ማርያምን አትሳደብ !
1.መግቢያ
1.2.ለምን ይሳደባሉ
1.3.የአሮን በትር ናት ?
1.4.'ማርያም' የዓለም መድኃኒት ናት ?
1.5."ዮሴፍን የሚታጽናኝው/የሚታረጋግው/ አንቺ ነሽ"(ው.ማርያም ፤ቅዳሴ ማርያም )
1.6 "አብ በሰማይ አይቶ እንዳንቺ አላገኘምና .." (ራቡዕ ው.ማርያም ቁ.1)
1.7 "አምላክን የወለድሽ እመቤታችን ሆይ ትውልድ ሁሉ አንችን ብቻ ያመሰግኑሻል" (ራቡዕ ው.ማርያም ቁ.2)
1.8 የነነዌ ሰዎች 'በማርያም' ምክንያት ከመጣው መቅሰፍት ተረፉ ?
1.9 ፍጥረት ሁሉ ከመፈጠሩ በፊት 'ማርያም ' ነበረች ?
1.10 "በእውነቱ ስለ ስለቃልኪዳኗ ነውን?"እያልኩኝ ነው።
ማጠቃለያ
ዋቢ መጽሐፍት
ማርያምን አትሳደቡ!
1. መግቢያ
ለምንስ ተቃወምኩ ? በማለት በራሴ በፊት ገፀ ላይ ያካፈልኩትን ሕይወተን ለማስፈር ፈለኩ፦<< " ብዙዎች ስለእኔ የመሰላቸው ብለዋል " አሁን ግን ግዜው ስለሆነ ከባለቤቱ እንድትሰሙ ወደድኩ።ሰዎች እኔን የምሉት "ተሃድሶ የሆነው ከካምፖስ ተባረው ነው ፣ ገንዘብ ስለምከፈለው ነው፣ እብዶ ስለሆነ ነው... ነው" ብለዋል ።እውነቱን ማወቅ ለብዙዎች ጥያቄ የሚመልስ እና በልበ ሰፊነት ለምመረመሩት እውነቱ ፤ ነገሩ እንደዚህ ይሆንን ? ለሚሉት ከሚመስል ነገር በማውጣት ወደ እውነቱ ያምራል በምል ነው።
በአርባምንጭ ዩንቨርሲቲ በጫሞ ካምስ በ2009 ዓ.ም ዩንቨርስቲውን ተቀላቀልኩ ።እዛ ነበር በህይወተ ጥያቄ ፣ግራ መጋባት ፣ለማመን የሚከብድ ነገር መስማት፣ መስማት ብቻ ሳይሆን ማዬት የጀመሪኩት ። የተማሪዎች ፈንት (ራስ መሳት)፣መንፈራፈር ፣በየትምህርት ክላስ መውደቅ ፣በየመንገዱ መውደቅ፣ በዶርም መውደቅ .... ከዚህ በፊት አይቼ ስለማላውቅ ጥያቄ ፣ ድንጋጤ እና ፍራት እየተሰማኝ "ይህ ምንድነው? ታይፖድ ፣ ብጫ ወባ ነው.. ምድነው ?"ስል የሰማው ነባሪ ተማሪ ነበረው ጉዋደኛየ እንድህ አለኝ በሀዘን መንፈስ "ጎበዝ ለመሆን ሲሉ የወሰዱት መድኃኒት ነው" አንዳንዶቹ ተደግሞባቸው ነው አለኝ" ። ድንብርብር አለብኝ ይልቁንም ፤ ጥያቄን በዚህ ብቻ ማቆም አልቻልኩም ነበር ፥ ሌላም ጥያቄ የፈጠረብኝ ነገር ነበረ ፤ እንድህ ብዬ ጠየኩ "ፈንት የሚነቅሉትን ወደ ቤተክርስቲያን ይወሰዳሉ? ትክክል ነው ፥ ነገር ግን ድነው ይመጡና "አሁንም በዚያ ሰዓት ለምን በድጋሚ ፈንት ይሰራሉ ? አንደ ከተፈወሱ በኃላ በድጋሜ የሚወድቁበት ምክንያት ምንድነው አልኩኝ ?" መጽሐፍ ቅዱስ የማንበብ ዚንባሌ ባይኖረኝም ኢየሱስ ሆነ ሐዋሪያት አንደ ሰይጣንን ካወጡ በኃላ ድነዋል፤እለት ተ እለት ፈንት የሚነቅሉት ለምንድነው እዝህ? በማለት በሃዘን መንፈስ እየተጨነቁ ጠየኩ" ። ነባሩ ተማሪም " እኔም አላቅም አለ" መልስ አለማግኘተ ጥያቄ እና ጭንቀት ጨመረልኝ ።
ጥያቄ እና ጭንቀት እለት ተእለት እያየለ የሄደብኝ በማልደራደርባት ፣በምወዳት ፣በምኮራባት ... በሃይማኖት ተቋሜ ላይ መሰማቱ እና መከሰቱ ነው። በወንጌላውያን አማኞች ጉዋደኞቼ ፊት ለማውራት ማፈር ፣መሸማቀቅ ፣የማውራት ሞራሌን ሙሉ በሙሉ አሳጣው ይህ ነገር ።
እኛ ወንጌል ይማራሉ የምንላቸው ልጆች ገዳም ብለው ሄደው ጥንቁልና ፣ድግምት ፣ሟርትን እንደምማሩት አወኩ ።የሚሄዱትም ልጆች ሁሉ አውቀው አይደለም ። አንዳንድ ልጆች ጥብብ ነው ብለው የሚያከብሩት ብኖሩም ውስጤ ጥንቁልና ነው ይለኝ ነበር እንድሁም "እኛን ይቀስፋል ይላሉ" እነሱን(ደጋሚዎቹን ) የማይቀስፈው ለምንድነው የሚል ጥያቄ ነበረኝ?። ወደ ቤተክርስቲያን ግብ እየተቀጠቀጥን እኛ እንገባለን እነሱ(ጥንቁልና የተማሩቱ) ደግሞ እንድሁም በቤተመቅደስ ውስጥ ናቸው ።ለምን? ይህን ትምርህት በሕጋዊ መልክ በቤተክርስቲያን መሰጠቱ ውስጠ እንድጮህ አደረገው ።
ልናገር ብል ፦ የተቋሙን ሕግ ስርዓት ሁሉን አክብረ አምኜ ያለ ነቀፋ እመላለስ ነበር ።ሌሎችን የማበረታታት ፣ከእንቅልፍ እየቀሰቀሱኝ የምወስዳቸው ፣በጾም የማልታማ ነበርኩኝ ። እንዴት ልተወው እሺ? ማንን ልያዝ ?ወደ ማን ልሂድ ?ጨነቀኝ።
አሁን ልተው አሰብኩ ለዘመናት እውነት ነው ብዬ የተከተልኩት ተቋም ፤ቦታ የሰጠውላት የማልደራደርባት እንዲህ ጠንቋዮችን ታቅፋለች ፥ እግዚአብሔርም እንዴት ዝም ይላል ? እኔ ምን አቃለሁ ከቤተሰብ ወረስኩ እንጂ በማንም ደጋም እግር ስሪ መውደቀን በምን አውቃለሁ ? እሽ ብሞትስ አዛው ? እግዚአብሔር እንዴት ዝም ይላል?። "ቅድስት ናት፤ አንድት ናት "ብዬ የዘመሪኩላት በውሸት የተጨቃየች ከሆነች ፥ የተኛውንም ሃይማኖት አላምን ብዬ ልበን ዘጋው !
