ነገረ ጸሎት
ነገረ ጸሎት
መግቢያ
1.ጸሎት ምንድነው !?
2.ለምን እንጸልያለን !?
3.ጸሎት ምን አይደለም !?
4.ጸሎት ወደ ማን !?
5.የኢየሱስ ጸሎት የእውነት ወይንስ ለምሳሌነት !?
6.እንዴት እንፀልይ !?
ማጠቃለያ
ዋቢ መጽሐፍት
መግቢያ
በዚህ ርዕስ ላይ ትንሽዬ ነገር ስለ ጸሎት ለመጽሐፍ ያነሳሳኝ ሰው የጸሎትን ትርጉም በትክክል እንዲገናዘብ ማድረጉ፣ለምን እና ወደ ማን እንደሚጸለይ መረዳቱ፣ደግሞም ጸሎት ምን እንዳልሆነ መገንዘቡ ለአንድ ሰው ወደ ቀድሞ ክብሩ ለመመለሱ፣ ከአምላኩ ጋር ቀጥ ለጥ ያለ ሕብረት እንድኖር ያደርጋል የሚል እምነት ነው።የአቅሜን ለመጽሐፍ ተጣጥርያለሁ።
ደግሞም የኢየሱስ የጸሎት ሕይወቱን ለማክፋፋት ፣ ድራማ ለማድረግ ለሚወተውቱም መልስ ለመስጠት ሞክሬያለሁ።በመጨረሻም የጸሎት አስተማሪ መንፈስ ቅዱስ ብቻና ብቻ እንደሆነ ለማስገንዘብ ጥሪያለሁ።
መታደስ፣መለወጥ፣ወደ ቅድሞ ክብራችን መመለስ ይሁን።በኢየሱስ ስም።አሜን ።
1.ጸሎት ምንድነው !?
☝ፀሎት ለአምላክን የሚቀርብ ልመና፥ምስጋና (የኢትዮጵያ .ቋንቋችና.ጥናትና ምርምር ማእከል አ.አ የካቲት 1993)
☝ጸሎት ልመና ምስጋና ፡ጸሎትስ ተናግሮተ ሰብእ ኀብ እግዝ ልዑል ..(ኪዳኔ ወልደ ክፍሌ መዝገበ ቃላት ሐዲስ)
☝ጸሎት << ሰው በእግዚአብሔር መልክና ምሳሌ የተፈጠረ ፣ ለእግዚአብሔር ስለተፈጠረ ከእግዚአብሔር ጋር ለመገናኘት ይፈልጋል ።መገናኛውም ጸሎት ስለሆነ ይጸልያል ።በማነኛውም ሃይማኖት ጸሎት አለ።የክርስቲያን ጸሎት ግን በክርስቶስ አማካይነት ሁኔታው የተለየ ነው።ጸሎት ከእግዚአብሔር ጋር ያለን የመገናኛ ምልክትና ግንኙነታችን ማጥኛ ነው።
ጸሎት ህብረት፥ምስጋናን ፥ ስግደትን፥ ንስሓን ፥ልመናን ፥ምልጃን ያጠቃልላል ። >> (መጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት ፣ገጽ 264-265 )
🌱ከመዘገበ ቃላቱ የሚንረዳው ጸሎት ከእግዚአብሔር ጋር መነጋገር እንደሆነ ነው።ሰው ሰውን የተለያየ ነገር ልለምን ይችላል ።ስለለመነ ግን እየጸለየ ነው ማለት አይደለም ።ለምሳሌ ብድር ልንለምን እንችላለንን ወይንም ማሳከምያ ልንለምን እንችላለን ፣ያ ማለት እየጸለይን ነው ማለት አይደለም ።
🌱ሰዎች ካጋጠማቸው ችግር የተነሳ ( ዘኃ 12) ወይንም ከፊላጎታቸው የተነሳ ሰዎችን ልለምኑ ይችላሉ (2 ነገ 2) ።
🌱"ጸሎት እየጸለየ ነው" ስንል ግን የፈጠረንን አምላካችን እያናገርነው፣እየሰማነው፣እየተገናኘነው ነው ማለታችን ነው።ወደ አምላካችን ስንጸልይ ውዳሴ፣ምስጋና፣ልመና፣ንስሓ (ሃጥአታችንን መናዘዝ )፣ለእርሱ መሰጠት ፣ለፈቃዱ እሺ ማለት፣መንግሥቱ እንድመጣ መናፈቅ ...ይህ ሁሉ ነው ጸሎት ።ወደ ሰው የሚጸለይ ሰው ይህንን ሁሉ ካደረገ እያመለከ ነው ማለት ነው።
