ታቦት (ሳጥን) ስላልተሰራ "ታቦትን ይስሩ " አለ።ከዚህ በፊት የተሰራ ሳጥን ብኖር "ይሥሩልኝ" አይልም ነበር።
#4ኛ.ታቦት ማለት መሠዊያ ማለት ብሆን ታቦቱን(ሳጥኑን) ሙሴ ከመሰራቱ በፊት ፥ሙሴ ራሱ መሠዊያ ሰርቶ ነበር ግን ታቦት ተብሎ አልተጠራም! (ዘፀ 17፥15፤24፥4)
*ሙሴ የሠራው የጭቃ መሠዊያ ነበረ! ዘፀ 20፥24።የጭቃ መሠዊያው ግን መሠዊያ በመሆኑ ታቦት ተብሎ አልተጠራም!
*የጭቃ መሠዊያ ብቻ አልነበረም የድንጋይም መሠዊያ ሰርቶ ነበር! ዘፀ 20፥25!
[[መሠዊያ መሠዊያ ተብሎ ይጠራል እንጂ ታቦት ተብሎ አይጠራም!]]
____________________________
[["የኢኦተቤ ታቦት በውኑ የቃል ኪዳኑ ታቦት !?" ነውን መባል ይችላልንን!?]]
በመጀመሪያው ክፍል እንደተመለከትነው አንድ ዕቃ ታቦት ተብሎ ለመጠራት ዕቃው ሙሉ በሙሉ ሥሪቱ "ሳጥን" መሆን አለበት በማለት በሰፊው ሞግተናል።ምክንያቱም "ታቦት" ተብሎ የሚጠራው፣ ከአገልግሎቱ በመነሳት አይደለምና ነው ።ከዚህም ነጥብ በመነሳትም የኢኦተቤ ዥርግ ሰላዳው የሆነው 'መሰዊያ' ፣ ''ታቦት'' ለመባል የሚያበቃ አንዳች ነገር የለውም ብለናል።በዚህ ክፍል ላይ የምናየው "የኢኦተቤ ታቦት "ታቦት" የተባለው በአገልግሎቱ ነው" " የሚለውን እሺ ብለን ተቀብለን ብንነሳ እንኳን ታቦት ለመባል የሚያበቃ አንዳች ነገር የለውም የሚለውን በቃሉ ልሞግትና ለማሳየት ጥረት አደርጋለሁ ።
#ሙሴ የሠራው ታቦት "የቃል ኪዳኑ ታቦት" ተብሎ ይጠራል ።ከዚህ በመነሳት የኢኦተቤክ በአድስ ኪዳን ቃል ኪዳን ስለተደረገበት "የቃል ኪዳኑ ታቦት" ብለን ሰለዳውን ዕቃ ወይንም መሠዊያውን እንጠራለን የሚል አስተምህሮ ነው።ይህ አካሄድ ፍጹም ስህተት ነው። እንደሚከተለውም ቀርቧል፦
#1ኛ.ሙሴ ታቦትን የሠራው "ታቦት" ብሎ እንዲጠራና እንድሠራ ስለታዘዘ ነው የሠራው። የኢኦተቤክ 'ታቦት' ግን ዥርግ ሰሌዳ ነው። ስሩ ያለ አካል የለም ።ለመስራትም ለመጥራትም አልተፈቀደም ።ስለዚህም የኢኦተቤክ "ታቦት" ብላ ስትሰራም ፣ ስትጠራም ከጅምሩ ስህተት መሆኑን ከወዲሁ ተገናዘቡልኝ።
#2ኛ.ሙሴ የሠራው ታቦት በምድር ያለ ሲሆን ፣ ለአድስ ኪዳን ታቦት ( በሰማይ ላለው) ምሳሌ ነው (መቅደሱ በሰማይ ነውና)።