ከወንጌላውያን አማኞች የሆነው ጉዋደኛዬን ጠየኩ ? እንዲህ ስል "ሰዎች ቤተከርስቲያን (የፀሎት ቦታውን ነው የምለው ) ስለማልሄድ አብዷል ይላሉ ፣ "ሴጣን አለበት"ይላሉ እስኪ አንተ ለኢየሱስ ስም ሁሉ ይቻላል አይደል የምትለው ?ለእኔ ጸልይ አልኩ ? እሱም እሺ አለ ።እሺ ስል ፈራውና አንተ ፀልይ ግን አሜን አልልም አልኩኝ ።እሱም እሽ አለ ፥ከእለታት አንድ ቀን እኔም ሳላስብ " አሁን ልጸልይል አለኝ" እኔም አዎ አልኩኝ ።ፀለየልኝ ። እኔም ደግሞ አሜን ሳልል ጨረስኩ ።ተገረምኩ ፤እጄን በአፈ ጫንኩ ፤ምነው አለኝ? ይህ ሁሉ ደቂቃ እንዴትስ ፀለይክ? እኛኮ ፀሎት ከተባለ ትንሹን የፀሎት መጽሐፍ ማንበብ እና በልምድ መሸምደድ ነው የሚናውቀው ምንም ነገር ሳትይዝ እንዴት? አልኩ ። ምንም አልመለስልኝም ግን እንድህ አለኝ እንድፀልይ ስለፈቀድክልኝ አመሰግናለሁ አለኝ ።
የመጀመሪያ ዓመት ጨሪሰን ወደ ቤት መጣን አሁንም አላስችል ብሎኝ ለማጣራት ስለፈለኩኝ ወደ አማራ ክልል ለዜማ ትምህርት ገዳም የሄደውን ፤ ዩንቨርስቲ ላይ ያጋጠመኝን ፈንት አጫወቱኩኝ ።ለምን ይሁን ብዬ ጠየኩ ? ያ ፈጣን ቆሎ ተማሪ እንዲህ አለኝ "እሱን ትገረማለህ እኔም አላምንም ፤''የለም ድግምት አይሰራም'' ስል በኔ ላይ በር ዘግተው ደግመው ወጡ ፥ ከዛ ቤቱ ጉንዳን በጉንዳን ሆነ " አለኝ ። ደነገጥኩ። አንተ መድኃኒቱን አልሞከረክም አልኩኝ ? እሱም እንዲህ አለኝ "ዝም ብሎ አይሰራም ቃል ክዳን ስታደርግ ነው " የምሰራው በማለት ከራሱ ጋ የሄዱት ሁሉም የተለያየ መድኃኒት እንደወሰዱ አጫወተኝ ።
እንዲሁ ዝም ብዬ በጨለማ ስመላለስ በ2011 ዓ.ም ጨረስኩ ።በልበ ፦አንዴ ጥያቄ ፣ አንደ ትዕቢት ፣ከዚህ ሁሉ በኃላ ህይወት Game ሆኖ መታየት ፣ተስፋ መቁረጥ፣ ደስታ ማጣት ፣ ማማረር ፣ የስጋ ሃሳብ ስፈራረቅብኝ፣ በበቀል ስሞላ ፣ እንደ ጭንቁር ሰውነቴ እየተበላ ፤ያለ ቃሉ ጠወለገ ሰውነቴ ........ ያ ፈጣን ቆሎ ተማሪ ግርግር በመፈጠሩ የዜማ ትምርቱን ትቶ እቤት መጥቶ ነበረና ፤ወደ እኔ መጣ እንድህም አለኝ ያንተን ጥያቄ ልመልስ የሚችል በቅዱስ ጳውሎስ ዩንቨርሲቲ የተማረ ሰው አለ አለኝ ።እኔም በደስታ በቆሸሸው እኔነት ከነግሳንግሰ ሄድኩ ።እከራከራለሁ ፣ግትር እላለሁኝ ፣ አንደኛው ስመል ሌላ እጠይቃለሁ እንዲህ እያልኩኝ መጽሐፍ እየወሰድኩ ማንበብ ጀመርኩ የተቀበረ መክሊት የሚባል በዲ.አግዛቸው ተፈራ የተፃፈ ሰጠኝ ። ጥያቄዎቼ ሁሉ መልስ አግኝተው እውነት በሚመስል ህይወት በከንቱ እንደተመላለስኩ ገባኝ ።
ማታ ማታ እየሄዱ ከሚማሩ ልጆች ጋር በመቀላቀል መማሪ ጀመሪኩ ፥ ያወኩት እውቀት ብቻ ሆኖ እንዳይቀር አጥብቆ ያስተምር ነበረና በመስከረም 17/2012 ዓ.ም የኢየሱስ መስቀል ከፊቴ ተሳለልኝ ፣ በእኔና በዓለም የክርስቶስ መስቀል ገባ ፣ እግዚአብሔርም እለት እለት ይጎበኘኝ እና ያሳድገኝም ነበር ።
የተቃወምኩት ለዚህ ነው ። ለራሴ ቃል ገባው ደጋምዎቹን ለመበቀል ፣ባለማወቅ ለምንከራተቱ እንድያመልጡ ድምፅ ለመሆን ፣የሰይጣን ስራ ነውና እስከሞት ለመቃወም ፣ ምህረት በተደረገለኝ መጠን አልታክትም ፣ ደግሞም ለመቃወም እንድያስችለኝ የእግዚአብሔርን ቃል እታጠቃለሁ ፤ ታጥቅያለሁኝም።ወስብሐት ለእግዚአብሔር ።>>
በዚህ መጽሐፍ ላይ ለማሳየት የሚጥረው በኢየሱስ ክርስቶስ እናት ላይ የተደረገውን አሽሙር ነው።አንዳንዶች ባለማወቅ ማክበር መስሏቸው እናቱን እየሰደቡ ስለሆነ አትሳደቡ በማለት ከኢየሱስ እናት ጋር ባላጋራ መሆኔን ወዳጅነተን ለማሳየት ይህችን አስቀመጥኩ።ስለ ፍደል ስህተት ይቅርታ እጠይቃለሁ ።
1.1 የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ እናት ብፅዕት ድንግል ማርያምን ለምን ይሳደባሉ ?