🌱ሰዎችን ስላደረጉት መልካም ስራ ልንመርቃቸው "ክብርት ይስጥልኝ" ልንል እንችላለን ።ግን የጸሎት አንዱ ክፍል ምስጋና ስለሆነ እየጸለይን ነው ማለት አይደለም ።ልመናው ብሆንም ያስፈልገን ነገር ልንለምን እንችላለን።ግን እየጸለይን ነው ማለት አይደለም።እንደዛው ሃጥአታችንን ልንናዘዝ እንችላለን ለመንግሥት ይሁን ለግለሰብ ግን እየጸለይን ነው ማለት አይደለም ።
🌱ጸሎት ስባል ሰዎች በተለይ ክርስቲያን ከእግዚአብሔር ጋር የሚገናኙበት ማለት ብቻ ነው።
2.ለምን እንጸልያለን !?
☝ጸሎት ማለት ከእግዚአብሔር ጋር መገናኘት ከሆነ የምንጸልየውም ከእግዚአብሔር ጋር ለመገናኘት ብቻና ብቻ ነው።አስተውሉ።በጸሎት ግዜ ከእግዚአብሔር ከአባታችን ጋር ተናግረን ፣ የእሱንም ድምጽ ሰምተን ፣ ፈቃዱን ምክሩን ተቀብለን የሚንመለስበት ነው።እኔ ብቻ አልናገርም ፤እርሱም ይናገራል እኔም ሰሚ ነኝ።
☝አንዳንድ ሰዎች ከራሳቸው ድኩማንነት የተነሳ ጸሎት የሚያደርጉት በችግር ግዜ ስለሆነ ጸሎት የሚጸልይ ሰው የሚጸልየው ስለተቸገረ ብቻ አድርገው ይወስዱታል።የሚንጸልየው ለችግራችን ብቻ አይደለም።ችግርን ለእግዚአብሔር መንገር የጸሎት ክፍል ብሆንም በራሱ ጸሎት ማለት ችግርን መናገር ማለት አይደለም ።እንዲያ ከሆነ ካለ ችግር ላንጸልይ ነው ማለት ነው።
☝ከእግዚአብሔር ጋር ስንገናኝ ፦ ገና ስንጀምር እናመሰግናለን ፣ ናፍቆታችንን እንገልፃለን ፣ፈቃዱን መሻታችን እንነግራለን፣የሚያስፈልገንን እንለምናለን ፣ንስሓ እንገባለን ፣ጠባቆቱ እንዲበዛ እንለምናለን ፣ደግሞም እናመሰግናለን ማቴ 6።ስለዚህ ጸሎት ይህ ሁሉ ውዳሴ ያለው ነው እንጂ ችግርን መናገሪያ የግንኙነት መንገድ ብቻ አይደለም ።
☝ሰዎች ችግር ስኖር ብቻ ፊቱን ልፈልጉ ይችላሉ ።እኛ ግን የምንመለከተው መመልከት ያለብንን ኢየሱስን እንጂ ሰዎችን አይደለም ።ለምሳሌ ኢየሱስ ያለችግር ግዜም ይጸልያል። እንያ እስኪ ፦
🌱“ነገር ግን እርሱ ወደ ምድረ በዳ ፈቀቅ ብሎ ይጸልይ ነበር።”ሉቃስ 5፥16። ኢየሱስ ያለምንም ችግር ጊዜ ከአባቱ ጋር ለመሆን ፣ ለመገናኘት ስለሚፈልግ ሰዎች ራሱ ተሰብስበው ስጠብቁ እርሱ ግን ከአባቱ ጋር ለመሆን መናፈቁ ፣ ጸሎት በችግር ጊዜ ብቻ የሚደረግ እንዳይደለ ያስረዳል ።እንደውም እኮ 'ዝና' እየመጣ እያለ ነው ፣ ትቶ ወደ አባቱ የሚሄደው ።
ስለዚህ ጸሎት ከአባት ጋር ለመገናኘት ነው በችግርም ያለችግርም ጊዜ የሚደረግ የፍቅር ሕብረት ነው
3.ጸሎት ምን አይደለም !?
