ጆሮ ያለው ይስማ (የዮሐንስ ራዕይ ም.2-3 ጥናት )
ጆሮ ያለው ይስማ !!
“በኤፌሶን ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፦ በቀኝ እጁ ሰባቱን ከዋክብት የያዘው በሰባቱም የወርቅ መቅረዞች መካከል የሚሄደው እንዲህ ይላል፦” — ራእይ 2፥1
+ በቀኝ እጁ የሰባቱን (የሙሉዑ) ቤተክርስቲያን አገልጋዮች የበላይ የሆነው ደግሞም አንድቷን የክርስቶስ ስብስብን በምድር የሚትወክለዋን ፣ የሚታሳየዋን ፦ሰባቱ (ሙሉዕ ) ቤተክርስቲያን የበላይ ጌታ እንዲህ ይላል።ይለናል ።
+ " ..መካከል የሚሄደው .." ያለ ክርስቶስ ማገልገል ወይንም ምዕመን መሆን የለም።ከአገልጋዮቹ እና ከሕዝቤ ክርስቲያኑ መካከል ያለው ብቸኛ ጌታ ክርስቶስ ነው።ክርስቶስ ብቻ ነው ከሽማግሌዎቹ እና ከምዕመናት ጋር ያለው ማለት አብንና ወልድን የሉም ማለት አይደለም ።ሽማግለዎቹ እና ምዕመናት ከፍጡር ስሪ ሳይሆን ከፈጣሪ ስሪ ብቻ ናቸው ማለት ነው፥የበላዩ እሱ ብቻ ነው ማለት ነው፤ጠባቂው እሱ ብቻ ነው ማለት ነው ።ስለዚህም ክርስቶስ ራሱ፣ ብቸኛው መሪ መሆኑን ስገልጽ እንዲህ ይላል ፦". የሚሄደው." ይላል እንጂ የምሄዱት አይልም ።ወይንም የሚሄዱት አይልም( ስለሌላ አካል መሪነት እንደሚናገር)።ይህንን የሚለው "እከሌ ወይም እከልት ባትኖር እንጠፋ ነበር " በማለት ባረፉት ወይም በሕይወት ስጋ ባሉ ሰዎች ስለሚመኩ ሰዎች የማንቂያ ደወል እንድሆን ነው።እንዱሁም የበላይ ፉጡር መላእክት እንዳልሆኑ ለማስጨበጥም ነው።ስለዚህ ሙሉ በሙሉ የበላይ ሆኖ የሚቆጣጠረው የሚጠብቀው እንዲህ ይላል ለኤፌሶን ምዕመናንን፦
“ሥራህንና ድካምህን ትዕግሥትህንም አውቃለሁ፤ ክፉዎችንም ልትታገሥ እንዳትችል፥ እንዲሁም ሳይሆኑ፦ ሐዋርያት ነን የሚሉቱን መርምረህ ሐሰተኞች ሆነው እንዳገኘሃቸው አውቃለሁ፤” — ራእይ 2፥2
+ልክ ኢየሱስን ሰዎች፦ "በሥራም በቃልም ብርቱ ነቢይ ነበረ " እንዳሉ በሉቃ 24፥19 ፤የኤፌሶን ምዕመናት መሪም ብርቱ እንደ ነበረ ክርስቶስ ይመሰክራል( ሙሉ በሙሉ ፍጹም ባይሆንም )።ብርቱነቱ ቃሉን በማስተማርና በመኖሩ ፤ የራሱን ሳይሆን የጌታ ደቀመዛሙርቱን በማፍራቱ እንደሆነ ይረዷል።ደግሞም ምዕመናትን ለመጠበቅ ስለ ሚደክምም ነው ።
+ትዕግስተኛ ነው።ስለ ስሙ የሚሰደብ ፣ዋጋውን ከጌታ እንደሚቀበል፣ እንደተቀበለ ሰውም በእምነት ተስፋ የሚያደርግ ፣በክፉ ሰዎች መካከል ስሙን በመጠበቅ የሚጸና ፣ደግሞም ከክፋታቸው ስመለሱ በሙሉዑ ልብ በምህረት የሚቀበል ፣ የሚደክመውም የጠፉት እንድመለሱ፤ ያሉት እንድጸኑ እንደሆነ ይረዷል።የኤፌሶን ቤተክርስቲያን አገልጋይ ሕይወት ላይ የሚታይ የመንፈስ ፍሬ አለ/ው ።
+ "ክፉዎችን አልታገሰም" ማለትም ምዕመናትን በሃሰተኛ ትምህርትና ኢ-መንፈሳዊ በሆነ ልምምድ ለመበከል የሚመጡትን ባለመመሳሰል፤ ባለመታከት በመቃወም ምዕመናትን ጠብቋል ። እንግዲህ፦ ሃሳዊያንን በፍጹም ልታገስ አልቻለም ማለትም በጓደኝነት ፣በዘር ፣በዝምድና እንድሁም ያለመፍራት ብርቱ ትግል በመታገል ሃላፊነቱን የተወጣ አገልጋይ ነው።
+ "ሐዋሪያት ነን" ሐዋሪያ ሳይሆኑ ነን የሚሉትን በማወቅ ፤ምዕመናትን በማሳወቅ፤ ሃሰተኛ መሆናቸውን የደረሰ ብርቱ ባሪያ ነው።
+"መርምረህ " ሀሰተኞች የሆኑትን ያወቀበት መንገድ ምርመራ ነው። “ወዳጆች ሆይ፥ መንፈስን ሁሉ አትመኑ፥ ነገር ግን መናፍስት ከእግዚአብሔር ሆነው እንደ ሆነ መርምሩ፤ ..።”— 1ኛ ዮሐንስ 4፥1 ቃሉ እንደ ሚል።ሳይታክት ከማን እንደሆኑ? ምነጩን በመመርመር፤ እውነት ሳይሆን የሚመስል ነገር እንደሆነ ያሳየ ፤የአግዚአብሔር ቃል " መርምሩ "የሚለውን ትዕዛዝ በመቀበል በመርመመር ለቃሉ የተገዛ ፤የሚኖር ባሪያ ነው።
+ስለዚህ ጌታ ለባሪያው እንዲህ ይላል ሰዎች ባያውቁም ዋጋ የሚሰጠው "እኔ አውቃለሁ" በማለት ተስፋውን እጥፍ ድርብ አድርጎለታል ።ዛሬም እንዲህ ነው እያልኩ እንደሆነ ይረዷል።
“ታግሠህማል፥ ስለ ስሜም ብለህ ጸንተህ አልደከምህም።”
— ራእይ 2፥3
+በትዕግሥት ያለ መታከት ለስሜ ሳትደክም አገልግለሃል።በቃልም በስራም መስክረሃል። አውቃለሁ።
“ዳሩ ግን የምነቅፍብህ ነገር አለኝ የቀደመውን ፍቅርህን ትተሃልና።”— ራእይ 2፥4
+ጌታ ስናገር በማሳሳብ ነው። ምንም እንኳን በዕቅበት ስራው(በምርመራው ) ፣በምህረት በመቀበሉ(በትዕግሥቱ ) የተመሰከረለት ብሆንም ፥አሁን ግን ይህንን አገልግሎት ነበረ አስብሏል፤ በመተዉ።ስለዚህም ጌታ ወደ ቀድሞ ፍቅር ማለትም ለምዕመናት ሕንፀት( እንዳይጠፉ ያለመታከት ወደሚትሰራው በጎ ስራ) ተመለስ! እያለው ነው።ሃሳዊያንን የሚያጋልጠው ለምዕመናን ካለው ፍቅር የተነሳ እንደሆነ ይረዷል።ፍቅሩ ለምዕመናትም ለክርስቶስ ጭምር ስላለውም ነው።የእግዚአብሔር ቃል እንዳይነካ ፣በአሕዛብ ዘንድ እንዳይሰደብ የሚተጋ ሀሉ ለምዕመናንን እና ለክርስቶስ ፍጹም ፍቅር እንዳለው/ላቸው ያስተውሏል ።
“እንግዲህ ከወዴት እንደ ወደቅህ አስብ ንስሐም ግባ የቀደመውንም ሥራህን አድርግ፤ አለዚያ እመጣብሃለሁ ንስሐም ባትገባ መቅረዝህን ከስፍራው እወስዳለሁ።” ራእይ 2፥5