*የኢኦተቤክ ታቦት ደግሞ በሰማይ ፣በእጅ ላልተሰራች መቅደስና በውስጧ ስላሉት ዕቃዎች (ታቦትን ጨምሮ) በምድር ምሳሌ ልትሆን አትችልም፤ምክንያቱም በአድስ ኪዳን ምሳሌ መቅደስ እና የመቅደሱ እቃ (ታቦት) የለም።
#3ኛ.ሙሴ ቃል ኪዳን ከመፈጸሙ በፊት ለሕዝብ ሕጉን አሳወቀ ፣ ሕዝቡም ሕጉን ተቀበሉ ።ከሕዝቡ እሽታ በኃላ ፣ ሙሴ የእንስሳትን ደም በመርጨት ኪዳኑን አጸና።ከዚህ በኃላ ነበር ኪዳን ስለተደረገበት "የኪዳኑ ታቦት" ተብሎ የተጠራው ዕብ 9።
*ኢየሱስ ፋሲካን ባዘጋጀው ሰው ቤትም ከመሞቱ በፊት ፣ ደሙን ከማፍሰሱ በፊት ፣ በእራቱ ላይ ተገኘቶ ኪዳን እንደሚያደርግ አሳወቀ፤አወጀ። ኪዳኑ ግን በማሳወቁ ብቻ የሚጸና አይደለም ።ለኪዳኑ ደሙን ያፈሰሰው በሰማይ በእጅ ባልተሰራች መቅደስ ነው።
*ለኪዳኑ ደሙ የፈሰሰበት ታቦት በሰማይ ካለ፣ኢየሱስ ደሙን ያቀረበበትም መቅደስ በሰማይ ከሆነ፣ የኢኦተቤክ ታቦት መሰዊያ ሆኖ ደም ሳይረጭበት እንዴት ኪዳኑ እንደተደረገበት ይቆጠራል !?ስህተት ነው።
*ሙሴ በሕዝቡ እና በእግዚአብሔር መካከል ሆኖ ብሉይ ኪዳኑን በደም መርጨት አጸና።ኢየሱስም በሰማያ መቅደስ ደሙን በማቅረብ አድስ ኪዳኑን አጸና።
*የኢኦተቤክ ታቦት የኪዳኑ ታቦት ለመባል ለአገልግሎቱ መጽናት በደም መርጨት አለበት እንደ ሕጉ።ዕብ 9።ስለዚህም በደም ስላልተረጨ የኪዳኑ ታቦት ለመባል የሚያበቃ አይደለም እንላለን ።(የሚረጨውም ራሱ ሊቀ ካህናት ኢየሱስ ክርስቶስ ነው)
#4ኛ.በምድር አንድት መቅደስ ብቻ አለች፣በሰማይም አንድት መቅደስ ብቻ አለች።እስራኤላውያን ሁለት መቅደስ አልሰሩም ።ምክንያቱም የእነሱ መቅደስ ለአድስ ኪዳን መቅደስ ጥላ ነው።ጥላው መቅደስ አካሉ ስመጣ ይጠፋል ።
*ለአንዷ ለአድስ ኪዳን መቅደስ ፣በሰማይ ብቻ ላለችሁ ፣ በምድር የሚትወክል ፣ምሳሌ ወይም ጥላ የሚሆናት መቅደስ የላትም።እንድንሰራም አልታዘዝንም።
*የኢኦተቤክ "ታቦት " ብላ በመጥራቷ ብቻ በሰማይ ያለውን መቅደስ ፣ ጌታ በራሱ እጅ የሠራውን መቅደስ፣ምሳሌ ወይም የሚትወክል ወይም የእሷ ብዘት አድርጋ በማቅረቧ ብቻ ተሳስታ አሳስታለች እንላለን ።
#5ኛ.ፋሲካን ባዘጋጀው ሰው ቤት በእራቱ ላይ"የኪዳኑ ታቦት ይህ ነው" ሳይሆን የተባለው "የኪዳኑ ደም ይህ ነው ፤ ነው " የተባለው ።ጌታ ትኩረት ያደረገው በደሙ እንጂ ምግብ መበያ ትሪው ላይ አይደለም ።ጌታ "የኪዳኑን ደም ይህ ነው" ያለውን በመቀየጥ "የኪዳኑ ታቦት ይህ ነው" እንዳለው ማወሳሰብ አግባብ አይደለም ።
