ኢየሱስ ክርስቶስ አሁን ፦ ሳይለምን ፣ ሳይቆም ፣ ተቀምጦ የሚያስታርቅ አማላጅ ነው።

 


ኢየሱስ ክርስቶስ ብቸኛ አማላጅ ነው።(1)

ኢየሱስ ክርስቶስ ከእግዚአብሔር አብ ጋር አማልዶ እንዳስታረቀ ክርስቲያን የተባሉቱ ሁሉ ያምናሉ ፣ይቀበላሉ ማለት ይቻላል ። የኢየሱስ ክርስቶስ ምልጃ  በሌሎች ፍጡራን የተኩ፦ "ኢየሱስ ክርስቶስ ከመስቀሉ፤ ከሞቱ በኃላ አያማልድም " ለሚሉቱ ሚልጃው ከሞቱ ከትንሳኤው በኃላ እንደቀጠለ ለማሳየት እኔም  የድርሻዬን ልወጣ ነው።ደግሞም " ኢየሱስ ክርስቶስ ከትንሣኤ በኃላ አምላክ ብቻ (መለኮት ብቻ ነው )"ማለት ኑፋቀ እንደሆነ ለማሳየትም የሚጥር ይሆናል ።  

እግዚአብሔር ቃል(ወልድ) ከድንግል ማርያም ማህፀን ስጋን ስካፈል አምላክነቱን አልጣለም፤ሰው ብቻም አልሆነም ፤ሰውነትን ደመረ እንጂ።ስለዚህም ክርስቶስ  በምድር ስኖርም ሙሉ ሰውም መለኮትም ነው።እግዚአብሔር ፦ አምላክ ሲሆን ለሰውነቱ ፤ ለዘላለምም ልጅነቱ ደግሞ አባት  ነው።ስለዚህም ነገር  ጌታ ስናገር ከትንሳኤው በኃላው ፍጹም ሰው ፍጹም አምላክ መሆኑን ስገልጽ፤የአብ የዘላለም አባትነትና  አምላክነት  ስገልጽ እንዲህ አለ “ኢየሱስም፦ ገና ወደ አባቴ አላረግሁምና አትንኪኝ፤ ነገር ግን ወደ ወንድሞቼ ሄደሽ፦ እኔ ወደ አባቴና ወደ አባታችሁ ወደ አምላኬና ወደ አምላካችሁ ዓርጋለሁ ብለሽ ንገሪአቸው አላት።” ዮሐንስ 20፥17 

ኢየሱስ ክርስቶስ ከትንሣኤ በኃላ መለኮት ብቻ ነው የሚሉት ባለማወቅም ነው፤ሆን ተብሎም ነው።ባለማወቅ የሚሉቱ መጽሐፍትን ካለማወቅ ለክርስቶስ የቀኑት መስሏቸው ነው።ሆን ተብሎ የተደረገው ደግሞ በኢኦተቤክ የታተመውን በተለምዶ 81 አሀዱ የሚባለው በ1954 ዕትም፤በ2000ዓ.ም ዕትም መጽሐፍ ላይ  ማየት ይቻላል ። ኤፌ 1፥3 ፤1ጴጥ 1፥3 ...።በነዚህና በሌሎች ክፍሎች "አምላክና አባት" የሚለው ቃል ከግሪክ ወደ አማረኛ ስተረጎሙት "አምላክ" የሚለውን በማጥፋት ነው በደል ያደረሱት ።ይህ ተራ ስህተት ሳይሆን ሆን ተብሎ የኢየሱስ ፍጹም ሰውነቱንና ፍጹም አምላክነቱን ለመካድ ነው፤በተለይ የኢየሱስ ፍጹም ሰውነቱን።የኢየሱስ ዘላለማዊ ፍጹም ሰውነት ማመን የኢየሱስ ክርስቶስ፦ የልቀ ካህናትነት ስራው  እንደሚቀጥል የሚያሳይ  ስለሆነ ለመካድም፣ ለማስካድም  ነው። 

የኢየሱስ ክርስቶስን ክህነት መጽሐፍ ስገልጽ ፦ የማይሻር ፣የማይለወጥ ፣የማይተካ ልቀ ካህናታችን እንደሆነ ይመሰክራል ።“እርሱ ግን ለዘላለም የሚኖር ስለሆነ የማይለወጥ ክህነት አለው፤”  — ዕብራውያን 7፥24።ደግሞም ከአሮጌው ክዳን ልቀ ካህናት እንደሚልቅ ከእሱም ሌላ የሚሻል ምርጫ እንደሌለ ስገልጽ “ቅዱስና ያለ ተንኮል ነውርም የሌለበት ከኃጢአተኞችም የተለየ ከሰማያትም ከፍ ከፍ ያለ፥ እንደዚህ ያለ ሊቀ ካህናት ይገባልና፤”— ዕብራውያን 7፥26። 

ኢየሱስ ክርስቶስ ስለእኛ የተሾመ ልቀ ካህናታችን ነው።ልቀ ካህናት ለመሆን ፦ ሰው መሆን ያስፈልጋል ፤ሰውን መምሰል ሳይሆን መሆን ያስፈልጋል ።ሙሉ ሰው ደም አጥንት ነፍስ ..  ደግሞም የሚራብ የሚጠማ ውሱን ድካም.. ያለው ሰው።ስለዚህም  ኢየሱስ ከትንሳኤ በኃላም ልቀ ካህናት ነው ካልን ሰውነቱን አልለቀቀውም ማለት ነው።ሰውነቱ በትንሳኤ ኃይል ለብሷል ግን ሥራው ቀጥሏል ። 

ምንም እንኳን በሰውነቱ ስራው ቀጥሏል ብልም እንደ ቀድሞው እየሰገደ ፣ እያለቀሰ ይለምናል ማለት አይደለም ። አንደ ባቀረበው መስዋዕት አብ ስለረካ በስራው  የሚያሙኑትን ሁሉን በእርሱ በኩል የሚመጡትን ይቀበላል ማለት ነው ።የአሮጌው ክዳን ልቀ ካህናት በየዓመቱ ብያቀርቡም ኢየሱስ ግን በየዓመቱ ማቅረብ አላስፈለገውም ምክንያቱም አብ ረክቷል።አብ ወዶ በእርሱ ከረካ አሜን ማለት ነው እንጂ የምን መቅበጥበጥ ነው ? የኢየሱስ ክርስቶስ ምልጃ ከትንሳኤው በኃላ ቀጥሏል።

የእግዚአብሔር ስም የማንነቱ መገለጫ እንጂ ከሌሎች ለመለየት ተብሎ የሚጠራ አይደለም ።የእግዚአብሔር ስም የእግዚአብሔርን ባህሪይ የሚያሳይ ነው።ኢየሱስ ክርስቶስ መድኃኒት ነው።ስሙ ፈውስ ይሰጣል ።ይህ ማንነቱ ነው።ጌታ ከመስቀል በፊት ስለ ወደፊቱ ስያስተምር ፦“እኔ ወደ አብ እሄዳለሁና፤ አብም ስለ ወልድ እንዲከበር በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ አደርገዋለሁ።”— ዮሐንስ 14፥13 ።

እንግዲህ ጌታ "ወደ አብ እሄዳለሁ" ያለው በመነጠቅ ሳይሆን ከመስቀል በኃላ በትንሳኤ እንደሆነ ይረዷል።ከትንሳኤ በኃላ በስሜ ብትለምኑትን ሁሉ አደርገዋለሁ በማለት ስለስሙ አንዳች ነገር እንደ ፈቃዱ ብንለምን ያለምንም ጥርጥር እንደምንቀበል ቃሉ ያረጋግጣል ።ቃሉ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እንድንለምን እንጂ ሌላ ፍጡር ስም ስለ እገሌ እንድንል አይጋብዝም ።ስለዚህም አንዴ ኢየሱስ ክርስቶስ በብቃት የምልጃውን ስራ ስለፈፀመ በስሙ የሚቀርብ ልመና ሁሉ ተሰሚነት እንዳለ ያረጋግጣል ።ማለትም በስሙ እንለምናለን መልስም እናገኛለን እንጂ ኢየሱስ ክርስቶስ በሰማይ እየሰገደ ይሰማለት/ላቸው አይልም ።

ኢየሱስ ክርስቶስ ስል ተራ መለያ ስም ሳይሆን ማንነት ነው።ይህም ማንነት ፈውስ ያስገኛል ።ስለ ማንነቱ መልስ እንደምናገኝ ይረዷል።ደቀመዛሙርቱ በስሙ ምንም ለምነው ስለማያውቁ እንደመውቀስ እንደማስተማር ጌታ እንዲህ አለ፦“እስከ አሁን በስሜ ምንም አልለመናችሁም፤ ደስታችሁ ፍጹም እንዲሆን ለምኑ ትቀበሉማላችሁ።” — ዮሐንስ 16፥24።ሙሉ በሙሉ ከጌታ የሆነ ነገር መቀበላችን የሚረጋገጠው በስሙ ብቻ በቀረበው ልመና እንደሆነ ያስውሏል።ይህንን ሐዋሪያ ዮሐንስ ጠንቅቀው ስለሚያውቅ ስለስሙ ይቅርታ የኀጢአት ስሪዬት አግኝቷቸዋል በማለት ይገልጻል ።“ልጆች ሆይ፥ ኃጢአታችሁ ስለ ስሙ ተሰርዮላችኋልና እጽፍላችኋለሁ።”— 1ኛ ዮሐንስ 2፥12። 

ኢየሱስ ክርስቶስ ሞቶ ከተነሳ በኃላ  በ 85-95 ዓ.ም ባለው የ1ኛ ዮሐንስ መልእክት እንደተጻፈ ይታመናል ።ኢየሱስ ክርስቶስ ገና ከመሰቀሉ በፊት በምድር ስመላለስ "በስሜ ለምኑ!"  "እስካሁን አልለመናችሁ!" ብሎ እንዳስተማረው ከትንሳኤው በኃላ ወደ ሌላ አካል ማለትም መዳፉ ላይ ምልክት ወደሌለው ወደ ሀሰተኛ ' ኢየሱሶች' ዮሐንስ አልለመነም።በሰው ሰው ከተማሩት፤ ልቅ ከሚባሉት በላይ፦ ዮሐንስ ልቅ እንደሆነ እሙን ነው።ዮሐንስ ልቅ ያደረገው ከታላቁ መምህር እግር ስር ቁጭ ብሎ መማሩ ብቻ አይደለም ። የመምህሩ  የቅርብ ቅርብ፤በመምምሩ የሚወደድ፤ደረቱ ጋ ተጠግቶ መናገርም ዮሐ 20፥21 መስማት የሚችል የተወደደ ባሪያውም ስለሆነም ነው። ታድያ ይህ በጌታ የተመረጠው ባሪያ ፤ከእግሩ ስር ቁጭ ብሎ የተማረው " በስሜ ለምኑ " እንደተባለው ስለስሙ ስሪዬት ሆኖላችኋል ስባል ለምን ለመቀበል ይጨንቀናል? ልቁ ማነው ? የተኛው እሙን ይሆናል ?ምን ጥያቄ አለው ሐዋሪያው ዮሐንስ ነው መልሱ።መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ የእውነት ሚዛን መጽሐፍ ነው።