ለምን ይሳደባሉ ስል የሚሳደቡበት ምክንያት ልተነትን አይደለም ።ምክንያቱ በግልፅ ይታወቃልና ፦አለማወቅ እንደሆነ።በዚህ ርዕስ ስር ለምን ይሳደባሉ ስል ስድብ አሽሙር አቁሙ!ይብቃችሁ !በማለት ባለማወቅ እየተሳደባችሁ እንደሆነ ለማሳየት ነው።
ወደ ሀሳቤ ከመግባት በፊት እስኪ ስለ ተምሳሌታዊ ንግግርን እንያ ፦
"አበበ እንደ አቦሸማኔ መጣ"
፨ አበበ በፍጥነት መጣ ማለት ነው።
"አበበ አቦሸማኔ ነው"
፨ እንስሳው አቦሸማኔ አበበ ነው ማለት ነው።አበበ አራት እግር ያለው እንስሳው ነው ማለት ነው።
"አበበ እንደ አንበሳ ነው"
፨ አበበ ጀግና ፤ብርቱ ነው ማለት ነው።
"አበበ እንደ ንብ ነው "
፨ ማለት አበበ በስራው ታታር ነው ማለት ነው።
ይህን ያህል ከተንደረደርኩ ይበቃል ።ወደ ቁም ነገሩ ስገባ የኢየሱስ እናት ድንግል ማርያምን ምን ብለው እንደሚሳደቡ ላሳያችሁ ፦
"ሙሴ በነደ እሳት ሳትቃጠል ያያት ዕፅ አንቺ ነሽ።"(ውዳሴ ማርያም የማክሰኞ ቁ.4)
፨ እዚህ ላይ ይህንን አማረኛ ቃል በቃል ብንፈታው ፦ሙሴ በሚነድደው እሳት ሳትቃጠል ያያት ዕፅዋቷ ራሷ 'የኢየሱስ እናት ድንግል ማርያም ናት' ማለት ነው።አስተውሉ።ይህንን ታርክ በዘፀአት መጽሐፍ በ3ኛው ምዕራፍ ላይ እናገኛለን ።ከመጽሐፍ ቅዱስ ታርክ ወስደን እንደዚህ ገለፃ እንደሚንረዳው ከሆነ ሙሴ ያያሁ ዕፅዋቷ 'ማርያም' ናት ማለት ነው።ስለዚህ ሙሴ እንደዚህ ገለፃ የተመለከተው 'ማርያምንና እግዚአብሔርን' ነው ማለት ነው።
፨ እንደዚኛው /ው.ማርያም/ በሚባለው መጽሐፍ ገለፃ ከሆነ የኢየሱስ እናት ድንግል ማርያም ኢየሱስን ከመውለዷ በፊትም ነበረች በአንድም በተለያየ ሁኔታ ትገልፃለች ማለት እንደሆነ ይመለከቷል ።
ምናልባት ጻፊው ለማለት የፈለገው ምን እንደሆነ ባላውቅም የኢየሱስ እናት ቅድስት ድንግል ማርያም ከመወለዷ በፊት ዕፅዋት እንዳልሆነች ይረዷል።ምክንያቱም እሷ ፍጹም ብፅዕት ሰው ብቻ ናትና ።
"የዝናብ ውሃ የታየብሽ የእውነት ደመና አንቺ ነሺ " (የራቡዕ ው.ማርያም ቁ.4 )
፨ ዝናብ የያዘ ወይንም ዝናብ ልጥል የደረሰው ደመና ማርያም ነው/ ናት/ የሚል ነው። ዝናብ ልጥል ከደረሰ፤ የጠቆረውን ፤በዝናብ የተጨናነቀውን ደመና ፤ከተመለከታችሁ ያ ደመና ማርያም ነው(ናት) ማለት ነው።
በምን ሕሳብ የኢየሱስ እናት ድንግል ማርያም ዝናብ የቋጠረ ደመና እንደሆነች ባይገባኝም እሷ አሁንም ጻድቅ እንስት ናት እንጂ ዝናብ የቋጠረ ደመና አይደለችም ።
ይህ በዚህ ይብቃና ማርያም ያልሆነች ቁስ የለም ፦አንደ ከቀንድ የተሰራ መጠጫ ፣አንደ መሶብ ፣አንደ ማሰሮ፣አንደ እርሻ፤ ...ብቻ እሷ ያልሆነች ቁስ የለም።አሽሙር ነው።
1.2 የአሮን በትር ናት ?
የመጽሐፍ ቅዱስ አንዷ ስንኝ ሙሉ ሀሳብን ልትሰጥም ላትሰጥም ትችላለች ።መጽሐፍ ቅዱስን ብቻ ጉርሙ መጽሐፍ ከሚያደርጋቸው ነገሮች አንደኛው በራሱ ያለ ሌላ መጽሐፍ መፈታቱ ነው።አንዷ ስንኝ ሙሉ ትርጉም ካልሰጠች ሙሉውን ዓ.ነገሩን ማንበብ ፤ዓ.ነገሩንም ካልተረዳን ሙሉ ምዕራፉን ፤ሙሉ ምዕራፉንም ካልተረዳን መጽሐፉን ሙሉውን ማንበብ የግድ ያስፈልጋል ።
ለምሳሌ ፦
“ላለው ይሰጠዋልና ይበዛለትማል፤ ከሌለው ግን ያው ያለው እንኳ ይወሰድበታል።”- ማቴዎስ 13፥12
፨ ይህ የኢየሱስን ንግግር አምላካችንን Capitalist ያስመስለዋል በመጽሐፍ ቅዱስ አውድ መሠረት ካላየነሁ።አውዱ የሚያወሳው ግን ስለ ኢኮኖሚ ሳይሆን ስለመንፈሳዊ ጥበብ ነው። እንዲህ ከተነደረደርኩ በቂ ነው።በዚህኛው ጹሑፍ ለማሳየት የምጥረው በአንድ አፍ ሁለት ሚላስ የሆነ በማርያም ላይ የተደረገውን አሽሙር ነው ።
ዘኤጲፋኖሲ ም.59 ቁ.8 ላይ በሃይማኖት አበው መጽሐፍ ላይ ስለ ጌታችን ትንሳኤ ስያመሳጥር እንዲህ አለ "ከብዙ ዘመን ጀምሮ ደርቃ የነበረች የአሮን በትር ይህንን ዳግመኛ ታስረዳለች .." አለ።
እንደ ቅዱስ አቡነ ዘኤጲፋኖሲ እና እንደ መጽሐፍ ባለበት እንደ ሆኑቱ እምነት ከሆነ የአሮን በትር ደረቋ ፤ውሃ እንኳን ለመጠጣት ስሪ የሌላት ፤ያልጠጣች ፦በእግዚአብሔር ኀይል የለመለመችዋ የሚታያሳየው የኢየሱስን ትንሳኤ ነው ብለው አበው ገልጸዋል ።በበኩሌ ውጫለሁ።
ውዳሴ ማርያም ዘእሁድ በቁ.8 እንዲህ ይላል ፦
"ሳይተኩሏትና ውሃ ሳያጠጧት የለመለመች የአሮን በትር ነበረች.."
፨ ይህ ጹሑፍ እንደሚነግረን ከሆን በመጽሐፍ ቅዱስ በዘኁልቁ መጽሐፍ በም.16 እንደተመዘገበው "አሮን ለምን ልቀ ካህናት ይሆናል እኛ ነን ልቀ ካህናት "ብለው የቆሮ ልጆችና ዳታን ባነሱት አመጽ ላይ ፥ሙሴ ባቀረበው ፈተና መሠረት ሁሉም የራሳቸውን በትራቸውን ካስቀመጡ በኃላ "የለመለመ በትር የልቀ ካህናትነት ማረጋገጫ ይሆናል " ብሎ ሙሴ በነገረው መሠረት የአሮን በትር ብቻ ለመለመች ።ከዛ ለሎች ልቀ ካህናት ነን በማለታቸው ምድር ተከፍታ ዋጠጭ። ታርኩ በአጭሩ እንዲህ ነው።
፨ይህ የአሮን በትር ደረቋ ልቀ ካህናትነቱ ለማሳወቅ የለመለመችሁ በትሯ 'የኢየሱስ እናት ድንግል ማርያም ናት' እያለ ነው የው.ማርያም ጸሐፍ።
፨በዚህ ላይ አሮን ከቦታ በታ ሰዎችን ስመራ እና እንደ ባህላቸው በትር ስይዝ ያች በትር 'ማርያም' ነበረች የሚል ነው።በሌላ አነጋገር አሮን 'ማርያምን' ይዞ ነው ያለው ማለት ነው። ምክንያቱም ጸሐፍው "..የአሮን በትር ነበረች.." ይላልና።ከነበረች ከመወለዷ በፊት ነበረች ማለት ነው።ካለች ደግሞ ዕድሜ የማይቆጥርላት ዘመኑ ስደርስ በስጋ ተገለጠች ከዛ በፊት ግን በትር የነበርች ማለት ነውና ። ያሳዝናል ።
ሌላው ደግሞ ሃ.አበው የምገልጸው የአሮን በትር መለምለሙ የኢየሱስን ትንሳኤ ይመሰክራል፤ ትንሳኤ ራሱ መኖሩን ይመስክራል የሚል ነው።ው.ማርያም ደግሞ በትሩ ማርያም ነው(ናት) እያለ ነው። ይህ የተለመደ ነው በአንድ አፍ ሁለት ምላስነት።
የኢየሱስን እናት ፦ለጌታ የተለየችዋን ፤የኖረችዋን ፤ብፅዕት ድንግል ማርያምን አትሳደቡ!!