*"ይህ ስለእናንተ የሚፈስ የኪዳኑ ደም ነው" ጌታ ያለው ፣ ኪዳኑን ያደረገው ከመስዋዕቱ እንጂ ከዕቃው ጋር እንዳልሆነ ተረድተናል ።ነገር ግን አዎን! "ደሙ እና ሥጋው ያቀረበበትን እቃ የኪዳኑ ታቦት ነው፤ እሺ" ብለን ፣የሚሉትን ይዘን ብንነሳ እንኳን ፣ ኪዳኑ የተደረገው ጌታ እራቱን ባደረገው ቤት ባለችው በእስራኤላውያን መብያ እቃ ላይ መሆኑን እንገነዘባለን ።ስለዚህም ኪዳን ሳይደረግበት "የኪዳኑ ታቦት" ብለን መጥራት አይቻልም እንላለን ።
እስራኤላውያን የኪዳኑን ታቦት ያሉት ኪዳን ስለተደረገበት እንደሆነ እሙን ከሆነ ፣ ኪዳን ያልተደረገበትን እቃውን ደግሞም በዚህ ልክ "የኪዳኑ ታቦት" ብለው አለመጥራታቸውም እሙን ነው።እንድሁም ከዚህ ኪዳን በፊትም በኃላም በተደረጉት ኪዳን የኪዳን ታቦት የሚባል መጠሪያ አልተሰጠውም ።
በመጨረሻም ኪዳን መደረጉ በራሱ እቃውን "የኪዳኑ ታቦቱ " አያስብልም ።የኪዳኑ ታቦቱ የሚያስብለው ኪዳኑ በታቦቱ ላይ መደረጉ መሆኑ እሙን ነው፤ታቦት የሚባለው ደግሞ ውስጥ ያለው እቃ ሳጥን እንደሆነም እሙን ነው።ስለዚህም የኢኦተቤክ "የኪዳኑ ታቦት" ብላ የጠራችው እቃ /ሰሌዳው/ "ታቦትም ኪዳንም" ለመባልም በራሱ ብቁ እንዳልሆነ ልብ ይሏል። ተባረኩ።
[[ከላይ ያሉትን ለመመለስ የሞከረ ካለ ምናልባት በቀጣይ ይኖረናል..ለግዜው በይደር ይቆይልን፤ ጸጋውን እንሰብካለን]]
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
[ጽላትና[ ውዝግቡ!]]
ወደዚህ ርዕስ ስሪ ከመግባቴ በፊት ከዚህ በፊት "የኢኦተቤክ ታቦተ የአድስ ኪዳን ታቦት ነው " ለሚሉ ሰዎች የቀረበውን ጹሑፍ ያንብቡ ፦
🌱መሠዊያ እና ታቦት https://t.me/FistumTehadiso/485
🌱የእግዚአብሔር ቃልኪዳን ታቦት ነውን !?
https://t.me/FistumTehadiso/488
#ለነዚህ ጹሑፎች መልስ የሚሰጥ ስገኝ እመለሳለሁ ብዬ ነበር! እስካሁን ግን የለም።
ወደ ርዕሰ ጉዳዩ ስገባ "ጽላት የሚለው ቃል በእብራይስጥ לוּחַ loo'-akh የሚል ቃል ሲሆን ትርጓሜው lûwach ማለት ነው።"[1]
ከእንጨት ፣ ከድንጋይ ፣ከማዕድናት የሚሰራ ዘርግ ሰለዳ ጠረቤዛ ማለት ነው።
ጽላትና ውዝግቡ!
