Posts

Showing posts from April, 2022

ነገረ ታቦት

ነገረ ታቦት  መግቢያ  1.የቃሉን ትርጉም  2.እንድሰራ ማን አዘዘ?ለምን ተሰራ?መቼ አዘዘ ? 3.አሰራሩን እና ስለ አሰራሩ የእግዚአብሔር አቋም! 4.ታቦቱ አሁን የት ነው ?  5. በአድሱ ኪዳን የብሉይ ታቦት አገልግሏልን ? 6.በአድስ ኪዳን አሰራሩ እና አጠቃቀሙ የተነገረለት፣ በአድስ መልክ የሚሰራ ታቦት አለን !? 7. የጌታ እራት የምንካፈልበት እቃ "ታቦት" ነውን !? 8. በአድስ ኪዳን አሰራሩ ለየት ያለ ታቦት አለ የሚሉት ለምን የብሉይን ታቦት ይጠቅሳሉ !? 9.በሰማይ ታቦት አለን !? የተኛው ነው (የብሉይ ነው ወይንስ የአድስ ኪዳን ታቦት ) ምን ማለት ነው በራሱ !?  10.የመጽሐፍ ቅዱስ ዝምታ ይከበር ! 11. ለቃሉ እና ለቃሉ ጌታ ታማኝ እንሁን ! ............................................                 መግቢያ  በዚህ ርዕስ ዙሪያ ለመጻፍ ያነሳሳኝ የከበረውን የእግዚአብሔርን ታቦት ነገር እንደ ቃሉ እንዲንረዳ እና እንድናውቅ ብሎም ለቃሉ ተማኝነትን ለማሳየትና ለቃሉ መሸነፍን ለማበረታታት ነው። ብዙ ግዜ ብዙ ትምህርቶች ላይ አቋም ይዤ፣ "ተሳስቻለሁ" ብዬ ፣ ከሰው ተምሬ አውቃለሁ ።ቃሉን ሳጠን ፣ ቃሉ ዘምበል ወደ ሚልበት ዘበል ማለትን ተምሬያለሁ ።ለምሳሌ የልሳን ጸጋ የለም የምል አቋም ነበረኝ ፤ትቸዋለሁ ፤ስህተትም ነበር።ይህንን በማድረጌ ተጠቀምኩ እንጂ አልተጎዳሁም ።እንደ ሽንፈት አልቆጥርም፤ቃሉ አሸነፈኝ፤ያስተማሩኝ ይባረኩ።       ትልቁ ችግር ከስህተት አለመማር እና ልብን እልከኛ ማድረግ ነው፤ሞኝነት ነው።ለማወቅ የሚጥር ሰው፣በልቤ ሰፊነት "ቃሉ ግን ምን ይላል?" ፤ "...

የልሳን ጸጋ (የቋንቋ ስጦታ )

  የቋንቋ ስጦታ (የልሳን ጸጋ) ☝ የልሳን ጸጋ ቀርቷልን !? ☝ የተገለጠው ቋንቋ የማይተረጎም ከሆነ ፥ በቤተክርስቲያን [ሳይተረጎም] መነገሩ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ነው ?  ☝ እንዴት እንጠቀም ? ☝ የልሳን ጸጋ በአግባቡ ከተጠቀምን ጥቁሙን ፣ ☝ በቤተክርስቲያን የልሳን ጸጋ በአግባቡ ካልተጠቀምን ጉዳቱ ፣ ☝ የልሳኑ መልእክት ስተረጎም ትክክለኛነቱን እንዴት እናውቃለን !?  ☝ "" አንድ አማኝ በልሳን ጸጋ ባይናገር በመንፈስ ቅዱስ አልተጠመቀም ማለት እንችላለን !? "" _____________________________________ ይህ የቋንቋ ስጦታ በመጽሐፍ ቅዱሳችን ፦"አደስ ቋንቋ ፣ልሳን " ተብሎአል ።ከዚህ በፊት የቋንቋ ስጦታ ወይንም ልሳን የተባለው "ቀርቷል ወይንም አሁንም አለ !?" ብዬ ጠይቄ ነበር።ስለሰጣችሁኝ ሀሳብ አመሰግናለሁ ግን በቂ የሙግት ነጥብ አላገኘሁትም (ቀርቷል በሚሉት ወገኖች )።  እኔ የልሳን ጸጋ አለ ብዬ በአራት ነጥብ ዘግቼ አምናለሁ( ሀሳብ ለመቀበል ነፃ መሆነ ይታወቅ) ።  ቀርቷል የሚሉት ሰዎች የሚያቀርቡትን ነጥቦችን (ከዚህ በፊት ካነበብኩት በራሪ ጹሑፉ "አንቀፀ ብርሃን" የሚል ነው) ላቅርብ ፦  1ኛ. "ልሳኖች ብሆኑም ይቀራሉ 1ቆሮ 13፥8 " ይህንን በመጥቀስ ይህ አንቀፀ ብርሃን የሚለው በራሪ ጹሑፍ "የልሳን ጸጋ ቀርቷል" ብሎ ይሞግታል ።   ይህ ክፍል  የልሳን ጸጋ አሁን መቅረቱን አያሳይም የሚለውን ላቅርብ፦ ፦ ሙሉ ቁጥሩን እንመልከት ።“ፍቅር ለዘወትር አይወድቅም፤ ትንቢት ቢሆን ግን ይሻራል፤ ልሳኖች ቢሆኑ ይቀራሉ፤ እውቀትም ቢሆን ይሻራል።”— 1ኛ ቆሮንቶስ 13፥8 በእርግጥም በዚህ ክፍል ላይ "ትንቢት ...