☝ መናገር ብቻ አይደለም መስማትም ነው ፣
☝የሰውን ጸሎት እንደራስ ጸሎት መጸለይም ጸሎት አይደለም ።ለምሳሌ፦ ዳዊት በመዝሙሩ ለተለያየ ችግር እና በተለያየ ጊዜ ፣ የተለያየ ምስጋና ከአፉ ፈልቋል።አንዳንዶቹ ትንቢታዊውም ናቸው ።
የዳዊትን መዝመር በእጄ ይዤ እርሱ ያለውን ማንበብ ፣ እየደጋገምኩም ማንበብም ፣ ጸሎት አይደለም ።እንደውም ዳዊት ጠላቶቹን ይራገማል ።“አቤቱ፥ የሚበድሉኝን በድላቸው፥ የሚዋጉኝንም ተዋጋቸው።”መዝ 35፥1 ።ይህ ጸሎት በብሉይ ኪዳን በራሱ ትክክል ልሆን ይችላል ።ግን ኢየሱስ ክርስቶስ እንዲህ ያለ ጸሎት እንዳናደርግ አድርጓል ማቴ 5፥44-45።
ደግሞም ዳዊት የጸለየው ለዙፉኑ ልሆን ይችላል የእኛ ጸሎት ደግሞ ለሥጋ በሽታ ልሆን ይችላል ።እናም የሰውን ጸሎት መጸለይ 'እጸልይኩ ነኝ' ማለት ነው እንጂ ጸሎት አይደለም ።
☝የተማሩ እና ሊቀ ሊቃውንት የተባሉቱ እንድንጸልይ ጽፈውልን የሰጠኑን ጹሑፍ ማንበብ ጸሎት መጸለይ አይደለም ።የተጻፈው ጹሑፍ አንደኛ ነገር የጸሎትን መርሆን የሚቃወም ነው።ጸሎት በሊቃውንት ጹሑፍ ሳይሆን በመንፈስ ቅዱስ ብቻና ብቻና ነው።ሌላው ደግሞ ይህ ጹሑፍ እንደ አጥቢያው ይሁን ፣ እንደየጊዜው ለሚነሳው ነገር ለመጸለይ ምቹ ላይሆን ይችላል ።ግን ምቹ መሆን አለበት በተሰበሰቡበት ካልተጸለየ መቼ ልጸለይ ነው!?።ሌላው ደግሞ ጉድለቱ "እንዴት መጸለይ እንዳለብን አናውቅም"የሚለውን የመጽሐፉን መርሆን 'እንዴት መጸለይ እንዳለባችሁ እናውቅላችኋለን' በማለት ይቃወማል ።
በቤተክርስቲያን የሃይማኖት መገለጫ ይነበባል እንጂ ጸሎት ስነበብ ተስምቶም አይታወቅም ።ግን በዚህ ችግር ውስጥ በተሃድሶአዊ አገልግሎት የሚትታወቀው #ማህበረ_አኀው_የክርስቶስ_ቤተክርስቲያን የእምነት ተቋም በማግኘታችን ተቃውመናል፤ በግልጽ።ምንም እንኳን መልሱ ተልእኮዋን ያማከለ ባለመሆኑ ብናዝንም፤ብያሳፍረንም፤በቃሉ ደስ ተስኝተናል [ ውግዘት ነበር ያስተናገድነው] ።ሳጠቃልለው ማንንም ጽፎልን የሰጠውን ጹሑፍ ማንበብ ጸሎት አይደለም ።
☝ጸሎት የሚያማማምሩ ቃላት ድግግሞሽ ሳይሆን በመንፈስ ቅዱስ በአባት ፊት መኮላተፍ ነው።
☝ጸሎት በዘመናዊ መገናኛ ዘዴ በስልክ ወይም በሚዲያ ወደ እግዚአብሔር የሚደረግ ሳይሆን በመንፈስ በእምነት የሚደረግ ግንኙነት ነው።
☝ጸሎት ከፊት ለፊት በተደቀኑ ቁሳቁስ ሆነ፣ፉጡራን ፊት ማንጓጠጥ ሳይሆን በመንፈስ ለማይታየው አምላክ መናገርና መስማት ነው።
4.ጸሎት ወደ ማን !?
