ትምህርተ ሦስትነት
ትምህርተ ሦስትነት
ትምህርተ ሦስትነትን ሳጠና እና ስናገር ሙሉ ድፍረት ተሰምቶኛል አሁን ።መጀመሪያም የማምነው ብሆንም ለማስረዳት ከባድ ይሆን ነበር።እናም ዶክተር ተስፋዬ ሮቤል በትምህርት ሦስትነት ላይ ያቀረበውን ትምህርት ካየሁ በኋላ ሙሉ ድፍረት አገኘሁ።እናም እናንተም ተማሩ።ተስፍሽ እግዚአብሔር ጸጋ ያብዛልህ፤እድሜህ ይርዘም ።
ትምህርተ ሦስትነት ያልኩት "ሥላሴ" የሚለው ስም ያለ አግባብ በጊዜ ሂደት ትርጓሜው ስለተቀየረ ነው።እናም ዋናው ምክንያት ""ሥላሴ የሚለው ስም በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የለም ስለዚህም ''አንዱ አምላክ ሥስት አካል አለው'' የሚለው ትምህርታችሁ ስህተት ነው"" ይሉናል።በእርግጥም "ሥላሴ" የሚለው ስም በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የለም።እኛም የእግዚአብሔር ስም ነው አላልንም።"ሥላሴ" ስንል <<አምላኬ፣ጌታዬ፣ እግዚአብሔር>> እያልን እየጠራን አይደለንም፤ይልቁንም "አምላኬ ሦስት አካል አለው" ብለን ለማስተማር የወጣ ቃል ነው እያልን ነው።ለማስተማር ብቻ እንጠቀምበታለን።ስለ "ሦስት ማዕዘን" ለማስተማር Triangle እንደምንል ፥ ስለ ሦስት አካል ለማስተማር ደግሞ Trinity እንላለን ።ስናጠና ይህንንም በልባችን እንያዝ ።
ሌላው ደግሞ ትምህርተ ሥስትነት ስንማር 'ሥስት ጽማም ሽማግሌዎች ልያማትቡ ያሉ የሚመስሉትን' ከአዕምሮ ፋቂ።ትምህርተ ሦስትነትን የምንማረው መጽሐፉ ላይ በተገለጠው ልክ በስም እና በግብር (በሥራ) አኳያ ብቻና ብቻ ነው።አንዱን አምላክ በስም እና በግብር ብቻ በሦስት አካል መገለጡን እናውቃለንና በዚህ ልክ እንማራለን።
ሌላውም ደግሞ አብ አባትነት ግብር አለው፤ወልድም ልጅነት ግብር አለው፤መንፈስ ቅዱስም የራሱ ግብር አለው።ይህንን ስንማር ከእኛ ልጅነት እና አባቶች እንዳይደለ ያስተውሏል ።አብ ወልድ አይደለም፤ ወልድም አብም መንፈስ ቅዱስ አይደለም ።መንፈስ ቅዱስም መንፈስ ቅዱስ ብቻና ብቻና ነው።ምክንያቱም ስም እና ግብር የራሱ የግሉ የአካል ማንነት ነው።
አንዱ አምላክ ሦስት አካል አለው ።አብ ራሱን የቻለ አካል አለው ።ወልድም መንፈስ ቅዱስም እንደዛው ።ስለዚህም አብ ሃሳቡን በወልድ በኩል ከነገረን ፥ አብን የማይናገር ወይንም መናገር የማይችል ነው አያስብለውም ፤ ወልደንም የአብ ንግግር ነው አያስብለውም።መንፈስ ቅዱስም እንደዛው።ስለዚህም እንዲህ እንላለን ፦
አብ ይናገራል ራሱ ፣
ወልድ ይናገራል ራሱ ፣
መንፈስ ቅዱስም ይናገራል ።
አብ የአንዱ አምላክ ፣ የግል ማንነት ስም ያለው እስከሆነ ድረስ አብ ፦ ይሰማል ፣ይመልሳል፣ ይናገራል ፣ ያያል ..።ወልድም መንፈስ ቅዱስም እንደዛው ።
ትምህርተ ሥስትነት እውነት ነው።አስተውሉ ።ገና አዳም ስፈጠር ፣በአንዱ በአዳም አካል ውስጥ ሁሉት ማንነት አለ ።ወንድነት እና ሴቷ ሔዋን።ዘፍ 1፥27።በአንዱ በአዳም አካል ውስጥ ሁለት ማንነት (ተፈጥሮ) ካለ አንዱ አምላክ ሥስት አካል እንዳይኖር የሚከለክለው ምንድነው !? በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ አይደለም አንዱ አምላክ ሥስት አካል መኖሩ ቀርቶ ሺህ አካል መኖሩንም ካረጋገጠልን የማንቀበለው ለምንድነው !? ለአዕምሮአችን ስለመተቸን ነው ወይንስ ቃሉ ስለሚል ነው ማመን ያለብን !?
ሌላው ደግሞም በኢየሱስ ፣ በአንዱ አካል ውስጥ መለኮትነት እና ሰውነት መኖሩ እሙን ከሆነ ፦አንዱ አምላክ ሥስት የተለያዩ አካላት መኖሩም ለምን እሙን አይሆንም !? በኢየሱስ አካል ውስጥ ፈጽሞ የማይገናኝ መለኮት እና ሰውነት እስካለ ድረስ አምላካችን በሦስት አካል መገለጡ ሃቅ ነው፤ለአዕምሮአችን ልከብደ አይገባም።
መለኮት ራሱን የቻለ አካል አለው ፣ ሰውም ራሱን የቻለ አካል አለው።ይህ ሁለት አካል እና ሁለት ማንነት በኢየሱስ ክርስቶስ አካል አንድ ከሆነ "መለኮትም ሰውነትም በአንድ አካል" ካለ ፥ አንድ አምላክ ደግሞ ሥስት አካል መኖሩንም እንደ ቃሉ መቀበል ይገባናል ። ከአዕምሮአችን ሁለም እርሱ የላይ ነው።በእኛ ምጥጥዬ አዕምሮአችን መለካት አግባብ አይደለም ።
ቁልፉ ነገር የአብ የአባትነት ስም እና ድርሻ ለአብ ብቻ ነው።የወልድም የመንፈስ ቅዱስም እንደዛው ነው።ለምሳሌ አብ አባት ነው።ሌላው አባት ተብሎ አይጠራም ።ወልድም ልጅ ነው ሌላ ልጅ ተብሎ አይጠራም ።ኢየሱስ በመንፈስ ቅዱስ ብፀነስም መንፈስ ቅዱስ አባቱ ወይንም ኢየሱስ የመንፈስ ልጁ አልሆነም ።ምክንያቱም አባትነቱ ተፈጥሮ ነው።ልጅነቱም ተፈጥሮ ነው ።አይነኬ እና አይነኬ የተፈጥሮ ማንነት ነው።
ይህ በስም እና በግብር የሚታወቀው የሦስት አካላት ልዩነት የበላይነትም የበታችነትንም አያሳይም፤በጊዜ ኡደት ድንገትም የተከሰተ አይደለም።ምክንያቱም ይህ አንዱ አምላክ በሥስት አካልነት ያደረገው የሥራ ድርሻ ብቻ ነው።ይህንን በልባችን ይዘን እናጠን እንደቃሉ።
"አንዱን አምላክ ሥስት አካል ስለመኖሩ [በስም እና በሥራ (በግብር) ] ብቻ ልዩነት መኖሩን" እናጠናለን በቀጣይ ።
.............
"አንዱ አምላክ ሦስት አካል ስለመኖሩ በሥራቸው እና በስማቸው ብቻ እንደሚንለይም" እንደሚከተለው ቀርቧል ፦
"በሥነ ፍጥረት ሥራ ላይ"
“እርሱም የማይታይ አምላክ ምሳሌ ነው፤ የሚታዩትና የማይታዩትም፥ ዙፋናት ቢሆኑ ወይም ጌትነት ወይም አለቅነት ወይም ሥልጣናት፥በሰማይና በምድር ያሉት ሁሉ በእርሱ ተፈጥረዋልና ከፍጥረት ሁሉ በፊት በኵር ነው፤ ሁሉ በእርሱና ለእርሱ ተፈጥሮአል፤”ቆላ 1፥15-16
የወልድ ድርሻ ምን ነበር !?
☝ከዚህ ክፍል እንደሚንረዳው ወልድ ሁሉን ፈጥሯል ፤ ፈጥሮም ፍጥረታትን አገጣጥሞታል(ሰርቷል)። ደግሞም አብም ስለ ልጁ ስመሰክር “ደግሞ፦ ጌታ ሆይ፥ አንተ ከጥንት ምድርን መሠረትህ፥ ሰማዮችም የእጆችህ ሥራ ናቸው፤”ዕብ 1፥10 ብሏል።ስለዚህም ፍጥረት የተፈጠሩት በወልድ ነው።ዮሐንስ እንዳለው “ሁሉ በእርሱ ሆነ፥ ከሆነውም አንዳች ስንኳ ያለ እርሱ አልሆነም።”ዮሐ 1፥3 ።
የአብ ድርሻ ምን ነበር !?
☝አብ ዓለምን የመፍጠር ሃሳቡ በወልድ በኩል ፈጸመው ።አብ ለመፍጠር አቂም አንሶት ሳይሆን መልእክት የሚያስተላልፈው በወልድ ስለሆነ ነው፤ድርሻው ይህ ነው።ስለዚህም አብ በልጁ የሚናገር ነው ሃሳቡን።“ሁሉን ወራሽ ባደረገው ደግሞም ዓለማትን በፈጠረበት በልጁ በዚህ ዘመን መጨረሻ ለእኛ ተናገረን፤”ዕብ 1፥2
☝አብ በልጁ መናገሩ መናገር ስለማይችል ሳይሆን "የአምላክ ቃልነት" የወልድ ግብር ስለሆነ ነው ። ዮሐ1፥1።
*ከላይ አብ በልጁ እንደፈጠረ አይተናል ።ፍጥረታት የተፈጠሩት በእጅ በመሰራት አይደለም፤ተቦክቶ አይደለም ።ይልቁንም በመናገር ነው።ስለዚህ የአብ ሃሳብ መፍጠር ከሆነ የሚፈጠረውም በመናገር ከሆነ ፣ የመናገር ተግባር የወልድ ስለሆነ ሁሉንም በሚገርም ሆኑታ ወልድ እንደ ግብሩ በመናገር ፈጠረው፤ገጠመው ።“እርሱ ብሎአልና፥ ሆኑም፤ እርሱም አዝዞአልና፥ ተፈጠሩም፤ የእግዚአብሔርን ስም ያመስግኑት።”— መዝ 148፥5 ፤ 33፥6።
የመንፈስ ቅዱስ ድርሻ ምን ነበር !?
☝መንፈስ ቅዱስም እንደ ግብሩ ለተፈጠረው ፍጥረት
ውበትን ሰጠ ።ሃሌ ሉያ ።“በመንፈሱ ሰማያት ውበትን አገኙ፥ ።”ኢዮብ 26፥13
#ሥነ ፍጥረት ላይ የአንዱ አምላክ የሥስት አካላት ድርሻ ፦
🌱አብ ሃሳብ አዘጋጀ፤አቀደ ፣
🌱ወልድ አከናወነ፤ገጠመው ፣
🌱መንፈስ ቅዱስ ያማረ አደረገ፤ውበትን ሰጠ፣
የአንዱ አምላክ በሦስት አካላት አደራረጉ ድንቅ ነው። ሃሌ ሉያ ።
.................
"ሰውን ከመሥራት አኳያ "
“እግዚአብሔርም አለ፦ ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር፤ የባሕር ዓሦችንና የሰማይ ወፎችን፥ እንስሳትንና ምድርን ሁሉ፥ በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ ይግዙ።” ዘፍ 1፥26
ሌላውን ፍጥረት "ይሁን" በማለት እንደፈጠረም ሰውንም "ሰው ይሁን" ብሎ አልፈጠረም ። ሰራ፤ አበጀው እንጂ። በዚህ ክፍል ላይ " እግዚአብሔር አለ "ወይንም "አምላክ አለ" የሚል ነው እንጂ "አምላኮች አሉ" አይልም።አምላክ አንድ እንደሆነ በግልጽ ያሳየናል ። "..አለ" ይለናልና ። አንዱ አምላክ ለሥራ ሦስቱን አካላትን እንፍጠር አለ።አምላካዊ ምክክር ነው።
የአብ ድርሻ ምን ነበር ?
ደግሞም አንድ አካል ብቻ አለመኖሩን ማለትም ይህንን ሥራ እንደ ግብራቸው እና እንደስማቸው ለመሥራት አንዱ አምላክ ስለወደደ "እንፍጠር አለ" የአምላክ አካል አንድ እንዳልሆነ ይገልጻል ።መላእክትን "እንፍጠር" ብሎ እንዳላማከረ ግልጽ ነውና።ምክንያቱም በሌላ ክፍል “ወይስ አማካሪው ማን ነበር? ወይስ ብድራቱን ይመልስ ዘንድ ለእርሱ አስቀድሞ የሰጠው ማን ነው?”
— ሮሜ 11፥35 ተብሏልና ።
*ይህ የእንፍጠር ምክክር አምላክ ፉጡርን እንስካላማከረ ድረስ አምላካዊ የሦስት አካላት ምክክር ብቻና ብቻ ነው።[የኢኦተቤክ አዋልድ መጻሐፍት ማርያምን አማክሮ ፈጠረ የሚለው ኑፋቄ እንደሆነ ግልጽ ነው]
ከዚህ በፊትም በቃሉ እንደሚታወቀው የአብ ግብር እንደ አባትነቱ ውጥን ማዘጋጀት ነው ፣ የወልድ ውጥኑን መፈጸም ነው፣ መንፈስ ቅዱስ ውበትን ማላበስ ነው።ይህ የአንዱ አምላክ የአንድ ፈቃድ የአንድ ሃሳብ ተግባር እንጂ የበላይነት ወይንም የበታችነት አይደለም ።በእኛ ነገር አይለካምና።
የወልድ ድርሻ ምን ነበር ?
በዚህ ተግባር ላይ መጽሐፍ ስናገር “እርሱም ከሁሉ በፊት ነው ሁሉም በእርሱ ተጋጥሞአል።” ቆላስ 1፥17 ስለሚል ።በወልድ የሰው ልጅ ከምድር አፈር እንደተጋጠመ /እንደተሰራ/ መረዳት እንችላለን ። ምክንያቱም ሰውም ፍጥረት ነው።
የመንፈስ ቅዱስ ድርሻ ምን ነበር ?