"ጽላት የሚለው ቃል በእብራይስጥ לוּחַ loo'-akh የሚል ቃል ሲሆን ትርጓሜው lûwach ማለት ነው።"[1]
ከእንጨት ፣ ከድንጋይ ፣ከማዕድናት የሚሰራ ዠርግ ሰለዳ ጠረቤዛ ማለት ነው።
"ጽሌ (ሰሌዳ) ፤ የመጻፍ ገበታ ፤ከመጻፉ ጋራ በቶታን በጥራዝ በድጕስ ቑርበት የሚያያዝ፤በቑርበቱ ብዙ ዓይነት ሐረግ ሥዕል መስቀል የሚሣልበት የሚታተምበት ጌጣም ሽልምልም።....ጽሌ ጽላት ለእፅና ለእብን ለማዕድን ይሆናል።እንጂ ለክርታስና ለብራና አይኾንም።...። ጽሌ ላንድ ሲሆን ፣ ጽላት ለሁለት ፤ለብዙም ይሆናል ።ባማርኛ ግን አንዱ ብቻ ጽላት ይባላል ይኸውም ሥራው በመጽሐፍ አምሳል መሆኑን ያሳያል፤አንድ ቅጠል ክርታስ ወይም ብራና በኹለት ወገን ስለተጻፈበት ሁለት ገጽ እንዲባል ጽላት ማለትም እንደዚሁ ነው። " [2]
ከነዚህ ትርጓሜዎች የሚንረዳው ጽላት የሚለው ቃል ፦
1.ሰሌዳ ወይም አሰራሩ ዠርግ ሰሌዳ እንደሆነ ፣
2.ከድንጋይ ፣ከእብነ በረድና ከማዕድናት የሚሠራ እንደሆነ ፣
3.ለወረቀት ፣ ለብራና ፣ለክርታስ ቃሉ ጥቅም ላይ እንደማይውል ፣
4. በግዕዙ አንድ ሰሌዳ ብቻ ለማመልከት ጽሌ ስባል ጽላት የሚለው ቃል ደግሞ ከአንድ በላይ ለሆነ ዥርግ ሰሌዳ ለማመልከት ጥቅም ላይ ይውላል ፣
5.ባማርኛ ግን ጽላት የሚለው ቃል ለአንድ ሰሌዳ ብቻ ጥቅም ላይ ይውላል ።ምክንያቱም አንዷ ሰሌዳ ላይ በሁለቱም በኩል ስለሚጻፍ ነው።አስተውሉ በአማርኛ አንዷ ሰሌዳ ብቻ ጽላት የሚትባለው ልክ እንደ መጽሐፍ በፊተኛው እና በጀርባውም በኩል ጹሑፍ ስላለው ጽላት ይባላል ።ያ ማለት በፊት በኩል ተጽፎም በጀርባው ካልተጻፈ "ጽላት" ልባል አይችልም ማለት ነው።
ቃሉን እንደዚህ ካየን የኢኦተቤክ ታቦቷን "ጽላትም ነው" ፣ "ጽላት ተብሎም ይጠራል" ማለቷ ትክክል ነው ወይስ አይደለም የሚለውን እናያለን ።የኢኦተቤክ የራሷን ታቦት ጽላት ነው ብላ የሚትጠራው ፣ "በዠርግ ሰሌዳው ላይ ዓልፋና ኦሜጋ ተብሎ የእግዚአብሔር ስም ስለተጻፈበት ነው " የሚል ነው ።ታዲያ ዓልፋና ኦሜጋ ተብሎ መጻፉ ጽላት ተብሎ እንድጠራ የሚያበቃ ነውን!? በፍጹም የሚያበቃ አይደለም፤ለዚህም ብዙ ምክንያቶችን ከታች በዝርዝር አቀርባለሁ ፦
#1.ከቃሉ ትርጓሜ አንፃር የኢኦተቤክ 'ጽላት' እንደ ግዕዝ ቋንቋ ከሆነ ጽላት የሚለው መጠሪያ አያገለግልም፤ጽላት ሳይሆን ጽሌ ነው መባል ያለበት ።ምክንያቱም አንድ ብቻ ዠርግ ሰሌዳ ስለሆነ።
የኢኦተቤክ ግን ጽላቷን ጽላት ብላ የጠራችው በዓማርኛ ቋንቋ ነው ብለን ብንሳንም እንኳንም አያስከድም እላለሁ ።ከላይ እንዳየነው ጽላት የሚለው ቃል በአማርኛ ለአንድ ሰሌዳም ያገለግላል ግን በሰሌዳው ላይ አጻጻፉ እንደ ሁለት ሰሌዳ በሁለት በኩል መሆን መሆን አለበት ።የኢኦተቤክ 'ጽላት' አንዷ ሰሌዳ በፊተኛው በኩል ብቻ ጽሕፈት ያለበት ስለሆነ "ጽላት" የሚለው ቃል እንደ አለቃ ኪዳኔ ወልደ ክፍሌ ትርጓሜ አያገለግልም እላለሁ ።