☝ጸሎት ማለት ከእግዚአብሔር ጋር መገናኘት ከሆነ ጸሎቱም ወደ እግዚአብሔር ብቻና ብቻ ነው ማለት ነው።
☝ጸሎት ወደ ሰዎች አይደረግም።ምክንያቱም ከሰው ጋር ለመገናኘት በመንፈስ መጸለይ አያስፈልግም፤የሚያስፈልገው በዘመናዊ መገናኛ ዜዴ ስልክ መጠቀም ወይንም ደብዳቤ መላክ ነው ።
☝አስተውሉ ከሰው ጋር ለመገናኘት በጸሎት መነጋገር የቻለ ሰው የለም።ሐዋርያው ጳውሎስ እንኳን ደብዳቤ ነው የጻፈው፤መልእክተኛ ነው የላከው።እንድሁም በአካል ለመገናኘት እንዲቻል ወደ እግዚአብሔር ነው የሚለምነው ።በእርግጥም ወደ ሰው ጸልየው "እንገናኛለን" የሚሉ አሉ፣እነዚያ ሟርተኞች እንደሆኑ እናውቃለን ።
☝ወደ መላእክትም ብሆን ጸሎት አይደረግም ።ከመላእክት ጋር ለመገናኘት ስልክም ደብዳቤም አይሰራም፤ጸሎትም አይሰራም።ለመገናኘት ያለው ብቸኛው መንገድ በአካል በግልጥ መገናኘት ብቻና ብቻና ነው።እንደ ዳንኤል 10 ፣እንደ ሎጥ ዘፍ 19 ፣እንደ ኢየሱስ እናት ብፅዕት ማርያም ሉቃ 1 ...
☝አስተውሉ ከመላእክት ጋርም ብሆንም እንኳን ፣ ከተገለጡም ልንገናኝ የምንችለው ፣ እግዚአብሔር በመልእክት ልኮአቸው ከመጡ ብቻና ብቻ ነው ።
5.የኢየሱስ ጸሎት የእውነት ወይንስ ለምሳሌነት !?
☝አንዳንድ ሰነፎች "ኢየሱስ አምላክ ነው ወይም አይደለም !? አያውቅም ወይም ያውቃል !? በማለት፣ የኢየሱስ ጸሎት የእውነት ሳይሆን ለምሳሌ ነው፤ለማስተማር ነው"ለማለት ይወተውታሉ ።እኔም ጥያቄ አለኝ ፦
🌱የኢየሱስ! ጸሎቱ ብቻ ነው ምሳሌ ወይም መስቀሉም ነው !? መጸለዩ ብቻ ከሆነ ለምን !? ጌታ ለማስተማር ብቻ ከሆነ ለምንስ ይሰቀላል (በመስቀል ላይ ሆኖሞ ይለምን ነበር) ፣ለምንስ ይሞታል !?
🌱ያለተማሪ አስተማሪ መባል የለም።"ኢየሱስ ለማስተማር ጸለየ" ካልን ያለ ተማሪዎች ብቻውን መጸለዩም ለማስተማር ነውን !?