ሌላው ደግሞ የመንፈስ ቅዱስ ምና በአንድነት ከመስማማት ባሻገር በወልድ የተጋጠመውን ሰውን ሕይወትን መስጠት ነው።“እግዚአብሔር አምላክም ሰውን ከምድር አፈር አበጀው፤ በአፍንጫውም የሕይወት እስትንፋስን እፍ አለበት ሰውም ሕያው ነፍስ ያለው ሆነ።”ዘፍ 2፥7 ፣
ስለዚህም በሌላ ክፍል ላይ በግልጥ እንደተቀመጠው ሰው "ነፍስ ያለው" እንድሆን መንፈስ ቅዱስ ምናውን ተጫወተው፤ሕይወትን በመስጠት ። “የእግዚአብሔር መንፈስ ፈጠረኝ፥ ሁሉንም የሚችል የአምላክ እስትንፋስ ሕይወት ሰጠኝ።”— ኢዮብ 33፥4
#የሰው አፈጣጠር ላይ የሦስቱ አካላት ድርሻ ፦
🌱በአብ ሃሳቡ አስቀድሞ ታቀደ ፣
🌱በወልድ ዕቅዱ ተጋጠመ ተከናወነ ፣
🌱በመንፈስ ቅዱስ ነፍስን አገኘ፤ህያው ሆነ፤ተዋበ።
"አንዱ አምላካችን በሥራ እና በስማቸው ብቻ የእርስ በእርስ የአካል ልዩነቱን እናውቃለን" [ ከጳውሎስ ፈቃዱ ፣ "የእግዚአብሔር ልጅ" ወሰድኩት በአጭሩ ]።
...................
"ወልድ ሰው ከመሆን አንፃር "
ሰው በኃጢአት ስሪ በመውደቁ ምክንያት የኀጢአትን ኃይል ማስወገድ ሰው በራሱ አልቻለም ፤መላእክቱም ብሆኑ አይችሉም።ስለዚህም ሰውን ልያድን የሚችለው አንዱ አምላክ ራሱ ነው።ስለዚህም የሰውን ልጅ ለማዳን አምላክ ራሱ መድኃኒት አመጣ።ኢሳ 59።
ለዚህ ሥራ ደግሞ ደም ያስፈልጋል ።ምክንያቱም "ሕጉ ደም ሳይፈስ ስሪዬት የለም"ይለናል ዕብ 9። የሰው ሕይወት ያለው በደም ነው።ስለዚህም አምላክ ሰውን አልመሰለም፤የሰውን ሥጋ የሚመስል ሌላ አልፈጠረም ፤ከሰማይም አላመጣም።ኀጥአተኞችን እንድወክል ከእነሱ እንደ አንዱ ሆነ (ንፁህ ሙሉዑ ሰው ሆነ)። አምላክነቱን ሳይቀይር ወደ ሰውነት ሳይለወጥ። በአምላክነቱ ላይ ሰውነትን የራሱ ማንነት አደረገው፤ደመረው።ቃሉ እንደሚል "ሥጋ ሆነ" ወይንም "ሰው ሆነ"።ዮሐ 1፥14።
ሰው የሆነበትን አደራረግ እንመልከተው ፦
የአብ ድራሻ ምን ነበር !?
☝ ከሰው ሴት ልጆች መካከል አብ ከገሊላ ማርያምን መረጠ።“መልአኩም እንዲህ አላት፦ ማርያም ሆይ፥ በእግዚአብሔር ፊት ጸጋ አግኝተሻልና አትፍሪ።” ሉቃ 1፥30 ። ወልድን በሥጋ ለመውለድ በእግዚአብሔር ፊት ጸጋ ወይንም ነፃ ስጦታ ማርያም አገኘች፤ታደለች ።
ስለዚህ ምርጫ የተደረገው በአብ ነው ማለት ነው።
☝“..፥ የልዑልም ኃይል ይጸልልሻል ስለዚህ ደግሞ ከአንቺ የሚወለደው ቅዱስ የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል።” — ሉቃስ 1፥35 ።"የልዑል ሃይል" የተባለው ከሁሉ በላይ የሆነውን /ከላይ/ በማለት አብን ለመግለጽ ጥቅም ላይ ውሏል።አብን አመልካች ነው።
☝የልዑል ሃይል "ምን ያደርጋል !? " ብንል ይሸፍናል፤ ይከለክላል፣ይጋርዳል እንደ መጋረጃ.. ።ቅዱስ ያረድ ፍልሰታ ድጓ ላይ መጽሐፈ ኪዳነ ምህረት ላይ "ሥጋዋን አንጽቶ፣እርሷን ቀድሶ፣በእርሷ ላይ አደረ" እንዳለው ።ምናልባት የልዑል ሃይል ልዩ ጥበቃም ራሱ ለማርያም ማድረጉ ከዚህ በፊት ያልተደረገ ስለሆነ ስለሚወደው ልጅ እንደሆነ እንረዳለን ።ደግሞም ማህፀን ብቻ ሳይሆን ሙሉዕ የማርያም አካልን ነው የሸፈነው ፤ የከለለው።ሃሌ ሉያ።
የወልድ ድርሻ ምን ነበር !?
☝ ወልድ አብ በመላኩ ፤ በተፈጥሮ መስማማታቸ ተስማምቶ ተልኮ መጣ ።“..፥ የላከኝን ፈቃድ እንጂ ፈቃዴን አልሻምና።”— ዮሐንስ 5፥30
☝ሰው የመሆን ወይንም ሥጋን ገንዘቡ ማድረግ የወልድ ተግባር ድርሻ ነው፤በአምላካዊ ምክክር።
☝በሰው ማህፀን ውስጥ ያደረው ከሦስቱ አካላት አንዱ አካል ወልድ ነው።ስለዚህም "አንዲያ ልጁ ነው የመጣው "
የመንፈስ ቅዱስ ድርሻ ምን ነበር !?
☝ ወልድ አምላክነቱን ላይጠቀም ሰው ለመሆን ስለተስማማ ማለትም "ራሱን ባዶ አድርጎ" እኛን ለመሆን ስለምመጣ ፣ ይህንን አገልግሎት እንድፈጽም መንፈስ ቅዱስ በሁሉም ነገር ከእርሱ ጋር ነበር።ምክንያቱም ወልድ የራሱን የአምላክነት ክብሩን፣ ሃይሉን "በይደር ይቆይልን" እንደማለት ስለማይጠቀም መንፈስ ቅዱስ እርሱን ይዞ መጣ ።“መልአኩም መልሶ እንዲህ አላት፦ መንፈስ ቅዱስ በአንቺ ላይ ይመጣል፥..።” ሉቃስ 1፥35 ።
☝መንፈስ ቅዱስ የተላከውን ወልድን ይዞ መጣ እንጂ ከወንድ አልወለደችም፤እዚህ ላይ መንፈስ ቅዱስ የሠራው በማህፀኗ ወልድን የማምጣት ሥራ ነው፤የመጽነስ ሥራ ነው።መንፈስ ቅዱስ ሰው ለመሆን አልመጣም፤ይዞ መጣ እንጂ። እንዲያ ባይሆን ኢየሱስ ብቸኛ ልጅ አይባልም ።መንፈስ ቅዱስም ልጅ ይባል ነበር።
☝መንፈስ ቅዱስ ስመጣም እንደ ማንነቱ መንፈስ ነው፤ ወልድም መንፈስ ነው ። ።ሥጋን ከአየር አልፈጠረም ፤አላመጣም።ግን ሰው ለመሥራት ለዚያውም ንፁህ ሰው ለመሥራት ወልድን አመጣ፤ንፁህ ልጅ እንድገኝም አከናወነ።
ስለዚህም ፦
*ከሥላሴ አካል አንዱ ደግሞ ወልድ ተላከ ፣ ወልድ ራሱን ባዶ አድርጎ፣አዋርዶ፣ዝቅ አድርጎ ፣መጣ ። በመንፈስ ቅዱስ እገዛ እንደ ምክክራቸው ወልድ መጣ ፣ ወልድ አምላክነቱን ስለማይጠቀም ( ራሱን ባዶ ስላደረገ ) በመንፈስ ቅዱስ እገዛ መጣ ፣
[የኢየሱስ አገልግሎት በምድር ላይ ሁሉም በመንፈስ ቅዱስ እገዛ ነው]
#ወልድ ሰው በመሆን ሥራ ላይ ፦
🌱አብ መረጠ፤አቀደ ፣
🌱ወልድ ተላከ፤አደረ ፣
🌱መንፈስ ቅዱስ ወልድን ይዞ አመጣ፤ከወልድ ጋር ሆነ፣
አንዱ አምላክ በሦስት አካላት ተገልጦ መስራቱ እንዲህ ድንቅ ነው።
................
ሰው ከማዳን ሥራ አንጻር !
“.፥ እግዚአብሔር አብ አስቀድሞ እንዳወቃቸው በመንፈስም እንደሚቀደሱ፥ ይታዘዙና በኢየሱስ ክርስቶስ ደም ይረጩ ዘንድ ..፤ ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ።”1ኛ ጴጥ 1፥1-2
የአብ ድርሻ ምንድነው ?
☝ዓለም ከመፈጠሩ በፊት አብ አወቀን፣ እኛ በለለብን ጊዜ እንኳን ከማንም አስቀድሞ በክርስቶስ በኩል መረጠ፤ ለማዳን አስቦናልም።ይህንን ያሰበው ከግዜ ኡደት በፊት ነው።አምላክ በማወቁ እውቀት አወቀ።
☝ በማወቁ እውቀት አውቆ ለማዳን በማሰቡ ወልድ የሚድነቱን እንድለይ ተልዕኮ ሰጠ ።
የወልድ ድርሻ ምን ነበር ?
ዕብ 5፥10 የሚታዘዙለት ሁሉ እንዲድኑ ምክንያት ሆነ እንደሚል።የሚታዘዙቱን የለየው በደሙ በማጠብ ነው። የሚታዘዙትን በደሙ እያነፃ ከዓለም ይለያቸዋል ።በዚህ ትግበራ ነው ድነት በአጭር ቃል።
የመንፈስ ቅዱስ ድርሻ ምን ነበር ?
የኢየሱስን የምድር አገልግሎቱ በመንፈስ ቅዱስ እገዛ ነው የተከናወነው።ለኢየሱስ የሚታዘዙት በደሙ ካነፃ በኃላ ፣ ከዓለም የመለየት ሥራ የምሰራው መንፈስ ነው ።መንፈስ በዚህ ሥራ ከኢየሱስ ጋር ያለ መለየት ይሰራል ።
ኢየሱስ አገልግሎት የጀመረው በመንፈስ ተቀብቶ ነው፤ተሞልቶ ነው።ራሱን ባዶ ስላደረገ በመንፈስ ቅዱስ ይታገዛል።ስያስተምርም በመንፈስ ነው።
#ድነት ላይ የሥስቱ አካላት ድርሻ ፦
🌱አብ አቅዶ በክርስቶስ መርጦ ወልድን ላከ፣
🌱ወልድ በአብ ተመርጦ ለራሱ የሚታዘዙትን በመንፈስ እየተመራ በደሙ አነፃ፣
🌱መንፈስ ቅዱስም ከኢየሱስ ጋር ሆኖ የሚታዘዙለትን ቀደሰ፤ለየ።
አደራረጉ ድንቅ ነው።"በእውነት ስም እና ሥራ ባይኖራቸውም ማንም ማወቅ እና መለየት አይችልም ሦስት አካላትን" ። ሃሌ ሉያ።
..............
" የድነታችን መስዋዕት "
“በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና።”ዮሐ 3፥16
የአብ ድርሻ ምን ነበር !?
አብ ዓለሙን በመውደዱ በልጁ በኢየሱስ ያመኑቱ እንድድኑ ፈቃዱ ነው።ይህም እንድሆን አስቀድሞ አስቦ ፣ አቅዶ በክርስቶስ በኩል እንድቀርቡ ፈቅዶ ክርስቶስን ላከ።“ነገር ግን ገና ኃጢአተኞች ሳለን ክርስቶስ ስለ እኛ ሞቶአልና እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን የራሱን ፍቅር ያስረዳል።”— ሮሜ 5፥8
የክርስቶስ ሞት ራሱ የአብን ፍቅር ያስረዳል ።ምክንያቱም በዘላለም መውደድ የሚዋደዱ ስለሆኑ በልጁ መጨቀኑ ፣ እንድሞት መፍቅዱ ፣ ፍቅሩን ያሳየናል ።ስለዚህም አንዱ አምላክ በሥላሴአዊ ምክክር ያደረጉት ስምምነት ለሰው ልጆች ያለውን ፍቅርን ያስረዳል ።
አብ በክርስቶስ በኩል እያስታረቀ እስካሁን አለ።“እግዚአብሔር በክርስቶስ ሆኖ ዓለሙን ከራሱ ጋር ያስታርቅ ነበርና፥ በደላቸውን አይቆጥርባቸውም ነበር፤ በእኛም የማስታረቅ ቃል አኖረ።”2ኛ ቆሮ 5፥19 ።እኛ የማስታረቅ ቃል ወይንም "ታርቁ" የሚል የእርቅ መልእክት አለን ማለት ነው እንጂ በእኛ በኩል ሰዎች ወደ እግዚአብሔር መንግስት ከኀጢአት እየነፁ ይገባሉ ማለት አይደለም።
"ነበርና" ይላልና አሁን በሰዎች በኩል ነው ከእግዚአብሔር ጋር መታረቂያው ማለት ስህተት ነው።አያስከድም ምክንያቱም ".ቃልም እግዚአብሔር ነበር" መጽሐፍ ይለናል።ነበር ስለተባለ ቃል (ወልድ )አሁን አምላክ አይደለም ማለት ነውን ?አይደለም አይሁንም አምላክ ነው።እንደዚያውም አሁንም በክርስቶስ በኩል ብቻ እርቅ አለ።ሃሌ ሉያ።ምክንያቱም መቼም ብሆን አብ በልጁ በኩል የሚያስታርቀውን በሰዎች አይተካም ።ምክንያቱም የአብ ዕቅዱ “በዘመን ፍጻሜ ይደረግ ዘንድ ያለው አሳቡም በሰማይና በምድር ያለውን ሁሉ በክርስቶስ ለመጠቅለል ነው።" ኤፌ 1፥10
ይቅር በማለት በመታርቅ ያነፃቸው የነበረው አብ ነው።መስዋዕቱ የቀረበው ለእርሱ ነው።“ነውር የሌለው ሆኖ በዘላለም መንፈስ ራሱን ለእግዚአብሔር ያቀረበ.." ዕብ 9፥14
የወልድ ድርሻ ምን ነበር !?
