ካህናት ነን
"ካህናት ነን "
ብዙ ግዜ እናስተምራለን እንጂ አንቀበለውም #በተለያየ_ትምህርቶች_ላይ_አስተያየት_ግሳጼ በተለይ ለታዋቂ 'አገልጋዮች' /ሰዎች/ ስቀርብ ቃሉን መቀበል አንወድም።
ይህንን ቃል "አማኝ ሁሉ አገልጋይ አይደለም" ለሚሉ ሰዎች ለመከራከያነት ከመጠቀም ውጪ እኛው ራሳችን ይህንን ቃል አንቀበለውም።
አንድ አስተማሪ ስገሰጽ "አንተ የምን ቤት ነህ!?" ፣ "ቁጭ ብለ በሚሰራው ላይ መናገር ብቻ! ወሬኛ! " ፣ "እስኪ ምን ሰርተሃል!?" ፣ "እሱ ያስተምራል አንተ ማንን አስተምረ ታውቃለህ !?" የሚሉ ሃሳቦች ይነሳሉ ።እነዚህ ሃሳቦች ቃሉን በጥንቃቄ ካለማወቅ የመነጩም ናቸው ።ምክንያቱም ቃሉ የሚለው ፦
“የእግዚአብሔር ቃል በሙላት ይኑርባችሁ፤ #በጥበብ_ሁሉ_እርስ_በርሳችሁ_አስተምሩና_ገሥጹ፤ ”(ቆላስይስ 3፥16) ፣ የሚል ነው።
*የቃሉ እውነታ የሚያሳየው አማኞች ሁሉ አገልጋዮች ስለሆኑ ፣በጥበብ ሁሉ እርስ በእርስ እንደጸጋቸው የሚያስተምሩ ፥ የሚገስጹም ፥ እንደሆኑም የሚገልጽ ነው።ስለዚህም የአስተማሪነት ፀጋ ያለውን ወይም የመጋቢት ፀጋ ያለውን ለመገሰጽ የግድ የእሱ ዓይነት ፀጋ አያስፈልግም ።"እርስበእርስ" እንደሚል መጋቢውን - መካሪ ልገስጽ ይችላል ፣አስተማሪውን -እውቀትን የመግለጽ ጸጋ ያለው ልገስጽ ይችላል ደግሞም ሁሉንም መንፈስን መመርመር የሚችል ልመረምር ይችላል ።
*ስለዚህም አንድን አስተማሪ ለመገሰጽ በብዙዎች ዘንድ የሚታወቅ ፐጅ ወይም ገጽ ወይንም የመድረክ አገልግሎት ሳይሆን የሚያስፈልገው "በክርስቶስ ካህን" መሆን ብቻ ነው የሚያስፈልገው ።
ስለዚህም ተግሳጽ ለቀረበላቸው ሰዎች "ተግሳጹ ትክክለኛ ነው!? ወይስ አይደለም !?" ብላችሁ በቃሉ መሠረት መርምሩ እንጂ የስንፍና ቃል አትናገሩ ።(አልፎም የሚትሳደቡ ሰዎች አላችሁ፣ ይገርማል የተቀበላችሁትን ፣በውስጣችሁ ያለውን ያደረውን መንፈስ የሚያሳይ ነው)
እኔ በበኩሌ አማኝ ነኝ ፣
በተሰጠኝ ጸጋ፦አገልጋይም ነኝ ፣
እገስጻለሁ ፣
እገሰጻለሁ ።
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
'ካህናት ነን' የምንለው መቼ መቼ ካህናት ለመሆን ነው!?