+"ከወዴት እንደ ወደቅህ አስብ" ጌታ የመጀመሪያውን እና አሁን ያለበትን ሕይወት ራሱ እንድመዝን ይጋብዘዋል።ስለዚህም አስብና "ንስሐ ግባ" እያለው ነው።በእርግጥ ከዚህ የሚንረዳው የቀድሞውን አገልግሎት መተውን ነው እንጂ ምን እንደተካና አድስ ነገር ምን እንደጀመረ አናውቅም ።ጌታ ለሕይወቱ ግን አሰላስሎ ከራሱ እንደተለየ እየገለጸው እንደሆነ ይናገራል ።ምንም ብተካ ባይተካ የቀድሞውን አገልግሎት መተው በራሱ ከእግዚአብሔር መለየት እንደሆነ ይረዷል።
+"..የቀደመውንም ሥራህን አድርግ.." ያለመታከት በቃልም በስራም ብርቱ በመሆን መንፈስን በመመርመር በማወቅ፣ በማሳወቅ ፣በማጋለጥ ፤ምዕመናንን በመጠበቅ ፤የሚመለሱትን በምህረት በመቀበል ለክርስቶስ እና ለምዕመናት ያለህ ፍጹም ፍቅር ወደ ሚታሳየው ሥራህ ተመለስ!!።ይህ ስራ የእግዚአብሔር ፈቃድም ትዕዛዝም እንደሆነ ይረዷል።
+"..አለዚያ እመጣብሃለሁ .." ፈቃደንም ትዕዛዘን ባትቀበል ቁጣ አመጣለሁ አለ።እንግዲህ ፦ለዚህ አገልግሎት ምን ያህል ጌታ እንደሚሳሳ ይረዷል።አትታከቱ።በቃልም በስራም በርቱ።ያውቃልና ።
+"..ንስሐ ባትገባ መቅረዝህን ከስፍራው እወስዳለሁ ።" ንስሐ ብትገባ፣ ብትመለስ ፦ምህረት አደርጋለሁ ግን ንስሐ ባትገባ፣ባትመለስ በቅጽበት፦ በፍርድ እመጣብሃለሁ ።
“ነገር ግን ይህ አለህ፤ እኔ ደግሞ የምጠላውን የኒቆላውያንን ሥራ ጠልተሃልና።”— ራእይ 2፥6
+ምንም እንኳን የቀድሞውን አገልግሎት ቸል ብትልም አንድ በጎ ነገር አለው ይላል ጌታ ።ይህም የኒቆላውያንን ሥራ (ተመሳስሎ መኖርን) ጠልተሃልና ።ነቆላዊያን " ክርስቲያን ነን "ብሉም ክርስቲያን ያይደሉ ፤መናፍቃን ናቸው ።ሰዎችን ለማስተማር ፣ለመስበክ ፣እውነቱን ለመግለጽ ሳይሆን ከእነርሱ ጋር የእነርሱን ''የአሕዛብ አምላክ ''እያመለከ መኖርን የሚኖሩ ናቸው ።"እኔ የሚጠላውን አንተም ጠልተሃልና በጎ ነገርን አይቻለሁ " ይላል ጌታ።ስለዚህም እርሱ የሚጠላውን መጥላት ያስወድደናል በጌታ።ነፃ ብንሆንም ነፃነታችን መልካሙን ለማድረግ ነው።እንደ ፈቃዱ ብቻ ለመኖር እንጂ እንደ ፈቃዳችን ለመኖር አይደለም ።
ስጠቃለል!
“መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚለውን ጆሮ ያለው ይስማ። ድል ለነሣው በእግዚአብሔር ገነት ካለው ከሕይወት ዛፍ እንዲበላ እሰጠዋለሁ።” — ራእይ 2፥7
+ ከዚህ የሚንማረው ነገር፦ ፍጹም እስከ ሚንሆን ድረስ ሳንታክት (በድክመት ልንታክት እንችላለን ) በቃልም በስራም ብርቱ አገልጋይ ሆነን ማለፍ እንዳለብን ነው።ዛሬ ዛሬ እንዲህ ያለ አገልግሎት (መንፈስን የመመርመር አገልግሎት) ፦ቅንዓት ፣ክብር ፍለጋ፣ያለ አቂም መንጠራራት ፣ ካለማወቅ የተነሳ እንደሆነ ፣ ስህተት ፈላግ በማድረግ ፣አሳዳጅ፣ማስተማር የማይችል ...ወዘተ በመባል ያሉትን የቤተክርስቲያን ቅን አገልጋዮችን በሚያሸማቅቁበት ግዜ ላይ ነው ያለነው ።ለዚህም ነው ማሰብ የምችል ሁሉ ማሰቢያውን በመጣል ትፎዞ የሆነው ።
ምንም እንኳን በሰዎች የሚያሰደብ ብሆንም በጌታ የተወደደው ነው። የፍቅር መገለጫ የሆነ አገልግሎት ነው።ቃሉ "መርምሩ" ካለን እንደ ቃሉ መመርመር እንጂ ሳናላምጠው መቀበል ወይንም ከእኛ ጋር ስለከረመ ትክክል ነው ማለት የለብንም፤ተወራርሶ የመጣ ብሆንም በአንተ ግዜ እንድፈርስ ያለመታከት በቃሉ ሚዛንነት በመርመር ለምዕመናንን እና ለክርስቶስ ያለህ ፍቅር ልታሳይ ይገባል ።
ምንም መንፈስን በመርመር ሃሳዊያንን በማውቅ ማሳወቅህን በለዘብተኛነታቸው ካለ ስም ስም ብሰጡ በጌታ የተወደደ እንደሆነ ግን እወቅ፤ይህም ብቻም ሳይሆን እንደዚህ የሚሉቱ ሁሉ ለቃሉ የማይታዘዙ ቸልተኛ የሆኑ ፣የእግዚአብሔር ቃል እውነታቸው ያልሆናቸው መሆናቸውን ተገናዘብ።ደግሞም ለክርስቶስም ለምዕመናትም ጥላቻ ያላቸው እንደሆኑ እወቅ።
በተለያየ ምክንያት በቃልም በሥራም የሚትመሰክረውን ብትተወው ጌታ ፈጣን ፍርድ እንደሚያመጣ አስተውል ።በንስሐ ከተመለስክ እሱ የወደደውን ሁሉንም በመውደድ ፣እሱ የሚጠላውን ሁሉንም በመጥላት ብትጠላ፣ፈቃዱን ብታደርግ ቶሎ ብሎ በምህረት እንደሚቀበል በመረዳት አትታክት።
መንፈስን በመርመር ሃሳዊ መሆናቸውን ያወቅንባቸው (የደርስንባቸው)፦ብመለሱ በምህረት እንደገና መቀበል እንዳለብን እንረዳለን ።ይህ ማለት ሙሉ በሙሉ ከሃሳዊነት መመለስ እንጂ የሆነ ሰዎችን በንግግር ስህተት አስቀይመዋለሁ ማለት አይደለም ።ይህንንም የንግግር ግድፈት በምህረት መቀበል መልካም ነው።የሚናወራው ግን ስለ ስሁት ትምህርት ነው።ማለትም ከምንጩ መመለስ ይጠበቃል ።ምህረትም ማድረግ የመንፈስ ፍሬ ምልክት ነው።