ኢየሱስ ክርስቶስ ብቸኛ አማላጅ ነው።(2)

ምንም እንኳን ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ከትንሳኤ በኃላ ማስታረቅ እንዳቆመ እና ፍርድ እንደ ጀመረ ብያስተሚሩም ፥ማማለዱ ከትንሳኤ በኃላም እንደቀጠለ አሁንም እየሰራ እንዳለ ከመጽሐፉ ቅዱስ መረዳት ይቻላል ።“የሞተው፥ ይልቁንም ከሙታን የተነሣው፥ በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው፥ ደግሞ ስለ እኛ የሚማልደው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው።”  — ሮሜ 8፥34 ። ብዙ ግዜ ያከራክራል የሚማልደው የሚለው ቃል ፍች ።እስኪ እንያ።አድስ ክዳን ከግሪክኛ ቋንቋ እንደተተረጎመ ያውቋዋል።ከግሪክኛ ወደ ተፈለገበት በቀጥታ ይተረጎማል እንጂ ከግሪክ ወደ እንግሊዝኛ ከዛ ወደ አማረኛ አይተረጎምም።ምክንያቱም ከሰው ሰው እንደመስማት ሆኖ ልሸራረፍ ስለምችል ።ወደ የሚማልደው ቃል ፍች ስንገባ ፦ 

በመጀመሪያው የተጻፈው በግሪክ ቋንቋ  በመሆኑ መጠን ቃሉ እንዲህ የሚል ነው ፦ "ኢንቱግካይኔ " ።የቃሉ ትርጉም አንድ ግዜ የተሰራው የመስቀል ስራ ልቀ ካህናትነቱ የማስታረቅ አገልግሎቱ አሁንም በቀጣይም እንደሚሰራ የሚያሳይ አመልካች ቃል ነው።የሚማልደው የሚለውን ቃል ደፈር ብለው የሚፈርድው ብለውታል የኢኦተቤክ የ2000 ዓ.ም ዕትም በተለምዶ 81 አሀዱ የሚባለው ።ይህ መጽሐፍ ምንም እንኳን ሽምጥጥ አድርጎ የሚማልደው የሚለውን የሚፈርደው ብልም በግርጌው ላይ በመጀመሪያ ቋንቋ በግሪኩ የሚማልደው የሚል ፍች እንደሚሰጥ አስቀሚጠውታል።ታድያ ለምን ሽብር መፍጠር አስፈለገ የሚለው  ጥያቄ  ነው?። የሚፈርደው የሚል ቃል ከሆነ በግሪኩ "ክሪኖ" የሚል ቃል እንደሆነ ያውቋዋል ። 

"ኢንቱግካይኔ" የግሪክ ቃሉን ወደ እንግሊዝኛ ስተረጉሙት "make intercession" ብለውታል ።በአማረኛ በአቻ ቃሉ የሚማልደው ብለውታል ።በግዕዝ "ወይተዋቀሥ" ብለውታል ።በኢኦተቤክ በ1954 ዕትምም እንደዚህ ተተርጉሟል ።በ2000 ዓ.ም ዕትም ላይ ግን ተቀይሯል።ለመቀየር የታሰበው አልመች ብሏቸው እንደሆነ ይረዷል። 

ሮሜ 8፥34 ን የቅድስት ሥላሴ የግሪክ ቋንቋ አስተማሪ የነበረው መምህር ጌታቸው ተረፈ  በመጽሐፈ  መልህቅ ክፍል ሁለት ላይ ስተረጉሙት እንዲህ ብለውታል ፦

+ "የሞተው " ኢየሱስ ክርስቶስ አንድ ግዜ ስለሰው ልጆች መሞቱንና በድጋሚ የማይሞት መሆኑን የሚሳይ ነው።

+ "የተነሣው" የሰው ልጆች ጠላት የሆነውን ሞትን አሸንፎ መነሳቱን የሚሳይ ነው። የአንድ ግዜ ክንውን ነው።

+ "የሚማልደው" አሁንም የሚማልድ በቀጣይም ሚልጃው እንደሚሰራ የሚያሳይ ነው። 

በዚህ አጋጣሚ መጽሐፉን እንድታነብ እጋብዛለሁ ።ቀንጨብ አድርገ ስለወሰድኩ ሙሉ መጽሐፉን እንድታነብ አበረታታለሁ ።  ምንም እንኳን ጌታ ኢየሱስ በአብ ፈቃድ እንደ ፈቃዱ ባቀረበው መስዋዕት አብ ስለረካ ኢየሱስ ክርስቶስ ቁጭ ብሎ፤ ጎንበስ ቀና ሳይል ሳይለምን ሳያለቅስ ማስታረቁ እግዚአብሔርን እንድናመሰግን ያደርገናል እንጂ ሚልጃውን  እንድንክድ አያደርገንም ። በፍቅሩ ፦በመቀበሉ  ስለሥራው እንድንደነቅ ልያደርግ ይገባል እንጂ ጥያቄ፣ ጥርጣሬ መጫር የለበትም ።እንዲህ ሳይለምን የሚያስታርቅ ከሆነ አሜን ማለት ነው እንጂ ከግሪግም ከቀራንዮ ውርደት በላይ አድርጋችሁ በአዕምሮአችሁ ስንፍና አትጫሩ።  

የጌታ ሚልጃው ከትንሣኤ በኃላም እንደቀጠለ መስባክ ጳውሎስ ፈቃዱ "በእግዚአብሔር ልጅ " በሚለው መጽሐፍ ስገልጽ እንዲህ ብለዋል ፦ << የብሉይ ልቀ ካህናት ከቅድስተ ቅዱሳን ወደ ሕዝብ ስመጣ ብቻ ነው ምልጃውን የጨረሰው ።ኢየሱስ ክርስቶስ ስለእኛ አሁንም እያማለደ እንደሆነ ዕብራውያን 7፥25 ይገልጻል ።የብሉይ ሕዝብ ልቀ ካህናቱ ከመቅደሱ ወጥቶ ወደ ውጭ እስከሚወጣ እንደሚጠባበቁ የአድስ ክዳን ሕዝቡም  የጌታን መምጣት በናፍቆት እየተጠባበቀ ነው።>>ቀንጨብ አድርገ ወሰድኩ ስለዚህም ሙሉ መጽሐፉን ብታነብ ብዙ ታተርፋላችሁ እላለሁ ።

ከላይ አሁን፤ ጌታ ፍርድ እንደሚሰጥ የሚያስተምሩ እንዳሉ አይተናል።ግን አሁን እየፈረደ አይደለም ።ፍርድ የሚጀመረው ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ሕዝብ  ስመጣ ብቻ ነው።ይህም ደግሞ ጌዜ ስደርስ ነው።አሁን ያለነው በምህረቱ ስሪ ነው።ለዚህም ነው የምህረት ዓመት የሚባለው ።እንግዲህ በኢየሱስ ያመኑቱ ድኀነትን አሁን እንደሚቀበሉ ጌታ ስመጣ ደግሞ ስለመቀበላቸው እና ስላለመቀበላቸው እንደየስራቸው ያስረክባል ።አሁን ኢየሱስ ክርስቶስ እያስታረቀ ነው ሳይለምን።ግዜው ስደርስ ይፈርዳል ።ፍርዱ ይደርሳል አትቸኩሉ ።አሁን ራሳችሁን አስመልጡ በምህረቱ ግዜ በሚጠራበት ግዜ።የእሱን ስራ ለሌላ አትስጡ።ምክንያቱም መናፍቅነት ነው።ሃሌ ሉያ ለሥራው 

ኢየሱስ ክርስቶስ ብቸኛ አማላጅ ነው።(3)

ስለኢየሱስ ክርስቶስ ምልጃ (ሳይለምን የሚያስታርቀውን ) ለመማማር ስጽፍ ያረጀ የሙግት ጥያቄ በዚህ ዘመንም አሁንም መነሳቱ ገርሞኛል። መጽሐፍ ቅዱስ ከተጻፈበት ከመጀመሪያው ቋንቋ ስተረጎም የትርጉም ችግር እንደሚገጥም በቋንቋ ሙሁራን የሚታመን  ነው ።ይሁን እንጂ ብሉይ መጽሐፍትን ከእብራይስጥ፣ የአድስ ክዳንን መጽሐፍ ደግሞ ከግሪክኛ ቋንቋ ወደ ግዕዝ ቋንቋ ስተረጎም ሙሉ በሙሉ በአቻ ቃላት ልተረጉም እንዳቻለ የዘርፉ ሙሁራን ይመሰክራሉ ።ለኢኦተቤ ቤሎም ለሀገር ኩራት መሆኑ የማይካድ ሃቅ ነው። 

ወደ ርዕሱ ስገባ የ1954 ዓ.ም  ዕትም የሆነው የኢኦተቤክ  ሮሜ 8፥26፣27ን "ይማልድልናል" በማለት ተርጉመውታል ።ትክክለኛ ትርጉም ነው።ግን በ2000 ዓ.ም ዕትም የሆነው  በኢኦተቤክ የታተመው ግን ይፈርዳል በማለት ቀይረውታል ።ይህንን በግርጌው ላይ ይማልድልናል የሚል ትርጉም እንደሚሰጥ አስቀሚጠውታል።ታድያ መቀየሩ ለምን አስፈለገ የምለው ጥያቄዬ ነው ?