ወልድ ( ልጁ) ነው መስዋዕት ያቀረበው ።ያቀረበውም ራሱ ራሱን ነው።“እርሱም በስጋው ወራት ከሞት ሊያድነው ወደሚችል ከብርቱ ጩኸትና ከእንባ ጋር ጸሎትንና ምልጃን አቀረበ፥ እግዚአብሔርንም ስለ መፍራቱ ተሰማለት፤”ዕብ 5፥7
የመንፈስ ቅዱስ ድርሻ ፦
“ነውር የሌለው ሆኖ በዘላለም መንፈስ ራሱን ለእግዚአብሔር ያቀረበ የክርስቶስ ደም እንዴት ይልቅ ሕያውን እግዚአብሔርን ልታመልኩ ከሞተ ሥራ ሕሊናችሁን ያነጻ ይሆን?”— ዕብራውያን 9፥14
ኢየሱስ በምድር ላይ ስያገለግል በመንፈስ ቅዱስ እገዛ ነው፤ተሞልቶ ነው፤ተቀብቶ ነው።ስለዚህም መስዋዕቱ ስቀርብም በመንፈስ ቅዱስ ነው ማለት ነው።
#ለድነታች ከቀረበው መስዋዕት አንፃር ሥስትነትን ስናይ ፦
🌱አብ መስዋዕቱ በልጁ እንድቀርብ አቀደ ፣እስከመጨረሻው በልጁ እየጠራ ለመጠቅለል ሃሳቡ ነው ፣
🌱ወልድ መስዋዕት አቅራቢ፣ያቀረበውም ራሱን ነው፣
🌱መንፈስ ቅዱስ ኢየሱስ እንዲያቀርብ አገዘው ፣ አጠነከረው ፣
እንግዲህ እንዲህ ነው፤ሥራው።የአንዱ አምላክ ።በሦስት አካላት የተገለጠው ።
..................
"ከጸሎት አኳያ"
“ሕፃኑም አደገ በመንፈስም ጠነከረ፥ ለእስራኤልም እስከ ታየበት ቀን ድረስ በምድረ በዳ ኖረ።”ሉቃስ 1፥80 ።የኢየሱስ እድገትም በመንፈስ የታገዘ ነው።ምልልሱም በመንፈስ ቅዱስ የታገዘ ነው።ምክንያቱም ሙሉዑ ሰውም ነው። ወደ መቅደስ ስወጣም በመንፈስ ቅዱስ ነው ሉቃ 2፥27።ወደ ምድረ በዳ ስመራም በመንፈስ ቅዱስ ነው።ሉቃ 4፥1።በኃይል ስያገለግልም በመንፈስ ቅዱስ ነው።ሉቃ 4፥14 ፤ሐዋ 10፥38።ስደሰተም በመንፈስ ነው ።ሉቃ 10፥21።መስዋዕት ስያቅርብም በመንፈስ ነው።ዕብ 9።
ስለዚህ ኢየሱስ ሁሉንም ነገር በምድር ስያደርግ እንደ ሰውነቱ በመንፈስ ቅዱስ በመሞላት (በቁጥጥር ስሪ ) በመሆነ ነው።ብታወክም በመንፈስ ነው።ስጸልይም በመንፈስ ቅዱስ ነው ።ከመንፈስ ቅዱስ ተለይቶ አንዳች አላደረገም ።ለኢየሱስም መንፈስ ቅዱስ አስፈልጎታል።[ጸሎቱም ወደ አብ (ወደ አባት) እንደተደረገ ያስተውሏል።]
የአብ ድርሻ ምን ይመስላል ?
ጸሎቱን ኢየሱስም ወደ አባቱ [ወደ አብ] ይጸልያል ። “ኢየሱስም ይህን ተናግሮ ወደ ሰማይ ዓይኖቹን አነሣና እንዲህ አለ፦አባት ሆይ፥ሰዓቱ ደርሶአል፤ልጅህ ያከብርህ ዘንድ፥ በሥጋም ሁሉ ላይ ሥልጣን እንደ ሰጠኸው፥ ለሰጠኸው ሁሉ የዘላለምን ሕይወት ይሰጣቸው ዘንድ ልጅህን አክብረው።”ዮሐ 17፥1-2
ኢየሱስ ወደ አባቱ እንድንጸልይ አስተምሮናል፤እንዳስተማረንም ወደ አባት (አብ) ጸሎት እናደርጋለን ።“አላቸውም፦ ስትጸልዩ እንዲህ በሉ፦ በሰማያት የምትኖር አባታችን ሆይ፤ ስምህ ይቀደስ፤ መንግሥትህ ትምጣ፤ ፈቃድህ በሰማይ እንደ ሆነች እንዲሁ በምድር ትሁን፤”ሉቃስ 11፥2
የወልድ ድርሻ ምን ይመስላል ?
“..እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ አብ በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ ይሰጣችኋል።” ዮሐንስ 16፥23
የሚንጸልየው በወልድ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ነው።ሁሉም በልጁ በኩል እንድቀርቡ የአብ ፈቃዱ ነው።ስለዚህም እኛም ኢየሱስ እንዳስተማረን "በልጅህ በኢየሱስ ስም ስልጣን" ብለን ወደ አብ እንለምናለን ።
የሚንጸልየው ጸሎት ወደ አብ የሚሄደው በልጁ ስም (ማንነት) በኩል ነው።ስለልጁ ብሎ ይመልሳል ማለት ነው።ምክንያቱም ልጁ አሁንም የሚታይልን ፣ስለ እኛ የተቀመጠ ሊቀ ካህናት ነው።በአባቱ ዘንድ ስለእኛ ስላለ ስለእሱ ተብሎ ጸሎታችን ይሰማል፣ይመለሳል አድራሻ አልባ አይደለም ማለት ነው።
የመንፈስ ቅዱስ ድርሻ ምን ይመስላል !?
ጸሎቱ ወደ አብ ስለ ኢየሱስ ማንነት(ስም) ተብሎ ይቅርባል ፣ እንዲህ እንድናቀርብ ደግሞ መንፈስ ቅዱስ ከደሙ ጋር የማይፃረር ጸሎት እንድናደርግ ያግዘናል ።“እናንተ ግን፥ ወዳጆች ሆይ፥ ከሁሉ ይልቅ በተቀደሰ ሃይማኖታችሁ ራሳችሁን ለማነጽ እየተጋችሁ በመንፈስ ቅዱስም እየጸለያችሁ፥”ይሁ 1፥20።[የሚንጸልየው በመንፈስ ነው።በእርሱ ምሪት ብቻና ብቻ ነው።]
ኢየሱስ ክርስቶስ በመንፈስ ታግዞ ራሱን እንዳቀረበ እኛም ጸሎታችንን በመንፈስ ታግዘን እናቀርባለን ።ከዚህ ባሻገር መንፈስ ቅዱስ ለእኛ ልገባ በማይችል መልኩ ይረዳናል ። "እንድህ በል፣እንድህ በል " እያለን በእኛ ውስጥ ሆኖ ለእኛ ከእኛ ጋር ይለምናል ።መንፈስ ቅዱስ እኛንም እያነቃቃ እያገዘ ደግሞም ከእኛ ጋርም ለእኛ ይለምናል ።[እኛ ወደምንጸልይበት]
“መንፈሱና ሙሽራይቱም፦ ና ይላሉ። የሚሰማም፦ ና ይበል። የተጠማም ይምጣ፥ የወደደም የሕይወትን ውኃ እንዲያው ይውሰድ።” ራእይ 22፥17 እንደሚል ነው።ከዚህ ክፍል ላይ እንደሚንገነዘበው "መንፈስ ቅዱስ ስለእኛ ይማልዳል" መባሉ ከእኛ ጋር ሆኖ እኛን በጸሎታችን ይተባበራል እያለንም ነው።ለምሳሌ "እኛ ጌታ ሆይ ና" እንድንል ፦ ያግዘናል፣ ይነግረናል ፣ይረዳናል ፥ እንድህ በልም" ይለናል።የአምላክ ፈቃድ ለእኛ አስታውቆ እርሱም ደግሞ ከእኛ ጋር "ና" ይላል በግልጽ ከዚህ ክፍል እንደሚንረዳው።[ስለዚህም መንፈስ ቅዱስም በእኛ ውስጥ ሆኖ ስለእኛ ይጸልያል]
*መንፈስ ቅዱስ በእኛ ውስጥ ሆኖ ለእኛ ይለምናል።እንዴት መጸለይ እንደሚገባን ፈቃዱን ይነግረናል፣ያግዘናል፣ያበረታናል።ሃሌ ሉያ።
*ከሦስቱ አካላት አንዱ አካል "አደረገ" ብንልም አድራጊው አንዱ አምላክ ነው።የሥራ ድርሻ ኖራቸው በስምም /በግል ማንነትም/ ስለሚጠሩ አንዱ አምላክ ሥስት አካላት መኖሩን እናውቃለን።ለምሳሌ ጸሎት ወደ አብ ብደረገ የተደረገው ወደ አንዱ አካል ብሆንም መቀበል ለእርሱ ድርሻ ብሆንም የድርሻው ባለቤት ራሱ አንዱ አምላክ ነው፤እንዲቀርብ ያደረገው የመንፈስ ድርሻም የአንዱ አምላክ ሥራ ነው።[ስለዚህም ወደ አብ እንድንጸልይ ኢየሱስ ብያስተምርም ኢየሱስም አምላክ ስለሆነ ወደ እርሱ ይጸልያል]።ምክንያቱም አንዱ አምላክ ሥስት አካላት አለው።
#በጸሎቱ የሦስቱ አካላት ድርሻ ፦
🌱አብ ጸሎትን ይቀበላል ፣
🌱በወልድ ማንነት (ስም) በኩል ጸሎት ይቅርባል፣
🌱በመንፈስ ቅዱስ እንደ ፈቃዱ ጸሎት እንድቀርብ ይታገዛል ፣
"ከአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ የአንዱን አምላክ ሃሳቡን ተቀበልን ፣ በዚያውም ደግሞም በመንፈስ ቅዱስ በወልድ በኩል ወደ አብ ይቀርባል ጸሎታችን" [ከጳውሎስ ፈቃዱ "የእግዚአብሔር ልጅ"]
...................
ኢየሱስ አንድ አካል ነው።ግን ሁለት የማይገናኝ ማንነት በውስጡ አለው።ሰውነት እና አምላክነት ። ያ ማለት በለስ ፦አንዱ ዛፍ በለስም ሙዝም የያዘ እንደማለት ነው።አንዱ አካል ላይ ሁለት የማይገናኝ ተፈጥሮ አለው።የአምላክ ሥስት አካልነትም የዚህ ተቃራኒ ነው ማለት እንችላለን።[አንዱ አምላክ ሦስት አካል አለው ።ራሱ አንዱ አምላክ ሦስት አካል አለው።]
☝ የኢየሱስ ፦ሁለት ተፈጥሮ በአንድ አካል ነው፣
☝ የአምላክ ፦አንድ ተፈጥሮ በሦስት አካላት ነው።
አንዱ አምላክ በተመሳሳይ ማንነት (ባህሪ) ሦስት አካላት አለው ።ስለዚህም አብ የሠራውን ወይንም የሆነውን ኢየሱስ ሲሆን ወይንም መንፈስ ቅዱስ ሲሆን ስያደርግ አንድ አምላክ እንደሆነ እንረዳለን ።
"በአብ በወልድ እና በመንፈስ ቅዱስ መካከል ያለው ልዩነት የሥራ ድርሻ እና ለድርሻው የተሰጠው ስም ነው"።አንድነቱ አምላክነት ነው።አምላክ ሦስት አካል መኖሩ ሦስት አምላክ ነው አያስብለውም።
ስም እና የሥራ ድርሻ መኖሩ መስተዳድራዊ ልሆን ይችላል እንጂ ማንነትን አይቀይርም።ማንነት ማለት ተፈጥሮ ነው።ባህሪ የሚንለው ነው።ደግሞም ባህሪ ስንል የማይቀየር ማንነት ወይንም ተፈጥሮ እያለን ነው እንጂ እንደየሰው መልኩ የተለያየውን ''ጠባይ'' እያልን አይደለንም።
የሰው ማንነት ፦ ሥጋ፣መንፈስ ፣ነፍስ፣አዕምሮ ፣ኩላልት፣ልብ፣.." ነው።ማነኛውም ሰው ይህ አለው።በሁለት እግር ብሄድ ባይሄድ ሰው ነው።ይህ የሰውነት ተፈጥሮ እስካለ ድረስ። የውሃ ተፈጥሮ ፈሳሽነት ነው።ድንጋይም ተፈጥሮ አለው፤ ጠጣርነት።ትልቅ ይሁን እጅግ ትንሽ ድንጋይ ጠጣር ነው ማንነቱ።የአምላክ ተፈጥሮ ወይንም ባህሪ ወይንም ማንነት ስንል መለኮት ነው እያልን ነው።አንዱ አምላክ በሦስቱ አካላትም ሙሉዑ መለኮት ነው።
ከሦስቱ አካላት አንዱ አካል የተኛውንም የሥራ ድርሻ ልሰራ ልያከናውን ይችላል ።ግን ከማንነቱ ጎደለ ማለት አይደለም ።ለምሳሌ ውሃ መልኩ እንደ እቃው እና እንደየቦታው ልቀየር ይችላል፤ማንነቱ ግን ፈሳሽነቱ ነው።አይቀየርም።ስለዚህ ከሦስቱ አካላት አንዱ አካል አንድን ሥራ ድርሻ ከሠራ ፥ ከሌሎች አካላት መብለጥን ሆነ ማነስን አያሳይም።
ከሦስቱ አካላት ሁሉንም ፍጥረታትን የሠራው ፣ በቃሉ የደገፈው የእግዚአብሔር ቃል ነው (ወልድ ነው)።ስለዚህም ይህንን ሥራ ድርሻ በወልድ በኩል ስለተሰራ ወልድ በማንነቱ ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ይበልጣል ማለት አይደለም ።አብም መንፈስ ቅዱስም በመለኮቱ አንድ ተመሳሳይ ናቸው ።የሥራ ድርሻ ብቻ ነው።[እንድሁም ወልድ ሰራ ብንልም ባለቤቱነቱ ለሦስቱ አካላት ለአንዱ አምላክ ነው።]
እንደዚያውም ደግሞ በብዙ ለሥላሴአዊያን ጭምር የማንነት ማነስ የሚመስለው የልጁ ጸሎት ማቅረቡ ነው።ይህ የሥራ ድርሻ "ማነስ" ከተባለ ሰው መሆኑ እንጂ ሥራው አይደለም ።ምክንያቱም ሰው ሲሆን ውስን ይሆናል ይራባል ይጠማል።ግን የአምላክ ማንነቱ ሁለም የሚቀየር አይደለም ።ልመና ራሱ ስያቀርብ ፣ እንዲያቀርብ የተደረገው በሦላሴአዊ ምክክር ነው፤ያቀረበውም በመንፈስ ነው።[ሥራውን በሦስት አካላት የሠራው አንዱ አምላክ ነው።]
ወልድ ሁሉንም መፍጠሩ እና ማጋጠሙ (መሥራቱ) ፣ ካለ እርሱ አንዳች እንኳን አለመሠራቱ ወልድን ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ከፍ እንደማያደርገው ሁሉ ፥ ለዓለም ራሱን ቤዛ አድርጎ ፣ ልመናና ጸሎት ማቅረቡም አያሳንሰውም።ይህ የሥራ ድርሻ እንጂ የተፈጥሮ ማንነት መቀየር አይደለም ። ስለዚህም አብ መለኮት ነው፤ ወልድም መለኮት ነው፤መንፈስ ቅዱስም መለኮት ነው።አምላክ አንድ ነው።አካሉ ግን ሦስት ነው።የአምላክ ተፈጥሮ በሦስቱ አካላት ውስጥም አይቀየርም ።
....................