1.3 'ማርያም' የዓለም መድኃኒት ናት ?
"እመቤታችን የዓለም ሁሉ መድኀኒት አድርጎ እንደ ፈጠራት ልብ አድርጋችሁ እነሆ እወቁ" (ተአምሬ ማርያም 1989 ዕትም)
የእግዚአብሔርን ቃል አስተውሉ ማመን ከመስማት ነው መስማትም የእግዚአብሔርን ቃሉን ነው ትልቁ መጽሐፍ እንደሚል። ተመልከቱ ፦
፨የኢየሱስ መወለድ እንጂ የማርያም መወለድ አልተነገረም ኢሳ7፥14፣
፨ኢየሱስ እንደሚወለድ ገብርኤል አበሰረ እንጂ የማርያምን አይደለም ሉቃ1፥32 ፣
፨በኢየሱስ ውልደት መላእክት ከሰማይ ወርደው ዘመሩ እንጂ በማርያም ውልደት አይደለም ሉቃ 2፥9 ፣
፨መላእክቱም ኢየሱስን የዓለም መድኀኒት ብለው መሰከሩ እንጂ ማርያምን አይደለም ሉቃ2፥10 ፣
፨ማርያምም ስለ ልጇ " ለራሷም ጭምር መድኀኒት እንደሆነ" እንጂ ስለራሷ መድኀኒትነት አልተናገረችም ሉቃ 1፥47፣
፨ዮሐንስ መጥምቁም ስለ ኢየሱስ የዓለም መድኀኒትነት እንጂ ሌላ አልጠቆመም ዮሐ1፥36፣
..
እንዲህ መጽሐፍ ሁሉ ስለ ኢየሱስ መድኀኒትነት ከመሰከሩ የኢየሱስን እናት " መድኀኒት ናት " ማለት አሽሙር ነው።
1.4 "ዮሴፍን የሚታጽናኝው/የሚታረጋግው/ አንቺ ነሽ"(ው.ማርያም ፤ቅዳሴ ማርያም )
እንግዲህ አስተውሉ ከላይ እንዳየነው 'ማርያም' በተለያየ ሁኔታ እየተገለፀች፦እንደረዳች ፤እንደሰራች እንደተናገረችም ብሎም እንደ ነበረች የሚገልጹትን አሽሙር የሆነውን ስድብ አይተናል ።እንደ ጸሐፍያኑ በተለያየ ሁኔታ የተገለጸችው 'ማርያም' አሁን ለዮሴፍ በየትኛው ሁኔታ እንደተገለጸች ጸሐፍው አይነግረንም ግን ስታጽናናው፤ ከጎኑ ሆና ስታረጋጋው ፦እንደ ነበረች ይተርካል ።
ዮሴፍ ካረጋጋች ፤ካጽናናች በምን ሁኔታ ተገልጣ ይሁን ያረጋጋችው? የሚለው የእኔ ጥያቄ ነው፤ ምክንያቱም ለአንዳንዶች በተለያየ ሁኔታ 'እንደተገለጸች ስላየን' እንደ ጸሐፍያኑ።ከዚህ በፊት "ማርያም ከመወለዷ በፊት ነበረች ፤ አለች፤ዕድሜ አይቆጠርላትም ብለው ያምናሉ" በማለቴ፥ "ምሳሌ አታቅም እንደ!" ?ቆጣ ብለው ያሉትን አይቻለሁ እና አሁን ተመልከቱ፦
መጀመሪያም ምሳሌ አልነበረም እንደ ጸሐፍያኑ ከሆነ ያለች የነበረች የሚትኖር እንደሆነ በማመን ይሰብካሉ ፤ ዮሴፍ ታጽናናለች ማለት በመንፈስ ከእሱ ጋር በውስጡ ሆና(ወይም ከጎኑ ሆና) እንደ 'መንፈስ ቅዱስ' እያጽናናች ናት ማለት ነው።በዮሴፍ ዘመን ካልነበረች የት አግኝታ ታጽናናለች ታረጋጋለች ? ይህ ምሳሌ ነው?ጥላና አካል ነውን ?
እንግዲህ እንደ ደራሲያኑ ፍጡር ናት ማለት በዚህ አካሄድ ይከብዳል ነገር ግን መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ዮሴፍ ስደት እና መከራ እንድሁም ማን ከእሱ ጋር እንደ ነበረ በአንድ ጥቅስ ስገልጽ፦ “እግዚአብሔር ከዮሴፍ ጋር ነበረ፥ ሥራውም የተከናወነለት ሰው ሆነ፤ በግብፃዊው ጌታውም ቤት ነበረ።”— ዘፍጥረት 39፥2
በመድኃኒቴ በጌታዬ በኢየሱስ ክርስቶስ እናት ላይ ተነስቶ የነበረ/ ወይንም የሚነሳ/ ስም የማጥፋት አሽሙር እቃወማለሁ !! እኔስ የኢየሱስ ክርስቶስ እናት ብፅዕት ማርያም ጋር ባላጋራ ነኝ።
1.5 'ቅዱሳን ማርያምን' አንክድም ብለው መከራ ተቀበሉ ?
"ጻድቃን ስምሽን በመውደድ ተጋደሉ ።ሰማዕታትም ስለአንቺ ደማቸውን አፈሰሱ (እንዚራ ስብሐት ፤መምህር ተስፋ ሚካኤል ታከለ 2007 ዓ.ም ገጽ 129)
እንደዚህ ጻሐፍ ከሆነ <<<'ቅዱሳን ማርያምን' ይሰብካሉ ማለት ነው።'ማርያምን ' ስሰብኩ ብዙ መከራ፤ እንግልት ፤ስቃይ ይደርስባቸዋል እስከሞት ድረስ በነፍሳቸው ተወራርደው አንክዳትም ብለው ሰማዕት ሆኖዋል ማለት ነው።>>
እንዲሁም አንድ 'መዝሙር' አስታውሳለሁ ፦
"ሮማዊ ነኝ ፍጹም ክርስቲያን
ከእመቤቴ ፍቅር የሚለኝ ማን ነው?
መከራ ነው ችግር ወይስ እስራት ነው ? " የሚል ዘፈ-ሙር።
ሁለቱን እንደ እግዚአብሔር ቃል እንያ፦
“በሁሉም ስለ ስሜ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ፤ እስከ መጨረሻ የሚጸና ግን እርሱ ይድናል።”— ማቴዎስ 10፥22
፨ መጽሐፍ ቅዱስ ስለኢየሱስ ስም እንጂ ስለማርያም ስም እንደሚንጠላ በጭራሽ አይናገርም ፣
፨ ኢየሱስ የሚለውን ስም(ማንነት) እንጂ ማርያም ለሚለው ስም መከራ አልተቀበሉም ፣
“መዳንም በሌላ በማንም የለም፤ እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና። — ሐዋርያት 4፥12
፨በኢየሱስ ክርስቶስ ስም መስበካቸው ብቻ ሳይሆን ሌላ አማራጭ ከዚህ ስም ውጪ የለም ስሉ በድፍረት ስያጸኑ ስቆሙሙ እናያለን ፣
“ሰሙትም፥ ሐዋርያትንም ወደ እነርሱ ጠርተው ገረፉአቸው፥ በኢየሱስም ስም እንዳይናገሩ አዝዘው ፈቱአቸው።”— ሐዋርያት 5፥40
በኢየሱስ ክርስቶስ ስም በመስበካቸው መከራ ተቀበሉ እንዳይሰብኩም ተደረጉ፣ ግን እነሱ በነፍሳቸው ተወራርደው እንዲህ ይላሉ ፦
ሮሜ 8
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
³⁵ ከክርስቶስ ፍቅር ማን ይለየናል? መከራ፥ ወይስ ጭንቀት፥ ወይስ ስደት፥ ወይስ ራብ፥ ወይስ ራቁትነት፥ ወይስ ፍርሃት፥ ወይስ ሰይፍ ነውን?
