Posts

Showing posts from June, 2022

አምልኮተ ሰብእ ከምንጩ ይነቀል! ለዘማሪ ልዑልሰገድ የቀረበ የኑፋቄ ምንጭ ምላሽ ።

  አምልኮተ ሰብእ ከምንጩ ይነቀል! መግባት ይቻላል ! በዚህ ርዕስ ላይ ለመጻፍ ያነሳሳኝ የሰሞኑ ገጠመኝ ነው።ዘማሪው ነው።ቋንቋው ሰብዒ የሆነለት።ተስፋም እምነቱ እና ትምክቱም ሰብዒ የሆነለት።ከአትሮኖሱ ስሰበክ በመስማቱ ማከፈሉን ብነግረንም ።ከብዙ ተቋውሞ በኃላ ነው ።"መጀመሪያም ሳያምን ነውን!?" ፣ ምክንያቱም አራተ እየደጋገመ "ኢየሱስ ያድናል ማለት ክህደት /ምንfikiና / ነው" ብሏልና።የጥያቄ እና የተቋውሞ ናዳ ስወርድበት ፣ ከቤቷ ሰባክና ከአትሮኖሱ መስማቱን በመንገር "ከደሙ ንፁህ ነኝ" ለማለት አላፈረም ። ከጎበዛዝቱ የመጣውን ተግሳጽ እንደ ስድብም መቁጠሩ አስገርሞኛል።ከሁሉ በላይ የሚያስገርመኝ በቦታው የሰሙት እና በደብሩ የሞሉቱ በሺዎች የሚቆጠሩ ሕዝቦች ፣ሳይጋጭባቸው 'ኢየሱስ ያድናል ማለት ክህደት ነው' ብለው መቀበላቸው ነው፤ከቦታው ተቋውሞ አልሰማንምና።"ቃለ ሕይወት ያሰማ" አዎን ያሰማ ወዳጄ፤ሄድክኮ።የአስተማረውም 'ሊቀ' ጥላቻ ካልሆነ በስተቀር ፣ በየትኛው መጽሐፍ ክፍል ስለትም ኢየሱስ የሚያድን እንደሆነ መመስከሩ ክህደት ሆኖ አያውቅም፤ጫፍ የወጣ ጥላቻ እና መመረዝ ካልሆነ በስተቀር።ከአንድ 'እውቅ' መምህር የማይጠበቅ ነው። ወንጌል የቋንቋ ማቀነባበሪያ አይደለም ሕይወት ነው።ወንጌል የቃላት ብልጫ ሳይሆን የቃሉ የነጠረ እውነት ነው። ዘማሪ ባወጣው በእምነት ቃል ፦"ኢየሱስ ያድናል ማለት ክህደት ነው " በሚለው በዚህች ቅጥበት ብቻ "ልክ ነው" ያለው ስንቱ ነው መሰላቹ ? ታዲያ የሚወዱቱ እና የሚያከብሩቱ ቀጥታ ከመምህር የሰሙት እንዴት ተበርዝው ይሁኑ !? ጌታ ይድረስላችሁ።በእኛ ሃገር ውሸት ስደጋገም እውነ...

ተአምረ ኢየሱስ የሚባለው መጽሐፍ ተአማኒነት አለው ?

 << ኢየሱስ ከ30 ዓመቱ በፊት ምልክት አድርጎ ነበርን? ተአምረ ኢየሱስ የሚባለው መጽሐፍ ተአማኒነት አለውን !? >> 👉" ተአምረ ኢየሱስ"የሚባለው መጽሐፍ ኢየሱስ ከፅንሰቱ እስከ ትንሳኤው ድረስ የሰራውን ተአምር የመዘገበ መጽሐፍ እንደሆነ ይነገራል፤ደግሞም ተምረናልም። ☝እንደ እግዚአብሔር ቃል <<ኢየሱስ ምልክት ማድረግን መቼ ጀመረ !? በእውነት ከ30 ዓመቱ በፊትም ምልክቶችን ያደርግ ነበርን !? >> የሚለውን ጥያቄ ይዘን ለመፈተሽ ተነስተናል ። ☝በእውነቱ.. ጌታ ከ30 ዓመቱ በፊት ምልክቶችን ያደርግ እንደነበረ የሚያሳይ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ይኖር ይሁን !?  ☝በእርግጥም የሚጠቀሰው አይጠፋም ፤ያው ማንም ይጠቅሳልና ፥ ግን "ተአማኒነት አለው ወይ !?" የሚለው ጥያቄ ልነሳ ይገባል። ☝ለዚህ ማስረጃነት የሚጠቀሰው የመጽሐፍ ቅዱስ  ክፍል የዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 20፥30 ነው።ቃሉ እንዲህ ይላል ፦ “ኢየሱስም በዚህ መጽሐፍ ያልተጻፈ ሌላ ብዙ ምልክት በደቀ መዛሙርቱ ፊት አደረገ፤”  ☝ይህ ክፍል  'ኢየሱስ ክርስቶስ ከ30 ዓመቱ በፊት ምልክቶቹን አድርጓል' ስለመባሉ ማስረጃ ልሆን ይችላል ወይ !? የሚለውን እንፈትሽ በጥልቀት ፦ 🌱 ኢየሱስ በዮሐንስ ወንጌል ያልተመዘገበ ሌላ ብዙ ምልክቶቹን እንዳደረገ ቃሉ ይገልጽልናል ።ግን ቃሉ የሚለው << ኢየሱስ ሌላ ብዙ ምልክቶችን፣በመጽሐፉ ያልተጻፉትን፣እንዳደረገ ነው፤ እንጂ ከ30 ዓመቱ  በፊት ምልክቶችን ስለማድረጉ አይነግረንም፤ይልቁንም ቃሉ የሚለው ፦ኢየሱስ ክርስቶስ ያደረገው ተአምር ሁሉ በቁጥር እንደ ብዛቱ መጠን እንዳልተጻፈ ነው።  🌱ግን የኢየሱስ.. ምልክቶችን፣ ዮሐንስ ሁሉንም  አለመዘገቡ በራሱ ሌ...