በአጭሩ ጌታ በተለያየ መንገድ እየተገለጠ ለሰዎች ማስተላለፍ የፈለገውን አስተላልፏል ፦በመላእክት አራያ ፣በሰው፣በፍጥረታት ..ወዘተ።ጌታ ስገለጥ የሚገለጠው ለማሳወቅ በፈለገው ዓላማ አንፃር እንደሆነ ይረዷል።ለምሳሌ ለኤፌሶን ቤተክርስቲያን ባለችበት ሁኔታ ተገልጧል። መልእክትም ስያስተላልፍ የሁሉም( የመሪዎችም የምዕመናትም) እያንዳንዷን ነገር የማውቀው በመካከላቸው ያለሁት እኔው ነኝ በማለት ነው።እሱ የበላይ ነው።በመካከላችሁ ያለሁትም እኔው ነኝ።ስለዚህም ያላችሁበት ሁኔታ ከእኔ የራቀ አይደለም ። ሙሉዕ ስልጣን አለኝ ።ያለእኔ የላችሁም ። ሙሉ ስልጣን፤ ሙሉ እውቀት፤እናንተም ሙሉ በሙሉ የእኔ እንደሆናችሁ አውቃችሁ ጥርዬን ተቀብላችሁ ተመለሱ የሚል ነው።ከጸናችሁ መና አይሆንባችሁም ።ስለዚህም ጽኑ የሚል ነው።ሃሌ ሉያ።
ጆሮ ያለው ይስማ (2)
“በሰምርኔስም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ። ሞቶ የነበረው ሕያውም የሆነው ፊተኛውና መጨረሻው እንዲህ ይላል፦” — ራእይ 2፥8
+ጌታ ራሱን ስያስተዋውቅ ፈጣሪነቱን በመግለፅ ነው፥ጅማሮ የሌለው መጀመሪያ ፣ፍጻመ የሌለው መጨረሻ ፤ዘላለማዊ ነኝ በማለት ነው።ስለዚህም ሰው የሆነ አምላክ ፈጣር ኢየሱስ ክርስቶስ እንዲህ ይላል፦
“መከራህንና ድህነትህን አውቃለሁ፥ ነገር ግን ባለ ጠጋ ነህ፤ የሰይጣንም ማኅበር ናቸው እንጂ አይሁድ ሳይሆኑ፦ አይሁድ ነን የሚሉት የሚሳደቡትን ስድብ አውቃለሁ።”— ራእይ 2፥9
+"መከራህንና ድህነትህን አውቃለሁ.." ስለ ስሜ እየደረሰ ያለውን ስቃይህንና ድሃ መሆንህን አውቃለሁ ።
+"..ነገርግን ባለጠጋ ነህ.." ሁሉ የእርሱ የሆነ አምላክ ስላለክ ባለጠጋ ነህ።የማይጠፋው ዘላለማዊ ሰማያዊ በረከት ስለተባረክ ባለጠጋ ነህ።የክርስቶስ መሆን የምድር ባለጠግነት ማግኘት አይደለም ።
+"አይሁድ ሳይሆኑ፦አይሁድ ነን .." እንዚህ በዘር አይሁዳውያን ናቸው ።ግን ጳውሎስ በሮሜ መልእክቱ እንገለጸው አይሁዳውነት በዘር በመወለድ ሳይሆን በልብ በመገረዝ የእግዚአብሔር ፈቃድ በማድረግ ነው ሮሜ 2፥29።እነዚህ የእግዚአብሔር ልጆች ነን ይላሉ ግን የሰይጣን ማህበር(ልጆች) ናቸው ።"ነን" በማለት ሳይሆን በመሆን ነው።መሳደብ የሰይጣን ልጅነት እንጂ የእግዚአብሔር ልጅነት እንዳልሆነ ይረዷል። ግን ጌታ አውቃለሁ ይላል ።
“ልትቀበለው ያለህን መከራ አትፍራ። እነሆ፥ እንድትፈተኑ ዲያብሎስ ከእናንተ አንዳንዶቻችሁን በወኅኒ ሊያገባችሁ አለው፥ አሥር ቀንም መከራን ትቀበላላችሁ። እስከሞት ድረስ የታመንህ ሁን የሕይወትንም አክሊል እሰጥሃለሁ።”— ራእይ 2፥10
+ "መጀመሪያም ስለስሜ እየተጠላህ ነው" ፤አሁንም ፅና።ከስድብ ከሞራል ጉዳት ያለፈ የእስር ፈተና ይመጣል ።ይህንን በፅናት ተወጣ! ስሜን ሳትክድ ፀንተህ ቁም!። እስከመጨረሻው ፅና!! በመጨረሻም እሸልማለሁ።የሚል ነው።
ስጠቃለል !!
በዚህች ቤተክርስቲያን ላይ ጌታ ራሱን ስገልጽ፦ በሞት ላይ ስልጣን ያለኝ " እኔው ነኝ" በማለት ነው።ምክንያቱም ከፊት ከሚጠብቃቸው መከራ አንፃር አትፍራ/ሩ ለማለት ነው።አንድ ቤተክርስቲያን እንደ ቤተክርስቲያን የክርስቶስ ብቻ ከሆነች በትንሹ ፦መከራ ፣ሞራልን የሚጎዳ፣ የፊት ግርፋት ፣የሚታስተናግድ ናት ።ክርስቲያን ባልሆኑ ሰዎች ፣ ነገርግን 'ነን' በሚሉት ሰዎች ማለትም ከቅርብ አስመሳይ ወንድድሞች የሚደርስባቸው መከራ ቀላል አይደለም።ይህንን በመቻል በመጽናት የሚቆሙ ከሆኑ ፦ከዚህ በላይ የሆነ አካላዊ ጥቃት( እስከሞት ድረስ የሚያደርስ ፈተና) እንደሚመጣ እንገነዘባለን ።መከራ ስለኢየሱስ ስም ብቻ ማለትም ከእኛ እንዝላልነት ያልሆነ የሚመጣ ከሆነ የጌታ ፈቃድ ነው።የእምነታችንም ፈታና እንደሆነም እንረዳለን ።እንዲህ ያለህ ፈተና የሚመጣው ያለ ዕድፈት በሚመላለሱ ላይ ብቻ እንደሆነ ይረዷል።ኤፌሶንን ብንመለከት መከራ ይመጣል አላለም ።ምክንያቱም የክርስትና ፈተና ለመምጣት የግድ ያለ ሕይወት ነቀዝ መቆም ያስፈልጋል ።በዚህ ዘመን "ክርስቲያን ነን" የሚሉት ባይበረከቱ መከራ ይበዛ ነበር።
ኢኮኖሚካልህ ድሃ ሆኖ እያለ፦ ሁሉ የእርሱ የሆነ ጌታ ግን "ሀብታም ነህ" ይላል።ሚናልባት ድህነት እንደየሃገሩ ይተረጎማል በኢኮኖሚስቶች የተባለውን እንዳለ ሆኖ ክርስቲያን እንደየሀገሩ ድሃ ሆኖ እንኳን በክርስቶስ ሀብታም ነው ማለት ነው።ጌታ ድህነቱን በማየት "ቁስ ይሞላልሃል አላለውም"።ነገርግን በዚህ መከራ ላይ ለላ መከራ ይመጣልና ፅና ነው ያለው ። ክርስቶስ ትኩረቱ፦ የሚያልፈው ሳይሆን የማያልፈው ስለሆነ ከየትኛውም ቁስ ብልጫውን እያሳየ ነው። አንድ ሰው የኢኮኖሚካል ድህነት " ልቀቀኝ ቁስ ና ሀብት ና " ብሎ ብጸልይ የጌታ ፈቃድ እንዳልሆነ ይረዷል።
ስለዚህም እንደ ፈቃዱ የቆመች ቤተክርስቲያን ብቻ ትፈተናለች ።ድሃ ብትሆን ሀብታም የእግዚአብሔርን ፈቃድ በመከተሏ፣ በማድረጓ ብቻ፦ የክርስቶስ እንደሆነች እንረዳለን ። ሁሉም የጌታ ነው። የጌታ ፈቃድ ሁሉንም መስጠት ሳይሆን ለነፍሳችን የሚጠቅመውን መስጠት እንደሆነ እናስተውላለን ።
በዚህ አጋጣሚ " መከራ ና" ብለ የሚታመጣው እንዳልሆነ ይረዷል።አንድ ሰው ከእግዚአብሔር ፈቃድ ወጥቶ የራሱን የሚድራዊ ምኞት ቁስ እያሯሯጠ ያመጣው መከራ፦ የክርስትና መከራ አይደለም ።ከራስ ምኞት የተነሳ የመጣ እንጂ።የራስ ምኞት ችግር ሆኖ ያመጣው ውድቀት እንጂ ፈተና አይደለም ።ምክንያቱም “ማንም ሲፈተን፦ በእግዚአብሔር እፈተናለሁ አይበል፤ እግዚአብሔር በክፉ አይፈተንምና፤ እርሱ ራሱስ ማንንም አይፈትንም።” — ያዕቆብ 1፥13።የእግዚአብሔር ፈቃድ ያልሆነውን ጸሎት በመጸለይ እግዚአብሔር መፈተን እንደሆነ ያስተውሏል።