³⁶ ስለ አንተ ቀኑን ሁሉ እንገደላለን፥ እንደሚታረዱ በጎች ተቆጠርን ተብሎ እንደ ተጻፈ ነው።
ስለዚህም ወንጌል የሚነገረው ስለስሙ ብቻ ሆኖ እያለ፤አሸፈረኝ ብለው ፤ሌላ ስም ጨምረው ፤ያልተጻፈ ሰብከው ፤ያልተጻፈ ዘምረው፤እንደት ቅዱሳን ተባሉ?የኢየሱስን እናት ትሁቷን ድንግል ማርያምን አቃልለው፤ እንዴት ያስችላቸዋል ? እንዴት ያሽሙራሉ ? ምን አጥፍታ ?ምን በድላ ? ከሌሎች ቅዱሳን ተለይታ ካለ ስም ስም በመስጠት ይሳደባሉ ? አሽሙር አቁም !
1.6 "አብ በሰማይ አይቶ እንዳንቺ አላገኘምና .." (ራቡዕ ው.ማርያም ቁ.1)
ይህኛው አገላለጽ አድስ አይደለም የተለመደ ነው።<<እግዚአብሔር አብ ሰውን ለማዳን ልጁን ለመላክ አስቦ እናት የሚትሆን ሴት ፈልጎ ወደ ምድር ስመለከት በምስራቅ በምዕራብ በሰሜን በደቡብም እንዳንቺ ያለ ሴት አላገኘም>> የሚል ነው።እንደ እሷ ያለ አላገኘም ማለት የተገኘችዋ ለእናትነት በራሷ ብቃት ንፁህ ሆና በቂታ ተገኝታለች ለማለት እንደሆነ ያስተውሏል ።
ፀጋን እስኪ እንያ ፦ፀጋ ነፃ ስጦታ ሲሆን ከሰጪው ፈቃድ ፤ማንነት የተነሳ፤ የተሰጠ ነፃ ስጦታ ማለት ነው።
ወደ ሀሳቤ ከመግባተ በፊት ይህን እንድትገነዘቡልኝ እፈልጋለሁ።አንዳንድ አማኞች አሁንም እንዲህ ይላሉ <<ይህን ፀጋ ለማግኘት ይህን ያህል ቀን ጾምኩ፣ ፀለይኩ ከዛ አገኘሁ>>ይላሉ ።ሌሎች ደግሞ <<አንዱን ፀጋ መርጠው ይህን ፀጋ ስጥ ጌታ ሆይ በማለት ተቀበልኩ >> የሚሉ እልፍ ናቸው ።ብቻ ስህተት ነው። ምክንያቱም ፀጋ በሰው ጥረት በፀሎቱ ብዛት እንዱሁም በሰው ምርጫ የሚሰጥ አይደለም ።እንዱሁ የተሰጠ ነፃ ስጦታ ነው እንጂ።በነገራችን ላይ <<ፀጋ ለመቀበል ይህን ያክል ጾምኩ ፀልየኩ፤ከዛ ተቀበልኩ>>ከማለት የተሰጠኝን ፀጋ ለማወቅ ፆምኩ ፤ጸለይኩ ብባል ያስኬዳል እላለሁኝ።
ወደ ሀሰቤ ስገባ በእውነት እግዚአብሔር ከሰማይ ስመለከት በፊቱ ልቆም የሚችል ሰው ተገኝቶ ነበር?
መዝሙር 14
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
² የሚያስተውል እግዚአብሔርንም የሚፈልግ እንዳለ ያይ ዘንድ እግዚአብሔር ከሰማይ የሰው ልጆችን ተመለከተ።
³ ሁሉ ዐመፁ በአንድነትም ረከሱ፤ በጎ ነገርን የሚሠራ የለም፤ አንድም ስንኳ የለም።
መጽሐፍ እንደሚል እግዚአብሔር አስተዋይን እና ራሱን የሚፈልግ እንደለ ለማየት ከሰማይ ወደ ምድር ስመለከት ፦አይደለም አስተዋይ ልገኝ ጭራሽኑ እግዚአብሔርን ሁሉም የሚሳደቡ እንደሆኑ ነበር ያገኘው/የተመለከተው/። እንድሁም ጭራሽኑ "የረከሱ ነበሩ" ይላል ልዑል ።
እግዚአብሔር አስተዋይን እና ራሱን የሚፈልግ ፈልጎ አገኘ ማለት ፃድቅ ተገኘ ማለት ነው።ግን አልተገኘም።ካልተገኘ ፦ሁሉም እርኩስ ናቸው ማለት ነው።ባለመገኘቱ " ሁሉም የሰው ልጆች የረከሱ ናቸው" መጽሐፍ ማለቱ ትክክል አይደለም ትላላችሁ ?
ደግሞም ቅዱስ ያሬድ የተናገረውን ስንመለከት ፦
"ሥጋዋን አንጽቶ፣እርሷን ቀድሶ፣በእርሷ ላይ አደረ" (ድጓ.ዘፍልሰታ ኪ.ምህረት)
ቅዱስ ያሬድ ለምን ቀደሰ (ለየ) ይላል? ከምን ቀደሰ የሚል ይመስላችኋል ? ደግሞም ሙሉን ማንነቷን (እርሷን) ቀደሰ የሚለው ከምን ቀደሳት ?ለምን የቀደሳት ይመስላችኋል ? ለምን ዝም ብሎ በቁ ሰው ሆና ከተገኘች አይመጣም ነበር ?
በተጨማሪም ወንገላዊ ሉቃስ እንደመዘገበውም በም.1 በቁ.35 "..የልዑል ኀይል ይጸልልሻል " ማለቱ ለምን ይመስላችኋል ? መጸለል ማለት መጋረድን ወይንም መሸፈንን ይገልጻል ።ታድያ የልዑል ኀይል ማህፀኗን ከምንድነው የሚጋርደው? ከማህፀኗ ምን እንዳይተላለፍ ? ባይጋርድስ ? ከዚህ በፊት ለሌሎች ሴቶች ያልተደረገው የማህፀን መጋረድ ለእሷ ለምን ሆነ ? የመንፈስ ቅዱስ መምጣቱ ፤የልዑል ኀይል መጋረዱ ንፁህ ካልሆነው ሰው ንፁሁ ሰው ለማስገኘት አይመስላችሁም ? ነው።
ወገኖቼ የኢየሱስ እናት ብፅዕት ማርያም ኢየሱስን የፀነሰችው ፣የወለደችውና ያቀፈችው ከራሷ ብቃት የተነሳ አይደለም ማለትም ሃጢያት ስለለባት አይደለም (ሃጢአተኛ ናት) ወይም ድንግል ሆና ስለተገኘች ሳይሆን ከጠሪው ከእግዚአብሔር የተነሳ ብቻና ብቻ ነው። “መልአኩም እንዲህ አላት፦ ማርያም ሆይ፥ በእግዚአብሔር ፊት ጸጋ አግኝተሻልና አትፍሪ።” — ሉቃስ 1፥30።ማርያም ያገኘችው ጸጋ (ነፃ ስጦታ) ነው።ጸጋ ደግሞ ለማይገባው የምሰጥ ነፃ ስጦታ ነው።ጸጋ ከሰጭው ቸርነት እና ፍቅር እንጂ ከተቀባዩ አይደለም ።
እውነት እውነት ከተነጋገርን ማርያም የኢየሱስ እናት ለመሆን የምያበቃት ምንም ነገር የላትም ይህ መዳፈር አይደለም ።መላአኩ ቅዱስ ገብርኤል "ከእግዚአብሔር ዘንድ ጸጋ አግኝተሻል" እንጂ ያላት መስፈርት አሟልተሻል አላላትም ። መስፈርት አሟልታ ወይም ከስራዋ ከሆነ ጸጋ አይደለም ። “በጸጋ ከሆነ ግን ከሥራ መሆኑ ቀርቶአል፤ ጸጋ ያለዚያ ጸጋ መሆኑ ቀርቶአል።” — ሮሜ 11፥6። መጽሐፉ ስከፈት" አንድም በቁ ሰው አልተገኘም"የሚል ነው።እናቱን እወዳታለሁ አልሳደብም!!