🌱አትሳቱ።ኢየሱስ በሥጋው ወራት ያደረገቻቸው ሁሉ የእውነት እንጂ ድራማ አይደለም፤ጸሎቱም የእውነት ነው፤መቸንከሩ፣መሰቀሉም፣መሞቱም የእውነት ነው።አትስነፉ።
🌱“ሕዝቡንም አሰናብቶ ይጸልይ ዘንድ ብቻውን ወደ ተራራ ወጣ። በመሸም ጊዜ ብቻውን በዚያ ነበረ።”ማቴ 14፥23 እንደሚል ። ያለ ማንንም ተማሪ ፣ ብቻውን ከጸለየ የኢየሱስ ጸሎት የእውነት እንጂ ለማስተማሪያነት አይደለም ።
🌱ኢየሱስ እንደ እኛ የተፈተነ ነው።ፈተናውም የእውነት ነው እንጂ ድራማ አይደለም።ድራማ ብሆን መጽሐፍ "የተፈተነ ነው" አይለንም ነበር።“እርሱ ራሱ ተፈትኖ መከራን ስለ ተቀበለ የሚፈተኑትን ሊረዳቸው ይችላልና።”ዕብ 2፥18
🌱ሌላው ደግሞ ኢየሱስ ስጸልይ ጸሎት እያስተማረ ነው ካላችሁ ፣ ለምንስ "ጸሎት አስተምረን ይላሉ !?
“እርሱም በአንድ ስፍራ ይጸልይ ነበር፥በጨረሰም ጊዜ ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ፦ ጌታ ሆይ፥ዮሐንስ ደቀ መዛሙርቱን እንዳስተማረ እንጸልይ ዘንድ አስተምረን አለው።”ሉቃ 11፥1
[የኢየሱስ ሕይወት ለሁሉም መመልከቻ መማሪያ ነው።ሕይወቱ የእውነት ነው እንጂ ድራማ አይደለም]
6.እንዴት እንፀልይ !?
☝"ጸሎት እንደዚህ ይጸለያል " ብዬ በአድሱ ኪዳን ላስተምር አይደለም።ምክንያቱም እኔም ራሴ ደግሞም ማንም እንዴት መጸለይ እንዳለበት አያውቅምና ነው።
☝በብሉይም ሆነ ፣ ወደ አድስ ኪዳን መሸጋገሪያ ጊዜ ላይም ሆነ፣ እንዴት እንደሚጸለይ አስተማሪዎች ያስተምሩ ነበር።ኢየሱስም በዚያ ልክ አስተምህሮ ነበር።“እርሱም በአንድ ስፍራ ይጸልይ ነበር፥ በጨረሰም ጊዜ ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ፦ጌታ ሆይ፥ ዮሐንስ ደቀ መዛሙርቱን እንዳስተማረ እንጸልይ ዘንድ አስተምረን አለው።”ሉቃ 11፥1
☝ጸሎትን የሚያስተምሩት በጸሎት ጊዜ ድካማቸውን ልረዳ የሚችል መንፈስ ቅዱስን ስልላተቀበሉ እና እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ መጸለይ እንዲችሉ ለማድረግ ነው።
☝በአድስ ኪዳን ግን መንፈስ ቅዱስ ስለሚያግዝ ፣ ስለሚረዳ እና የእግዚአብሔርን ፈቃዱን ስለሚያሳውቅ ደግሞም "እንዲህ በል ብሎ ስለሚቃትትልን " (ስለሚማልድልን በውስጣችን ) ፣ ጸሎት ማስተማር አላስፈለገም ።