የእግዚአብሔር ፈቃድ ሳይውቁ እግዚአብሔርን መለመን እግዚአብሔርን መፈታተን እንደሆነ እንረዳለን ።በዚህ ቤተክርስቲያን ያለው ችግር ድህነት ነው ። "ሀብት ና " ብሎ እንድጸልይ መንገድ አልከፈተም ጌታ ።የሚልቅ መከራ ይጠብቃል አለ እንጂ።መከራ ውስጥ ስለሆነ "መከራ ና" አላለም ።እንዲህ ማለት መከራ ያልደረሰበት ለምን እንደሆነ ካለማወቅ የተነሳ ነውና።መከራ ባትወድም እንደ ፈቃዱ ብቻ ስትመላለስ ይመጣል እንጂ "ና "አትለውም።"ና" የሚትል ከሆንክ ካለማወቅ የተነሳ እንደሆነ እወቅ።ከፈቃዱ እንደወጣም እወቅ።ደግሞም ጌታን አንተን ሳያስተካክል ሳይጠርብ ፈትነኝ በማለት በክፉ እየፈተንክ እንደሆንክ እወቅ ።ስለዚህ ጌታ ያለ ፈቃዱ የሚመላለስ ሰውን አይፈትንም።ያለፈቃዱ የሆነ ጸሎት በክፉ እኛን የማይፈትነውን ጌታ በክፉ መፈተን እንደሆነ አውቃችሁ በክፉ አትፈትኑ።
“መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚለውን ጆሮ ያለው ይስማ። ድል የነሣው በሁለተኛው ሞት አይጐዳም።” ራእይ 2፥11
ጆሮ ያለው ይስማ (3)
“በጴርጋሞንም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፦ በሁለት ወገን የተሳለ ስለታም ሰይፍ ያለው እንዲህ ይላል፦”— ራእይ 2፥12
+ለዚህች ቤተክርስቲያን ጌታ ራሱን ስገልጽ ቤተክርስቲያንቷ ባለችበት ሁኔታ አንፃር ፦ቅን ፈራጅ መሆኑን በመግለጽ ነው።ይህም መለኮታዊ ፍርድ ያመለክታል ።
“የሰይጣን ዙፋን ባለበት የምትኖርበትን አውቃለሁ፤ ስሜንም ትጠብቃለህ፥ ሰይጣንም በሚኖርበት፥ በእናንተ ዘንድ የተገደለው የታመነው ምስክሬ አንቲጳስ በነበረበት ዘመን እንኳ ሃይማኖቴን አልካድህም።” — ራእይ 2፥13
+ሰይጣን በሚመለክበት ፣ብዙዎችን መኖሪያ ባደረገበት ፣ታላቅ መከራ እያለ ፦ስሜን አልካድክም፤ እንዲህ ባለ ሁኔታ ፣ቦታ እንደሚትኖር አውቃለሁ ።
+"..ሃይማኖቴን አልካድህም.." የእምነት ተቋም ሳይሆን ኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝ እንደሆነ አልካደምም የሚል ነው።ሃይማንቴ ማለት ተቋም ብሆን ኑሮ በዚያ ሰዓት የነበረ የእምነት ተቋም ይኖር ነበር።ጌታም ሃይማኖቴን (ኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝ ነው) አይለውም ነበር።ሃይማኖቴን እንጂ ተቋመን አይልም ።ወይንም ሃይማኖታችሁ አይልም።ሃይማኖት ስንል መሠረታዊ ትርጉሙ፦እምነትን መግለጽ(outward expression )ማለት ነው።ስለዚህ "ኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝ ነው" የሚለውን ሃይማኖቱን(ውጫዊ ግላጠ)አልተወም የሚል ነው ።በእግሬ መንገዱ በተቋም መሰንበትን ከመጽናት ጋር አይገናኝም እያልኩ እንደሆነ ይረዷል።
“ዳሩ ግን ለጣዖት የታረደውን እንዲበሉና እንዲሴስኑ በእስራኤል ልጆች ፊት ማሰናከያን ሊያኖርባቸው ባላቅን ያስተማረ የበልዓምን ትምህርት የሚጠብቁ በዚያ ከአንተ ጋር ስላሉ፥ የምነቅፍብህ ጥቂት ነገር አለኝ።”— ራእይ 2፥14
+ "ችግር እኮ የለውም" በሚል ሰበብ የራሳቸውን የሰይጣን አምልኮ ማስገባት ቀስ በቀስ ቦታቸውን እንድቀይሩ ያደርጋል ማለትም ክርስቶስን እንድተው የሚያደርግ የሰይጣን ዘዴ ነው።
+"..በዚያ ከአንተ ጋር ስላሉ.." እነዚህ ሀሳዊያን አብሮ ከክርስቶስ ቤተክርስቲያን ጋር መሆናቸው ጌታ አልወደደም ።ምክንያቱም አብሮ ካሉ አብሮ ቀላቅለው ያመልካሉ ፤ቀላቅሎ ካመለኩ ልባቸው ይሸፊትና ይሰናከላሉ ።የሰይጣን ዜድ ስለሆነ ጌታ ለቤተክርስቲያኒቱ የንስሐ ጥር እያቀረበ ነው።አብሮ ተደምሮ ተቻችሎ ማምለክ የለምና።አምላካችን ብቻውን ይመለካል።ጌታ ተመሳስሎ መኖርን ይጸየፋል ።ውግድ ማለት ያስፈልጋል ።
+በለዓም የሚከተለው ስድብና ሴሰኝነትን ነው።ይህንን እግዚአብሔር ይጸየፋል ።
“እንዲሁ የኒቆላውያንን ትምህርት እንደ እነዚህ የሚጠብቁ ሰዎች ከአንተ ጋር ደግሞ አሉ።” — ራእይ 2፥15
+ ኒቆላውያን ፦ተመሳስሎ ከሰይጣን አመላክዎች ጋር የሚኖሩ ናቸው ።ችግር የለውም የሚሉ ናቸው ።ኒቆላዊያነትም በለዓምነትም የሰይጣን ዜደ ናቸው እንጂ ከሁለቱ አንደኛው ይሻላል አያስብልም ።"ከዝንጆሮ ቆንጆ አይመረጥም" እንደሚሉ ጌታ እንደሚጸየፍ መጸየፍ የግድ ያስፈልጋል ።
“እንግዲህ ንስሐ ግባ፤ አለዚያ ፈጥኜ እመጣብሃለሁ፥ በአፌም ሰይፍ እዋጋቸዋለሁ።” — ራእይ 2፥16
+ ኤፌሶን ቤተከርስቲያንን፦" የቀደመው ፍቅርህን ትተሃል "ብልም የቀደመውን አገልግሎታቸውን መተዋቸውን እንደሆነ ስገልጽ አይተናል ።ለጴርጋሞን ቤተክርስቲያን ግን ጌታ ራሱ እንድያሰላስል አልጋበዘም።ቀጥታ ጉድለታቸውን በመናገር የንስሐ ጥር አቀረበ ።
ስጠቃለል !!