1.7 "አምላክን የወለድሽ እመቤታችን ሆይ ትውልድ ሁሉ አንችን ብቻ ያመሰግኑሻል" (ራቡዕ ው.ማርያም ቁ.2)
ብዙ ግዜ የራስ ጓዳ ሳይፈተሹ የሰውን መጠቆም ዋጋ ያስከፍላል ። <<አንድ ሰው የዘላለም ሕይወት እንድኖረው ከድንግል ማርያም በስጋ የተወለደውን የናዝሬቱን ኢየሱስን በማመን ማለትም ስለእኔ ተወልዷል፣ስለእኔ ተገርፏል ፣ስለእኔ ተስቅሏል፣ ስለ እኔ ሞቷል፣ ስለእኔ ተነስቷል ፣ብሎ የሚያምን ከሆነ በስጋ የመጣውን ኢየሱስን ፦የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ የሚቀበል ከሆነ ፤ይህንን በማመኑ ብቻ የዘላለም ሕይወት አለው>> መጽሐፍ እንደሚል በማለታችን ፥ "እምነት ብቻ "የሚል አስተምህሮ የለም? ብቻ የሚል ከየት አመጣችሁ "?ይላሉ። በዚህ ላይ ስለ ብቻ ላብራራ አይደለም ። የራሳችሁን የላይኛውን ሀሳብ "ብቻ" የሚለውን ቃል እያሰላሰላችሁ ጎስጉሱ ለማለት ያክል ነው እንጂ።እንደ እውነቱ ከሆነ በእርግጥም የዘላለም ሕይወት በእግዚአብሔር በተላከው በክርስቶስ በማመንና በማመን ብቻና ብቻ ነው።
ወደ ሀሳቤ ስጠልቅ "ትውልድ ሁሉ" ከአዳም ጀምሮ ያለው ማለት ነው፤ "አንቺን ብቻ ያመሰግኑሻል " ስባል ፤በቃ አበቃ ጉድ በል ጎንደር ማለት አሁን ነው ። ትውልድ ሁሉ እሷን ብቻ የሚያመሰግኑ ከሆነ ፦እሷ ምንድናት? ሌላ የሚመሰገን በትውልድ የሚወደስ ለትውልድ እንዴት ጠፋ? እሷስ ምን ስለሰራች ነው? የእውነት እናከብራለን ብቻ ማለት ይቻላል በዚህ ህሳብ ? አምላክ ማን ነው?(አምላክ ማናት ለማለት እየተገደድኩ ነው)፤ለምንድነው የማይመሰገነው?
መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል ፦
“የባሪያይቱን ውርደት ተመልክቶአልና። እነሆም፥ ከዛሬ ጀምሮ ትውልድ ሁሉ ብፅዕት ይሉኛል፤”— ሉቃስ 1፥48
፨ እናቱ ከኤልሳቤጥ ጋር ከተገናኘችበት ቀን ጀምሮ ያለው ትውልድ፦እናቱን "የተባረከች ናት ይሏታል" ምክንያቱም መጽሐፉ የሚለው ከዛሬ ጀምሮ እንጂ ከመጀመሪያም ብፅዕት ናት ተብላ ትመሰገን ነበር አይልም፣
፨ "ከዛሬ ጀምሮ "ከተባለ ከተናገረችበት ቀን አንስቶ እንጂ ከመጀመሪያም ማለት አይደለም ፣
፨ ''ከዛሬ ጀምሮ የተባረከች ናት ይሉኛል'' ስትል ከዚያች ቀን በፊትም የተባረከች ናት ማለት አይደለም ።
፨ ''ከዛሬ ጀምሮ የተባረከች ናት ይሉኛል'' ስትል ከዚያች ቀን በፊት በሕዝቡ ዘንድ የተዋረድኩኝ ነበርኩኝ ማለቷ ነው እንጂ፣
፨ ''ከዛሬ ጀምሮ የተባረከች ናት ይሉኛል'' ስትል የዛሬን ቀን ፦ከዛሬ ጀምሮ በማስባል ታርከን የቀየረው እሱ ናት እያለች ነው እንጂ፣
እንደ ውዳሴ ማርያም ጸሐፍ ከሆነ ትውልድ ሁሉ አንቺን ያመሰግናሉ ማለቱ ብቻ ሳይሆን ችግሩ""አንቺን ብቻ ያመሰግኑሻል "" የሚለው ጭምር ነው። ብሉም ግን በኢየሱስ እናት ንግግር ብቻ የከሸፈ ሆኗል ።
"..አንቺን ብቻ ያመሰግኑሻል " የሚለውን ስመለከት አሽሙሩ አናድዶኛልና በአንድ ጥቅስ ብቻ የእናቱን ክብር ልመልስ አሽሙሩን በማስወገድ፦
“ሃሌ ሉያ። እግዚአብሔርን ከሰማያት አመስግኑት፤ በአርያም አመስግኑት።” — መዝሙር 148፥1።ስለዚህም ትውልድ ሁሉ 'ማርያምን' ብቻ ያመሰግናሉ የሚለው አሽሙር እንደሆነ አውቀዋል።አትሳደቧት።አሽሙር አይገባትም።ብፅዕት ናትና።የሚለው መልእከተ ነው።
1.8 የነነዌ ሰዎች 'በማርያም' ምክንያት ከመጣው መቅሰፍት ተረፉ ?
"..የነነዌ ሕዝቦች በአንቺ ይቅር ተባሉ ፣ከመገልበጥ በአንቺ ዳኑ ፣በአንቺም ከመጥፋት ዳኑ " (እንዝራ ስብሃት ፣መምህር ተስፋ ሚካኤል ታከለ 2007 ዓ.ም ገጽ 134 )
አሽሙሩ ቀጥሏል።ነነዌ ከተማ ዛሬ ላይ ስለመኖሩ ማረጋገጥ አዳጋች ነው ።ይህንን ታርክ በዮናስ መጽሐፍ እናገኛለን ።ግን ዮናስ በመጽሐፉ ምን ብሎ መዘገበ ? ተመልከቱ ፦
ዮናስ 3
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁵ የነነዌም ሰዎች እግዚአብሔርን አመኑ፤ ለጾም አዋጅ ነገሩ፥ ከታላቁም ጀምሮ እስከ ታናሹ ድረስ ማቅ ለበሱ።
…
¹⁰ እግዚአብሔርም ከክፉ መንገዳቸው እንደተመለሱ ሥራቸውን አየ፤ እግዚአብሔርም ያደርግባቸው ዘንድ በተናገረው ክፉ ነገር ተጸጽቶ አላደረገውም።
ስለዚህ እንደ መጽሐፍ ቅዱስ የነነዌ ሰዎች መትረፋቸው በእግዚአብሔር ማመናቸው ሲሆን ማመናቸውንም ወደ እግዚአብሔር በመመለስ በንስሓቸው አሳዩ/አረጋገጡ/ ።
እንግዲህ ከዚህ በላይ ስም ማጥፋት እግዚአብሔርንም የእግዚአብሔር ባሪያ የሆነችዋን በግልጽ ማሾፍ አለ እንደ? በዚህ ሁሉ ግን የኢየሱስ የደሙ ምህረት ይደኝቀኛል።አሽሙር አቁሙ!! የሚለው መልእክተ ነው።
1.9 ፍጥረት ሁሉ ከመፈጠሩ በፊት 'ማርያም ' ነበረች ?