ጆሮ ያለው ይስማ (የዮሐንስ ራዕይ ም.2-3 ጥናት )

  ጆሮ ያለው ይስማ !!     “በኤፌሶን ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፦ በቀኝ እጁ ሰባቱን ከዋክብት የያዘው በሰባቱም የወርቅ መቅረዞች መካከል የሚሄደው እንዲህ ይላል፦” — ራእይ 2፥1 + በቀኝ እጁ የሰባቱን (የሙሉዑ) ቤተክርስቲያን አገልጋዮች  የበላይ የሆነው  ደግሞም አንድቷን የክርስቶስ ስብስብን  በምድር የሚትወክለዋን ፣ የሚታሳየዋን ፦ሰባቱ (ሙሉዕ ) ቤተክርስቲያን የበላይ ጌታ እንዲህ ይላል።ይለናል ። + " ..መካከል የሚሄደው .."  ያለ ክርስቶስ ማገልገል ወይንም ምዕመን  መሆን የለም።ከአገልጋዮቹ እና ከሕዝቤ ክርስቲያኑ መካከል ያለው ብቸኛ ጌታ ክርስቶስ  ነው።ክርስቶስ  ብቻ ነው ከሽማግሌዎቹ  እና ከምዕመናት ጋር ያለው  ማለት  አብንና ወልድን የሉም ማለት አይደለም ።ሽማግለዎቹ እና ምዕመናት ከፍጡር  ስሪ ሳይሆን ከፈጣሪ  ስሪ ብቻ ናቸው ማለት ነው፥የበላዩ እሱ ብቻ  ነው ማለት ነው፤ጠባቂው እሱ ብቻ ነው ማለት ነው ።ስለዚህም ክርስቶስ ራሱ፣ ብቸኛው መሪ መሆኑን ስገልጽ እንዲህ ይላል ፦". የሚሄደው." ይላል እንጂ የምሄዱት አይልም ።ወይንም የሚሄዱት አይልም( ስለሌላ አካል መሪነት እንደሚናገር)።ይህንን የሚለው "እከሌ ወይም እከልት ባትኖር እንጠፋ ነበር " በማለት ባረፉት ወይም በሕይወት ስጋ ባሉ ሰዎች ስለሚመኩ ሰዎች  የማንቂያ ደወል እንድሆን ነው።እንዱሁም የበላይ ፉጡር  መላእክት እንዳልሆኑ ለማስጨበጥም ነው።ስለዚህ ሙሉ በሙሉ የበላይ ሆኖ የሚቆጣጠረው የሚጠብቀው እንዲህ ይላል ለኤፌሶን ምዕመናንን፦  “ሥራህንና ድካምህን ትዕግሥትህንም አውቃለሁ፤ ክፉዎችንም ...

ማርያምን አትሳደብ !

1.መግቢያ  1.2.ለምን ይሳደባሉ  1.3.የአሮን በትር ናት ? 1.4.'ማርያም' የዓለም መድኃኒት ናት ? 1.5."ዮሴፍን የሚታጽናኝው/የሚታረጋግው/ አንቺ ነሽ"(ው.ማርያም ፤ቅዳሴ ማርያም )   1.6 "አብ በሰማይ አይቶ እንዳንቺ አላገኘምና .." (ራቡዕ ው.ማርያም ቁ.1)  1.7 "አምላክን የወለድሽ እመቤታችን ሆይ ትውልድ ሁሉ አንችን ብቻ ያመሰግኑሻል" (ራቡዕ ው.ማርያም ቁ.2)  1.8 የነነዌ ሰዎች 'በማርያም' ምክንያት ከመጣው መቅሰፍት ተረፉ ? 1.9 ፍጥረት ሁሉ ከመፈጠሩ በፊት 'ማርያም ' ነበረች ? 1.10 "በእውነቱ ስለ  ስለቃልኪዳኗ ነውን?"እያልኩኝ ነው።             ማጠቃለያ                 ዋቢ መጽሐፍት                      ማርያምን አትሳደቡ!  1. መግቢያ   ለምንስ ተቃወምኩ ? በማለት በራሴ በፊት ገፀ ላይ ያካፈልኩትን ሕይወተን ለማስፈር ፈለኩ፦<<  " ብዙዎች ስለእኔ የመሰላቸው ብለዋል " አሁን ግን ግዜው ስለሆነ  ከባለቤቱ እንድትሰሙ ወደድኩ።ሰዎች እኔን የምሉት "ተሃድሶ የሆነው ከካምፖስ ተባረው ነው ፣ ገንዘብ ስለምከፈለው ነው፣ እብዶ ስለሆነ ነው... ነው" ብለዋል ።እውነቱን ማወቅ ለብዙዎች ጥያቄ የሚመልስ እና በልበ ሰፊነት ለምመረመሩት እውነቱ ፤ ነገሩ እንደዚህ ይሆንን ? ለሚሉት  ከሚመስል ነገር በማውጣት ወደ እውነቱ  ያምራል በምል ነው።      ...