"ለነ ክርስትያን ነን" ባዮች ባለመታለል ፦ልብን ፣ኩላልትን ፣ቅልጥም እመረምራለሁ በማለት ቤተክርስቲያኗ ባለችበት ሁኔታ ራሱን ገለጸ።ስለዚህ ማን እንደ ፀና እና እያስመሰለ እንዳለ ፦" ማን ስመ አማኝ እንደሆነ እና እንዳልሆነ ለይቼ አውቃለሁ "እያለን ነው።
እነዚህ የበለዓምን ትምህርት የሚከተሉ ለአሕዛብ አማልክት የተሰዋውን መብል ይባላሉ ። መስዋዕት የቀረበ መብል ሐዋሪያት፦ ማንም እንዳይበሉ ይከለከላሉ ሐዋ15፥29 ።ምክንያቱም ለሰይጣን የቀረበ ምስጋናና ፍቅርን የሚያሳይ መብል ስለሆነ ይህንን መካፈል ከሰይጣን ጋር ሕብረት ማድረግ ነው።ይህን ማድረግ" ችግር የለውም" በማለት ሰይጣንነቱን አምላክ ማድረግ ነው።ቀላቅሎ ማምለክ ነው።የሰይጣን መግቢያ ዜደም ነው። ሁሉም የሚንበላው መብል፦ ለእግዚአብሔር መስዋዕት የቀረበ መብል እንዳልሆነ ሁሉ፤ ሁሉም የአሕዛብ ሰዎች መብል፦ ለሰይጣን የቀረበ መብል አይደለም ።ዋናው ችግር ከአሕዛብ ጋር መብላት ሳይሆን ለአምላካቸው የተሰዋውን መብላት ነው።ከአሕዛብ ገዝቶ ፦መብላትና መጠቀም ሳይሆን ከእነርሱ ጋር ቁጭ ብሎ ለመስዋዕት የቀረበውን እየበሉ በመለማመድ መሸፈት ነው።አትብሉ የሚለው ቃል የታመነ ነው።
መብል ቅዱስ አያደርግም ።መብል እርኩስም አያደርግም ።ጉዳዩ ከመብሉ ወይንም ከሚበላው መብል አይነት ሳይሆን ክርስቶስን ቸል ስለማለት ነው።በሰይጣን አጃንዳ ስሪ ስለመውደቅ ነው።የተኛውንም ቁስ ሆነ መብል ገዝተን መጠቀም እንችላለን ።ግን የተሰዋውን ከእነርሱ ጋር "ለጤናችን" እየተባባልን አምላኮቻቸውን ማምለክ ነውር ነው።የአምላኮቻቸውን ፍቅር ምስጋና በመቀበል ሕብረት ማድረግ እግዚአብሔርን መተው ነው።
መብል መካፈል ከሚታደርጉት ዓላማ አንፃር ማየት ጠቃሚ ነው።ምክንያቱም ወንጌል በዘመናቱ እንደየዘመኑ ይሰበካል።ዓላማችሁ ለመስበክ ከሆነ መልካም ነው ።ግን ለመስበክ ብላችሁ ስትጣጣሩ ሌላኛው ደካማ ወንድማችሁ ባለማወቅ እንዳይሰናከል በመጠንቀቅ ይሁን ።መብሉን ስትካፈሉ "የእነሱም ፈጣሪ ነው" ችግር የለውም" በማለት ከሆነ ወደ ጥፋት መሄድ ነው።ስለዚህም አስመሳይነት ልያታልለው የማይችለው ጌታ እንዲህ ይላል ፦
“መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚለውን ጆሮ ያለው ይስማ። ድል ለነሣው ከተሰወረ መና እሰጠዋለሁ፥ ነጭ ድንጋይንም እሰጠዋለሁ፥ በድንጋዩም ላይ ከተቀበለው በቀር አንድ ስንኳ የሚያውቀው የሌለ አዲስ ስም ተጽፎአል።” ራእይ 2፥17 ።አብሮ ያላመለከ ፣አብሮ ለሰይጣን 'ላልዘመረ' ፣የሰይጣን ፍቅር ያልተጋራ፣ያልተቀበለ ፦የሚጠፋውን ሳይሆን የማይጠፋውን ዘላለማዊ መብል ይቀበላል ፥ይህንንም የተቀበለው ብቻ ያውቀዋል ።
ጆሮ ያለው ይስማ (4)
“በትያጥሮንም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፦ እንደ እሳት ነበልባል የሆኑ ዓይኖች ያሉት በእቶንም የነጠረ የጋለ ናስ የሚመስሉ እግሮች ያሉት የእግዚአብሔር ልጅ እንዲህ ይላል፦” — ራእይ 2፥18
+ጌታ ለትያጥሮን ቤተክርስቲያን ራሱን ስገልጽ ፦ሁሉንም መመርመር እንደሚቻለው በመግለጽ ነው።
“ሥራህንና ፍቅርህን እምነትህንም አገልግሎትህንም ትዕግሥትህንም ከፊተኛውም ሥራህ ይልቅ የኋለኛው እንዲበዛ አውቃለሁ።” — ራእይ 2፥19
+ከኤፌሶን ቤተክርስቲያን ጋር ይመሳሰላል በብዙ።ግን በአንድ ነገር አይመሳሰልም ።የኤፌሶን ቤተክርስቲያን ይህንን አገልግሎት መተው ተወች ጭራሽኑ ።ይህች የትያጥሮን ቤተክርስቲያን ግን አልተወችም እንድሁም ከመጀመሪያው የበለጠ እየተጋች ነው።ታድያ እንዲህ ሳትታክት ስታገለግል ሁሉንም መመርመር የሚችለው ጌታ ምን አገኘባት ?
“ዳሩ ግን፦ ነቢይ ነኝ የምትለውን ባሪያዎቼንም እንዲሴስኑና ለጣዖት የታረደውን እንዲበሉ የምታስተምረውንና የምታስተውን ያችን ሴት ኤልዛቤልን ስለምትተዋት የምነቅፍብህ ነገር አለኝ፤”— ራእይ 2፥20
+በአገልግሎት እየደከምም፣ እየተጋም እያለ ጌታ ግን የሚጠላውን ነገር አገኘ።ከቃሉ እንደ ሚንረዳው ልክ እንደ ኤፌሶን ቤተክርስቲያን፦ በትዕግሥት መንፈስን በመርመር የሚትተጋ ፤ነቢይ ነኝ ሐዋሪያ ነኝ እያሉ የሚያታልሉትን በማወቅ እንደሚትያዝ፤ ይህች ቤተክርስቲያንም አገልግሎቷን ሳታቋርጥ የሚትተጋ ናት ።ፍቅሯ አልቀዘቀዘም ።ግን አንድ ነገር ይጎድላታል ጌታ እጅግ የተቆጣባት ።እሱም ነቢይ ሳትሆን " ነኝ "በማለት የሚታሳስተውን ሴትን እያወቀ፦ እንዳላወቀ ፣እየሰማ ፦እንዳልሰማ ማለፉን ነው።ሀሳብ መጨመር አይሁንብኝና ሚናልባት ይህችን ሴት የተዋት ስለፈራት ወይምን ሚናልባት ዝምድና ኖራቸው ወይምን ትፎዞ ስለበዛባት ወይንም ጓደኝነት ልሆን ይችላል ።ከዚህ መልእክት የሚንማረው እንደ ኤፌሶን ቤተክርስቲያን ፦አገልግሎት መተው ታላቁ ቁጣ የሚያመጣ መሆኑን እና እንደ ትያጥሮን ቤተክርስቲያን ደግሞ መርጦ መውቀስ፣ መርጦ ማሳወቅ፣ መቃወም ፤በእግዚአብሔር የከፋ ጥፋት እንደሆነ ጭምር ነው።ማንንም ፣ምንንም ፣መቼም ፣የትም ፣ሳትመርጡ ፣በመርመር፣ በማሳወቅ ፣ምዕመናንን መጠበቅ እንደሚገባን እንረዳለን ።ያለመምረጥ ይሁን ።
“ንስሐም እንድትገባ ጊዜ ሰጠኋት ከዝሙትዋም ንስሐ እንድትገባ አልወደደችም።”ራእይ 2፥21
+ጌታም ትመልስ ይሆን በማለት እንደጠበቀም ፣ ሴትቱም ሳትመለስ እያባሰባት እንደቀጠለች ፤ጭራሽ የጌታን ምህረት የራሷን አስጠያፍ ተግባር እንደ ተቀበለ እንደ ወደደ አድርጋ ንስሐ የሚባል ነገር እንዳልወደደች እንረዳለን ።የጌታ ምህረት አይናቅም።
“እነሆ፥ በአልጋ ላይ እጥላታለሁ፥ ከእርስዋም ጋር የሚያመነዝሩትን ከሥራዋ ንስሐ ባይገቡ በታላቅ መከራ እጥላቸዋለሁ፤” ራእይ 2፥22“ልጆችዋንም በሞት እገድላቸዋለሁ፤ አብያተ ክርስቲያናትም ሁሉ ኵላሊትንና ልብን የምመረምር እኔ እንደ ሆንሁ ያውቃሉ፥ ለእያንዳንዳችሁም እንደ ሥራችሁ እሰጣችኋለሁ።”— ራእይ 2፥23
+እሷን እና ግብር አበሮቿን ጭምር ንስሐ መግባት ስላልወደዱ "..እጥላቸዋለሁ.." አለ።ለዚያውም በታላቅ መከራ።እሷን ለሚከተሉት መንፈሳዊ እናት ለሆናቸውም ደግሞ "..በሞት እገድላቸዋለሁ.." አለ። ንቁ።
“ዳሩ ግን ይህን ትምህርት ለማትይዙ ሁሉ የሰይጣንንም ጥልቅ ነገር እነርሱ እንደሚሉት ለማታውቁ ለእናንተ በትያጥሮን ለቀራችሁት እላለሁ፤ ሌላ ሸክም አልጭንባችሁም፥”ራእይ 2፥24
+ በቤተክርስቲያኒቷ ውስጥ ሆነው ያልተባበሩትን ፣ያልተከተሉትን ፣ያልተቀበሉትን ፦ፀንታችሁ፤ የያዛችሁትን አጥብቃችሁ (ከመጀመርያም አብልጣችሁ) ያዙ የሚል መልእክት አስተላለፈ።“ነገር ግን እስክመጣ ድረስ ያላችሁን ጠብቁ።”— ራእይ 2፥25
“ድል ለነሣውና እስከ መጨረሻም ሥራዬን ለጠበቀው እኔ ደግሞ ከአባቴ እንደ ተቀበልሁ በአሕዛብ ላይ ሥልጣንን እሰጠዋለሁ፥ በብረትም በትር ይገዛቸዋል፥ እንደ ሸክላ ዕቃም ይቀጠቀጣሉ፤”— ራእይ 2፥26-27
+ጌታ፦ መንፈስን በመርመር ማሳወቁን ". ሥራዬን. "ብሎ እንደ ጠራ ያስተውሏል ።ስለዚህ ይህንን ሥራ ሳይታክት፣ ፊት ባለማየት ለሚተጉት የብዙዎች እረኛ በማድረግ ከሰይጣን ትምህርት እጠብቃለሁ ፣ሰይጣን የማይደፍርበት ሃይል እሰጠዋለሁ ።ይላል ጌታ።ቃሉ የታመነ ነው። አሜን ይሁን ። ደግሞም “የንጋትንም ኮከብ እሰጠዋለሁ።” ራእይ 2፥28።ጌታ ለጸኑት ስመጣ እንዲህ ነው ፦ጠብብ ያደርጋል፣እንቁቁልሽ ፈች ..ያደርጋል ።የጸናውን ።
ስጠቃለል !!