<<ለኢየሱስ ክርስቶስ መፍርድን ፥ ለፍጡር ልመና ስለተሰጠ >>ከዚህ አስተምህሮ ጋር ስለሚጋጭ በየግዜው የሚነሱ ጥያቄዎችን ለመመከት የተወሰደ እርምጃ እንደሆነ እሙን  ነው።ወንድም ዳንኤል ክብረት  ገድላትን እየቀየረ እየቀነሰ እየተካ እንደጻፈው(የኢትዮጵያዊው  ሱራፊ)፤የቤተክርስቲያን ልቃዊንትም ከመጀመሪያው ከእናት ቋንቋ ጋር አቻ ትርጉም ልሰጥ የማይችል ቃል በመቀየር በመተካት በመቀነስ 'ቅዱስ' መጽሐፍ ነው በማለት  ማዘጋጀት አግባብ አይደለም ።በየግዜው ለሚነሱት ጥያቄዎች አሁንም ለሚነሱት ጥያቄዎች ሳይቀንሱ ሳይበርዙ መመከት እንጂ ቃሉን መቀየር ደንታቢስነት ነው።መጀመሪያውኑ ያለውን አባቶች በግዕዝ ያስቀመጡትን በቀጥታ መጠቀም እየተቻለ ለራስ ለግል አስተምህሮ ግዜ ለወለደው ትምህርት ቃሉን እስከመቀየር መድረስ ያለንበት ቸልተኛነትን ያሳየናል ።ወየው ልቃዊንት።

በሰማይ ያለው የእኛ ፤የአማኞች ልቀ ካህናት ኢየሱስ ክርስቶስ አሁን ወደ ሕዝብ አልወጣም ማለትም እሱ ከመጣ ምልጃ ብሎ ነገር የለም።ምህረት ብሎ ነገር የለም።ፍርድ ብቻ ነው።አዎ ፈራጅ ነው ያላችሁት እንደየስራችን ለመፍረድ ይመጣል ።ላመኑበት ፍስሃ ።ላላመኑት ደግሞ ዋይታ ነው።ጌታ ኢየሱስ በአብ ፈቃድ በራሱ ፈቃድ   ልቀካህናት እንደሆነ ሁሉ አሁንም ልቀ ካህናት ነው ። አልተሻረም ።ጌታ ስሄድ "መንፈስ ቅዱስ ይመጣል" እንዳለው መንፈስ ቅዱስም መጣ።እውነቱኑም አረጋገጠ ።ኢየሱስ ክርስቶስ "መንፈስ ቅዱስ ብመጣ ይሻላል" አለ።መንፈስ ቅዱስ ደግሞ ኢየሱስ ብመጣ ይሻላል ብሎ ከእኛ ጋር ና ይላል።ና እንድንል ያደርገናል ።ራዕይ 22፥17።

መንፈስ ቅዱስን በእኛ ሆኖ የሚሰራውን ለመረዳት ጌታን መቀበል ያስፈልጋል ።ያለመቀላቀል ።እኔንም በብዙ ያዳግተኝ ነበር።ግን መንፈስ ቅዱስ በእኔ ውስጥ ሆኖ እንደሚረዳ የገባኝ፦ ፀሎት መጸለይ በማልችልበት ግዜ እንድጸልይ አንደበትን ስከፍት ነው።የጸሎት መጽሐፍ የሚለው ማንበብ ጸሎት መጸለይ የሚመስልብኝን፤ስያስጥለኝ፤ በእርሱ እገዛ ብቻ ስጸልይ ነው፦ የመንፈስ ቅዱስ እርዳታ የገባኝ።ሮሜ 8፥27ም።ስለዚህ ጌታ ያለ ቅራቅንቦ መመልከት እንድሆን(ላችሁ) ጸሎተ ነው።እንዲህ ይላል ቃሉ ፦ “እንዲሁም ደግሞ መንፈስ ድካማችንን ያግዛል፤ እንዴት እንድንጸልይ እንደሚገባን አናውቅምና፥ ነገር ግን መንፈስ ራሱ በማይነገር መቃተት ይማልድልናል፤”— ሮሜ 8፥26። 

ድካም አለብን ይህ ሃቅ ነው።ታድያ ምን ይሻላል ? መፍትሔ ምንድነው ? መንፈስ ቅዱስ ነው።በእኛ ውስጥ ሆኖ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ እንድንጸልይ ይረዳናል ።እንዲህ በል።እንዲህ በል ይለናል ።ምክንያቱም ሁሉም ልመና የእግዚአብሔር ፈቃድ አይደለም ።የእግዚአብሔር ፈቃድ ካልሆነ ደግሞ ጌታ አይሰማም ።አይመልስም ።ስለዚህ በእኛ ውስጥ ሆኖ ይለምናል ።አንድ ጌዜ የሚያደርገው ሳይሆን በምንጸልይበት ግዜ ሁሉ ።ያግዘናል ።<< ስለዚህም መንፈስ ቅዱስ በውስጣችን ሆኖ የሚያደርገውን ፣ጌታ ኢየሱስ በሰማያዊቱ መቅደስ ውስጥ ያደርጋል >>ጳውሎስ ፈቃዱ የእግዚአብሔር ልጅ ገጽ 355። 

ስለዚህ እዚህ በምድር ላይ በውስጣችን መንፈስ ቅዱስ ልረዳን ልያስታውቀን መጥቷል፤በፈቃዱ ይረዳናል ይቀሰቅሰናል ፣በሰማይ ያለው የልቀ ካህናችንን ፈቃዱም ይህ ነው።እግዚአብሔር እንዳንጠፋ ከእኛ ጋር በምድር መንፈስ ቅዱስን ፣በሰማይ ደግሞ እንድን'ሰማ የሚያደርግ የእኛ ሰው እንድቀመጥ ማድረጉ የሚደንቅ ፣ውብ ምስጥር ነው። እንጂ ስንፍና ልሆንብን በጭራሽ አይገባም ።  ሃሌ ሉያ 

ኢየሱስ ክርስቶስ ብቸኛ አማላጅ ነው።(4)

እስካሁን እያየነው ያለነው ፦ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ሳይለምን ከአብ ጋር የሚያስታርቅ  አስታራቂ  እንደሆነ ነው።ይህም አግራሞትን ውዳሴን ምስጋናን እንድናበዛ የሚያደርግ ነው። ተቀምጦ( ሳይቆም ሳይወድቅ )አንደ ባደረገው መስዋዕት የሚያማልድ እንደሆነ እያየን እንገኛለን ።ከዚህ ጋር ተያይዞ ያ የተለመደው የድሮ ሙግት ለሙግት የማይሆን ውሃ የማያነሳ ነጥብ እየተነሳ ይገኛል ።መልስ ለመስጠት ጥረት አደርጋለሁ ።

አሁን የምናየው ቃል "ማለደ" የሚለውን ነው።ወደ ርዕሱ ከመግባቴ በፊት ትንሽ ልንግደረደር።የቋንቋ ሙሁራን እንደሚሉት ከሆነ<< ተመሳሳይ ፊደል ያላቸው ግን የተለያየ ትርጉም የሚሰጡትን homonyms>> ይባላል  ይሉናል ።ለምሳሌ skate ፦ስባል የበረዶ ላይ መንሸረታቻ እቃ ነው  ።ሌላው ደግሞም  skate  ስባል ፊደል ሳይቀይር ራሱ ቃሉ የአሳ ዝርያ ማለትም ነው።ታድያ እንዲህ ያለ ነገር በእንግሊዝኛ ብቻ ሳይሆን በአማርኛችንም ያጋጥመናል ።ተጠቃሹም "ማለደ"  የሚለው ቃል ነው።እንዲህ ያሉት ቃላት ስገጥሙን ክፍሉ ስለምንድነው የሚያወራው በማለት አውዱን ማየት ያስፈልጋል ።ደግሞም የተተረጎመው መጽሐፍ ከሆነ ከመጀመሪያው ቋንቋ ማየት ሁነኛ መፍትሔ ነው።ይህ እኮ ልጋጭብን አይገባም ።ልቃዊንት በሞሉባት ሀገር።ለተንኮል ካልሆነ በስተቀር ማነኛውም የመጽሐፍ ቅዱስ አንባቢ ልረዳው ይችላል ።“አባቶቻችሁ ከግብጽ ምድር ከወጡበት ቀን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ፥ በየዕለቱ እየማለድሁ ባሪያዎቼን ነቢያትን ሁሉ ልኬባችሁ ነበር።”— ኤርምያስ 7፥25 ።እየማለድሁ የሚለው ቃል እየለመንሁ የሚል አይደለም በዚህ ቦታ ላይ።የመጀመሪያውን ስናይ በየግዜው በየጡዋቱ ማለት ነው።

ማለደ የሚለው ቃል ከላይ እንዳየነው መዝገበ ቃላትም እንደሚቀበሉት ጧት ኸዴ ፣ገሠገሠ፣ ለመነ፣ጉቦ ሰጠ በማለት abissinica መዝገበ ቃላት አስቀምጧል ።የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገብ ቃላትም 1.ጧት ተነሳ ማቴ 20፥21፤ሉቃ 21፥38 ። 2.አንዱ ስለላው ለመነ ሮሜ 8፥26፥34 "ምልጃ" ብለውታል ።መዝገብ ቃላት ሁለት ትርጉም ከሰጡን ፤ይህን ይዘን እንደ አውዱ ማየት ልባምነት ነው።ከዚያም የመጀመሪያ ቋንቋውን ወይም ግዕዝ ወይም እግሊዘኛውም ቸክ ማድረግ ብልህነት ነው።

ጌታ ስናገር".. በየዕለቱ እየማለድሁ.." ይለናል ።የቃሉ አውዱ በየጧቱ መገስገስን እንደሚሰጥ ከቀጣይዩ ንግግሩ መረዳት ይቻላል ።በየጧዋቱ እልካለሁ ።ማንን? ባሪያዎቸን ነቢያትን።መቼ ?በየጊዜው ።ነቢያት በየጧቱ በመሄዳቸው ምን ተፈጠረ ?“ነገር ግን አንገታቸውን አደነደኑ እንጂ አልሰሙኝም ጆሮአቸውንም አላዘነበሉም፤ አባቶቻቸውም ካደረጉት ይልቅ የባሰ አደረጉ።”— ኤርምያስ 7፥26 ።አልሰሙም። እንዲህ እንደ አውዱ ካልን እየማለዱሁ የሚለውን ቃል በእንግሊዝኛው በዚህ ቦታ ላይ daily rising up early ብለውታል ።እንደውም ይህ ግልፅ ነው። ታድያ ይህ እንዲህ ካየን ስለእኛ ይከራከርልናል፣ይሟገታል ፣ይለምናል የሚለው ትርጉም በጭራሽ አይሰጥልንም ኤር 7፥25።