[ሦስት አካላት ለአንዱ አምላካችን ስላለው ፣ስንጸልይ አንደኛው አካል ብንጠራ ወይንም በእርሱ ብንታመን በአንዱ አምላክ መደገፋችን ፣ መታመናችን እንጂ ሦስት አምላክ ማምለካችን አይደለም ።]
አምላክ ሦስት ብሆን ሦስት የተለያየ ተፈጥሮ ይኖር ነበር።የሃሳብ አለመግባባት ፣አለመስማማት ፣የሥልጣን ልዩነት ፣የፈቃድ ልዩነት ይኖር ነበር።ግን አንድ ብቻና ብቸኛ ስላለን በሦስቱም አካላት ላይ ፍጹም አንድነት አለ።
ለምሳሌ ወደ አብ ወደ አንዱ አካል ይጸለያል ፤ወደ ኢየሱስም ይጸለያል ።“ጌታም ወደ እግዚአብሔር ፍቅር ወደ ክርስቶስም ትዕግሥት ልባችንን ያቅናው።”2ኛ ተሰ 3፥5 ።ክርስቶስም አምላክ ነው ጸሎት የሚቀበል ፣ አብም አምላክ ነው ጸሎት የሚቀበል ።አንዱ አምላክ ስለሆነ ሦስቱ አካላት ይጋራሉ።
ከሦስቱ አካላት አንደኛውን አካል ብንክደው ሦስቱንም አካላትን መካዳችን ነው።በአንዱ አካል ብንታመን በእርሱ በኩል ሦስቱን አካላትን አውቀን ፣ በሦስቱም አካላት መታመናችን ነው።“እኔንም የሚያይ የላከኝን ያያል።”ዮሐ 12፥45 ፤44 እንደሚል ነው።መጽሐፍ ስናገር “ወልድን የሚክድ ሁሉ አብ እንኳ የለውም፤ በወልድ የሚታመን አብ ደግሞ አለው።”1ኛ ዮሐ 2፥23 ይለናል።
ስለዚህም አንዱን በሥጋ የተገለጠውን ወልድን (ኢየሱስን ) ብንክድ ሦስቱንም አካላትን መካዳችን ነው ።መጽሐፍ ስናገር ፦“የእግዚአብሔርን ልጅ የረገጠ ያንንም የተቀደሰበትን የኪዳኑን ደም እንደ ርኵስ ነገር የቆጠረ የጸጋውንም መንፈስ ያክፋፋ፥ እንዴት ይልቅ የሚብስ ቅጣት የሚገባው ይመስላችኋል?”ዕብ 10፥29 ፣ ይለናል ።
ስለዚህም አንዱን አካል የካደ ሰው ፦ የእግዚአብሔርን ልጅ የረገጠ ነው፣ የኪዳኑንም ደሙን የሰደበ ነው ፣ መንፈስ ቅዱስንም ያሳዘነ ነው፤ ከአንዱ አካል ጋር ብቻ መጣላቱ አይደለም ።ይልቁንም አንዱን አምላክ መተው' ነው እንጂ፤ሥራውን ማገርሸጡ ነው።ስለዚህም “በሕያው እግዚአብሔር እጅ መውደቅ የሚያስፈራ ነው።” ዕብ 10፥31 ፣ ይለናል የአምላክ ቃል።ሃሌ ሉያ።
"አንዱ አምላክ ነው የሥራው ባለቤቱ" ማለታችን ፥ አንዱ አምላክ ታዲያ "እንዴት ነው የሚሰራው?" የሚለውን ብንጠይቅ ፦ በሦስት አካላት ተገልጦ እንደሆነ እንረዳለን።ለምሳሌ የኢየሱስ ትንሳኤ በተመለከተ “ነገር ግን ኢየሱስን ከሙታን ያስነሣው የእርሱ መንፈስ በእናንተ ዘንድ ቢኖር፥ ክርስቶስ ኢየሱስን ከሙታን ያስነሣው እርሱ በእናንተ በሚኖረው በመንፈሱ፥ ለሚሞተው ሰውነታችሁ ደግሞ ሕይወትን ይሰጠዋል።”— ሮሜ 8፥11
አንዱ አካል ኢየሱስ (በሥጋ የተገለጠው የሞተው) ፣ እንድነሳ አንዱ አምላክ ነው ያደረገው ።አንዱ አምላክ ግን "እንዴት ነው የሠራው?" ስንል የሦስቱ አካላቱን ድርሻ እንገነዘባለን ።አብ ኢየሱስ እንዲነሳ አቅዶ ለመንፈስ ቅዱስ ሃሳብን ስያወርድ ፣ መንፈስ ቅዱስም የአብን እቅድ ኢየሱስን በማንሳት ፈጸመው ።አንዱ አምላክ የሠራው ድንቅ ስራ ስለሆነ ኢየሱስም በራሱ ስልጣን እንደሚነሳ ተመዝግቧል ዮሐ 2፥19 ።ስለዚህም አንዱ አካል መስራቱም ሦስቱም አካላት እንደሰሩ ይቆጠራል ።አንድነቱ ይህ ነው።
አንዱ አምላክ አንዷን ሥራ በአንዱ አካል በኩል ብቻ ብፈጽምም ባለቤትነቱ ግን ለሦስቱ አካላት ለአንድ አምላክ ነው።ለምሳሌ ሐዋርያ ጳውሎስን የሾመው ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ሐዋ 9 ፤26፥16።ድርጊቱን ያከናወነው ከሦስቱ አካላት አንዱ አካል ኢየሱስ ነው።ግን በሌላ ቦታ ራሱ መልሶ ፣ ኢየሱስ የአብ ልጁ እንደሆነ አስረግጦ የሚመሰክረው ጳውሎስ "አብ እንደሾመው ይነግረናል ፦“በኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታንም ባነሣው በእግዚአብሔር አብ ሐዋርያ የሆነ ..፤”ገላትያ 1፥1-2 ፣ በማለት።
ኢየሱስ ሐዋርያትን መሾሙ ሌሎች አካላት ሐዋርያ አይሾሙም ማለት አይደለም ።በኢየሱስ በኩል ይልቁንም ሾመዋል ማለት ነው።ምክንያቱም እያንዳንዱ አካል የሌላው አካል ማንነት አለው ። ለዚህ ነው የተኛውን ሥራ የማንነት ማነስ ሆነ መብለጥን አያሳይም የምንለው ።ማንነት የማይቀየር እኔነት ነው።ተፈጥሮ ነው።ለሃገር ልማት አንዱ ሰው ከሰዎች መካከል አስተዳደር ብሆን ከሰውነት ከፍ ብሏል ማለት አይደለም ።ሌሎችም ከሰውነት ዝቅ ሆኖዋል ማለት አይደለም ።አንዱ ትዕዛዝን የመቀበል የማድረግ የማከናወን ከሆነ ፣አንዱ ማቀድ ከሆነ ፣ የተኛውንም ሥራ መስራታቸው ሰው መሆናቸውን አይቀየርም ።
ልክ እንደዛው አንዱ አካል አብ አቅዶ አስቦ ወልድን ይልካል ብንል፣ወልድም ይላካል ፣መንፈስ ቅዱስም ያላብሳል ውበትን ብንል ፣ የሥራ ድርሻ እንጂ ማንነት አይቀየርም ።በሥራ ድርሻ አብ አስተዳደር ከሆነ ከተፈጥሮ ማንነቱ ከፍ አይልም ፣ወልድም ብፈጽምም አያንስም፤መንፈስ ቅዱስም እንደዛው ።አቢይ የኢትዮጵያ አስተዳደር ነው።እንደ እኛ ሰው ነው።ከአስተዳደርነት ብወርድ የሥራ ድርሻ ቀየረ እንጂ ከሰውነት አልጎደለም ።ኢየሱስም በምድር እያለ በአስተዳደር ከአብ አንሶ ነበር ፤ግን የሥራ ድርሻውን ስፈጽም ተመልሶ ወደ ቅድሞ ክብሩ ተመልሷል ።እንጂ ማንነት አይቀየርም ።አንድ አምላክ ሦስት አካላት ።
ሃሌ ሉያ።
........
"በሥጋ የተገለጠው ማን ነው !?"
“እግዚአብሔርንም የመምሰል ምሥጢር ያለ ጥርጥር ታላቅ ነው፤ በሥጋ የተገለጠ፥ በመንፈስ የጸደቀ፥ ለመላእክት የታየ፥ በአሕዛብ የተሰበከ፥ በዓለም የታመነ፥ በክብር ያረገ።” 1ኛ ጢሞ 3፥16
ከላይ ያለውን ክፍል ጳውሎስ የተናገረው “.፥ በእግዚአብሔር ማደሪያ ቤት መኖር እንዴት እንደሚገባ ታውቅ ዘንድ እጽፍልሃለሁ፤ ቤቱም የእውነት ዓምድና መሠረት፥ የሕያው እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን ነው።”1ኛ ጢሞ 3፥15 ብሎ ለማስተማር።ስለዚህም የእግዚአብሔር ቤት እኛ የፈጠርነው ተቋም ሳይሆን እርሱ የመሠረተው አንድቷ መንፈሳዊቷ ቤት ቤተክርስቲያን ናት።
ጳውሎስ "እግዚአብሔርን መምሰል" በማለት የተጠቀመው ቃል እግዚአብሔርን በእወነተኛ መንፈሳዊ አምልኮ ማምለክን የሚያመለክት ቃል ነው።እግዚአብሔርን መምሰል የሚለው ቃል በግርኩ አውሰብያ የሚል ነው።አምልኮ፤እውነተኛ አምልኮ ማለት ነው።ስለዚህም ለእኛም ዛሬም በቤተክርስቲያን በአግባቡ ለመኖሩ የእውነተኛ አምልኮ ምስጢር ማወቁ በብዙ ይጠቅመናል ። እውነተኛ አምልኮ የሚኖረው እንዴት ነው !? እንደሚከተለው እንያ ፦
"በሥጋ የተገለጠ፥ "
በሥጋ የተገለጠው በእግዚአብሔር ዘንድ የነበረው "ቃል" የተባለው ወልድ አምላክ ነው ።ዮሐ 1፥14 ። በሥጋ የተገለጠው ኢየሱስ (ወልድ) ስለሆነ "አይተናል ፣ ዳስሰናል" ይሉናል ሐዋርያቱ ።1ኛ ዮሐንስ 1 ፥¹ ስለ ሕይወት ቃል ከመጀመሪያው የነበረውንና የሰማነውን በዓይኖቻችንም ያየነውን የተመለከትነውንም እጆቻችንም የዳሰሱትን እናወራለን፤ ² ሕይወትም ተገለጠ አይተንማል እንመሰክርማለን፥ ከአብ ዘንድ የነበረውንም ለእኛም የተገለጠውን የዘላለምን ሕይወት እናወራላችኋለን፤
*ከአብ ዘንድ የነበረው፥የተገለጠው ፥ የታየው ፥ መጀመሪያም በእግዚአብሔር ዘንድ የነበረው ቃል ፦ ወልድ ነው፤ኢየሱስ ነው።ሃሌ ሉያ።
"በመንፈስ የጸደቀ ፥ "
ይህንን ክፍል የቃል እምነት አስተማሪዎች ኢየሱስ ኀጥአተኛ ስለሆነ በመንፈስ ጸደቀ ለማለት ይጠቅሱታል ።ጸደቀ ማለት ሃቅ፣ ትክክልኛ ፣እውነተኛ..ማለት ነው።ስለዚህም "ኢየሱስ በመንፈስ ቅዱስ እንዴት ሃቀኛ ወይንም እውነተኛ ወይንም ትክክለኛ ሆነ !? "ብንል መልሱ “ዳሩ ግን እኔ ከአብ ዘንድ የምልክላችሁ አጽናኝ እርሱም ከአብ የሚወጣ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ፥ እርሱ ስለ እኔ ይመሰክራል፤”ዮሐ 15፥26 ።እንዳለው ነው።
*ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ እና ከአብ ዘንድ እንደመጣ የእውነት መንፈስ በመጣ ግዜ "ስለ ኢየሱስ ይመሰክራል" ቃሉ እንደሚል ፥ በበዓለ ሃምሳ ቀን መጣ ።ከዛም ኢየሱስ የነገረውን ሁሉንም ትክክል ፣እውነተኛ እንደሆነ አረጋገጠላቸውም፤መነሳቱንም።ስለዚህም እነሱም መሰከሩ፤በመንፈስ ቅዱስም ትክክለኛ መሆኑ ተረጋገጠ።
"ለመላእክት የታየ ፥."
ደግሞም ይህ ነገር እንዴት ነው !? ሰው ብቻ ሳይሆን መላእክቱም እግዚአብሔርን እንዳላዩ እንገነዘባለን ።ኢሳይያስ በግልጠት መላእክት እንኳን ፊታቸውን ሸፋነው እንደሚያመሰግኑ (እንደማያዩ) መስክሮ ነበርና ።" 6፥ ² ሱራፌልም ከእርሱ በላይ ቆመው ነበር፥ ለእያንዳንዱም ስድስት ክንፍ ነበረው፤ በሁለት ክንፍ ፊቱን ይሸፍን ነበር፥ በሁለቱም ክንፍ እግሮቹን ይሸፍን ነበር፥ በሁለቱም ክንፍ ይበር ነበር።³ አንዱም ለአንዱ፦ ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፤ ምድር ሁሉ ከክብሩ ተሞልታለች እያለ ይጮኽ ነበር። "
*መላእክት እንኳን አይተው የማያውቁትን ፣ ፊታቸውን ሸፊነው የሚያመልኩትን ጌታን በሥጋ ስገለጥ አዩ ።ሉቃስ 2 ፥¹⁰ መልአኩም እንዲህ አላቸው፦ እነሆ፥ ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ የምሥራች እነግራችኋለሁና አትፍሩ፤¹¹ ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋልና።
[ስለዚህም ከአብ የወጣው ፣ በመንፈስ የፀደቀው፣ በመላእክት የታየው ፦ኢየሱስ (ወልድ) ነው።]
" በአሕዛብ የተሰበከ፥ "
በአሕዛብ ዘንድ ጭምር የተሰበከው ኢየሱስ ነው።መጽሐፍ ስናገር ፦“ይህም በዓለም ሁሉ ደግሞ እንዳለ ወደ እናንተ ደርሶአል፥ የእግዚአብሔርንም ጸጋ በእውነት ከሰማችሁበትና ካወቃችሁበት ቀን ጀምሮ፥ በእናንተ ደግሞ እንዳለ እንዲህ በዓለም ፍሬ ያፈራል ያድግማል።” ቆላስይስ 1፥6
*የተሰበከው "የእግዚአብሔር ጸጋ" ኢየሱስ ነው። ምክንያቱም ይህ የተሰበከው ጸጋ ሁሉንም የሚያድን ነው።ያም ኢየሱስ ነው። “ሰዎችን ሁሉ የሚያድን የእግዚአብሔር ጸጋ ተገልጦአልና፤” ቲቶ 2፥11።ሃሌ ሉያ።
"በዓለም የታመነ ፥"
ቆላስይስ 1
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²¹-²² እናንተንም ነውርና ነቀፋ የሌላችሁና ቅዱሳን አድርጎ በእርሱ ፊት ያቀርባችሁ ዘንድ፥ በፊት የተለያችሁትን ክፉ ሥራችሁንም በማድረግ በአሳባችሁ ጠላቶች የነበራችሁትን አሁን በሥጋው ሰውነት በሞቱ በኩል አስታረቃችሁ።²³ ይህም፥ ተመሥርታችሁና ተደላድላችሁ ከሰማችሁትም ከወንጌል ተስፋ ሳትናወጡ፥ በሃይማኖት ጸንታችሁ ብትኖሩ ይሆናል፤ ያም ወንጌል ከሰማይ በታች ባለው ፍጥረት ሁሉ ዘንድ የተሰበከ ነው፥ እኔም ጳውሎስ የእርሱ አገልጋይ ሆንሁ።
*ስለዚህም የታመነ ነው፤ወንጌሉ ።
" በክብር ያረገ "
“ይህንም ከተናገረ በኋላ እነርሱ እያዩት ከፍ ከፍ አለ፤ ደመናም ከዓይናቸው ሰውራ ተቀበለችው።”ሐዋርያት 1፥9 ። [መላእክት ስወለድም ስያርግም አይተውታል፤በመላእክት የታየው ኢየሱስ በሥጋ የተገለጠ (ወልድ) ነው።]
🌱ከላይ ያለውን በትክክል ያመናችሁ ብቻ ቤቱ ናችሁ ።
......