ከላይ ያየናቸው ቤተክርስቲያን ችግሮች ካልተመለሱ ወደ ዘላለም ሞት እንደሚወስድ ያስተውሏል ።በንስሐ መመለስን በደስታ በመቀበል ጌታ እንደማይቆጣ መልእክቶቹ ያስረዳሉ ።በዚህ ዘመን ማሰቢያ አልባ መሆን ጥበብ በሚመስልበት ግዜ ይህንን መንፈስን የመርመር ሥራችሁ ፦ሥራው እንደሆነ አውቃችሁ፤ ፊት ባለማየት እንድትበረቱ ያስገነዝበናል ።ደግሞም ከሃሳዊያን መካከል የመሆን አጋጣሚ፣ የመኖር እድል ፤ለክርስቲያን የማይቀር ነው።በዚህ ሰዓት በመጠበቅ፣ በሚመጣው ሳይወሰዱ መቆም፦ እንዴት ያለ መባረክ እንደሚጠብቅ መልእክቱ ያስረዳል ።ደግሞም በመጣው ንፋስ ከተወሰዱ ልጁቹ ከተኮነ፦ ፍርድ እንደሚጠብቅ ያስተውሏል ።ስለዚህም ፦
“መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚለውን ጆሮ ያለው ይስማ።” ራእይ 2፥29
ጆሮ ያለው ይስማ (5)
“በሰርዴስም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፦ ሰባቱ የእግዚአብሔር መናፍስትና ሰባቱ ከዋክብት ያሉት እንዲህ ይላል፦ ሥራህን አውቃለሁ ሕያው እንደ መሆንህ ስም አለህ ሞተህማል።” — ራእይ 3፥1
+ ይህች ቤተክርስቲያን ከጌታ የተደበቀች አይደለችም ።አለች የሚያስብል በሰውኛ የደመቀ ስም አላት ።ግን ግብር የላትም።ስለዚህም ጌታ በፊቱ ስመለከታት ስለጌታ ምንም ስሜት(እንቅስቃሴ )የሌላት" የሞቶች ሆና "እንዳገኛት ይገልፃታል።
“ሥራህን በአምላኬ ፊት ፍጹም ሆኖ አላገኘሁትምና የነቃህ ሁን፥ ሊሞቱም ያላቸውን የቀሩትን ነገሮች አጽና።”ራእይ 3፥2
+ መልእክቱ ስጀምር ስራ እንዳላቸው ገልጾ ነበር።ግን ፍጹም ባለመሆኑ በሞት መስሎታል ።አሁን ንቃ እያለ ነው።ሳይሞቱ የቀሩትን፦ የክርስቶስን የወንጌል ሥራህን አጽና፤የሞቱትን እንደገና ቀስቅስ እያለ ነው።
“እንግዲህ እንዴት እንደ ተቀበልህና እንደ ሰማህ አስብ፥ ጠብቀውም ንስሐም ግባ። እንግዲያስ ባትነቃ እንደ ሌባ እመጣብሃለሁ በማናቸውም ሰዓት እንድመጣብህ ከቶ አታውቅም።” ራእይ 3፥3
+ወንጌልን የተቀበልነው ደቀመዛሙርቱ ብቻ ለመሆን እንደሆነ አስታውስ የሚል ነው።የደቀመዛሙርቱነት ተግባር ፈቃዱን ብቻ ማድረግ ነውና ንስሐ ግባ የሚል ተልዕኮውን እንድወጣ ያሳስባል ።አለዚያ በታላቅ ቁጣ እመጣለሁ እያለ አለ።ችግሯ ተልዕኮዋን መርሳት እንደሆነ ይረዷል።
“ነገር ግን ልብሳቸውን ያላረከሱ በሰርዴስ ጥቂት ሰዎች ከአንተ ጋር አሉ፥ የተገባቸውም ስለ ሆኑ ነጭ ልብስ ለብሰው ከእኔ ጋር ይሄዳሉ።” — ራእይ 3፥4
+እስካሁን እንደተመለከትነው ጌታ በቤተክርስቲያን ብናደድ ብቆጣ ግን ጭራሽኑ ጌታ በየ አጥቢያው ምዕመናን አላጣም።ስለዚህም ስለእነዚህ ቅረታዎች" አሉኝ" ብሎ እንደሚመጣ ይረዷል።
“ድል የነሣው እንዲሁ በነጭ ልብስ ይጐናጸፋል፥ ስሙንም ከሕይወት መጽሐፍ አልደመስስም፥ በአባቴና በመላእክቱም ፊት ለስሙ እመሰክርለታለሁ።” ራእይ 3፥5
+በሁሉም ቤተክርስቲያን የጋራ መልእክት የሆነው ንስሐ እና ለተመለሱት አክልል ነው ደግሞም ለሸፈቱት ፍርድ እንደሚያመጣ መልእክቱ ያስረዳል ።ይህች ቤተክርስቲያን መልክ ብቻ ያላት ፣በመምሰል ብቻ አለው የሚትል፣ የመንፈስ ፍሬ የሌላት ፣ደቀመዛሙርቱን ማፍራት የሌላት ፣ ከዚህ በፊት ባለው ድል አድራግነት ስም የሚትኮራ እንደሆነች ጌታ ይገልጻል ።ስለዚህም መልእክቱ እንደግለሰብም ወደራስ መመልከትን ደግሞም እንደስብስብም እንዴት ነን አሁን ? ማለትን የሚጠይቅ እንደሆነ እንማራለን ።ስለዚህም የሚሰማም የሚያደርገውም ፦“ድል የነሣው እንዲሁ በነጭ ልብስ ይጐናጸፋል፥ ስሙንም ከሕይወት መጽሐፍ አልደመስስም፥ በአባቴና በመላእክቱም ፊት ለስሙ እመሰክርለታለሁ።” ራእይ 3፥5
“መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚለውን ጆሮ ያለው ይስማ።” — ራእይ 3፥6
ጆሮ ያለው ይስማ (6)
“በፊልድልፍያም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፦ የዳዊት መክፈቻ ያለው፤ የሚከፍት፥ የሚዘጋም የሌለ፤ የሚዘጋ፥ የሚከፍትም የሌለ፤ ቅዱስና እውነተኛ የሆነው እርሱ እንዲህ ይላል።”ራእይ 3፥7
+ ጌታ ራሱን ስገልጽ ከዳዊት ወገን በስጋ እንደመጣ ፣ ወደ መንግሥቱ ለማስገባትም ለመከልከልም መሉ ስልጣን እንዳለው ፣ሌላ አካል(ማንም) ውሳኔውን በምንም ማስቀየር እንደማይቻል ፣የተለየና የታመነ እንደሆነ ይገልጻል ፣
“ሥራህን አውቃለሁ፤ እነሆ፥ በአንተ ፊት የተከፈተ በር ሰጥቼአለሁ ማንምም ሊዘጋው አይችልም፤ ኃይልህ ምንም ትንሽ ቢሆን ቃሌን ጠብቀሃልና፥ ስሜንም አልካድህምና።” — ራእይ 3፥8