እንዲህ ወደ ቃላት ጨዋታ መግባት አያዋጣም ። ኢየሱስ ክርስቶስ አንደ ባቀረበው መስዋዕት አሁንም እያስታረቀ ከጨለማ ወደ ብርሃን እየጠራ ፣ለራሱ እየማረከ ሕዝብን እያዳነ ነው።ይህንን መካድ አይቻልም ።አንድ ሙስሊም ወይም ቡድሂዝም .. ተከታይ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል ስራ ስያምን ማለትም ኢየሱስ ክርስቶስ ያነ የሞተው ስለእኔ ኀጢአት ነው ስለ እኔ በደል ነው ብሎ ስያምን ስቀበል፣ ደሙ አሁንም የዘላለም ሕይወት እንድያገኝ ያደርጋል ፤ከጨለማ ወደ ብርሃን በማውጣት መዳንን ይሰጣል ማለት ነው።ግን ኢየሱስ ክርስቶስ ወድቆ እየተነሳ አልለመነም  ።ስለዚህ ነው ኢየሱስ ክርስቶስ ሳይለምን ያስታርቃል የምንለው ።አንድ ግዜ በለመነው ልመና ከልመናው ጋር ባቀረበው መስዋዕት ያስታርቃል ።አሁን አሁንም እንደሚለምን እንደ ትኩስ ይሰራል ።እግዚአብሔር ረክቷልና።

ያስታርቃል የሚለው ቃል ብዙዎቹን አይጎረብጥም።ግን አማላጅ የሚለው ቃል ይጨንቃቸዋል።የሆነ የኢየሱስ ክብር የወረደ ይመስላቸዋል ። አማላጅ ከሚለው ቃል ይሉቁንም ያለ ጨርቅ (ያለ ፋንቲ) በእርቃኑ በአደባባይ መሆን አይከብድም ?ይህ አይጎረበጥም? አጥንት መቆጠሩ አይጎረብጥም? የሰው ለዚያውም የሚያስጠላ ምራቅ በፊቱ ማስተናገድም እያለ "አማላጅ" ሚለው ቃል እንዴት በልጦ ውርደት ሆኖ  ይጎረብጣል?።እንደ እውነቱ ከሆነ ሰዎች ልመና ብያቀርቡም ግዜያዊ መፍትሔ ብቻ የሚሰጡ ስለሆኑ ደግሞም ትውልድ መሻገር ስለማይችሉ ጉድለት አለ በልመናቸው ላይ።የኢየሱስ ግን ልመናው ተሰማለት ፣ደግሞም ዐነባ ዐለቀሰ፣ጮኸ ፣ምህረትን ለመነ ዕብ5፥7 ፤ታድያ ከዚህ በላይ ልመና ያቀረበ አለ? ይህ እኮ ውርደት አይደለም ።ፍቅር ነው።አሁንም የሚገልጸው ፍጹም ፍቅሩን ነው።ስንፍና አስወግዱ።

           ✍   ሃሌ ሉያ   🗣 

ኢየሱስ ክርስቶስ ብቸኛ አማላጅ ነው።(5)

ኢየሱስ ክርስቶስ እንዴት እንደሚያማልድ እስካሁንም ስንመለከት ነበር።የበኩሌን ተወጣው ማለት እችላለሁ።ኢየሱስ ክርስቶስ ሳይለምን ፣ሳይወድቅ፣ ሳይቆም፣ ቁጭ ብሎ እንደሚያስታርቅ የተገናዘባችሁ ይመስለኛል ።በዚህም ስራው ብቸኛ አማላጅ እንደሆነ ስመሰክር  ነበር።አሁን የሚጥረው  ከጥያቄዎቹ እየመለስን  ለመረዳት ነው።አንድ ሰው እንዴት ነው ጌታ ቁጭ ብሎ (ተቀምጦ )የሚያማልደውን ምልጃ ተካፋይ መሆን የሚችለው ? የሚለው እንመልከት ።

ያነ ኢየሱስ ስሞት እኔ አልነበርኩም ።ወንጌል እስከሚሰማ ድረስ ድኅነትን  ተካፋይ አይደለሁም ።ታድያ አንድ ሰው  ኢየሱስ ክርስቶስ ያኔ  አንዴ  ባቀረበው ምልጃ አሁንም የሚድነው እንዴት ነው? ወንጌል የሚሰበክበት ምክንያት ካወቅን ይህ አይጠፋብንም።የኢየሱስ ክርስቶስ ምልጃ አሁንም የሚሰራው ለምንድነው ? በእውነት እየሰራ ነውን? የማይሰራ ከሆነ በእርሱ ስራ  የተተካው ምንድነው ? 

የብሉይ አገልግሎትን  አሮጌ አድርጎ አድስ አገልግሎት የተጀመረው ፣የታወጀው የብሉይ  አገልግሎት ጉድለት ስላለበት ነው።የአድስ  ክዳን አገልግሎት በኢየሱስ ደም ተጀመረ ።ተፈፀመ ።እስካሁንም ሌላ ክዳን ሳያስፈልግ አድሱ ክዳን እየሰራ ነው።የብሉይ ካህናት ደካማ የሚሞቱ ስለሆኑ እነሱ ስሞቱ ሌላ ይተካል ።እንዲህ እየተደረገ በቁጥር ብዙ ሰው ልቀ ካህናት ሆኖ አልፏል ።መሞት ብቻ ሳይሆን ሕልናን የማያነፃ መስዋትም ስለሆነ በየዓመቱ መስዋዕት ይቀርባል ።የአድሱ ልቀ ካህናት  ኢየሱስ ክርስቶስ ሞትን ስላሸነፈ አይለወጥም አይተካም።መስዋዕቱም ራሱ ነው።መስዋዕቱ ፍጹም የሚያደርግም ስለሆነ ሌላ መስዋዕት በድጋሚ ማቅረብ አላስፈለገውም ።ብሉይ ክዳንን አሮጌ እንዳደረገው አድስ ክዳንንም አሮጌ የሚያደርግ ክዳን እግዚአብሔር እስካልገባ ድረስ አሁንም ይሰራል ማለት ነው።አድሱ ክዳን ፍጹም ሆኖ  እየሰራ ስለሆነ ሌላ ክዳን አልተደረገም ።ስለዚህ አድስ ክዳን በሌላ ክዳን አልተተካም። 

ኢየሱስ ክርስቶስ አንዴ ፍጹም የሚያደርግ መስዋዕት አቅርቦ መቀመጡ ማሰናከያ ሆኖ ብዙዎች ስስቱ ማየት የተለመደ ሆኗል ።የብሉይ ክዳን ካህን እና መስዋዕት ፍጹም የማያደርገው፦በምህረት 1 ዓመት ካስታገሰ ፥የኢየሱስ ክርስቶስ ምልጃና ልቃነካህናትነቱ  እንዴት ለዘላለም አይሰራም ?  እግዚአብሔር ያልተቀበለው  ያልረካው የብሉይ ክዳን መስዋዕት በምህረት 1 ዓመት ካስታገሰ ፣ የኢየሱስ ክርስቶስ መስዋዕት ደሙ እንዴት ለዘለዓለም አይሰራም ? ለእግዚአብሔር ያልታዘዙት፤ ያልፈሩት ፤በእግዚአብሔርም ያልተሰማላቸው ምልጃ ፦አንድ ዓመት በምህረት  ካስታገሰ ፣ የኢየሱስ ክርስቶስ ምልጃ እንዴት አብልጦ ለዘላለም አይሰራም ?  ሃሌ ሉያ የኢየሱስ ለዘላለም ይሰራል ።

አድስ ክዳን እስካልተሻረ ድረስ የአድስ ክዳን መስዋዕት እና የመስዋዕቱ አቅራቢ አይሻርም።ሃሌ ሉያ።ስለዚህም አይተከው መስዋዕት እና የመስዋዕቱ አቅራቢ እንዴት ነው በሌላ አካል መተካት ፣ መወከል የሚችለው ?።በቡሉይ ክዳን ሰው የራሱን ኀጢአት አምኖ ፦መስዋዕቱ ምትክ እንድሆንለት ይናዘዛል።ስለዚህም ወዳጆቼ ይህንን በልባችን ይዘን የሮሜ ሰዎች መልእክት እንመልከት ፦

“ሁሉ ኃጢአትን ሠርተዋልና የእግዚአብሔርም ክብር ጎድሎአቸዋል፤” — ሮሜ 3፥23

+ ሁሉም ኀጢአተኛ እንደሆነ ቃሉ ስለምመሰክር ፣ ኀጢአተኛ መሆኑን ማንም ማመን አለበት ።ራሱንም ልክድ ልዋሽ አይገባም ።ኀጢያት ካለ፦ የእግዚአብሔር ክብር እንደሚጎድል እሙን ነው።ጉድለቱን ለማሟላት ማለትም ለመጽደቅ ምን ማድረግ ያስፈልጋል  ?የሚለው ጥያቄ መያዝ መልካም ነው።

“በኢየሱስ ክርስቶስም በሆነው ቤዛነት በኩል እንዲያው በጸጋው ይጸድቃሉ።” — ሮሜ 3፥24

+ ሁሉም ኀጢአተኛ ስለሆነ ስለ አንድ  ሰው እንደሚናገር " ይጸድቃል" አይልም ።ግን ይጸድቃሉ ይለናል ።ሁሉም ኀጢአተኛ ስለሆኑ የሁሉም ሰው መፍተሔው፦ የኢየሱስ ክርስቶስ ምትክነት ነው።ያም ስለሁላችን መሞቱ ነው።ኢየሱስ የሞተው ለኀጥአተኞች ብቻ ነው።ኀጢአት አልባ ሰው ካለ የኢየሱስ ሞት አይጠቅምም ።አልሞተለትም ።አያስፈልገውም ማለት ነው።

+ በቤዛነቱ (እኛን ወክሎ ስለእኛ በመሞቱ )፦በጸጋው (በነፃ) ይጸድቃሉ ።ከኀጢአት ነፃ ይሆናሉ ።የእግዚአብሔር ክብርም ይሞላባቸዋል። 

“እርሱንም እግዚአብሔር በእምነት የሚገኝ በደሙም የሆነ ማስተስሪያ አድርጎ አቆመው፤ ይህም በፊት የተደረገውን ኃጢአት በእግዚአብሔር ችሎታ ስለ መተው ጽድቁን ያሳይ ዘንድ ነው፥”— ሮሜ 3፥25