ነገረ ጸሎት

                          ነገረ ጸሎት መግቢያ 1.ጸሎት ምንድነው !? 2.ለምን እንጸልያለን !? 3.ጸሎት ምን አይደለም !? 4.ጸሎት ወደ ማን !? 5.የኢየሱስ ጸሎት የእውነት ወይንስ ለምሳሌነት !? 6.እንዴት እንፀልይ !? ማጠቃለያ ዋቢ መጽሐፍት                           መግቢያ            በዚህ ርዕስ ላይ ትንሽዬ ነገር ስለ ጸሎት ለመጽሐፍ ያነሳሳኝ ሰው የጸሎትን ትርጉም በትክክል እንዲገናዘብ ማድረጉ፣ለምን እና ወደ ማን እንደሚጸለይ መረዳቱ፣ደግሞም ጸሎት ምን እንዳልሆነ መገንዘቡ ለአንድ ሰው ወደ ቀድሞ ክብሩ ለመመለሱ፣ ከአምላኩ ጋር ቀጥ ለጥ ያለ ሕብረት እንድኖር ያደርጋል የሚል እምነት ነው።የአቅሜን ለመጽሐፍ ተጣጥርያለሁ። ደግሞም የኢየሱስ የጸሎት ሕይወቱን ለማክፋፋት ፣ ድራማ ለማድረግ ለሚወተውቱም መልስ ለመስጠት ሞክሬያለሁ።በመጨረሻም የጸሎት አስተማሪ መንፈስ ቅዱስ ብቻና ብቻ እንደሆነ ለማስገንዘብ ጥሪያለሁ። መታደስ፣መለወጥ፣ወደ ቅድሞ ክብራችን መመለስ ይሁን።በኢየሱስ ስም።አሜን ። 1.ጸሎት ምንድነው !? ☝ፀሎት ለአምላክን የሚቀርብ ልመና፥ምስጋና (የኢትዮጵያ .ቋንቋችና.ጥናትና ምርምር ማእከል አ.አ የካቲት 1993) ☝ጸሎት ል...

ትምህርተ ሦስትነት

  ትምህርተ ሦስትነት ትምህርተ ሦስትነትን ሳጠና እና ስናገር ሙሉ ድፍረት ተሰምቶኛል አሁን ።መጀመሪያም የማምነው ብሆንም ለማስረዳት ከባድ ይሆን ነበር።እናም ዶክተር ተስፋዬ ሮቤል በትምህርት ሦስትነት ላይ ያቀረበውን ትምህርት ካየሁ በኋላ ሙሉ ድፍረት አገኘሁ።እናም እናንተም ተማሩ።ተስፍሽ እግዚአብሔር ጸጋ ያብዛልህ፤እድሜህ ይርዘም ። ትምህርተ ሦስትነት ያልኩት "ሥላሴ" የሚለው ስም ያለ አግባብ በጊዜ ሂደት ትርጓሜው ስለተቀየረ ነው።እናም ዋናው ምክንያት ""ሥላሴ የሚለው ስም በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የለም ስለዚህም ''አንዱ አምላክ ሥስት አካል አለው'' የሚለው ትምህርታችሁ ስህተት ነው"" ይሉናል።በእርግጥም "ሥላሴ" የሚለው ስም በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የለም።እኛም የእግዚአብሔር ስም ነው አላልንም።"ሥላሴ" ስንል <<አምላኬ፣ጌታዬ፣ እግዚአብሔር>> እያልን እየጠራን አይደለንም፤ይልቁንም "አምላኬ ሦስት አካል አለው" ብለን ለማስተማር የወጣ ቃል ነው እያልን ነው።ለማስተማር ብቻ እንጠቀምበታለን።ስለ "ሦስት ማዕዘን" ለማስተማር Triangle እንደምንል ፥ ስለ ሦስት አካል ለማስተማር ደግሞ Trinity እንላለን ።ስናጠና ይህንንም በልባችን እንያዝ ። ሌላው ደግሞ ትምህርተ ሥስትነት ስንማር 'ሥስት ጽማም ሽማግሌዎች ልያማትቡ ያሉ የሚመስሉትን' ከአዕምሮ ፋቂ።ትምህርተ ሦስትነትን የምንማረው መጽሐፉ ላይ በተገለጠው ልክ በስም እና በግብር (በሥራ) አኳያ ብቻና ብቻ ነው።አንዱን አምላክ በስም እና በግብር ብቻ በሦስት አካል መገለጡን እናውቃለንና በዚህ ልክ እንማራለን። ሌላውም ደግሞ አብ አባትነት ግብር...