+"..የተከፈተ በር ሰጥቼአለሁ .." ይህ በር ወደ ጌታ መንግስት ለመማረክ ፣አገልግሎት(የወንጌል አገልግሎት ) እንድቀናልህ የሚማረኩትንም (መከሩን) አዘጋጅቻለሁ የሚል ነው ።ስለዚህም " ውጣ በግዜውም አለግዘውም ስበክ ዝመት" የሚል ነው።ይህችን ክፍል ጌታ ለሌላ አገልግሎት (የኢኮኖሚ ፣የክብር ፣የዝና ማግኛ..) እንደከፈተ የሚናገሩ አሉ።በእርግጥ ጌታ ይባርካል በሚያስፈልግ ነገር ሁሉ።ይህ ማለት ግን የመጽሐፉን ቃልን ያለ አሀዱ እንድናስጨንቀው እንድናጠመዝዘው ቃሉ አይፈቅድም ።
+ምንም እንኳን የተቀበለው ትንሽ መክልት ብሆንም አትርፏል ።ጌታም፦ታምነሃል በማለት ለብዙዎች መትረፍ ማምለጥ መዳን እንድሆን ለማድረግ በትልቁ ባርኮት ባርኳል። ቃሉም “..፥ አንተ በጎ ታማኝም ባሪያ፤ በጥቂቱ ታምነሃል፥ በብዙ እሾምሃለሁ፤ ..” — ማቴዎስ 25፥21 እንደሚል ነው።
“እነሆ፥ አይሁድ ሳይሆኑ፦ አይሁድ ነን ከሚሉ ነገር ግን ከሚዋሹ ከሰይጣን ማኅበር አንዳንዶችን እሰጥሃለሁ እነሆ፥ መጥተው በእግሮችህ ፊት ይሰግዱ ዘንድ እኔም እንደ ወደድሁህ ያውቁ ዘንድ አደርጋቸዋለሁ።” ራእይ 3፥9
+ ልክ በጌታ ላይ "አባታችን አብርሃም ነው" ብለው ስፎክሩ ኢየሱስ እንደገሰጸ በዮሐ 8፥44 ላይ እዚህም በቀጥታ የሰይጣን ማህበር ናችሁ በማለት ይገልጻል ።አይሁዳውነት ለእግዚአብሔር በመሆን እንደሆነ ሁሉ፥ ዛሬ ክርስቲያን ነን ማለትም ለክርስቶስ በመሆን ብቻ እንደሆነ እንረዳለን ።ለራሳቸው የሳይጣን ማህበር ሆነው እያሉ እንኳን ብሳደቡ ብጠሉ ፥በእኔ የተወደድክ መሆንህን ያውቃሉ..። ልክ ነህ፣ ማረን፣ እያሉ ወደ አንተ ይመጣሉ ይለናል ።
“የትዕግሥቴን ቃል ስለ ጠበቅህ እኔ ደግሞ በምድር የሚኖሩትን ይፈትናቸው ዘንድ በዓለም ሁሉ ላይ ሊመጣ ካለው ከፈተናው ሰዓት እጠብቅሃለሁ።” — ራእይ 3፥10
+የእምነትም ፈተና ተፈትነው ስላለፉ ጌታ ከዚያ ታላቁ መከራ እጠብቃቹዋለሁ እያለ እንደሆነ ይረዷል።መልእኩቱ በመቅቱ ላለች ቤተክርስቲያን ብቻ እንዳልተጻፈ የሚያስረዳ ነው።ምክንያቱም ታላቁ መከራ ውስጥ "ከዚያ ሰዓት" መጠበቅ እስካሁን ያልተፈፀመ ነው።ጌታ ከመፍረዱ በፊት ከታላቁ መከራ በሕይወቴ ስጋ ያሉትና ያረፉቱን በንጥቀት ጌታ ከታላቁ መከራ እንደሚጠብቃቸው ያስተውሏል ።ማር 13፥19።
“እነሆ፥ ቶሎ ብዬ እመጣለሁ፤ ማንም አክሊልህን እንዳይወስድብህ ያለህን አጽንተህ ያዝ።”ራእይ 3፥11
+ እስካሁን የያዝከውን እምነት ሃይማኖቴን አጽንተህ ያዝ በማለት የማጽናት መልእክት አስተላልፏል ።
ስጠቃለል !
ይህ መልእክት ከሰርምኔስ ቤተክርስቲያን ጋር ያስመስለዋል ሃይማኖቱን በመጠበቃቸው። የሰርምኔስ ቤተክርስቲያን የጠበቃት ፈተና ለላ የሚልቅ፣ እምነታቸው የሚፈትን ፣ክርስቶስን በሕይወታቸው እንድሰብኩ የሚያደርግ ፣የማጥራት ፈተና ነበር።በዚህች ቤተክርስቲያን ግን የማጥራት ፈተና ተፈትነው ለመነጠቅ ስለደረሱ ከሚመጣው ከታላቁ መከራ እጠብቃቸዋለሁ የሚል ነበር።ምን እያልኩ እንደሆነ ይረዷል።የሴርምነስ ቤተክርስቲያን እየታጠረች ነው።የፊልድልፊያ ቤተክርስቲያን ግን ስለታጠረች ሌላ ተጨማሪ የእምነት ፈተና አልጨመረም ።እንድሁም ከታላቁ መከራ እጠብቃችሁዋለሁ ነው ያለው ።የፊልድልፊያ ቤተክርስቲያን አንድ እርከን ቀድማለች።የሚጠብቃት መጽናት ነው።የሴርምነስን ግን ሌላ የሚልቅ የእምነት ፈተና ነበር የሚጠብቃቸው ።
ጌታ ለመንግሥቱ እንድበቁ አብዝቶ ያጠራል ከዚያም ከየትኛውም ክፉ መከራ ይጠብቃል።ያሳለፉት በቂ ነውና ።እስካሁን የተቀበሉት በቂ ነውና።ስለዚህም አሁን እንደ ፈቃዱ ብንመላለስ ከታላቁ መከራ እንደሚጠብቀን ያውቋል። የሚፈተኑቱ ፦በንስሐ የተመለሱቱ ብቻ እንደሆኑ ፤ ተፈትነው ካለፉ ደግሞ ንጥቀት እንደሚጠብቃቸው ይረዷል።“ድል የነሣው በአምላኬ መቅደስ ዓምድ እንዲሆን አደርገዋለሁ፥ ወደ ፊትም ከዚያ ከቶ አይወጣም፤ የአምላኬን ስምና የአምላኬን ከተማ ስም፥ ማለት ከሰማይ ከአምላኬ ዘንድ የምትወርደውን አዲሲቱን ኢየሩሳሌምን፥ አዲሱንም ስሜን በእርሱ ላይ እጽፋለሁ።”— ራእይ 3፥12
“መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚለውን ጆሮ ያለው ይስማ።” — ራእይ 3፥13
ጆሮ ያለው ይስማ (7።)
“በሎዶቅያም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፦ አሜን የሆነው፥ የታመነውና እውነተኛው ምስክር፥ በእግዚአብሔርም ፍጥረት መጀመሪያ የነበረው እንዲህ ይላል፦” — ራእይ 3፥14
+ጌታ ለቤተክርስቲያኒቷ ራሱን ስገልጽ እውነት እውነት አምላክ ፣የፍጥረት ሁሉ ገዥ እንደሆነ ያስረዳል ።
“በራድ ወይም ትኩስ እንዳይደለህ ሥራህን አውቃለሁ። በራድ ወይም ትኩስ ብትሆንስ መልካም በሆነ ነበር።”
— ራእይ 3፥15
+ መንፈሳዊ አገልግሎት በቤተክርስቲያኗ ምንም የሚታይ ነገር እንደሌለ ይገልጻል ።የሴርደስ ቤተክርስቲያን ሞተህማል ብትባል እንኳን ጌታ ተስፋ ያደረገቻቸው ቅረታዎች አሏት ።የዝች ድንዛዜ ይብሳል ።የሴርደሷ ቤተክርስቲያን ስራ አላት ፍጹም ግን አይደለም ።ይህች ግን ሥራም የላትም።