+ ጽድቁም  በእምነት የሚገኝ ነው ፣እምነቱም በቤዛነቱ ባፈሰሰው ደም ላይ  እንደሆነ እንረዳለን ።በኢየሱስ ክርስቶስ ቤዛነት የፈሰሰው  ደም  ስሪዬት (ይቅርታ) እንድገኝ ማለትም ይቅርታ እንድያሰጣ እግዚአብሔር  መሠረት አደረገ(አቆመው )።ቃሉን እናስተውል ።አቆመው ።አቆመው ማለት እግዚአብሔር በልጁ ሞት በመረካቱ ፣በመቀበሉ፤ ሁሉም ሰው በዚህ ደም መስዋዕት ስራ በማመን ፤የዘላለም ሕይወት እንድገኝ አቆመው ።ማለትም ሌላ አማራጭ የለም።ሌላ የምተካ የለም ማለት ነው።ምልጃውን የሚንቀበለው በእምነት ነው።በማመን ብቻ ነው።ይህ ነፃ ስጦታ ነው። የእርሱ ችሎታ ነው።

 ስለዚህም ነው ኢየሱስ ክርስቶስ አሁን ሳይለምን ሳይወድቅ ሳያለቅስ ሳይጮኽ ፥  በክብር ተቀምጦ አንደ ባቀረበው መስዋዕት እንደ ትኩስ ልመና ይሰራል የሚንለው።የምልጃው ተካፋይ መሆን የሚቻለው ኀጢአተኛ መሆኑን በማመን ስለኀጢአቱ የቀረበው መስዋዕት በኢየሱስ ክርስቶስን በማመን በመቀበል እንደሆነ ቃሉ ይገልጽልናል ። ስለዚህም ኢየሱስ ክርስቶስ አሁን  አይለምንም ግን አንደ በለመነው ልመና ፣ባቀረበው ምልጃ አሁንም ይሰራል ።በዚህም ምክንያት  ሳይለምን የሚያማልድ ብቸኛ አማላጅ ነው እንላለን ። 

 እኛ በእምነት በእርሱ ስራ ከፀደቅን፤ ይህ የማን ስራ ነው? ለምንስ አደረገ ? እግዚአብሔር ጽድቁን ለማሳየት ስለወደደ ነው።ማንም "ናልኝ" "ክርስቶስን ላክልን" ሳይል ፥ወድዶ ፈቅዶ ለማዳን ያደረገው ነው።ክብር ይግባውና ሳይለምን ተቀምጦ ለሚያስታርቀው ፍጹም ሰው ፍጹም አምላክ ለሆነው ለኢየሱስ ክርስቶስ።አሜን ።ሃሌ ሉያ።

የዳኑት ሰዎች ድርሻ ምንድነው ? (በቀጣይ ) 

......... 

ኢየሱስ ክርስቶስ ብቸኛ አማላጅ ነው።(6)

ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በሰማይ ተቀምጦ ለእኛ ቆሞዋል።ማለትም ተቀምጦ ይታይልናል።ኢየሱስ በሰማይ ከታየልን በምድር ደግሞ ፈቃዱን ለማስታወቅ መንፈስ ቅዱስ በውስጣችን ይቃትትልናል።  ኢየሱስ በሰይማይ ተቀምጦ ለማይታይላቸው እና መንፈስ ቅዱስ በውስጣቸው ለማይቃተትላቸው ይህንን የሚስራች ላልሰሙት እና ሰምተው  ለማይኖሩት የእኛ ድርሻችን ምንድነው ? ከታች ለማሳየት ጥረት የማደርገው የእኛን ድርሻ በመጽሐፍ ቅዱስ መሠረት ነው። 

የዳነ ሰው ፣ኢየሱስ በሰማይ የተቀመጠለት ሰው፣ኢየሱስ በሰማይ የሚታይለት ሰው ፤ለሌሎች  ሰዎች ድርሻው ምንድነው ? 2 ኛውን  የቆሮንቶስ ሰዎች መልእክት ም.5 ቁ.18-20 መመልከት ግንዛቤያችንን ያሳድግልናል ።በብዙም  ይጠቅመናል ። እስኪ እንያ ፦

“ነገር ግን የሆነው ሁሉ፥ በክርስቶስ ከራሱ ጋር ካስታረቀን የማስታረቅም አገልግሎት ከሰጠን፥ ከእግዚአብሔር ነው፤” — 2ኛ ቆሮ 5፥18

▸ በእምነት ፡ በክርስቶስ  በማመን፣ ከእግዚአብሔር ጋር እንድታረቁ እግዚአብሔር ስለወደደ በደሙ ስሪዬት ያገኛሉ ።በክርስቶስ ስራ እግዚአብሔር ሰላምን ምህረትን ሰጠን። የክርስቶስ ስራ ማንም ልሰራው የማይችል አይተከ ነው። 

▸ በእምነት ከጥፋት ልጅነት ወደ እግዚአብሔር ልጅነት ለመጡት " የማስታረቅ አገልግሎት " ኀላፍነት ፣ግደታ  ተሰጣቸው ። ይህም የወንጌል አደራ ነው።

▸ በክርስቶስ በኩል ያልታረቁት  እንድታረቁ ፥ ለታረቁት ደግሞም የማስታረቅ አገልግሎት የሰጣቸው እግዚአብሔር ነው።ፈቃዱ ነውና ።

“እግዚአብሔር በክርስቶስ ሆኖ ዓለሙን ከራሱ ጋር ያስታርቅ ነበርና፥ በደላቸውን አይቆጥርባቸውም ነበር፤ በእኛም የማስታረቅ ቃል አኖረ።”— 2ኛ ቆሮ 5፥19

▸ በክርስቶስ ቤዛነት ያመኑትን ሁሉን እግዚአብሔር ከራሱ ጋር ያወዳጃል።በቤዛነቱ ስያምኑ የተኛውንም በደል ይቅር ይላል ።ይህችኛዋ በደል ትገዝፋለች አይልም ።ኃጢአት እንዳልሰራ ይቆጥራል ።ሙሉ በሙሉ ከዚህ በኃላ አድስ ሰው ነህ ይላል።ያ በደለኛው ማንነት ሞቷል ይላል።

▸ በደለኛውን ይቅር ካለ በኃላ ኀላፍነትን ( ቀለል ያለ ሸክም) ይሰጣል ።ይህም የማስታረቅ ቃል ነው።የማስታረቅ ቃል ራሱ ምንድነው ? "ደም ሳይፈስ ስርዬት የለም "የሚለውን ቃል ይዘን እናጠን ።መጀመሪያ በደም የሚሰጠው ይቅርታ አሁን በሰዎች በኩል  ያለ ደም በቃል ብቻ ይሰጣል ማለት ነው? በእግዚአብሔር እና በበደለኛው ሰው መኃል የዳኑቱ ይቆማሉ  ማለት ነው ? ወይንም በደለኛው ሰው የማስታረቅ ቃል ያለውን (የዳነውን)ሰውን ይለምናል ማለት ነው ? ወይንም የማስታረቅ ቃል አለኝ የሚል ሰው ይቅርታ  ይደረግ ወይም ይቅርታ አይሰጥ ይላል ማለት ነው? ሚናልባት የማስታረቅ ቃል አለኝ ማለት  ቃላቸው መስዋዕት ነው ማለት ነው ? የማስታረቅ ቃል አለኝ ማለት የአድስ ክዳን መሃላ የሚያስረጅ አሮጌ የሚያደርግ ነው ማለት ነው ?

 እርቅ  አሁንም ክርስቶስ አንዴ ባቀረበው ምልጃ እና ደም ነው እንጂ  በሰዎች ልመና አይደለም።በሰዎች  ልመና የምንልን ከሆን እግዚአብሔር ከክርስቶስ ጋር ያደረገውን መሃላ አሮጌ አድርጎ ከሰዎች ጋር አድስ መሃላ ገብቷል ማለት ነው።ይህ ስንፍና ነው። 

“እንግዲህ እግዚአብሔር በእኛ እንደሚማልድ ስለ ክርስቶስ መልክተኞች ነን፤ ከእግዚአብሔር ጋር ታረቁ ብለን ስለ ክርስቶስ እንለምናለን።”— 2ኛ ቆሮ 5፥20

▸  ከክርስቶስ ጋር ስለታረቅን ያልታረቁትን ለማስታረቅ ፦በእኛ( በታረቁቱ) በኩል እግዚአብሔር ጥሪ ያቀርባል ።እግዚአብሔር ለስራው ሰዎችን እንደሚጠቀም እንረዳለን ። 

▸ " እግዚአብሔር በእኛ እንደሚማልድ" ይህ አማረኛ በታረቁቱ በኩል እግዚአብሔር እንደሚጠራ ያስረዳል ።ማለትም እግዚአብሔር በታረቁቱ በኩል  ያልታረቁትን ይለምናል ። የሚለምነው ራሱ እግዚአብሔር ነው።እግዚአብሔር የሚለምነው በቀጥታ በደለኛውን ሳይሆን ከበደል በነፃው አማካኝነት ነው። እግዚአብሔር ይህንን ልጅ ከእኔ ጋር ታርቅ በል የሚል መልእክት ለታረቀው ሰው የእርቅ ቃል ይሰጣል ።የታረቀውም ደግሞ መልእክቱን ተቀብሎ በደለኛውን ሰውን፦ "እግዚአብሔር ከራሱ ጋር ታረቅ ብሎአል" ይለዋል። ልመና ያቀረበው ጌታ እግዚአብሔር ራሱ ነው።የልመናው መልእክት ወይንም እርቁን እንደሚፈልገው የሚያስታውቁት የታረቁቱ ናቸው ።

ቃሉን በጥልቀት ስንመለከት እነኚህ የታረቁቱ፣ አድስ ሰው የሆኑቱ ፤ልክ ክርስቶስ ''የአባቴ ፍቃድ እንድትድኑ ነው" በአባቴ እመኑ" እንደሚል ፤የታረቁትም በደለኞችን ይለምናሉ ።ክርስቶስ በደለኞችን እንደለመነ እነኚህ ተወካዮችም በደለኞችን ይለምናሉ ። ተወካዮቹ የሚለምኑት  በደለኞችን  ነው። "ከእግዚአብሔር ጋር ታረቁ ብለን ስለ ክርስቶስ እንለምናለን "የሚለው ቃል የመልእክቱን ጭብጥ ያስረዳናል ። 