"ሰማይና ምድር ገና ሳይፈጠሩ የምድር ገነትም ገና ሳትሰራ ቅድስት ድንግል ማርያም አለች" (ዝክረ ቃል ገጽ 77 ፣2005 ዓ.ም )
ከላይ በርዕሱ ማርያም ብዬ በኮማ ውስጥ ማስገባተን ስትመለከቱ የኢየሱስ እናት ድንግል ማርያምን አይወክልም ለማለት እንደሆነ ይረዷል።
ከዚህ በፊት አንድ የቃል እምነት ተከታይ የነበረ የfb frd<< የሰው ልጅ ከመፈጠሩ በፊትም ነበረ>>አለ፤እንደ እሱ ንግግር << ሰው በሥጋ ከመገለጹ በፊት በክርስቶስ ውስጥ ነበረ ፤ከዛ ሥጋው ተዘጋጀ ከዛ፤በሥጋው ውስጥ አደረ ፤ከዛ ታየ ተዳሰሰ በማለት እንደሚያምን በጹሑፉ ገልጾ ነበር፥ ያም ስህተት እንደሆነ ለማሳየት ጥረት አድርግያለሁ።>> የመጽሐፉ ጻሐፍ እና ተቀባይ የሆኑቱ የቃል እምነት አስተማሪ እና ተከታይ ናቸው። ማለትም መናፍቃን ናቸው እያልኩ እንደሆነ ይገነዝቧል። ምክንያቱም የሰው ልጅ ፍጥረት ከመፈጠሩ በፊት ከነበረ "በስድስተኛው ቀን እግዚአብሔር ሰውን ፈጠረ" የሚለው የመጽሐፉ ቃል ስህተት ይሆናል ።ደግሞም ሰውን ፍጡር ሳይሆን ፈጣር ያደርገዋልና መናፍቅነት ነውና ተጠንቀቁ ።
ወደ ሀሳቤ ስገባ "..አለች" እንደሚለው ቃል ከነበረች እንዴት ነው ያለችው? ለሚለው ጥያቄ ከዚህ በፊት የተለያየ ቁሳ ቁስ የተገለጸችው እሷ ናት በሚለው ጹሑፋቸው ተመልክተናል ።ስለዚህም ይህንን የቃል እምነት ትምህርት ለመቃወም ያልበቃች ቤተከርስቲያን እንደ ቤተክርስቲያን ምንድነው የሚትቃወመው ?መናፍቃንን ፦መናፍቅ ለማለት ይህ በቂ አይመስላችሁም ?
እንዱሁ በየዋህነት ይህንን ለማድበስበስ "እግዚአብሔር ወደ ፊት ለመፍጠር አስቦ ስላለ ታስባ ነበረች ማለት ነው" የሚሉም አይታጡም ።አስተውሉ ፦
በእርግጥም እግዚአብሔር በእቅድ የሚሰራ አምላክ ነው።በራሱ ግዜ የሚሰራ አምላክ ነው።ይህ ማለት ግን እግዚአብሔር ዓለምን ለመፍጠር አሰበ ስባል ዓለም መጀመሪያ የተፈጠረ፣ የነበረ ነው ማለት አይደለም ፤እግዚአብሔር ሰውን ለማዳን አሰበ ማለት በአሰበበት ግዜ አዳነ ማለት አይደለም ፤እግዚአብሔር ሰው ለመሆን አሰበ ማለት በአሰበ ግዜ ሰው ሆነ ማለት አይደለም ።ነገርግን በዘመኑ ፍጻሜ፤በራሱ ግዜ ለመስራት አቀደ ፤ግዜው ስደርስ ይፈጽማል ማለት እንጂ አትታለሉ ።
ከዓለም በፊት የነበረችው ፤ያለችው 'ማርያም' እኔ አላውቃትም ።እኔ የማውቃት የዳዊት ዘር የሆነችውን የኢየሱስን እናት ወንጌላውያን የመዘገቧትን ነውና አትሳድቧት። የሚለው መልእክተ ነው።
1.10 "በእውነቱ ስለ ስለቃልኪዳኗ ነውን?"እያልኩኝ ነው።
"ስለ እመቤታችን ስለቃልኪዳኗ በመጀመሪያይቱ ቀን ሰማያት ጸኑ።.. ስለእመቤታችን ስለቃልኪዳኗ ምድር በውሃ ላይ ፀናች።ስለ እመቤታችን ስለቃልኪዳኗ እግዚአብሔር በሰባተኛው ቀን ከሥራው ሁሉ ዐረፈ " (ድ.ኪ.ምህረት ገጽ 59/2010 ዓ.ም )
እንግዲህ ከፍጥረት አስቀድማ የነበረችው እንደ ገድላትና ድርሳናት ጸሓፍያን በተለያየ ሁኔታ የተጋለጠችው 'እግዚአብሔርን' ቃል አስገብታ" እንፈጥር "በማለት አስፈጥራ፤ በመጨረሻ " ደክመሃል እረፍ " በማለት ለማሰረፍ ጭምር መሃላ አስምላለች።እንደሚል ይመለከቷል ።
እንደ ጸሐፍያኑ ከሆነ እንድያርፍ ቃለ መሃላ ያደረገችውን ሳስብ የደራስያኑ' እግዚአብሔር ' ቃል ባታስገባ የሚያርፍ አይመስልም ። ደራስያን የረሱት ነገር ብኖር ከዓለም በፊት የነበረችው 'ማርያም ' መቼ እንደተፈጠረች አለመናገራቸው ነው ።ወይንም የማትፈጠር ዘላለማዊ እንደሆነች አለመጻፋቸው ትንሽ የደበቋት ይመስለኛል ።ወደ ቃል ኪዳኑ ስገባ ደራስያኑ መቼ እና በምን ምስክርነት መሃላ እንደ ገቡ ?ለምን መሃላ እንዳስፈለገ እና አለመግለፃቸው ትንሺ አሳስቦኛልii ።
አሁን ስለቃል ኪዳን ላብራራ አይደለም።እግዚአብሔር ግን ወድዶ ፈቅዶ ማንንም ሳያማክር የሰራውን የእጁን ስራ ጥላሽት በመቀባት አምላካችንን ድኩም ስላደረጉት ሃዘኔን ልነግራችሁ ነው እንጂ።
ምንም ነገር በሌለበት እግዚአብሔር መፍጠር ከመጀመሩ በፊት “..፤ የእግዚአብሔርም መንፈስ በውኃ ላይ ሰፍፎ ነበር።” ዘፍ 1፥2 ።ይላል እንጂ የእግዚአብሔር መንፈስ እና የማርያም መንፈስ ወይንም የሰው መንፈስ ሰፊፎ ነበር አይልም፣
በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ፈቃድ ሰውን እንፍጠር በማለት ፈጠረ እንጂ ማንንም አላማከረም።መጽሐፍ እንደሚል ፦
ሮሜ 11
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
³⁴ የጌታን ልብ ያወቀው ማን ነው?
³⁵ ወይስ አማካሪው ማን ነበር? ወይስ ብድራቱን ይመልስ ዘንድ ለእርሱ አስቀድሞ የሰጠው ማን ነው?