"ካህናት ነን" የሚለውን ፈልጥ ላይ ሃሳብ ስሰጥ ይህ ሁለተኛዬ ነው።አንደኛው ላይ ያካፈልኩት << አንድን በብዙዎች ዘንድ የሚታወቅ 'አገልጋይ' ለመተቸት ፣ለመገሰጽ በኢየሱስ መሆን ብቻ ብቅ ነው፤የግድ የእሱ እኩል በብዙዎች ዘንድ የሚታወቅ ፣ብዙ ተከታይ ያለው ሚዲያ አያስፈልግም>> ብዬ ነበር ምክንያቱም በኢየሱስ ክርስቶስ እኔም በተሰጠኝ ጸጋ አገልጋይ ነኝ፤ ካህን ነኝና በማለት።አሁንም ከዚህ ጋር በተያያዘ አንድ ልበል ..
ብዙ ግዜ በመድረክ ላይ የሚታይ አገልግሎት ያላቸውን አስተማሪዎችን ፣መጋቢያዎችን፣ዘማሪዮችን ፣ዲያቆናትን፣ሽማግሎችን ...እንድሁም በልዩ ልዩ አገልግሎት በቤተክርስቲያን የሚተጉቱ ፥ አንዳች ስህተት ከተገኘባቸው ጩኸታችን እንደ አጉል ነው፤ እንዴት እንደዚህ /አገልጋይ ሆኖ/..እንላለን፤በክርስቶስ ያለውን ማንነት ለእርሱ ብቻ አድርገን ።(እንዲያ ማለቱ በራሱ ክፋት የለውም)
በዚያ ልክ ደግሞ ከምዕመናን አብዛኛው ሃገር ጉድ የሚያስብል ነገር ስያደርግና ስሆን ፣ በዘፈቀደ ስመላለስ ስንመለከት ፣ ምንም አይመስለንም ።"እንደው ሰው እንዴት ተበላሸ" እንላለን እንደ ማንኛውም ዓለማዊ ሰው፤በክርስቶስ ያለውን ማንነት በመተው ።(እንደዚያ ማለት በራሱ ስህተት አይደለም)
#ግን
*እኛ አገልጋይ ያልናቸው በተሳሳተ መንገድ ከተመላለሱ ፣ "እሱ እኮ አገልጋይ ነው እንዴት እንደዚህ !?" መባሉ መልካም ነው ።ነገርግን ከምዕመናትም ስናጠፋ ፣ "አገልጋይ ነው እንዴት እንደዚህ!?" ማለት መቻል አለብን የሚል ነው። ምክንያቱም እኛ ሁላችንም በተሰጠን ጸጋ የሚናገለግል ባሪያዎች ነን።ሁላችንም ኢየሱስን በሕይወታችን ለመግለጥ ፣ለመመስከር ፣የተጠራን ፣የተለያየ ጸጋ ያለን አገልጋዮች ነን።
*ኢየሱስን ማሳየት ማስከበር የሁላችን እንጂ ለሆኑ ሰዎች አይደለም!
ስለዚህም 'ሁላችንም አገልጋይ አይደለንም' የሚሉትን ለመቃወም ብቻ ፣ ካህናት ነን ብለን ከመጥቀስ ባለፈ ፣ኢየሱስን በሕይወታችን ለማሳየት እንደተጠራን በድፍረትም መጥቀስ መቻል አለብን።[[ምክንያቱም ፦እንዲያ ብሆን ብዙ ሰው አይሰናከልብንም ]]
እኔ በክርስቶስ ካህን ነኝ፣
በተሰጠኝ ጸጋ አገልጋይም ነኝ፣
እገስጻለሁ ፣
እገሰጻለሁ።
🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱
"ካህናት ነን "
#በዚህ_ቃል_ላይ_ይህ_ሦስተኛዬ_ነው። በእውነት በመዝሙርም እንዲያ እንላለን ፣ በቃልም እንዲሁ። አንዳንደ እንደ መፈክርም ።ግን በእውነት ካህናት ነን ለማለት የሚያበቃውን አውቀናል !?