ክርስቶስ በደለኞቹን "በአባቴ እመኑ" ብሎ የአባቱን መልእክት አሳውቀዋል ።የአባቱ መልእክት እርቅ እንደሚፈልግ ያስረዳል ።ክርስቶስ ወደ አባቱ ለምኗል ።ስለሚነውም " ስለ እንትና" ብሎ ሳይሆን ስለ ደሙ ያውም ስለ ንፁህ ደሙ ይቅር እንዲል ነው።በእኛ ዘንድ ባለው ፍቅር አንድ አድርጋቸው በማለት ነው ዮሐ 17።በፍራትም ስላገለገልኩ በማለት ይቅር እንዲንባል ይለምናል ።የክርስቶስ ተወካዮች በዚህ ክፍል የሚናያቸው ግን እንደ አውዱ ስናይ ወደ እግዚአብሔር ስለ በደለኞች ወደ እግዚአብሔር  እንለምናለን አላሉም ።ክፍሉም አይነግረንም ።ስለ በደለኛ ወደ እግዚአብሔር አይጸለይም እያልኩ እንዳልሆነ ይረዷል።ስለ ምበድሉት ሰዎች እንድንለምን ታዘናልና።ይህ ክፍል የሚያሳየው  ግን የማስታረቅ ቃል ያሉቱ የማስታረቅ አገልግሎት የሚሰሩት የዳኑቱ ወደ እግዚአብሔር በመጸለይ  ሳይሆን ወደ በደለኛው በመለመን  ነው የሚል ነው።ይህ ወደ ጎንዮሽ ልመና እንጂ ወደ ሰማይ አይደለም ።

በሰው ልጆች ኀጢአት ምክንያት  ክህደት የተፈጸመው  በእግዚአብሔር ላይ ነው።ይህ ሆኖ እንኳን መታረቅ እፈልጋለሁ በማለት ፍላጎቱን ያሳውቃል ።እግዚአብሔር መታረቅ ፈልጎ የሰዎችን ፈቃደኝነት ይጠይቃል ። ለምሳሌ ይህን ለመረዳት አባት ፣ልጆቹ እና ከአባቱ ጋር የተጣሉት ልጆች አሉ እንበል ።አባት ብበደልም በዚህ ከተቀጠለ ለልጆቹ መጨረሻ መልካም ስለማይሆን ብሎ መታረቅ ይፈልጋል ።መታረቅ መፈለጉንም ከራሱ ጋር ለታረቁት ልጆች በእቅፉ ስሪ ላሉት ልጆች "ወድሞቻችሁን ከእኔ ጋር አስታርቁ " ይላል ። እነዚህ በእቁፉ ስሪ ያሉ ልጆቹም አባታችን መታረቅ ይፈልጋል ብለው ከእቅፉ ውጪ ላሉ ልጆች ይነግራሉ ።እነሱም መልእክቱን  ተቀብለው አባታችን ከእናንተ ጋርም መታረቅ ይፈልጋል ይላሉ።ይህንን  ማለት ብቻ ሳይሆን "እንቢ አትበሉ እባካችሁ "ብለው ይለምናሉ ። እንግዲህ ይህ ልመና መጀመሪያ የተጠነሰሰው በአባታቸው ሲሆን በልጁቹ በኩል ተስምቷል።እዚህ አባቱም መልእክተኞችም እንደሚለምኑ እንረዳለን ። 

ከላይ ምሳሌው እንዳለ ሆኖ ልጆቹን እንደ መጽሐፍ ክፍል ብናጠን ፦" እባካችሁ ታረቁ  ብቻ" በማለት የሚለምኑ ሳይሆን ስለክርስቶስ  ብላችሁ ታረቁ ብለው የሚለምኑም  ናቸው ።ስለክርስቶስ ማለታቸው አባታቸው የእውነትም ይቅርታ ለማድረግ እና መታረቅ እንደሚፈልግ ለመሰብሰብ ያለው ፍላጎት የሚያስረዳ ነው።ስለክርስቶስ ብሎ መልእክተኞች ይለምናሉ ።አስታዋላችሁ ። የሚድኑት በእነሱ ንግግር ሳይሆን በክርስቶስ ቤዛነት በማመን ነው።አሁንም ጌታ እግዚአብሔር ሰዎቹን የሚያስታርቀው በክርስቶስ ነው።መልእክተኞች በእግዚአብሔር ዘንድ ያለው ሀሳብ ያሳውቃሉ ።በእግዚአብሔር ዘንድ ያለው ሀሳብ ሰዎቹን ሁሉ በክርስቶስ መጠቅለል ነውና ኤፌ 1፥10።

የማስታረቅ ቃል አለን ማለት "ድኀነት በክርስቶስ ቤዛነት በማመን ነው" የሚለውን የእግዚአብሔርን ቃል አይሽረውም።የማስታረቅ ቃል አገልግሎት፦ አገልግሎት ነው።አገልግሎቱም " እግዚአብሔር በክርስቶስ ስራ ይቅር ይላችኋልና" ፣ "በእርሱ እመኑ"፣"ከጌታ ጋር ታረቁ "የሚል ነው እንጂ መዳን በክርስቶስ በቤዛነቱ በማመን የሆነውን የሚቀይር፤ የሚተካ፤ በፍጹም  አይደለም ። አውዱ የሚነግረን ይህንን ነው።

አሁን እኔም የማስታረቅ ቃል አለኝ።ከእግዚአብሔር ጋር ታረቁ ብዬ እለምናችኋለሁ ።ይህንን የሚለው እናንተን ነው።ስለክርስቶስ ደም ብላችሁ ታረቁ።የክርስቶስ ስቃይ ስለናንተ ነውና። ታረቁ። ይህ የእግዚአብሔር መልእክት ነው። መልእክቱ ስለዘላለም ሕይወት እንጂ ስለሚጠፉ መብል አይደለም ።  

ታረቁ ብሎ በደለኞቹን መማጸናቸው  የሚለምኑትን ፦መካከለኛ አያደርጋቸውም።የክርስቶስ መካከለኛነት ቸል እንድንል አያደርገንም ።ምክንያቱም የክርስቶስ መካከለኛነት ስለእኛ ነው።ያም ብቻ ሳይሆን በእግዚአብሔር ዘንድ ልወክል በመቻል ነው ።ማለትም ፍጹም ሰው ፍጹም አምላክ በመሆን ነው ። ቃሉ እንደሚል መካከለኛችን አንድ ነው።“አንድ እግዚአብሔር አለና፥ በእግዚአብሔርና በሰውም መካከል ያለው መካከለኛው ደግሞ አንድ አለ፥ እርሱም ሰው የሆነ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው፤”  — 1ኛ ጢሞቴዎስ 2፥5። ለእግዚአብሔርም የቅርብ ቅርብ ራሱ እግዚአብሔር የሆነ ደግሞም  ለሰውም የቅርብ ቅርብ ራሱ ሰው የሆነ ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው። ስለዚህም የኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል ሥራ አያረጅም ፣አይታደስም፣ አይተካም፤ ፍጹም ነው። ሃሌ ሉያ።

.............  

ኢየሱስ ክርስቶስ ብቸኛ አማላጅ ነው።(7)

እስካሁን የኢየሱስ ክርስቶስ የመቤዠት ስራ አሁንም እንደሚሰራ እንደሚያስታርቅ ስናይ ነበር።ይሁን እንጂ ሰዎቻችን ለምንድነው የኢየሱስ ክርስቶስ ሚልጃ የሚክዱት የሚለውን ማጤን መልካም ሆኖ ታይቶኛል።ሰዎቻችን "ኢየሱስ ክርስቶስ ከሞት ስለተነሳ አሁን ፈራጅ ነው" ለምንድነው የሚሉት ? የሚለውን ጥያቄ በአጭሩ ለመመለስ የሚጥር ይሆናል። 

" የአምላክ ባህሪ መፍረድ ነው ፣በማለት የአምላክ ማንነት ፍርድ መስጠት ነው፣ ለባህሪው መለመን አይሆንለትም እሱ የሁሉ በላይ ነው ፣ታድያ ማንን ይለምናል ወደ ማን ይለምናል "የሚል ሙግት ይገጥማሉ ።በእርግጥም “..፥ እርሱም ከሁሉ በላይ ሆኖ ለዘላለም የተባረከ አምላክ ነው፤ አሜን።” — ሮሜ 9፥5። ሃሌ  ሉያ።

የእግዚአብሔር ባህሪ መፍረድ ነው ስሉ ፍርድ የሚሉት ከምን አንፃር ነው? ሰው ሰውን ወይም እግዚአብሔርን ብበድል የእጁን መስጠት ነው በማለት ነው።አዎ በእርግጥም  እግዚአብሔር ቅን ፈራጅ ነው።አያዳላም ።ኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ ሆኖ እያለ፣ የአምላክ ባህሪ መፍረድ ሆኖ እያለ፣ እነሱም እንደሚሉትም " የእጁን መስጠት ከሆነ" ኢየሱስ ክርስቶስ አምላክነቱን የት ጥሎ የለመነው ?የሚለው የእኔ ጥያቄ ነው።ወይንስ አልለመነ? እያስመሰለ ነው ? ክብር ይግባውና ኢየሱስ ክርስቶስ ስለእኛ ለምኗል ዮሐ 17 ፣ ዕብ5፥7፣ሉቃ 22፥32 ።ታድያ ስለምን አምላክ አልነበረምን ?ይህ ስንፍና ነው። ምክንያቱም ኢየሱስ ክርስቶስ የእውነቱም እያለቀሰ ስለእኛ ለምኗል ።አምላክነቱን ግን አልጣለም ።እርሱ ፍጹም ሰው ፍጹም አምላክ ነውና።ለዘለዓለሙ ። ኢየሱስ ክርስቶስ የእውነትም በስጋው ወራትም ከለመነ ለምን ሚልጃ  የአምላክ ባህሪ አይደለም ትላላችሁ ? ይህ ስንፍና አይደለምን ? ።በእውነትም እግዚአብሔር እኮ ፈርዷል።ፍርድ አልተዛባም።የሚፈርድ እንደየስራው የሚሰጥ አምላክ ብሆንም ይቅር ለማለት ወደደ፣ እንደገና ፍለጋ ጀመረ፣ መጥራት ጀመረ፤ ለምን?ልጆቹን እንዴት አባት  ጨክኖ ይተዋል ?