“እኔ ስለ እኔ ስለ ራሴ ብመሰክር ምስክሬ እውነት አይደለም፤” ዮሐንስ 5፥31
☝ ኢየሱስ ስለ ራሱ መመስከር አልችልም፣
☝ብመሰክር እንኳን የእውነት አይሆንም ተአማንነት የለውም ፣
“ስለ እኔ የሚመሰክር ሌላ ነው፥ እርሱም ስለ እኔ የሚመሰክረው ምስክር እውነት እንደ ሆነ አውቃለሁ።”ዮሐንስ 5፥32
☝ ኢየሱስ ስለራሱ "ሌላ የሚመሰክር አለ ፣ የእውነት ምስክርነት ስለሆነ እቀበላለሁ" ይለናል ።
☝ስለዚህ " ሌላ " የተባለው መስካሪው ማን ነው !?
ዮሐንስ 5 ³³ እናንተ ወደ ዮሐንስ ልካችኋል እርሱም ለእውነት መስክሮአል።³⁴ እኔ ግን ከሰው ምስክር አልቀበልም፥ እናንተ እንድትድኑ ይህን እላለሁ እንጂ።
☝ ከሰው ፦ዮሐንስ ምስክሯል፤ትክክል ነው ግን የሰው ምስክርነት አይቀበልም።ከማን ነው ምስክርነት የሚቀበለው ስለራሱ !? "ከሌላ" ።ሌላ የተባለው አካል ማን ነው!? አብ ነው። ተመልከቱ ፦
ዮሐንስ 5³⁶ እኔ ግን ከዮሐንስ ምስክር የሚበልጥ ምስክር አለኝ፤ አብ ልፈጽመው የሰጠኝ ሥራ፥ ይህ የማደርገው ሥራ፥ አብ እንደ ላከኝ ስለ እኔ ይመሰክራልና።³⁷ የላከኝ አብም እርሱ ስለ እኔ መስክሮአል። ድምፁን ከቶ አልሰማችሁም፥ መልኩንም አላያችሁም፤³⁸ እርሱም የላከውን እናንተ አታምኑምና በእናንተ ዘንድ የሚኖር ቃሉ የላችሁም።
☝ ስለዚህ ለኢየሱስ የሚመሰክር ሌላ አካል እስካለ ድረስ "ኢየሱስ ራሱ አብ ነው" ማለት ያሳፍራል ።
☝አብ የራሱ ድምጽ ያለው፣ ገጽ ያለው ፣መልክም ያለው ነው፤ማንም ያላየው ነው።
ስለዚህም ኢየሱስ አብ አይደለም ።እግዚአብሔር በሦስት አካል የተገለጠ አምላክ ነው፤ሃሌ ሉያ።
.......
“ኢየሱስም አለው፦ አንተ ፊልጶስ፥ ይህን ያህል ዘመን ከእናንተ ጋር ስኖር አታውቀኝምን? እኔን ያየ አብን አይቶአል፤ እንዴትስ አንተ፦ አብን አሳየን ትላለህ?”ዮሐ 14፥9
☝"እኔን ያየ አብን አይቷል" ማለት ተምሳሌታዊ ነው።ምክንያቱም አብ መለኮት ብቻ ነው።ኢየሱስ ብቻ ደግሞ ሙሉዕ ሰው ሙሉ መለኮት ነው።መለኮት በባሪው አይታይም ።
☝"ማየት" የተባለው ቃል አካላዊ ማየት ከሆነ የሚታየው ሥጋው ነው።ስለዚህ ሥጋው አብ ነው ልንል ነውን? ማየት ተባለው የአብን ባህሪ ወይንም ማንነት ነው እንጂ ኢየሱስ አብ ነው ማለት አይደለም።
☝ለምሳሌ “መቼም ቢሆን እግዚአብሔርን ያየው አንድ ስንኳ የለም፤ በአባቱ እቅፍ ያለ አንድ ልጁ እርሱ ተረከው።”— ዮሐንስ 1፥18 ፣ እግዚአብሔር ያየው ለዚያውም መቼም ከሌለ ፣ አሁን ፊልጶስ የተመለከተው ሥጋ "አብ ነው" ማለት ነውር ነው።
☝ኢየሱስ የመጣው አብን ለመተረክ ነው።መተረክ ማለት መግለጥ ማለት ነው።ለምሳሌ እኛ የፀሃይ ብርሃን አይተን ፦ፀሃይ ወጣ እንላለን ።ግን የፀሃዩን ቅርጽ አላየንም።ልክ እንደዚሁ ኢየሱስም የአብን ማንነት ያሳየናል እንጂ የአካሉን ቅርጽ አላሳየንም፤አላየንም።
☝የፀሃይ ማንነት ብርሃንነት ነው።ኢየሱስም የአብን ማንነት ፍቅርን አሳይቷል ።ስለዚህ ኢየሱስ ገልጦ መስክሮ እያለ ስጠየቅ ይገረማል ምክንያቱም ሥራዎች ሁሉ የአብን ባህሪ የሚያሳዩ ናቸው ።
☝ደግሞም ከፍ ብለን ብናነብ "በእግዚአብሔር እመኑ" ብሎ "በራሱም እመኑ" ስል አንድ አካል አለመሆናቸውን ያሳያል ።
☝ለምሳሌ ራሱን "መንገድ ነኝ" በማለት ወደ ሌላ አካል (አብ) እንደሚወስድ ገልጿል ።ያ ደግሞ ኢየሱስ አብ ነው አያስብልም።የራስ ማንነት መኖሩን ያሳየናል ።
ኢየሱስ አብ አይደለም ፤አንድ አካል አይደለም ።ሃሌ ሉያ።ልባችሁ አይታወክ።
....
“እኔ በአብ እንዳለሁ አብም በእኔ እንዳለ አታምንምን? እኔ የምነግራችሁን ቃል ከራሴ አልናገረውም፤ ነገር ግን በእኔ የሚኖረው አብ እርሱ ሥራውን ይሠራል።”ዮሐ 14፥10
☝በኢየሱስ አካል ውስጥ "የአብ አካል አለ" ማለት አይደለም ፤የአብ ባህሪ ወይንም ማንነት አለ ማለት ነው እንጂ ።
☝በኢየሱስ አካል ውስጥ የአብ አካል ስለ መኖሩ ሳይሆን ስለ ባህሪ መኖር እንደሆነ፦"ስለ ሥራው " ብሎ መናገሩ ያረጋግጥልናል ።ምክንያቱም የኢየሱስ ሥራ የአብን ማንነት የሚያሳይ ነው።
☝ለምሳሌ ጳውሎስ “ከክርስቶስ ጋር ተሰቅዬአለሁ፤ እኔም አሁን ሕያው ሆኜ አልኖርም ክርስቶስ ግን በእኔ ይኖራል፤ አሁንም በሥጋ የምኖርበት ኑሮ በወደደኝና ስለ እኔ ራሱን በሰጠው በእግዚአብሔር ልጅ ላይ ባለ እምነት የምኖረው ነው።”— ገላትያ 2፥20 ይለናል ፣
☝ስለዚህ "ጳውሎስ ውስጥ ኢየሱስ አለ" ስለሚል ጳውሎስ፦"ኢየሱስ ነው" ማለት እንችላለን !? አንችልም ።ግን የኢየሱስ ባህሪ አለው ማለቱ ነው።ያም ከኀጢአት ጋር የማያተባብር ፣ ብርሃን የሆነ ማንነት አለው ማለት ነው።
ስለዚህም ምክንያት ኢየሱስ አብ አይደለም ።ምክንያቱም እግዚአብሔር ሥሉሳዊ ቅዱስ አምላክ ነው።
...
“ስለ ልጁ ግን፦ አምላክ ሆይ፥ ዙፋንህ እስከ ዘላለም ድረስ ይኖራል፤ የመንግሥትህ በትር የቅንነት በትር ነው።”— ዕብራውያን 1፥8
☝በዚህ ክፍል ላይ ተናጋሪው አብ ነው፣
☝የሚናገረውም ስለ ልጁ ነው፣
☝ልጁን አብ ራሱ ስገልጸው፦"አምላክ ሆይ " አለ ፣አብ ልጁን "አምላክ" ካለው ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ ደግሞ የአብ ምስክርነት ነው የሚቀበለው፤ደግሞም ስለራሱ "አልመሰክርም"ብሎ ገልጿል።ስለዚህም ይህ ምስክርነት የታመነ እና ሁሉም እንድቀበሉት የተገባ ምስክርነት ነው።
☝አንዳንድ ሰዎች "ኢየሱስ አምላክ ነኝ አላለም ፣ስለዚህም አምላክ አይደለም "ይሉናል ፣ አዎ "አምላካችሁ ነኝ" አላለም ምክንያቱም ስለራሱ አልመሰክርም ብሏል፣ስለእሱ ሰው ሳይሆን አብ እንደሚመሰክር እና የአብን ምስክርነት እንደሚቀበል ገልጾልናል ዮሐ 5፥30-38።
☝ስለዚህ አብ ኢየሱስን "አምላክ ሆይ"ካለው አምላክ ነው ማለት ነው፤ኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ መሆኑን አብ ራሱ መስክረዋል ስለዚህም አምላክ ነው በአብ የተመሰከረለት ።
☝እንድሁም ዙፋኑ ዘላለማዊ የሆነ ፣ በመንግሥቱ ለሰው የማያደላ እውነተኛ አምላክ ነው።
☝ደግሞም አብ ስመሰክር ፣መስካሪው ሌላ አካል መሆኑን እንገነዘባለን ።“እኔ ከራሴ አንዳች ላደርግ አይቻለኝም፤ እንደ ሰማሁ እፈርዳለሁ ፍርዴም ቅን ነው፥ የላከኝን ፈቃድ እንጂ ፈቃዴን አልሻምና።”— ዮሐ 5፥30
☝ኢየሱስም ደግሞ ስናገር "እኔ ከራሴ.. "በማለት አብ አለመሆኑን ስያሳይ ፣ "የላከኝም"ማለቱ ደግሞም ሌላ ላኪ አካል መኖሩን ያሳየናል ።ስለዚህም የአብም የኢየሱስም ምስክርነት የታመነ ነው።
ኢየሱስ ክርስቶስ ሰው ብቻም አይደለም፤አምላክም ነው፤አብም አይደለም ፤ሃሌ ሉያ።
...
“እኔ በአባቴ ስም መጥቻለሁ አልተቀበላችሁኝምም፤ ሌላው በራሱ ስም ቢመጣ እርሱን ትቀበሉታላችሁ።”ዮሐ 5፥43
☝ በመጀመሪያ የእግዚአብሔር ስም ፦" የእግዚአብሔር ማንነት ፣ ባህሪን የሚገልጹ ስሞች ናቸው።ኢየሱስ (አዳኝ) ፣አማኑኤል እግዚአብሔር (ከእኛ ጋር ነው)..።" (የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገብ ቃላት ገጽ 81)
☝ ስም የተባለውን የመጽሐፍ ቅዱስን App (srong) ስደረግ ፦( authority፣character ) ይለናል ፣
☝ እዚህ ክፍል ላይ "በአባቴ ስም" ማለቱ የሚያሳየው "ኢየሱስ አብ ነው" የሚል ሳይሆን በእርሱ በአብ ሥልጣን መጥቻለሁ የሚል ነው።
☝ከዚህ ጋር ተያይዞ " 'ሥላሴ' የሚል የእግዚአብሔር ስም የለም" ይሉናል።በእርግጥም አዎ የለም።እኛም የእግዚአብሔር ስም ነው አላለንም።ምክንያቱም ሰው የእግዚአብሔርን ስም አያወጣም።የእግዚአብሔርን ሦስት አካልነት ለማስተማር የወጣ የሙያ ስም ነው።በግዕዙ ''ትምርተ ሥላሴ''እንላለን ፤"ሥስት አንግል፣የሦስትዮሽ .." እንዲሉ ።በእንግሊዘኛ Trinity፣Tri-unit እንላለን ሦስት አካልነትን ለማስተማር፤የአስተምህሮ ስም ነው።
☝በእርግጥም "ሥላሴ" የሚለው ስም የእግዚአብሔር ሥስት አካልነት ለማስተማር መውጣቱ ይታወቃል ።ግን በአንዳንድ ቤተክርስቲያን ዘንድ እንደ እግዚአብሔር ስምነት ይገለግላሉ።[ከዚህ በፊት ሥላሴ የሚለውን ስም የአስተምህሮ ቃል እንደሆነ በግልጽ በመግለጠ፤መቃወምም ይታወቃል።]
☝ማለትም "ሥላሴ አመስግኑ ፣ ዘምሩለት" በመባል ከዚያም አልፎ "በሥላሴ ስም" በማለት ለመፈወስ የሚወተውቱ አሉ፤"ሥላሴ" የሚለው ስም ግን የሚፈውስ ስም አይደለም ።
☝ይህንን የሚለው "ሥላሴ" የሚለውን ቃል ያለ አግባብ ስንጠቀም አይተው በሥሶስትነት የማያምኑቱ ፦" የእግዚአብሔር ስም አይደለም" በማለት ፣ "ነው" ካልክ ከመጽሐፍ ቅዱስ አውጣ!? በማለት ፣ "የለም" በማሰኘት ፤ትምህርተ ሥስትነትን ብዙዎችን እንዲክዱ ስላደረጉ ነው በትክክል ማወቅ ይጠቅማል ብዬ ነው፣
☝በእግዚአብሔር ሥስት አካልነት የሚያምኑቱ ፣ ስለእግዚአብሔር ስም ግንዛቤ ይኑረን፤ማንም አያስተን።ትክክለኛ እና በግልጽ የተገለጠ የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት ነው ትምህርተ ሥስትነት።
☝ወደ ሃሳቡ ስጠልቅ ለምሳሌ“ዳዊትም ፍልስጥኤማዊውን አለው፦ አንተ ሰይፍና ጦር ጭሬም ይዘህ ትመጣብኛለህ፤ እኔ ግን ዛሬ በተገዳደርኸው በእስራኤል ጭፍሮች አምላክ ስም በሠራዊት ጌታ በእግዚአብሔር ስም እመጣብሃለሁ።"1ኛ ሳሙ 17፥45
☝ዳዊት "በእግዚአብሔር ስም መጥቻለሁ ፣እመጣለሁ " ማለቱ ዳዊትን እግዚአብሔር አያደርገውም፤በእግዚአብሔር ሥልጣን እመጣለሁ ማለቱ ነው እንጂ ።
☝ስለዚህም ኢየሱስ "በአባቴ ስም .." ማለቱ ኢየሱስን "አብ ነው" አያስብልም።
የእግዚአብሔር ስም ማንነት ነው፤መለያ ስም አይደለም፤ስለዚህም ኢየሱስ አብ አይደለም
...