አምላካችን እግዚአብሔር እንደ ጸጋው ባለጠግነቱ መጠን በቤተክርስቲያን ለአንዳንዶቹን ልሳን መናገርን ፣በልሳን የተነገረውን መተርጎምን...ወዘተ አድርጓል ።
መጽሐፍ ስናገር ሁላችንም ተመሳሳይ ጸጋ ባይኖረንም ግን ጸጋ የሌለው ሰው እንደ ሌለ ይገልጽልናል ።ቃሉ “.. ያ አንዱ መንፈስ እንደሚፈቅድ ለእያንዳንዱ ለብቻው እያካፈለ ያደርጋል።” ( 1ኛ ቆሮ 12፥11) ፣ እንደሚል።
ስለዚህም ካህናት ነን ካላችሁ ፣ጸጋ አላችሁ ማለት ነው። ስለዚህም በቤተክርስቲያን ለቤተክርስቲያን አገልግሎት (ሕንፀት)፣ እግዚአብሔር የምን ጸጋ ነው የሰጣችሁ !?
*ማነኛውም የዳነ ሰው የተሰጠውን ጸጋ አላውቅም ማለት ይችላል እንጂ ጸጋ የለኝም ማለት አይችልም ።ምክንያቱም ይህ እግዚአብሔርን መሸንገል ነው።
*የመልእክቱ ጭብጥ ስንቶቻችሁ ናችሁ ጸጋችሁን የሚታውቁት !? የተሰጠውን ጸጋ ያላወቀ 'አማኝ' በምን ሞራል ነው "ካህን ነኝ" የሚለው !? የሚል ነውና ፤ጸጋችሁን እወቁ!!
🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱
"ካህናት ነን"
#በዚህ ርዕስ ላይ ስጽፍ 4ኛዬ ነው።በቀደም የዳነ ሰው ሆኖ ጸጋ የሌለው የለም።ምናልባትም ጸጋውን ካላወቀ በስተቀር ብለናል።አሁን ደግሞ ጸጋ የተሰጠው ለምንድነው !? የሚለውን እናያለን ።ይህንን ለማየት አንድ ታርክ ከመጽሐፍ ቅዱስ እንመልከት የመክሊቶቹ ምሳሌ ፦
“ለእያንዳንዱ እንደ ዓቅሙ፥ ለአንዱ አምስት መክሊት ለአንዱ ሁለት ለአንዱም አንድ ሰጠና ወደ ሌላ አገር ወዲያው ሄደ።”ማቴዎስ 25፥15
በዚህ ክፍል ላይ ባለ ከአንድ መክሊት በስተቀር ሌሎች ሁሉም እንዳተረፉት ቃሉ ይነግረናል ።እንዲህ በማለት ፦ ማቴዎስ 25
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²⁴ አንድ መክሊትም የተቀበለው ደግሞ ቀርቦ፦ ጌታ ሆይ፥ ካልዘራህባት የምታጭድ ካልበተንህባትም የምትሰበስብ ጨካኝ ሰው መሆንህን አውቃለሁ፤
²⁵ ፈራሁም ሄጄም መክሊትህን በምድር ቀበርሁት፤ እነሆ፥ መክሊትህ አለህ አለ።
²⁶ ጌታውም መልሶ እንዲህ አለው፦ አንተ ክፉና ሃኬተኛ ባሪያ፥ ካልዘራሁባት እንዳጭድ ካልበተንሁባትም እንድሰበስብ ታውቃለህን?
*ይህ ባለአንድ መክሊት የራሱን መክሊት የጣሉቱን የዛሬዎቹን ከአብዛኛው ምዕመናት ይመስላል ። ለነቢዩም፣ ለሐዋሪያው ፣ ለመጋቢው ፣ለአስተማሪው ...እንድሁም ለሁሉም እንደሚያስፈልግ ያላወቀ ፣የራሱን የናቀ ፣ጸጋውንም የተውቱን ይመስላል ።
*አብዛኛው ምዕመናት አገልግሎትን ለመድረክ ሰዎች ትተዋል ፣እኛ የተጠራነው በአንድ ክፍት ቦታ እንደሆነ አናስተውልም።የራሳችንን አናሳድግም በሌሎች አይናችንን ጥለን የሰው ተከታይ ሆነን ቀረን ።ያለእኛ ያለአንዷ መክሊት ቤተክርስቲያን ሙሉእ እንዳማትሆን አናውቅም።
*ወንድሜ የግድ አስተምር ወይም ጻፍ እያልኩ አይደለም ።ግን በተሰጠኸ ጸጋ ማገልገል አለብህ እያልኩ ነው እንጂ።ምክንያቱም ጌታ ይጠይቃሃል። እንደዳንክ ካወክ ጸጋም እንዳለ እወቅ፣ጸጋውንም ካወክ አጥብቀ ሥራ ። በጌታ ፊት ትቆማለህና።
*በጸጋችሁ ምን ያህል አተረፋችሁ !?