ምንም እንኳን እግዚአብሔርን፦ ያላመኑቱ በማይረዱት መልኩ ፈርዷል።በፍርድ ሕግ የበደለው፦ ዋጋውን ያገኛል ።በዚህ ሕግ መሠረት እኛ ዋጋችን ሞት ነው።እግዚአብሔር ፍርዱን አልሻረም ።ፈርዷል።ግን የፈረደው በልጁ ነው።በራሱ ላይ ነው።ድንቅ ሃቅ ነው።ስለዚህ እግዚአብሔር ፈርዷል።እኛ ካሰብነው ውጪ በሆነው መንገድ እግዚአብሔር ፈርዷል።ስፈርድ ለማጥፋት ሳይሆን ለመጥራት ነው።ለማጽደቅ ነው።ለማዳን ነው።እስካሁን የተንደረደርኩ እግዚአብሔር ፈራጅ ነው ስሉ ዋጋውን ማለትም ለጥፋት ሞትን ብቻ የሚሰጥ አድርገን ማሰብ ትክክል አይደለም ለማለት  ነው።ስለዚህም እግዚአብሔር ፈራጅ ነው፥ የሚፈርደው ለሞት ብቻ ሳይሆን ሕይወትንም ለመስጠት ነው።እግዚአብሔር ሕይወትንም ለመስጠት የሚፈርድ ፈራጅ ነው።  

ከላይ የእግዚአብሔርን ፍርድ እና  የወዳጆቻችን  ስለፍርድ ያላቸውን  እሳቤያቸውን ለየቅልነትን  አይተናል ። የእውነት ኢየሱስ  ክርስቶስ ፈራጅ ሆኖ እየፈረደላቸው ነው የቆሙት አሁን ? የሚለው ጥያቄዬ ነው።ምክንያቱም ጌታ ፍርድን ቢሰጠን ማን በፊቱ ልቆም ይችላል አሁን ? አሁን ፈራጅ ነው ካልን እየፈረደ ነው ማለት ነው።እየፈረደ ነው ማለት በቸርነቱ በምህረቱ አውለን ማለትም ትወና ይሆናል ።ማለትም እያንዳንዱ ሰው በየቀኑ የሚኖረው በብቃቱ ነው፣ጽድቅ ስለ ሰራ ነው።የሚል መልእክት አለው ።ግን ምንም እንኳን እንደየስራችን የሚፈርድ አምላክ ብሆንም አሁን እየፈረደ አይደለም ።ግዜ ሰቶናል።የምህረት ግዜ።የቆምነው በቸርነቱ በምህረቱ ነው።አንዳች ብቃት የለንም። 

"ጌታ ከትንሳኤ በኃላ ፈራጅ ነው" ስሉ በውስጥ አዋቅነት የሰው ልጆች ሁሉ ያኔ ኢየሱስ ባፈሰሰው ደም<< በሕይወት ያኔ የነበሩትም  ፣ ገና የሚወለዱትም ኀጢአት የለባቸዉም ፤(ከውርስ ሃጢያት ነፃ ሆኖአል እንድሁም>> የሚል እሳቤ አላቸው ። ስለዚህም "ጌታ ያኔ ስሞት ማንም ከአዳም ኀጢአት ነፃ ሆኖአል ምክንያቱም የጌታ ሞት  ስለጥንተአብሶ እንጂ ስለዛሬ በደል አይደለም>> የሚል እሳቤ  ነው። ትምህርቶቹ ሁሉም ስህተት ባይሆንም ከስህተት ትምህርት ሁሉንም ስህተት አንጠብቅም ።ምክንያቱም ስህተት ትምህርት በበባህሪው ትክክል_ስህተት ሆኖ ስለሚመጣ ።  

እሳቤዎችን እጅግ አድርገ እፈራለሁ ።የተኛውንም። ኢየሱስ ያኔ ስሞት የዳኑት ፦ የተቀበሉት ብቻ ናቸው እንጂ የሸጡትም ጭምር አይደሉም ።ኢየሱስ ያኔ ስሞት የዳኑት ፦ያመኑቱ  ብቻና ብቻ ናቸው ።ሰው ኢየሱስ በመሞቱ የኀጢአት ዕዳ የለበትም ተሰርዟል ማለት ፦ ሰው ኀጢአትነቱን ሳይቀበል፣ ለኀጢአቱ የቀረበውን መስዋዕት ሳይቀበል፣ሳያውቅ፣ መስዋዕቱን ያቀረበውን የተቀበለውንም ሳያውቅ ፣ ሳይቀበል ይድናል ፤ነፃ ሆኗል የሚል ዓለም አቀፋዊ እንዲሁ ፈውስ አስተምህሮ ነው። ምንም እንኳን ጌታ እንዲሁ በነፃ እንዲድኑ  ፈቃዱ ብሆንም በነፃ መዳን  በእምነት እንደሆነ መዘንጋት የለበትም ። ምንም እንኳን ጌታ ለዓለም ብሞትም የሚድኑቱ ግን የተቀበሉቱ ያወቁቱ ብቻ እንደሆነ መታወቅ አለበት ።ምንም እንኳን ጌታ ያኔ ስሞት  ፦ያልተወለዱቱ ጭምር ጌታን ሳይቀበሉ ቡዲስት ብሆንም እንኳን ይቅርታን አግኝቷል ብሉም መጽሐፉ “እንግዲህ በክርስቶስ ኢየሱስ ላሉት አሁን ኵነኔ የለባቸውም።”  — ሮሜ 8፥1 ይላል። በክርስቶስ ላሉት አሁን ኩነኔ የለባቸውም ማለት በክርስቶስ ሰው የሚሆነው ክርስቶስን አሁን ስቀበል ነው።አሁን ስቀበል ከሆነ ከዚያ በፊት ኩነኔ አልባ አልሆነም ማለት ነው። የኢየሱስ ክርስቶስን  የመስቀል ስራ፦" ዓለም አቀፋዊ እንዲሁ ሳያውቁ ሳይቀበሉ ፈውስ አይሰጥም ።ይህንን ኢ-መዳን ከሚያስተምሩም ተጠበቁ። 

ኢየሱስ ክርስቶስ የሰራው የመስቀል ሥራ ለዓለም ነው።ለዓለም ብሆንም እንዲሁ በነፃ በእርሱ ቦታ  ተተክቶ የሞተውን ን ሳያውቁ መዳን የለም ፤በማመን ነው የሚድኑት ።ይህን በደንብ ለመረዳት ኢየሱስ ክርስቶስ በስጋው  ወራት "ማመን ስራ ነው " ያለውን መጥቀስ አስፈላጊ ነው።“ኢየሱስ መልሶ፦ ይህ የእግዚአብሔር ሥራ እርሱ በላከው እንድታምኑ ነው አላቸው።"  — ዮሐንስ 6፥29 ።መዳን እንዲሁ ብሆንም እንዲሁ የሚሆንላቸው እግዚአብሔር የላከውን ልጁን  ለተቀበሉት ብቻና ብቻ ነው።እምነት ሥራ ነው።ያውም የእግዚአብሔር ሥራ ነው።ያውም የዘላለም ሕይወት የሚያሰጥ ስራ።ስለዚህ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ እመኑ።የሚለው መልእክቴ ነው።

ኢየሱስ ክርስቶስ በደሙ በሚጠራበት ግዜ፦ በግዜ ወደመርከቡ ግብ ፤ አምልጡ።የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ስለጥንተ አብሶ (ውርስ ሃጥአት) ብቻ ሳይሆን ስለ እለት በደልም የሚሰራ ነው።ደሙ ትኩስ ነው።ምህረትን ይለምናል ።ይህ ማንነቱ ነው።“ነገር ግን እርሱ በብርሃን እንዳለ በብርሃን ብንመላለስ ለእያንዳንዳችን ኅብረት አለን፥ የልጁም የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከኃጢአት ሁሉ ያነጻናል።”— 1ኛ ዮሐንስ 1፥7 ።ሃሌ ሉያ አለማስተዋልን በነበር ላስቀረው።

መላእክት ብሆኑስ ...?

...............

ኢየሱስ ክርስቶስ ብቸኛ አማላጅ ነው።(8)

ስለኢየሱስ ክርስቶስ ምልጃ ስናጠና ከማንኛውም ፍጥረት ልመና ጋር ማስተያየት እና መተካት ከክርስትያን የማይጠበቅ ነገር  ነው።ምክንያቱም ሰው ፦አይደለም ለሌላው ለመቆም ይቅርና ለራሱም ብቁ ስላልሆነ ነው  የመጣው ።አብም የላከው ለዚህ ነው።ይህን ነው መንፈስ ቅዱስ ያስታወቀው ። ኢየሱስ ክርስቶስ ያደረገው ምልጃ የማይካድ ዘላለማዊ መሆኑ በልባችን መክበድ አለበት ።ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ የጀመረውን በትንሳኤው ከጨረሰ( ካረጋገጠ) በኃላ ሰዎች እና መላእክት በኢየሱስ ክርስቶስ ስራ እንደተተኩ ማሰብ ስንፍና ነው። በእውነቱ ቅዱሳን መላእክት በኢየሱስ ቦታ ተተኩ ? ወደ ፍጡራን ለምኔን ነው መንግስት ሰማይ የምንገባው ?  

ከሰዎች በብዙ ብርቱ ኀያላን እንደሆኑ ስለ መላእክት መጽሐፍ ይነግረናል ። ኀያላን ብቻ ሳይሆኑ ቅዱሳን ናቸው ።ምንም እንኳን  ቅዱሳን ብሆኑም ከእግዚአብሔር ቅድስና ጋ አይነፃፀርም።ግን ብነፃፀር  ስንፍና የሚከሳቸው  ናቸው ። “እነሆ፥ በባሪያዎቹ አይታመንም፤መላእክቱንም ስንፍና ይከስሳቸዋል፤”  — ኢዮብ 4፥18 ።ምንም እንኳን እኛ ቅዱሳን ብንልም የፈጠራቸው አምላክ ግን "folly" ናቸው ይላል።ይህንን ቃል በአማርኛ ማየት ለእኛ ልከብድ ይችላል ።ምክንያቱም በኢትዮጵያ ልዩ ክብር ለመላእክት ስለሚሰጥ ። ቃሉ ነውና ልከብደን አይገባም ።ሰነፍ ፣የሚሳሳቱ ፣ጅል ፣ከንቱነት በማለት ቃሉን መዝገበ ቃላት ይተረጉመዋል ።የሚሳሳቱ ወይንም ሰነፍ የሚለው ትርጉም ብንወስድ መልካም ይመስለኛል ። ምንም እንኳን መጽሐፍ ቅዱስ ላይ እግዚአብሔር መላእክትን ሰነፍ የሚሳሳቱ ብሎ ብገልጽም ይህንን ያለው ጌታ እግዚአብሔር ብቻ ነው።ምክንያቱም ከእግዚአብሔር ጋር ብነፃፀሩ እንዲህ የማያስተውሉ ናቸው ።እግዚአብሔር ሰነፍ ደካማ ናቸው ብልም እኛም ማለት አለብን ለማለት እንዳልሆነ ይረዷል። ምክንያቱም ከመላእክት ጋር  አንነፃፀርም።መናፍስት ናቸውና ።እግዚአብሔር ግን ሰነፍ ናችሁ ማለት ብቻ ሳይሆን ይከሳቸዋል ።ንቁ ይላል ።ለዚህም ነው መላእክት ብሆኑም እንኳን ብቁ ሆኖ በፊቱ የማይቆሙት።አበውም "ፊታቸውን ሸፍነው ቅዱስ " ይላሉ የሚለው ምስጥር እዚህ ጋር ነው። 