“እርሱም የማይታይ አምላክ ምሳሌ ነው፤የሚታዩትና የማይታዩትም፥ዙፋናት ቢሆኑ ወይም ጌትነት ወይም አለቅነት ወይም ሥልጣናት፥በሰማይና በምድር ያሉት ሁሉ በእርሱ ተፈጥረዋልና ከፍጥረት ሁሉ በፊት በኵር ነው፤ሁሉ በእርሱና ለእርሱ ተፈጥሮአል፤”ቆላ 1፥15-16
☝"ከፍጥረት ሁሉ በኩር ነው"ኢየሱስ ክርስቶስ ቅድሞ በመጀመሪያ የተፈጠረ ፉጡር ነው አያስብልም ፤ምክንያቱም ብኩርናው በዚህ ክፍል ላይ የሚያሳየው በጊዜ መቅደምን ሳይሆን በክብር መብለጡን ያሳየናል ፣
☝ለምሳሌ “..፤ ብኵርናውንም ለያዕቆብ ሸጠ።”ዘፍ 25፥33 ፣ ኤሳው ብኩርናውን መሸጡ ዕድሜውን መሸጡ አይደለም ፤ክብሩን ሸጠ ማለቱ ነው እንጂ።
☝ደግሞም በሌላ ክፍል “እኔም ደግሞ በኵሬ አደርገዋለሁ፥ ከምድር ነገሥታትም ከፍ ይላል።”መዝ 89፥27 ፣ ዳዊት በኩር መባሉ የመጀመሪያ ልጅ ሆነ ማለቱ ሳይሆን በክብር ከፍ አደርጋለሁ ማለቱ ነው፣
☝“እርሱም የአካሉ ማለት የቤተ ክርስቲያን ራስ ነው፤ እርሱም በሁሉ ፊተኛ ይሆን ዘንድ፥ መጀመሪያ ከሙታንም በኵር ነው።”ቆላ 1፥18 ፣ ስለዚህም ከሙታ በኩር ነው መባሉ ፣መጀመሪያ ከእርሱ በፊት ከሞት የተነሳ የለም ማለት ሳይሆን በከበረ አካል እርሱ ብቻ መነሳቱ በክብር እንደሚልቅ የሚያሳይ ነው።
☝በእርግጥ በኩር የሚል ቃል ጊዜን ልያሳይ ይችላል ግን በዚህ ክፍል ለግዜ የሚጠቀስ አይደለም፤ክብርንም እንደሚያሳይ መረዳት ያስፈልጋል ፣
☝ስናጠቃልለው "ሁሉ በእርሱ ተፈጥረዋል" ለዚያውም "የሚታየውም የማይታየውም" ማለቱ ኢየሱስን ፉጡር አያደርገውም ፤ምክንያቱም፦
ኢየሱስ ሁሉን የፈጠረ ነው፤እርሱ ፈጣሪ ነው፤ሃሌ ሉያ።
...
“.፥ በእግዚአብሔርም ፍጥረት መጀመሪያ የነበረው እንዲህ ይላል፦”ራእይ 3፥14
☝"..ፍጥረት መጀመሪያ"መባሉ በጊዜ ቀድሞ የተፈጠረ ፋጡር ነው አያስብልም፤ምክንያቱም መጀመሪያ የሚለው ቃል እንደ አውዱ ለየት ያለ ትርጉም ልሰጥ ይችላል።"መጀመሪያ" የተባለው ቃል በግሪኩ "archê" የሚለው ቃል ነው።ስለዚህም ቃሉን እንደ አገባቡ እንመልከት ፦
🌱“መኖሪያቸውንም የተዉትን እንጂ የራሳቸውን አለቅነት ያልጠበቁትን መላእክት በዘላለም እስራት ከጨለማ በታች እስከ ታላቁ ቀን ፍርድ ድረስ ጠብቆአቸዋል።”ይሁዳ 1፥6 ፣በዚህ ክፍል ላይ "አለቅነት" የተባለው ቃል "archê" የሚለው ቃል ነው።ስለዚህ ቃሉ ሥላጣንንም ያሳያል ማለት ነው።
🌱“በመጀመሪያው ቃል ነበረ፥ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፥ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ።”ዮሐ 1፥1 ፣በዚህ ክፍል ደግሞ "ጅምር መሆንን" በማመልከት ጥቅም ላይ ውሏል።
🌱“እርሱም፦ ሙሴስ ስለ ልባችሁ ጥንካሬ ሚስቶቻችሁን ትፈቱ ዘንድ ፈቀደላችሁ፤ ከጥንት ግን እንዲህ አልነበረም።”ማቴ 19፥8 ፣በዚህ ክፍል ላይ "ከጥንት "የሚለው ቃል "archê" የሚል ነው።የሚያመለክተውም ከዚህ በፊት ያልተለመደ ነገር ጅማሮን በማመልከት ጥቅም ላይ ውሏል።
🌱ስለዚህም archê የሚለውን ቃል ኦርጅናል ቃሉን መደበኛ ትርጉም በአውዱ ስፈታው "የፍጥረት ምንጭ" ብለውታል፤እንድሁም "መጀመሪያ የሆነው" ወይንም ከማዕረግ አንፃር ከታየ "ገዥ" ተብሎ ልተረጎም እንደሚቻል አስቀምጠውታል ።
🌱ስለዚህም ቃሉ በአውዱ መሠረት የሚያመለክተው የፍጥረት አስገኝነቱን ወይንም ገዥነቱን ነው።ያ ደግሞ ኢየሱስ “..፤ ፊተኛውና መጨረሻው ሕያውም እኔ ነኝ፥”ራእይ 1፥17፣እንዳለው ዘላለማዊ አምላክነቱን የሚያሳይ ነው።
ኢየሱስ ጊዜን የፈጠረ ፈጣሪ ነው፤ሃሌ ሉያ።
...
“አብ በራሱ ሕይወት እንዳለው እንዲሁ ደግሞ ለወልድ በራሱ ሕይወት እንዲኖረው ሰጥቶታልና።”ዮሐ 5፥26
☝"ሰጥቶታል" ስባል ኢየሱስ በአብ ተፈጠረ የሚል ይመስላል ፣ ግን አሁዱ የሚያወራው ስለ "ሥራ ነው"፣
☝ይህም ሥራ አብ እና ወልድ ተባብረው የሚሰሩት ነው፣ሥራውም ለሰው ዘላለማዊ ሕይወት ትንሳኤን ወይንም መዳንን መስጠትን ነው፣
☝"ኢየሱስ በራሱ ሕይወትን መስጠት አይችልም ወይ ለምን ከአብ ተቀብሎ ይሰጣል!?"ብባል የባሪያን መልክ ይዞ በሰውም ምሳሌ ሆኖ ራሱን ባዶ አደረገ፥”ፊል 2፥7 ፣ እንደሚል አምላክነቱን አልተጠቀመምና ነው።
☝“እኔ ከራሴ አንዳች ላደርግ አይቻለኝም ዮሐ 5፥30" ማለቱ የመለኮት ሃይሉን ባለመጠቀሙ ፣ ለዚህ ሕይወትን ለመስጠት ሥራ ከአብ ተቀብሎ ይሰራል ማለት ነው።ይህ ስለእኛ የተደረገ ፍቅር ነው።
☝"አምላክነቱን አጣላው፣ክብር ይጎልብኛል"ሳይል ለእኛ ራሱን ባዶ አደረገ እንጂ እርሱ ዘላለማዊ አምላክ ነው“ሞቼም ነበርሁ እነሆም፥ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ሕያው ነኝ፥ የሞትና የሲኦልም መክፈቻ አለኝ።”ራእ 1፥18 እንዳለው ።
☝ስለዚህም በአምላክነቱ በተፈጥሮ ማንነቱ ማነስ ሳይሆን ለእኛ ድነትን ለማምጣት ወድዶ፣ፈቅዶ ራሱን ዝቅ ማድረጉን የሚያመለክት ክፍል ነው።
ኢየሱስ ራሱን ለእኛ ስል ባዶ አድርጎ ዘቅ ማለቱ በተፈጥሮው ማነስ ሳይሆን የሚያሳየው ፍቅሩን ነው
...
ፊልጵስዩስ 2 ⁶ እርሱ በእግዚአብሔር መልክ ሲኖር ሳለ ከእግዚአብሔር ጋር መተካከልን መቀማት እንደሚገባ ነገር አልቈጠረውም፥⁷ ነገር ግን የባሪያን መልክ ይዞ በሰውም ምሳሌ ሆኖ ራሱን ባዶ አደረገ፥⁸ በምስሉም እንደ ሰው ተገኝቶ ራሱን አዋረደ፥ ለሞትም ይኸውም የመስቀል ሞት እንኳ የታዘዘ ሆነ።
☝በእግዚአብሔር መልክ ይኖራል መባሉ ፍጹም አምላክነቱን ስያመለክት ፣በባሪያ መልክ መባሉ ደግሞ ሰው መሆኑን ያመለክታል ፣
☝"እንደ ሰው" በማለት ሰው ብሆንም በጅምሩ ሰው እንዳይደለ ያመለክታል ፣
☝"በአምላክነቱ የተተካከለ ነው" ማለትም ከአብ ጋር እኩል፣አቻ ነው ።ግን አቻነቱን "አጣለሁ" ሳይል ስለእኛ ራሱን ባዶ አደረገ ፣
☝ስለእኛ ራሱን ባዶ ማድረጉ ለድነት ሥራ ዝቅ ማለቱን የሚያሳይ እንጂ በአምላክነቱ ያንሳል ማለት አይደለም፣
☝ለምሳሌ አቢይ አስተዳደር መሆኑ ከሰውነት ከፍ አያደርገውም።ግን በአስተዳደርነት ከፍ ያለ ቦታ አለው እንጂ ከእኛ ጋር እኩል ድኩም ሰው ነው ፣
☝ኢየሱስም የሰው ልጅን በማዳን ሥራ ላይ ዝቅታ (የአስተዳደራዊ ቦታ) ስወስድ ፣ አብ ደግሞ በአስተዳደርነት ቦታ ከፍታ ወስዷል።ግን በተፈጥሮ ማንነት ያውም በአምላክነት አብን አላነሰውም፤አብም አልበለጠውም ።
ስለዚህም ኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ ነው፣በተፈጥሮው የማያንስ፣ለድህነት ሥራ ዝቅ ራሱን ያደረገ፣ግን አብ ያይደለ ነው
...
“እኔና አብ አንድ ነን።” ዮሐ 10፥30
☝ኢየሱስ ክርስቶስ አብ ነው ማለት አይደለም፣አንድ ባህሪ ወይንም ማንነት ወይንም ተፈጥሮ አለን ማለት ነው እንጂ ፣ምክንያቱም ተመልከቱ ፦
🌱"እኔ አብ ነኝ" አይልም ፣"we are"ይለናል እንጂ ፣
🌱"እኔ" ብሎ "ና" ማለቱ በራሱ ከአንድ በላይ ቁጥርን የሚያመለክት ነው፣ሌላ አካልን የሚጠቁም ነው።" ጳውሎስና.. "እንዲሉ ማለት ነው፣
🌱ሌላው አካል አብ ነው።ስገልጸውም ".ነን"ብሎውታል ፣ "የአብርሃም ዘር ነን "እንዲሉ ብዛትን የሚገልጽ ነው ፣
🌱እንዲያ ባይሆን "ነኝ"ይለን ነበር ፣ "ነን" ማለቱን ትቶ።
☝ደግሞም በሌላ ክፍል"የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ" ስል ፣አባት መኖሩን ያሳየናል እንጂ ራሱ አብ ነው አያስብልም፣
☝በሌላ ክፍልም “እኛም አንድ እንደ ሆንን አንድ ይሆኑ ዘንድ፤ እኔም በእነርሱ አንተም በእኔ ስትሆን፥ በአንድ ፍጹማን እንዲሆኑ፥ የሰጠኸኝን ክብር እኔ ሰጥቻቸዋለሁ፤ እንዲሁም ዓለም አንተ እንደ ላክኸኝ በወደድኸኝም መጠን እነርሱን እንደ ወደድሃቸው ያውቃል።”ዮሐንስ 17፥22-23 ፣ይህንን ማለቱ የሚያሳየው ፦
🌱የአብ እና የኢየሱስ አንድነት የዓላማ አንድነት መሆኑን ነው፣
🌱እንዲያ ባይሆን "አንድ ይሆኑ ዘንድ" ስባል ሁሉም ደቀመዛሙርቱ ተጨፍልቀው አንድ አካል ይሆኑ ነበር፤የክፍሉ አውድ የሚያሳየው ግን የሀሳብ (የዓላማ) አንድነት ነው።
ስለዚህም ኢየሱስ አብ አይደለም
..