ወይም ስንቱን አሰናከላችሁ !?
(እግዚአብሔር ይጠይቀናል ይህንን ያውቋል)
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
"ካህናት ነን"
በዚህ ርዕስ ሥር እስካሁን ከተመለከትነው ልባችሁ እንደተነቃቃ አስባለሁ ።አሁን በመጨረሻው ላይ ግን አንድ ምስጥር እነግራችኋለሁ ። ከዚህ በፊት አካፍየ ነበር "የሙሴ በስም መታወቅ " በሚል ፦
“እግዚአብሔርም ሙሴን፦ በፊቴ ሞገስ ስላገኘህ በስምህም ስላወቅሁህ ይህን ያልኸውን ነገር አደርጋለሁ አለው።”ዘጸአት 33፥17
#እግዚአብሔር ሙሴን በስምህ አውቃለሁ አለ። የተጠራበት ዓላማ /የተሰጠውን ተልዕኮ እግዚአብሔር ያውቃል/ ፤ማትረፋችንንም ይጠብቃል።የእግዚአብሔር ማወቅ እንኳን አይገርምም ማንነቱ ነውና ።ግን ሙሴም የተጠራበት ዓላማ /የተሰጠውን ተልዕኮ / ያውቃል ።ይህ ነው ዋናው ነገር።
እኛ ክርስቲያኖች የቤተክርስቲያን ብልት ነን ።በአንድቷ ቤተክርስቲያን የተሰጠን ተልዕኮ(ጸጋ) ማወቅ እንዳለብን እንገነዘባለን ። የግድ ማወቅ አለብን።
*የቤተክርስቲያን የምድራዊ የተቋም አባላት ብቻ መሆን የለብንም።የቤተክርስቲያን አካላት ልንሆንም ይገባል። አባላቱ ብቻ የሆኑቱ በወረቀት ላይ እና እዚሁ በምድር ላይ ብቻ፣ በሆነ በክርስትና እምነተ ተቋም ውስጥ የሚታወቁ ብቻ ስሆኑ ፣የቤተክርስቲያን አካላቱ ግን በዓለም አቀፋዊቷ ፣በአንድቷ ፣በመንፈሳዊቷ ቤተክርስቲያን ላይም ይታወቃሉ፤ አካልም ናቸው።
<< *በምድር ላይ የአንድ የክርስትና ቤተ-እምነት አባላት ብቻ የሆኑቱ ያልዳኑቱ ናቸው ።እነዚያ መጠራትንም ፣ የተሰጠውን ተልዕኮውን አያውቁም ።ለዚያ ነው የትኛውም ቤተ-እምነት አባል መሆን፣ የመዳን ማረጋገጫ አይደለም የሚንለው።የዳነ ሰው ፣ አካል የሆነ ሰው ፣ ስለሰው ልጅ ነፍስ ያስባል ፣ስለሰው መዳን ይጨነቃል እንጂ የአባላቱን ቁጥር መጨመርን አይደለም ። ያለህበት ተቋም የመዳንህ ማረጋገጫ አይደለም ። >>
ስንቶቻችን ነን እግዚአብሔር የሰጠውን /የሚያውቅልን ማንነት/ የምናውቀው !?
እድሉ ዮሐንስ ጋምሳ
( ደቀመዛሙርቱ )
Comments
Post a Comment