 በእግዚአብሔር ፊት ለመቆሚ ክስ አልባ መሆን እንደሚገባ ያውቋል።ምንም እንኳን እኛ መላእክትን ቅዱሳን ብንልም እግዚአብሔር የሚስቱ ሰነፎች እንደሚል አሁን  ያስተውሏል። እኛ መላእክትን ቅዱሳን ናቸው ማለታችን ስህተት ነው እያልኩ እንዳልደሆነ ይረዷል።እግዚአብሔር ሰነፎች ካለ፣እግዚአብሔር የሚሳሳቱ ናቸው ካለ ፤ደግሞም ከከሰሳቸው ማንን ልወክሉ ይችላሉ ? ለራሱ ተከሳሽ የሆነ አካል እንዴት ሌላውን ልወክል ይችላል ? በፍጹም አይችልም ። ይህንን ስጽፍ ምልጃን  እንድትመለከቱ  የሚወደው ከነፍስ ባርነት ነፃ ስለማውጣት እንጂ ስለ ስጋ እስራት (ባርነት ) አይደለም ። የእግዚአብሔር መላእክት ቅዱሳን ናቸው ።ማለትም ለእግዚአብሔር ብቻ የተለዩ ፣ለእግዚአብሔር ብቻ የሚገዙ ናቸው ።  

ከእግዚአብሔር መላእክት አንዱን  እከሌ ኀያል ነው ፣ እገሌ የሚባለው ሀለቃ( ዋና) ነው ብሎ ሳይለይ ቅዱሱ መጽሐፍ ሁሉንም መላእክትን "ሰነፎች ናቸው" እግዚአብሔር እንደሚል ነው የሚገልጸው።እንዲህ  መቀበል እንጂ ምንም ማድረግ አይቻልም ።ደንግጣቹ ልሆን ይችላል ።እኔም ለመጀመሪያ ግዜ ሳይ ደነገጥኩ ።ግን ቃሉ ነው።እርሱ ትክክል ነው።የእግዚአብሔር መላእክት ለምን ለሰው ልጆች አይለምኑም ? 

“ሰውም እንደሌለ አየ፥ ወደ እርሱ የሚማልድ እንደሌለ ተረዳ ተደነቀም፤ ስለዚህ የገዛ ክንዱ መድኃኒት አመጣለት፥ ጽድቁም አገዘው።  — ኢሳይያስ 59፥16።እግዚአብሔር ስለሰውም ስለራሱም የሚለምን  ሰው ስፈልግ ሰው የለም።ማለትም ልቆም የሚችል ሰው የለም።እግዚአብሔር ለምን መላእክትን አይመለከትም ? ከላይ መላእክት እንኳን ሰነፎች ናቸው ብሎ እግዚአብሔር እንደሚከሳቸው አይተናል ። በዚህ ስንፍናቸው ደግሞ ደም የላቸውም ? ስለዚህም  ምክንያት  እግዚአብሔር ስለሰው ነፍስ  ሰውን ተመለከተ ።  

መላእክት በቁጥር" አይላፋት ግዜ አይላፋት ናቸው" ብሎ መቁጠር እንደማይቻል መጽሐፉ ይገልጻል ራዕይ 5፥11። ለእግዚአብሔር ብቻ የሚገዙትን የእግዚአብሔር መላእክት ይጠብቃሉ ።የንጉሥ ትዕዛዝ ነውና። እለት እለት የሚጠብቅ መላእክት በስም ማን እንደሆነ የሰው ልጅ አያቅም ። ምናልባት መልእክት ይዞ ከመጣ፣ ስሙን ካስተዋወቀ፣ እገሌ መጣ ልል ይችላል እንጂ ' እገሌ ከልጅነት እንከ ሽምግልና ከእኔ ጋር ነበር ያሳደገኝ ይህኛው መላእክት ነው' ማለት አለማወቅ ነው።የመላእክት ጥበቃ ለአማኞች ብቻ ነው።  ቅዱሳ መላእክት ፍጡር ናቸው ።መናፍስት ናቸው ።እግዚአብሔር ብቻ ያዛቸዋል እንጂ ሰው አያዛቸውም።እግዚአብሔር ብቻ ይልካቸዋል እንጂ ሰው አይልካቸውም። እግዚአብሔር ከላከ ብቻ ይመጣሉ እንጂ የፈለጉትን እንደ ዲያብሎስ  አያደርጉም ።የእግዚአብሔር መላእክት በሰማይ ወይንም  በምድር በአንድ ቦታ ከተገኙ ሌላ ቦታ ላይ አይገኙም ።በቦታ ይወሰናሉ ።ቅዱሳን መላእክት የአቅም ማነስ ችግር ስላለባቸው እርስ በእርስ ይረዳዳሉ ዳንኤል 10። ቅዱሳን መላእክት አያገቡም ።  ቅዱሳን መላእክት ሰውን ከኀጢአት ነፃ ማውጣት አይችሉም ፣እግዚአብሔር ነፃ ያወጣውን ግን ይጠብቃሉ ።ቅዱሳን መላእክት ስለሰው ልጅ ስጋ ባሪነት ወደ እግዚአብሔር አሳስበዋል (ለምነዋል)  ዘካ 1፥12። ነፍስን  ለማውጣት ግን ደም ያስፈልጋል ። 

ይህንን በልባችን ይዘን የእግዚአብሔር መላእክት ለሰው ልጆች የኀጢአት ይቅርታ ልያስደርግ ይችላል ወይንስ አይችልም ? ለምን ? የሚለው እንመልከት ፦  

▸ ታርኩ በዘፍጥረት ም.18 ይጀመራል ።ለአብርሃም ሶስት ሰዎች በእንግድነት  መጡ ።ከአብርሃም ጋር የነበረውን ጉዳይ  ስጨርሱ የመጡቱ ሰዎች ወደ ሰዶምና ጎመራ ከተማ አቀኑ ። “ሰዎቹም ከዚያ ፊታቸውን አቀኑ፥ ወደ ሰዶምም ሄዱ፤ አብርሃም ግን በእግዚአብሔር ፊት ገና ቆሞ ነበር።”  — ዘፍጥረት 18፥22 ። 

▸ አብርሃም ጋ ከመጡ ከሶስቱ ሰዎቹ አንዱ ከአብርሃም ጋ ይነጋገር ነበር።ማለትም አብርሃም እየለመነው እየተማፀነው ነበር። የቀሩቱ ደግሞ ጉዞአቸውን( አብርሃምንና እግዚአብሔርን) ትተው ጉዞአቸውን ቀጠሉ ። ጉዞአቸውን የቀጠሉ ሰዎች ሰዶም እንከሚደርሱ ድረስም አብርሃም እግዚአብሔርን እየለመ በፊቱ ቆየ። 

▸ ወደ ሰዶም የሄዱቱ ደግሞ ሁለት ሰዎች ቅዱሳን መላእክት እንደሆኑ ዘፍ 19 ይገልጻል ።   አብርሃም ከሶስቱ ሰዎች፦ አንዱ እግዚአብሔር ሁለቶቹ ደግሞ መላእክት እንደሆነ አውቀዋል ማለት ነው። እነዚህ ሰዎች በስውር አይደለም ወደ ሰዶም የተላኩት ።አብርሃም እቤት ጋብዞአቸው ስሸኛቸውም  ነበር።ስሸኛቸውም ለማጥፋት እንደሚሄዱ ተረድቷል ።ሁለቱ መላእክት ለማጥፋት እንደሚፈጥኑ አውቆ፤ አብርሃም ግን ፦" እባካችሁ ተመለሱ ? ይቅር በሉ ? "አላለም ።እነሱ እየሄዱ እንኳን በእግዚአብሔር ፊት ቆሞ "..አትምርምን.." እያለ ይለምን ነበር ። 

የእግዚአብሔር  መላእክት አይደለም በአካል መጥተው፣ በምናብ ብቻ ሰው፦" እገሌ ስማ" በሚልበት ሀገር ይህ ቃል የሚያስታዝብ ነው።ደወል የሚሆን ነው።የማንቂያ ደወል ። አብርሃም ወደ እግዚአብሔር በመለመኑ ሎጥ የንስሐ እንድል እንድያገኝ አደረገ።“እግዚአብሔርም እነዚያን የአገር ከተሞች ባጠፋ ጊዜ አብርሃምን አሰበው፤ ሎጥ ተቀምጦበት የነበረውንም ከተማ ባጠፋ ጊዜ ከዚያ ጥፋት መካከል ሎጥን አወጣው።” — ዘፍጥረት 19፥29 ።

ስለዚህ አይደለም ለነፍስ ፦ለስጋ ባርነትም እግዚአብሔር ብቸኛ ምርጫ እንደሆነ ያስተውሏል ። ስለዚህ አብርሃምም አባታችን የዛሬን ጉዳችን ብያይ ምን ይል ይሁን ?እግዚአብሔርን  እኮ ረስተናል።አብርሃም በአካል አግኝቶ ፣ለዚያውም ለያጠፉ ስጣደፉ ፤ከእግዚአብሔር ጋር ብቻ ተጣበቀ ።አዎ በቀጥታ እንደ መግደላዊት ማርያም በእግዚአብሔር ፊት ተደፉ ። ይግባን። 

ስለዚህ  መላእክት የኢየሱስ ደም መተካት አይችሉም ።ደሙ አሁንም ያመኑትን ያድናል ።ይሰራል ። ለስጋም ለነፍስም ባሪነት የነፃነት መውጫው ከህልና ባሪነት ነፃ መውጣት ነው።ኢየሱስ ያደረገልን ይህንን ነው።ከህልና ባሪነት ነፃ ማውጣት ።ማንም ?በምንም ልያደርገው አይችልም ። የኢየሱስ ደም ለምህረት ይጮሃል ።እመኑ ።ነፃ ትሆናላችሁ ።ተባረኩ 


እድሉ ዮሐንስ ጋምሳ 

( ደቀመዛሙርቱ )

Comments

Popular posts from this blog

"ደብተራ ማን ነው?" ጸረ ደብተራ ንቅናቄ በሊቀ ጠበብት በዶክተር ዘሪሁን ሙላቱ

ካህናት ነን

የኢየሱስን እናት ብፅዕት ማርያምን አትሳደቡ! (2)