“ኢየሱስ አብ ሁሉን በልጁ እንደ ሰጠው ከእግዚአብሔርም እንደ ወጣ ወደ እግዚአብሔርም እንዲሄድ አውቆ፥”ዮሐ 13፥3
☝"ከአብ ተሰጠው፣ከእግዚአብሔር መጣ፣ደግሞም ወደ እግዚአብሔር ተመልሶ ይወጣል" ማለቱ ኢየሱስ ክርስቶስ አብ እንዳልሆነ ያስረዳል ፣
☝ሊቀ ካህናት ሆኖ በእግዚአብሔር ዘንድ መቀመጡ ዕብ፣ጠበቃ መሆኑ 1ዮሐ 2 ፥ ኢየሱስ ክርስቶስ ፦ኢየሱስ ክርስቶስ መሆኑን ያሳያል እንጂ አብ መሆንን አያመለክትም ፣
☝“አሁንም፥ አባት ሆይ፥ ዓለም ሳይፈጠር በአንተ ዘንድ በነበረኝ ክብር አንተ በራስህ ዘንድ አክብረኝ።”ዮሐ 17፥5 ፣ እንደውም "ከአባቱ ጋር መነጋገሩ፣ "አባት ሆይ" ማለቱ ሁለት አካል የሚያመለክት ነው፣
☝“በዚያን ቀን በስሜ ትለምናላችሁ፤ እኔም ስለ እናንተ አብን እንድለምን የምላችሁ አይደለሁም፤”ዮሐ 16፥26። "በዚያ ቀን በኢየሱስ ስም ሥልጣን ትለምናላችሁ "ይለናል ፣ ግን "ስለእናንተ አብን አልለምንም"ማለቱ ራሱ ኢየሱስ አብ አለመሆኑን ያሳያል፣
☝ደግሞም “ከአብ ወጥቼ ወደ ዓለም መጥቻለሁ፤ ደግሞ ዓለምን እተወዋለሁ ወደ አብም እሄዳለሁ።”ዮሐ 16፥28 ፣ ስለዚህ ኢየሱስ ወደ አብ የሚሄድ ከሆነ ፣ እሄዳለሁ እንዳለው ከሄደ ሐዋ 1፥10-11 ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ አብ አይደለም ።
ኢየሱስ ክርስቶስ በመለኮቱ ላይ ሥጋን የደመረ አምላክ እንጂ አብ አይደለም
...
“ያለውና የነበረው የሚመጣውም ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ፦አልፋና ዖሜጋ እኔ ነኝ ይላል።”ራእ 1፥8
☝ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱን ዘላለማዊ ነኝ በማለት ገልጿል፣በብሉይ ኪዳን ደግሞ አብም "ዘላለማዊ ነኝ" ብሏል፦“ይህን የሠራና ያደረገ፥ ትውልድንም ከጥንት የጠራ ማን ነው? እኔ እግዚአብሔር፥ ፊተኛው በኋለኞችም ዘንድ የምኖር እኔ ነኝ።”ኢሳ 41፥4፤44 ።
☝በዮሐንስ ራዕይ 1፥8 የተናገረው ኢየሱስ አይደለም በማለት ለመሸምጠጥ ይሞከራል።እንዲህ በማለት ፦<< ራእይ መልእክት ፣ ከእግዚአብሔር ወጥቶ ለኢየሱስ ተሰጥቶ ፣ከኢየሱስ ወደ መላአኩ ተሰጥቶ ፣ከመላአኩ ወደ ዮሐንስ ወርዷል፥ስለዚህ ራእ 1፥8 የተናገረው ኢየሱስ አይደለም>> የሚል ነው።የመልእክት ቅብብሎሽ መኖሩ እምኑ ነው ግን ይህንን 1፥8 ላይ ያለውን ቃል የተናገረው ኢየሱስ አለመሆኑን ልያመለክት አይችልም።ምክንያቱም ፦
☝"አልፋና ዖሜጋ እኔ ነኝ" የሚለው ድምፅ ዮሐንስ ስሰማ "ጻፍ ፣ከዛም ለአብያተክርስቲያናት ላክ '" የሚል ትዕዛዛዊ መልእክት መጣ ቁ.11 ፣ ዮሐንስንም ዘወር ብሎ አየ ራእይ 1፥12 ፣ ካየ በኃላም የተናገረው ማን እንደሆ ይገልፃል ፦
🌱ዮሐንስ ማየቱን ይቀጥላል “በመቅረዞቹም መካከል የሰው ልጅ የሚመስለውን አየሁ፥ እርሱም እስከ እግሩ ድረስ ልብስ የለበሰው ደረቱንም በወርቅ መታጠቂያ የታጠቀ ነበር።” ራእይ 1፥13 ፣ "የሰው ልጅ የሚመስለውን አየሁ " ሊቀ ካህናታችንን ኢየሱስን ያመለክታል አለባበሱም የሊቀ ካህናት ነው ዘፀ 28፣
🌱ዮሐንስ ማየቱን ቀጥሏል እኛም እንመልከት ከእርሱ ጋር “ራሱና የራሱ ጠጕርም እንደ ነጭ የበግ ጠጕር እንደ በረዶም ነጭ ነበሩ፥ ዓይኖቹም እንደ እሳት ነበልባል ነበሩ፤”ራእይ 1፥14፣ "ነጭ ጠጉር" ጥበብና ክብር ያለው መሆኑን ስያመለክት ፣ "ነበልባል የሆነ አይኖቹ"ደግሞም ሁሉንም መመርመር መቻሉን ይገልጻሉ ፣
🌱ከዮሐንስ ጋር እንቀጥል “እግሮቹም በእቶን የነጠረ የጋለ ናስ ይመስሉ ነበር፥ድምፁም እንደ ብዙ ውኃዎች ድምፅ ነበረ።”ራእይ 1፥15 ፣ "የነጠረ የጋለ ናስ"ንፁህ ነው ተፈትኗልና ፣ የድምፁ አስፈርነት ሥልጣኑን ግርማውን ያሳያሉ ፣
🌱እንቀጥል ከዮሐንስ ጋር “በቀኝ እጁም ሰባት ከዋክብት ነበሩት፥ ከአፉም በሁለት ወገን የተሳለ ስለታም ሰይፍ ወጣ፤ ፊቱም በኃይል እንደሚበራ እንደ ፀሐይ ነበረ።”ራእይ 1፥16 ፣መልእክቶኞችም በእጁ ናቸው፣ ለማንም የማያደላ መልኮታዊ ፍርድም የሚፈርድ ነው፣
🌱እስካሁን ዮሐንስ ዘወር ብሎ የተመለከተውን እየገለጸ ነው። አስተውሉ።እንቀጥል ከዮሐንስ ጋር “ባየሁትም ጊዜ እንደ ሞተ ሰው ሆኜ ከእግሩ በታች ወደቅሁ። ቀኝ እጁንም ጫነብኝ እንዲህም አለኝ፦ አትፍራ፤ ፊተኛውና መጨረሻው ሕያውም እኔ ነኝ፥”ራእ 1፥17 ፣ ስለዚህ ፊተኛውና መጨረሸኛው ኢየሱስ ነው።የሚያናግረውም ኢየሱስ ነው።
🌱እንቀጥል “ሞቼም ነበርሁ እነሆም፥ ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ሕያው ነኝ፥ የሞትና የሲኦልም መክፈቻ አለኝ።”ራእይ 1፥18 ፣ "ሞቼ ነበርሁ"ሃሌ ሉያ ሞቶ የነበረው ኢየሱስ ነው።አዎ ኢየሱስ አልፋና ዖሜጋ ነው።
🌱ስለዚህም እዚህ ክፍል ላይ የሚናገረው ኢየሱስ ነው "ጻፍ" እያለውም ነው።“እንግዲህ ያየኸውን አሁንም ያለውን ከዚህም በኋላ ይሆን ዘንድ ያለውን ጻፍ።”ራእ 1፥19
🌱ስለዚህም መልእክቱ የተላለፈው በመላአኩ ብቻ ሳይሆን በኢየሱስ በኩልም እንደሆነ እንረዳለን ።
ኢየሱስ ዘላለማዊ አምላክ ነው፤ኢየሱስ አብ አይደለም
...
"ወደ ኢየሱስ ጸሎት ተደርጓል፤ስለዚህ ኢየሱስ አምላክ ነው"
☝በብሉይ ሆነ በአድስ ክዳን ጸሎት የሚቀርብለት ወደ እግዚአብሔር ብቻ ነው፤ወደ ፉጡራን ጸሎት አይደረግም፤ከተደረገ መገዛትን ማምለክን ያሳያል፤ጸሎት የተደረገለት አካል ለአድራጊው አምላኩ ነው ማለት ነው።አስተውሉ ።ኢየሱስ አምላክ ስለሆነ ሰዎች ወደ ኢየሱስ ጸልዮዋል።ለምሳሌ ፦
🌱“እስጢፋኖስም፦ ጌታ ኢየሱስ ሆይ፥ ነፍሴን ተቀበል ብሎ ሲጠራ ይወግሩት ነበር።”ሐዋ 7፥59 ፣ ማንም ነፍስን የመቀበል ሥልጣን የለውም ኢየሱስ አምላክ ስለሆነ ነፍስን ይቀበላል ።ደግሞም ጸሎት ይደረግለታል ።ስለዚህም አምላክ ነው።
🌱በእርግጥ ኢየሱስ ሰው በመሆኑ ጸሎት ወደ ሚገባው አብ ጸልዮአል።የእውነትም ጸሎት ነው፤ለማስተማር አይደለም።"ምክንያቱም ኢየሱስ አንድም ደቀመዛሙርት (ሕዝቡ) በሌሉበት ብቻውም ይጸልይ ነበርና"“ሕዝቡንም አሰናብቶ ይጸልይ ዘንድ ብቻውን ወደ ተራራ ወጣ። በመሸም ጊዜ ብቻውን በዚያ ነበረ።”ማቴ 14፥23 ፣
🌱አንዳንድ ሥላሴአዊያን ኢየሱስ "መጸለዩን" ለማስተማር ነው ብለው ይክዱታል።ይህ እነዚህ ሃራጥቃን የፈጠሩት ተጽዕኖ ነው፤ኢየሱስ ድራማ አይሰራም፤አይተውንም።ኢየሱስ ሙሉዕ ሰውም ነው።
🌱"እንዴት እያወቀ ይጸልያል ይሉናል" መልሰው፣መጸለይ እኮ ያለማወቅ ጉዳይ አይደለም፤አባትን የማናገር እና ከእርሱ ጋር ግዜ የማሳለፍ ፍላጎት ነው እንጂ።
🌱"እንትና ሆይ" ብሎ ወደ ፉጡር መጸለይ ክህደት ነው፤ፉጡራንን ማምለክን፤አምላክ ማድረግን ይገለጻል ።["እመቤታችን ሆይ" የሚሉም ሃራጥቃን እንደሆኑ እወቁ፤እያልኩ እንደሆነ ይረዷል]
☝ወደ ቅድሞ ነገራችን ስንመለስ ከላይ እስትፋኖስ ወደ አምላክ ካልለመነ ፣ ኢየሱስም ወደ አምላክ አልለመነማ!?እንደዚህ ግን አይደለም።በዚህ ክፍል ላይ “ኢየሱስም በታላቅ ድምፅ ጮኾ፦ አባት ሆይ፥ ነፍሴን በእጅህ አደራ እሰጣለሁ አለ። ይህንም ብሎ ነፍሱን ሰጠ።”ሉቃስ 23፥46
☝ስለዚህም ኢየሱስ አምላክ ስለሆነ ራዕይ መጽሐፍ ወደ ኢየሱስ ጸልዮ ይዘጋል ።“ይህን የሚመሰክር፦ አዎን፥ በቶሎ እመጣለሁ ይላል። አሜን፥ ጌታ ኢየሱስ ሆይ፥ ና።” ራእይ 22፥20
ጸሎት ወደ ፈጣር ብቻ ይደረጋል፤ኢየሱስ ፈጣሪ ስለሆነ ወደ እርሱ ተጸልዮአል፤ስለዚህ ኢየሱስ አምላክ ነው፤አብ አይደለም
..
“በሰማይና በምድርም ከምድርም በታች በባሕርም ላይ ያለ ፍጥረት ሁሉ በእነርሱም ውስጥ ያለ ሁሉ፦ በረከትና ክብር ምስጋናም ኃይልም ከዘላለም እስከ ዘላለም በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠው ፥ ለበጉም ይሁን ሲሉ ሰማሁ።” ራእይ 5፥13
☝"በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠው" ዙፋን ላይ የተቀመጠው አብ ነው፣አምልኮታዊ ክብርን ስሰጡ ወይንም ስያመልኩ እናስተውላለን ፣
☝ለአብ በዙፋኑ ለተቀመጠው የተደረገው አምልኮ በቀጥታ ሳይጎድል "ለበጉም ይሁን "በማለት ለኢየሱስም ቀርቧል።ስለዚህ በዚህ ክፍል ላይ ብቻ ኢየሱስ ከአብ በተፈጥሮው ማንነቱ እንደማያንስ፤እኩል ክብር እንዳለው እንረዳለን ፣
☝ደግሞም ለተቀመጠው ተብሎ "ለበጉም" መባሉ ኢየሱስ አብ እንዳልሆነ፣ ሁለት አካልነትንና ማንነት መኖሩን እናስተውላለን ፣
☝አብ ኢየሱስ ብሆን "ለተቀመጠው ለበጉ ይሁን" ይለን ነበር ግን መጽሐፍ የሚለው "..ለተቀመጠው፥ ለበጉም ይሁን.." ነው የሚለን፤አዎ ለበጉም ነው፤ሃሌ ሉያ።
☝ከትንሳኤው በኃላም ኢየሱስ ፦ ኢየሱስ ነው፥አብም አብም ነው።
☝የተቀመጠው አብ ፦ አብ ነው፤ለበጉም የተባለው ኢየሱስም ፦ ኢየሱስ ነው፤ሁለት አካል በግልጽ ይታያል።
ኢየሱስ አምላክ ነው፤በሥጋ የተገለጠ ወልድ እንጂ አብ አይደለም።ኢየሱስ ከአብ ጋር እኩል ክብር ያለው
..
“የእግዚአብሔርም ልጅ እንደ መጣ፥ እውነተኛም የሆነውን እናውቅ ዘንድ ልቡናን እንደ ሰጠን እናውቃለን፤ እውነተኛም በሆነው በእርሱ አለን፥ እርሱም ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። እርሱ እውነተኛ አምላክና የዘላለም ሕይወት ነው።”1ኛ ዮሐ 5፥20
☝የመጣው የእግዚአብሔር ልጅ የተላከ ነው።የላከውም "አባት" ተብሎ የተገለጠው አብ ነው።
☝ኢየሱስ ስመጣ አይደለም ልጅ የሆነው ።ይልቁንም ልጅ ስለሆነ ነው የመጣው ።
☝የልጅነቱ ጅማሮ ሆነ ፍጻሜ የለውም።እርሱ ብቸኛ የእግዚአብሔር ልጅ ነው።ምክንያቱም እርሱ ብቻ ነው ከአብ ጋር የነበረ ፣ልገልጠውም የሚችል ፣ያልተፈጠረ እና በመለኮቱ እኩል የሆነ።
☝ይህ የእግዚአብሔር ልጅ ልቡናንም የሰጠ ወይንም የሚሰጥ ነው።ከአምላክ በቀር ልቡናን ልሰጥ የሚችል ማን ነው!?ማንም። "የሚያበራው ብርሃን" በእርሱ ዘንድ ጨለማ የሌለው አምላክ ነው።
☝እውነተኛ የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ ደግሞም ሌሎችን የታመኑትን ደግፎ የያዘ ነው።ሰዎች ልታመኑበት የሚችሉት አምላክ ነው።
☝ኢየሱስ እውነተኛ አምላክ ነው።ደግሞም ለሁሉም የሚሆን ሕይወት ነው።የዘላለም ሕይወት ራሱ ኢየሱስ ነው ።
☝የዘላለም ሕይወት ማንነት ነው እንጂ ቦታ አይደለም ።ያም ኢየሱስ ነው።ኢየሱስ አምላክ ካልሆነ እንዴትስ የዘላለም ሕይወት ይሆናል !?