“ሀብታም ነኝና ባለጠጋ ሆኜአለሁ አንድም ስንኳ አያስፈልገኝም የምትል ስለ ሆንህ፥ ጐስቋላና ምስኪንም ድሀም ዕውርም የተራቆትህም መሆንህን ስለማታውቅ፥” — ራእይ 3፥17
+ይህች ቤተክርስቲያን በኢኮኖሚው የበለጸገች ስለሆነች ፤ ሀብት ስላላት ጌታዋን የረሳች እንደሆነች እንገነዘባለን ።እንደ ቤተክርስቲያን( እንደ ቅዱሳን ስብስብም) መልእክቱን እንደግለሰብም የሚንማርባቸው እንደሆነ ይረዷል። ይህች ቤተክርስቲያን ብዙ የተንቆጠቆጠ ለስጋ ዓይን ያማረ እንደ ሰውኛ የሚያስመካ ብመስልም ፤በጌታ ፊት ግን ከንቱ ከንቱ ፣ራቁትነት እንደሆነ ይገልጻል ።
“ባለ ጠጋ እንድትሆን በእሳት የነጠረውን ወርቅ፥ ተጐናጽፈህም የራቁትነትህ ኃፍረት እንዳይገለጥ ነጭ ልብስን፥ እንድታይም ዓይኖችህን የምትኳለውን ኵል ከእኔ ትገዛ ዘንድ እመክርሃለሁ።” — ራእይ 3፥18
+ጌታ ፦በልጽግያለሁ ያለውን የኢኮኖሚ ሀብት አይጠላም ።ለዚህም እንዲህ ይላል ፦በውጭም እንዳማረብህ እኔ የሚፈልገው ውስጠኛውም እንድያምርብህ ወደ እኔ ተመለስ!።የሚል መልእክት አስተላልፏል ።ያለራሱ ሁሉም ከንቱ ነው በማለት ገሰጸ።“እኔ የምወዳቸውን ሁሉ እገሥጻቸዋለሁ እቀጣቸውማለሁ፤ እንግዲህ ቅና ንስሐም ግባ።” ራእይ 3፥19።
“እነሆ በደጅ ቆሜ አንኳኳለሁ፤ ማንም ድምፄን ቢሰማ ደጁንም ቢከፍትልኝ፥ ወደ እርሱ እገባለሁ ከእርሱም ጋር እራት እበላለሁ እርሱም ከእኔ ጋር ይበላል።”— ራእይ 3፥20
+ጌታ በደጅ ቆሞ ድምፅ ያሰማል ይከፍት ይሁን ?ይመለስ ይሁን ? ይቀበለኝ ይሁን በማለት በፍቅር መጎዳቱን ይነግራል።የከፈለውን በእጆቹ ላይ ያለው ምልክት ያሳያል ።ስለ ፍቅር እንደሆነ በእንባ ያናግራል ።ሕይወትን ለመስጠት በር ላይ ቆሞ በዝናብ ይመታል ።ለጥቅማችን ይለምናል ። የክብር ጌታ ገብቶ መካፈል ይፈልጋል ።መባረክ ይፈልጋል ።በነገር ሁሉ ልባርክም ይወዳል ።“እኔ ደግሞ ድል እንደ ነሣሁ ከአባቴም ጋር በዙፋኑ ላይ እንደተቀመጥሁ፥ ድል ለነሣው ከእኔ ጋር በዙፋኔ ላይ ይቀመጥ ዘንድ እሰጠዋለሁ።” ራእይ 3፥21።
“መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚለውን ጆሮ ያለው ይስማ።” ራእይ 3፥22
ስጠቃለል ሃሌ ሉያ !!
የተኛውም ቅዱሳን ስብስብ ከጣዩን ምዕራፍ ለመተርጎም እንደ ስብስብም እንደ ግለሰብም፦ በ7 ቱ ቤተክርስቲያን ተግሳጽ ያለበትን ፤የቆሜበትን ፤መፈተሽ ይኖርበታል ።ቀጣይ ያለውን የትንቢቱን ቃል ለማንበብ ጌታ የሰጠውን ተግሳጽ በመቀበል በንስሐ መመለስ ያስፈልጋል ።በንስሐ የማይመለስ የሞት ሞት እንደሚሞት ይሰመርበት ።
እነኝህ ቤተክርስቲያናት ዛሬ ልኖሩም ላይኖሩም ይችላሉ።ታርክ የሚያረጋግጥ ይሆናል ።ግን ዘላለማዊ ቃሉ አለ።ጌታ ቤተክርስቲያንን ከቤተክርስቲያን ጋር ማለትም አንድ አጥቢያ ከሌላኛው አጥቢያ ጋር እያነፃፀረ አልወቀሰም።ከራሱ ከማንነቱ አንፃር እንጂ።ስለዚህም ማንም" አለን!!በሕይወት ነን !!የእግዚአብሔር ነን !! "ለማለት ከተሳሳቱት ጋር በማነፃፀር ከሆነ የሚጠፋ ይሆናል ።ሚናልባት ሀሰተኛ ኒቢያት ፣ሐዋርያትና አስተማሪዎች ጋር ካሉት ሰዎች በማነጻጸር ከሆነም ዋጋ የለውም።ወይንም ልክ እንደ እኔ የእውነትን እውቀት ተቀበለው አውቀው መጀመሪያ የነበረው በአዕምሮ ላይ የተጠቀጠቀውን ተረት ገድል እና ድርሳን ከሚከተሉ ሰዎች አንጻር ካየንም መጥፋታችን የማይቀር ነው።እኛ ክርስቲያኖች ክርስቲያን ነን! አለን! ለማለት የሚያስችለው ከኢየሱስ ሕይወት አንፃር ፣ከቃሉ አንጻር መሆን እንዳለበት ይረዷል።
ጌታ በባሪያው "መርምሩ "ያለው ብዙ ሀሳዊያን እንደሚነሱ ስላስታወቀ ነው። ለመለየት በሚያቅተን መልክ ስለሚመጡ እንደሆነ በማወቅም ነው፤ መንፈስን ስንመርመር እግዚአብሔር "መከራህን አውቃለሁ " እስከሚል እንወቅ !!።ካለመርመር የተነሳ ሚን ያህል ጌታ እንደተቆጣ አይታችኋል ።መንፈስን መርመር ጌታ ሥራዬ ብሎ እንደሚጠራ አይታቿኋል።ስለዚህ እግዚአብሔር የሰጠውን አዕምሮ አንድፈን!!።
እያንዳንዷ መልእክት የቤተክርስቲያን የሕይወት ፦ወደ ቀድሞ ስራቸው መመለስ እንደሆነ አይታችኋል ።ወደ ቀድሞ ሥራ የመመለስ እንቅስቃሴ ተሃድሶ ነው።ተሃድሶ አድስ መመሰረት ሳይሆን ቀድሞ ወደ ነበረ ግን በግዜ የተበላሸውን የማጥዳት የመመለስ እንቅስቃሴ ነው።ታድያ ጌታን ያልበደለ አለ? "ተሃድሶ አያስፈልግም" የሚል "ፍጹም ነኝ "የሚል ልክ እንደ ሎዶቅያ "ሁሉም አለኝ" " ሙሉ ነኝ" እንደማለት እንደሆነ ያውቋል።ተሃድሶ ለሕይወታችን ተሃድሶ ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ።አዎ መመለስ ወደ ጌታ ፈቃድ ይሁን ።አሜን ።ሃሌ ሉያ
እድሉ ዮሐንስ ጋምሳ
(ደቀመዛሙርቱ )
Comments
Post a Comment