³⁶ ሁሉ ከእርሱና በእርሱ ለእርሱም ነውና፤ ለእርሱ ለዘላለም ክብር ይሁን፤ አሜን።
“እግዚአብሔርም ያደረገውን ሁሉ አየ፥ እነሆም እጅግ መልካም ነበረ። ማታም ሆነ ጥዋትም ሆነ፥ ስድስተኛ ቀን።” — ዘፍጥረት 1፥31።አምላካችን ያደረገውን ማለትም ብቻውን ያደረገውን አሁንም ብቻውን ተመልክቶ "እጅግ መልካም ነበረ" አለ እንጂ << ' እግዚአብሔር' ያስደረገችውን ሁሉን አየ>> አይልም ።''አማካሪዋ ናት ''እንደሚሉት መጽሐፍ ቅዱስ አይልም።እነሆ እጅግ መልካም ነበረ አለ ራሱ ብቻው ተመልክቶ ።
ብቻ ይህ ሁሉ የመናፍቃን አካሄድ የእግዚአብሔር አምላክነት በመደበቅ ፍጡርን በማጉላት ፦ፈጣር በማድረግ፤ እንድትጠፉ ለማድረግ ፤እንደሆነ አውቃችሁ ብያንስ ልባችሁን አስመልጡ።የሚለው መልእክተ ነው።
ማጠቃለያ
በዚህ በአጭር ማስታወሻ ላይ እንደገለጽኩት ማርያምን እናከብራለን የሚሉቱ ከማክበር አልፎ ወደ ማምለክ ከዚያም ካለ ስም ስም በመስጠት እግዚአብሔርንና የእግዚአብሔር ባሪያ የሆነችውን የኢየሱስን እናት እስከ መሳደብ የተደረሰውን ለማሳየት ሞክርያለሁ።በዚህ ነገር ላይ ማርያምን እናከብራለን የሚሉ እንደምያመልኩ ብሎም እንደ ሚሳደቡ አንድ ልቤ ሰፊ የቋንቋ ተማር የሆነ ብቻ እንደሚረዳው አልጠራጠርም ።
የኢየሱስን እናት ማርያምን "ትሳደባለህ" ባለማወቅ ለምሉኝ እንደማልሳደብ በማሳየቴ ትንሽ ጮራ የፈነጠቀ ይመስለኛል ።ይልቁንም ትሳደባለህ የሚሉኝ ባለማወቅ በስድብ እንደሚያጠረገርጉ በግልጽ በማሳየት ያሳፈርኩኝ ይመስለኛል ።
ቃሉ እንደሚል “እንግዲያስ እምነት ከመስማት ነው መስማትም በእግዚአብሔር ቃል ነው።”— ሮሜ 10፥17 ።አንዳንዶች "ዋናው በእምነት መጽናት ነው" ይላሉ።በእርግጥ ትክክል ነው። ግን " ዋናው በእምነት መጽናት ነው" ለማለት ትክክለኛ አምላክን በትክክለኛ ክብሩ፤ ማንነቱ ሳያውቁ ፤አደበላልቀው በማምለክ "ዋና መጽናት ነው" ብባል መጨረሻው አያምርም።ይልቁንም ቁልቁል ይወስደናል ። "ዋናው መጽናት ነው "ብሎ መጽናትም በእግዚአብሔር ቃል ከሆነው ፤በሆነው ፤እምነት ነው እንጂ በተደበላለቀው አይደለም ወይንም በተቋም መሰንበትም ማለት አይደለም ።
“ወዳጆች ሆይ፥ መንፈስን ሁሉ አትመኑ፥ ነገር ግን መናፍስት ከእግዚአብሔር ሆነው እንደ ሆነ መርምሩ፤ ብዙዎች ሐሰተኞች ነቢያት ወደ ዓለም ወጥተዋልና።”— 1ኛ ዮሐንስ 4፥1 ።ሰይጣን የብርሃን መላአክ መስሎ ይመጣል ግን ብርሃን አይደለም ።ብርሃን የምመስሉ ትምህርቶችን የእግዚአብሔር ቃል ነው ተብሎ የሚታወጁትን ፤በእግዚአብሔር መንፈስ በመርመር አጣርተን ፣አላምጠን ፤ልንውጠው ይገባል እንጂ ሁሉንም የእግዚአብሔር ስም ስለተጠራ በመዋጥ መታለል የለብንም ።ብዙ ግዜ ከላይ ያለውን ጥቅስ 'በነብይነት መንፈስ ' እናገለግላለን ለሚሉት እንጠቅሳለን እንጂ በሙሉ አናስተውልም ምክንያቱም ነብይ ማለት ለእኛ የወደፊቱን የሚተንበይ ብቻ ስለሚመስለን።ነብይ ማለት ግን የእግዚአብሔርን ቃል የሚናገር ማለት ነው።
“ይህም ድንቅ አይደለም፤ ሰይጣን ራሱ የብርሃንን መልአክ እንዲመስል ራሱን ይለውጣልና።”— 2ኛ ቆሮ 11፥14።ካላይ እንደገለጽኩት ፦
፨ሰይጣንን ወደ ጨለማ የሚያመራ እራሱ ጨለማ ነው። ነገር ግን ስመጣ እኛ ልንቀበል በሚንችለው ብርሃን (ትክክለኛ) ትምህርት ይመጣል ።ይህም ለእኛ ትክክለኛ ትምህርት ልመስለን ይችላል ግን ሀሰተኛ ምስክርነት እንደሆነ ማወቅ አለብን።"ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ ነው "ስላለ ፥ እኛም የሚንቀበል ትምህርት ስለሆነ ብቻ መቀበል የለብንም።ይህ ቃል የወጣው ከማን ነው? በማለት ምንጩን ልናውቅ ይገባል ።ምክንያቱም ይህንን የሚለው አገባቡን ለማሳመር ፤በማሳመርም በራሱ እግር ስሪ ለመጣል እንጂ ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ልያመጣችሁ አይደለም ።
፨ ብርሃን እስከሚመስል ስል ብርሃን አይደለም ግን ይመስላል ማለት ነው።አብዛኛው ማህበረሰብ ያለው በእውነት ሳይሆን እውነት በሚመስል ነገር በመጣበቅ ነው።ይህም የእግዚአብሔርን ቃል ካለማወቅ የተነሳ ነው።
፨ ራሱን እየለወጠ ይመጣል ስባል አካላዊ ለውጥ ማለትም ጥቁር ከሆነ ነጭ፣ ቆንጆ ብቻ አድርገን በአካል አስበን ከሆነ የሚንወድቅ ይሆናል ።የሚመጣው በተለያየ በአለም በሚያማምሩ ነገርች ብሆንም ሰይጣን ግን መንፈስ ነው።የሚመጣው ከኢየሱስ ክርስቶስ ልያርቅ በሚችል መንገድ እንጂ ብርሃን የሆነ አካላዊ መላአክ አትጠብቁ።በትምህርት እንደሚመጣ አስተውሉ ለማለት ያክል ነው።የመጀመሪያ ሰው በሀሰተኛ ትምህርት ከእግዚአብሔር እንደለየሁ ካስተዋላችሁ ይህኛው ማለትም ሀሰተኛ ትምህርት ወደ ኀጥአት የሚወስደው ትልቁ በር እንደነሆነ እወቁ ።ይህም ብርሃን የሚመስለው ሀሰተኛ ትምህርቱ ነው ።እውነት ከሚመስል ነገር ፤ብርሃን ከምመስል ነገር አምልጡ።
ዋቢ መጽሐፍት
፨ መጽሐፍ ቅዱስ የ1962 GC እትም
፨ መርጌታ ሙሴ መንበሩ፣ ነገረ ማርያም በመናፍቃን አንደበት ፣2013 ዓ.ም ዕትም
፨ ውዳሴ ማርያም (app)
፨ቅዳሴ ለማርያም (pdf )
፨ሃይማኖተ አበው (pdf )
እድሉ ዮሐንስ ጋምሳ ነኝ
(ደቀመዛሙርቱ )
Comments
Post a Comment