[ኢየሱስ ክርስቶስ እውነተኛ አምላክ ነው፤የዘላለምም ሕይወት ነው።]
.......
“ደግሞም በኵርን ወደ ዓለም ሲያገባ፦ የእግዚአብሔር መላእክት ሁሉም ለእርሱ ይስገዱ ይላል።”ዕብ 1፥6
☝ለኢየሱስ ክርስቶስ ሰዎች ለዚያውም በአይሁድ ሕግ ለእግዚአብሔር ብቻ እንደሚሰገድ እያወቁ አለቃ የሆነቱ ሰግደውለታል (አምልከዋል) ማቴ 9፥18 ፣
☝እኛ የሚናውቀው ሰዎች በተለያ አጋጣሚ ፣ መላእክት ስገለጡ ለመላእክት በግንባራቸው ስደፉ እና እንደ ሞተ ሰው ሲሆኑ ነው።
☝ነገር ግን ኢየሱስ ሰው ሆኖ እያለ የሚያገለግሉ እና የሚያበረቱ መላእክት እንኳን የሚሰግዱለትም ነው።
☝መላእክት መስገዳቸውን ፣ እጂ እንደ መንሳት ወይንም ለማክበር እንደተደረገ አንገታቸውን ዝቅ እንዳደረጉ ብናስብ እንኳን ፣ መላእክት ለአምላክ እንጂ ለሰው ሰግደው አያውቁም ።
☝መጽሐፍ ስናገር ኢየሱስ ከመላእክት ጥቅት አንሶ ነበር ዕብ 2፥9።በጥቅቱ ስለሚያንሰው ማን ወድቆ ሰግዶ ያውቃል !? ይህ እኮ ግሩም ነው።
☝ነገር ግን የመላእክት ስግደታቸው ዝም ብሎ "እጂ መንሳት"ወይንም ለክብር የተደረገ አይደለም ።መላእክት የሰገዱት አምልኮ ነው፤ስለሚገባውም አምልከዋል።ሃሌ ሉያ።
☝ሰገዱ የሚለው የግሪኩ አቻ ቃል "ፕሩስክኖ" የሚል ነው።የቃሉ ትርጉም አምልኮን ያመለክታል ።በእንግሊዝኛው Worship ብለውታል።በአማርኛችን "ሰገዱ" ብሉም በመጀመሪያ ቋንቋው ስንመለከተው "አምልኮ/መገዛትን" የሚያሳይ ነው።[እጂ መንሳትን አያመለክትም እያልኩ እንደሆነ ይረዷል።]
☝“..፤ በጉም የጌቶች ጌታና የነገሥታት ንጉሥ ስለ ሆነ እነርሱን ድል ይነሣል፥ ከእርሱም ጋር ያሉ የተጠሩና የተመረጡ የታመኑም ደግሞ ድል ይነሣሉ።”ራእይ 17፥14 ፣ በጉ ኢየሱስ ነው።የጌቶች ጌታ ነው፤ከሁሉም በስልጣን የበላይ ነው።ሃሌ ሉያ።
[ኢየሱስ ክርስቶስ የተፈጥሮ አባት ያለው፤የምመለክ አምላክ እንጂ አብ አይደለም፤ሰው ብቻም አይደለም]
...
“መቼም ቢሆን እግዚአብሔርን ያየው አንድ ስንኳ የለም፤ በአባቱ እቅፍ ያለ አንድ ልጁ እርሱ ተረከው።”
— ዮሐንስ 1፥18
☝"አንድ/አንዲያ ልጁ" መባሉ የኢየሱስ ልዩ መሆኑን (ብቸኛ ልጅነትን )የሚያሳይ መለኮታዊ ቃል ነው።ምክንያቱም የሰው ልጆችም፤መላእክቱም የእግዚአብሔር ልጆች ተብለዋል እዮ 1፥6፣።የኢየሱስ ግን ልዩ ነው።ልጅነቱ በመወለድ ወይንም በመፈጠር አይደለም።የነበረ የሚኖር ነው ለዘላለም።
☝ይስሃቅ ለአብርሃም ብቸኛ ልጅ ተብሎዋል "ስለተስፋው ቃል" ፣ ኢየሱስም ለአብ ብዙ ልጆች ብኖሩትም የባሕርይ ልጅ በመሆኑ ብቸኛ ነው ሁለም።
☝ኢየሱስ ክርስቶስ ወልድ ነው፤ቀዳሚ ተከታይ የሌለው የአብ የባሕርይ (የተፈጥሮ) ልጁ ነው።
☝በአባቱ እቅፍ ያለ ነው።አይደለም ሰው መላእክትም ልቀርቡት የሚያስፈራ ነው።ኢየሱስ ክርስቶስ ግን በእቅፉ ነው።እንዴትስ ያለ መቀራረብ ነው !? እንዴትስ ያለ ድንቅ ማወቅ ነው አባቱን !? [በእቅፉ በመሆኑም ብቸኛ ነው]
☝ኢየሱስ በተፈጥሮ ልጅ የተባለ ወልደ እግዚአብሔር ነው።ማንም እንዲህ ቀርቦ አያውቅም ።ኢየሱስ ግን ትክክለኛ አብን የሚያሳይ አምላክ ስለሆነ የቅርብ ቅርብ ነው።ይህ ቃል ይገልጸው ይሆን ፦ኢየሱስ ማለት ከአብ ተፈጥሮ ምንም ልዩነት የሌለው ፍጹም ትክክለኛ ምሳሌ ልጅ ነው።
☝መቼም ብሆን ማንም ያለየውን አብን፣ በእቅፉ ያለው ብቸኛው የባሕርይ ልጁ ገለጠው ። እናስ ማንም የማያውቀውን ፣ ያላየውን እንዴትስ ይገልጡታል !? ኢየሱስ ፉጡር ብሆን እንዴት ልገልጠጸው ይችላል !?
☝"ኢየሱስ አምላክ አይደለም" የሚሉት ራሳቸው ይህንን ክፍል በመጽሐፋቸው እንዲህ ብለውታል
፦ "በየትኛውም ጊዜ ብሆን አምላክ ያየው አንድም ሰው የለም፤ስለ እሱ የገለጸልን ከአብ ጎን ያለውና #አምላክ_የሆነው_አንዲያ_ልጁ ነው" በማለት ገልጸዋል (በአድሱ ዓለም ትርጉም) ።
መንፈስ ቅዱስ በጥፍ ብሎ እውነት ሳያስወራ አይቀርም <<ልጁ ራሱ አምላክ ነው>> ብለው መስክረዋል ።አንዳንድ ጊዜ እኮ ሰይጣንም ያምናል አምላክነቱን ፤ለዚያም ነው "ልታጠፋኝ መጣ !? ጊዜ እኮ ገና ነው" ብሎ የሚቀባጥረው።አምላክ ባይሆን ባይበልጠው፣ሉዓላዊ ባይሆን !? እንዴትስ እንዲህ ይላል !? ክብር ምስጋና ይግባውና ለሃያሉ ለአምላካችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ።ሃሌ ሉያ።አሜን።
[ኢየሱስ የአብ ዘላለማዊ ልጁ ነው፤መለኮት ነው]
....
“እርሱም የክብሩ መንጸባረቅና የባሕርዩ ምሳሌ ሆኖ፥ሁሉን በስልጣኑ ቃል እየደገፈ፥ኃጢአታችንን በራሱ ካነጻ በኋላ በሰማያት በግርማው ቀኝ ተቀመጠ፤”ዕብ 1፥3
☝"የባሕርዩ ምሳሌ" የሚለው ቃል በግሪኩ "khar-ak-tare " የሚል ቃል ነው።ትርጓሜውም ትክክለኛ ምሳሌ ማለት ነው፤Exact Copy ወይንም Exact representation ማለት ነው።
☝ኢየሱስ ብቸኛ የተፈጥሮ ልጅ በመሆኑ መጠን፣ብቸኛ እና ትክክለኛም ምሳሌም ነው ለአባቱ።
☝እኛ ከእውቀት ከፍለን እናውቃለን።ማወቅ የአምላክ ተፈጥሮ ስለሆነ ጥቅቷን እውቀት እናውቃለን ።ጥበበኛ ብንሆን እንኳን የሰውን ልብ ፣ የውስጡን ማወቅ አንችልም፤ኢየሱስ ግን ይችላል፤ልዩ ነው።
☝እኛ የሰው ልጆች በምሳሌው ነው የተፈጠርነው ።ግን የእኛ ምሳሌነት ትክክለኛ (exact) ባሕርይ ማሳያ አይደለም ።
☝ኢየሱስ ብቻ Exact ምሳሌ ነው።የቃል እምነት አስተማሪዎች እንደሚሉ አይደለንም ።ምክንያቱም የአምላክ ተፈጥሮ ወይንም ማንነት ሙሉ በሙሉ ልወክል እና ልያሳይ የሚችለው አምላክ ብቻ ነው።
☝የቃል እምነት አስተማሪው ሃይሉ ዮሐንስ " I'am exact like God " በማለት ማስተማሩ፣ራሳቸውን ኢየሱስ ክርስቶስ ማድረጋቸው ነውና ተጠበቁ እያልኩም እንደሆነ ይረዷል።
☝ኢየሱስ አንዲያ ልጅ የተባለው ለዚህ ነው።ኢየሱስ አምላክ ነው።ፍቅር ነው።እኛ ግን በአምላክ ምሳሌ የተፈጠርነው ፍጹም #ፍቅር አይደለንም፤በፍቅራችን እንኳን ጉድለት አለና።ለዚህ ነው ትክክለኛ ምሳሌ ባለመሆናችን "ቢቻላችሁስ ከማንም ጋር በፍቅር ኑሩ" የተባልነው ፣ድኩማን ፉጡሮች ነንና።
☝መላእክት መንፈስ ናቸው ፤እግዚአብሔርም መንፈስ ነው።እግዚአብሔር ግን ሳይታክት ያለ ስንፍና ይሰራል እስከዛሬ ።መላእክት ግን ሰነፎች ናቸው እዮ 4፥18 ።ደግሞም ..
☝ሰዎችም የእግዚአብሔር መንፈስ ተካፍለዋል ግን አይደለም ሠርተው፣ተራምደው፣ ተናግረው.. የሚደክሙ ድኩማን ናቸው፤ነን ።
☝ምንም እንኳን የእግዚአብሔር መንፈስ ብንካፈልም መጽሐፍ እኛን ትክክለኛ ምሳሌ እንደሆንን አይመሰከርም።እንደሁም "ትክክለኛ " የሚለውን ቃል ለክርስቶስ መጠቀሙ ፣ ሌሎች ሁሉ የእጁ ሥራዎች "ትክክለኛ ምሳሌ አለመሆናቸውን እና የክርስቶስ ምሳሌነት እንደሚልቅ ፣ ፍጹምም እንደሚለይ" የሚያሳይ ነው።
☝ጌታ "እውነተኛ የወይን ግንድ እኔ ነኝ"ዮሐ 15 ላይ ስል ፣ ከዚህ በፊት ያሉ የወይን ግንድ የተባሉቱ ሁሉ "እውነተኛ አይደሉም" ማለቱ እንደሆነ ሁሉ ፣ "ትክክለኛ ምሳሌ ነው" መባሉ ሌሎችን "ትክክለኛ ምሳሌ አለመሆናቸውን ያስረዳል" ፤ ስለዚህም የቃል እምነት አስተማሪዎች እናንተ ትክክለኛ ምሳሌ (Exact copy) አይደላችሁም፤እወቁ።መቼም ክርስቶስ ጋር እኩል አይደላችሁም።አምላክ አይደላችሁም ።
[ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ፦ብቸኛ ፣ ትክክለኛ የአብ ምሳሌ ነው፤አምላክ ነውና]
..
“ቶማስም፦ ጌታዬ አምላኬም ብሎ መለሰለት።”
— ዮሐንስ 20፥28
☝ቶማስ "ጌታዬ አምላኬ" ብሎ መለሰለት።ማንን አለ !? ከማን ጋር እያወራ ነበር !? የሚለውን ከፍ ብለን ስናነብ ይገልጽልናል ።
☝“ከዚያም በኋላ ቶማስን፦ጣትህን ወደዚህ አምጣና እጆቼን እይ፤እጅህንም አምጣና በጎኔ አግባው፤ ያመንህ እንጂ ያላመንህ አትሁን አለው።”ዮሐ 20፥27
☝ቃሉ እንደሚል ቶማስን ያናገረው ኢየሱስን ነው።ከኢየሱስ ጋር ነው ምልልሱ ።
☝የቶማስም መልስ ለኢየሱስ በጌትነቱ እና በአምላክነቱ ማመኑን የሚገልጽ ነበር። ቶማስ "ጌታዬ አምላኬ ነህ" ብልም ኢየሱስ ግን ይህንን ምስክርነት ተቀብሎታልን !?
☝“ኢየሱስም፦ ስለ አየኸኝ አምነሃል፤ ሳያዩ የሚያምኑ ብፁዓን ናቸው አለው።” ዮሐንስ 20፥29
🌱ኢየሱስ ምስክርነቱን "አይገባኝም" ወይንም "ጌታና አምላክ አይደለሁም" አላለም ።ይልቁንም "ሳታየኝ ማመን ነበረብ" ብሎ ወቅሶታል።
🌱"ሳያዩ በጌትነቱ እና በአምላክነቱ የሚያምነቱ የተባረኩ ናቸው" በማለት ሳያዩ ማመንን አበረታቷል ።
🌱ልክ አብ "አምላኬ ጌታዬ" እንደተባለው ሥጋ የሆነው ወልድም ተብሏል መዝ 83፥23፣5፥2..።በሥጋ የተገለጠው ወልደ እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ ነው።
🌱መጽሐፍ እንደሚል “አባቶችም ለእነርሱ ናቸውና፤ ከእነርሱም ክርስቶስ በሥጋ መጣ፥እርሱም ከሁሉ በላይ ሆኖ ለዘላለም የተባረከ አምላክ ነው፤አሜን።”ሮሜ 9፥5
[ስለዚህም ዛሬ ላይ ሳታዩ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ አምላክነት ያመናችሁ ብፁዓን ናችሁ።]
(እንቀጥላለን በጌታ ፈቃድ፤ተባረኩ)
....
Comments
Post a Comment