#3.እግዚአብሔር እንደ ሰጠ ተቆጥሮ እንደ ቃል ኪዳን ተቆጥሮ "የቃል ኪዳኑ ጽላት" ለመባል ብቁ አይደለም ።ምክንያቱም ፦
#ሀ.እግዚአብሔር የቃል ኪዳኑን ጽላት ሙሴ በድጋሚ እንደ ቀድመው እንድሰራ አዝዟል እንጂ እንደ ቀድመው ጽሕፈት የመጻፍ መብት አልሰጠውም ።ቃሉ እንደሚል ፦
ዘዳግም 10
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ በዚያን ጊዜ እግዚአብሔር፦ እንደ ፊተኞች ያሉትን ሁለት የድንጋይ ጽላቶች ጠርበህ ወደ እኔ ወደ ተራራው ውጣ፥ ...፤² በሰበርሃቸውም በፊተኞቹ ጽላቶች የነበሩትን ቃሎች በእነዚህ ጽላቶች #እጽፋለሁ፥..።
ጽላቶቹን ሥራ ፣
በእነዚህም ጽላቶች ላይ እጽፋለሁ አለ።
ስለዚህም እጽፋለሁ እንጂ ጻፍ ወይም አስጻፍ አላለውም ።ስለዚህም እግዚአብሔር አያውቀውም በስሙ ልጠራ አይገባም እላለሁ ።
#ለ.እግዚአብሔር ቃል ኪዳን ያደረገው በ10ሩ ሕግጋት ከሙሴ ጋር እንጂ "በዓልፋና ኦሜጋ" በሚለው ስም አይደለም ።ስለዚህም ዓልፋና ኦሜጋ የሚለው ስም በጽላቱ ላይ ስለተጻፈ "የቃል ኪዳኑ ጽላት" ብለን እንጠራለን የሚለው ትክክል አይደለም ።
#4.ዓድስ ኪዳንን እግዚአብሔር ስያደርግ በድንጋይ ፣ በዠርግ ሰሌዳ ላይ የተጻፈ 10ሩ ሕጎችን ሳይሆን የሰጠው ጸጋንና እውነት ነው።ቃሉ እንደሚል ፦
ዮሐንስ 1 ፥ ¹⁶ .. ሕግ በሙሴ ተሰጥቶ ነበርና፤ ¹⁷ ጸጋና እውነት ግን በኢየሱስ ክርስቶስ ሆነ።
ስለዚህም የኢኦተቤክ ጽላት 'የአድስ ኪዳን ጽላት ነው' ለማለት ፣ በአድስ ኪዳን መሰጠት አለበት ።በአድስ ኪዳን ሳይሰጥ እንደተሰጠ ተቆጥሮ የዓድስ ኪዳን ጽላት ነው ማለት ዋሾ ነው።
#5.ዓልፋና ኦሜጋ የሚለው ስም የእግዚአብሔር ማንነት እንጂ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ያደረገው ቃል ኪዳን አይደለም ።ስለዚህም ዓልፋና ኦሜጋ የሚለው ስም በዠርግ ሰሌዳው ላይ መጻፋችሁ የቃል ኪዳን ጽላት ነው አያስብልም ።
#6.ጽላት እንደ ቃሉ ትርጓሜውም ፣በእንጨት ይሁን በድንጋይ ወይም በማዕድን ላይ የተኛውንም ቃል የቧጨረ "ጽላት" ብሎ ልጠራው ይችላል ።ግን የእግዚአብሔር የቃል ኪዳኑ ጽላት ወይም የሕጉ ጽላት ነው የማለት መብት የለውም ።
ስለዚህም ከነዚህ ነጥቦች ተነስቼ 'የኢኦተቤክ ጽላት ' አይደለም የእግዚአብሔር የቃል ኪዳኑ ጽላት መባል ይቅርና ፣ ጽላት በሚባለው ቃልም ልጠራ አይገባም፤እንደ ግዕዙም እንደ ዓማርኛ ቋንቋም እላለሁ ለመጠራት ብቁ አይደለም እላለሁ ።
[1].Bible strong Dictionary
[2].ኪዳኔ ወልደ ክፍሌ መዝገበ ቃላት ወሐድስ
#ተባረኩ
እድሉ ዮሐንስ ጋምሳ (ደቀመዛሙርቱ)
Comments
Post a Comment