☝ስለዚህም የተኛውም አስተማሪ የመጸለይ ጥቅም እና ያለመጸለይ ጉዳት ከመጽሐፍ ቅዱስ ያስተምራል እንጂ እንዴት መጸለይ እንዳለብን አያስተምሩም ።ምክንያቱም አስተማሪዎች ለራሳቸው አያውቁም ተማሪዎች ናቸው፤ያውም የመንፈስ ቅዱስ ተማሪዎች ፤ ተረጅዎች ።ስለዚህም ቃሉ እንደሚል ፦
🌱 አንደኛ እንዴት መጸለይ እንዳለብን አናውቅም
🌱ስቀጥል የሚያስተምርም ሰውም የለም፤አይኖርም ። ይህ የእግዚአብሔር ሥራ ነው።
☝“እንዲሁም ደግሞ መንፈስ ድካማችንን ያግዛል#እንዴት_እንድንጸልይ_እንደሚገባን_አናውቅምና፥ ነገር ግን መንፈስ ራሱ በማይነገር መቃተት ይማልድልናል፤”ሮሜ 8፥26
እንዴት መጸለይ እንዳለብን የሚያስተምረን የሁሉም አስተማሪ መንፈስ ቅዱስ ነው፤ሃሌ ሉያ
ማጠቃለያ
ጸሎት ፈጣሪያቸውን የሚያውቁ ሰዎች ከእርሱ ጋር ለመገናኘት የሚያደርጉት ግንኙነት (መነጋገሪያ) ነው።አሕዛብም ወደተለያየ አማልክት ለመገናኘት ጸሎት ያደርጋሉ።ለክርስቲያኖች ግን ይህ ዓይነቱ ልምምድ ጣኦትን ማምለክ ነው እንጂ እውነተኛ ጸሎት አይደለም ።እውነተኛ ጸሎት የፈጠረውን እግዚአብሔርን ብቻ ማነጋገር ከእርሱ ጋር ጊዜ ማሳለፍ ፣ መታዘዝ ፣በራስ ላይ ማሰልጠን፣ማወደስ፣....ነው ።
እግዚአብሔርን የተናፈቀው ከእርሱ ጋር ጊዜን ለማሳለፍ ወደ ሰፈሩ ውጪ (ብቻውም ብሆንም) በመውጣት የተኛውንም የምድር ክብር ንቆ ፣ ከእርሱ ጋር መነጋገር እንደሚናፍቅ አይተናል ።ሰው ሳይቸገር ካልጸለየ አምላኩን አልወደደም፤አልተረዳውም ማለት ነው።ጸሎት ግን የናፍቆት ውጤት ነው እንጂ የችግር ውጤት አይደለም ፤ይህንን ከክርስቶስ እንማራለን።
በቀረው ግን ወደ ሰው ለመጸለይ ከመጥቀሳችሁ በፊት ከፈጣሪያችሁ ጋር መጸለይን መነጋገርን ልመዱ።እርሱ ፍቅር ነው።በቀጥታ እንድትመጣ፣በእግሩ ስሪ እንድትወድቅ ይፈልጋል ፤አባት ስለሆነ እጆቹ ለመቀበል የተዘረጉ ናቸው ።ይቅር ባይ ስለሆነ ዓይኖቹ ይሳሳሉ።ላንተ ፣ ላንች ፣ ለእኛ እኮ ነው የሞተው፤ የተገረፈው።አንተን አንቺን የኢየሱስ ደም የማያቀርብ ከሆነ ለምን ኢየሱስ ተሰቀለ!? ተሰቃየ!? ለምንስ ሞተ !?
እመን! እመን! ይቀበላል።የሆነው ሁሉ እኮ ላንተም ላንችም ነው።አጉል አትቦዝን።ደሙን ዋጋ አታሳጣ።የደሙ ኀይል ከኀጢአትህ/ሽ በላይ ነው።ደሙ ይጠራል።ኑ ቅረቡኝ ይላል።ችላ አትበሉ።ሳኦል አሳዳጁን ፣ገዳዩን ፥ አቅርቦ ለዚያውም ሐዋርያ ካደረገ አንተንስ እንዴታ !? እመኑ በእርሱ።እግዚአብሔር ለማንም አያዳላም ።አንተንም ይቅር ይላል ።በማንም በምንም በኩል ለመቅረብ አትወትፍ፤ጊዜ አታባክን።በክርስቶስ ፣ በደሙ በኩል እግዚአብሔር ራሱ ይጠራሃል።ሃሌ ሉያ።
መመለስ መለወጥ መታደስ ማደግ ይሁን።በኢየሱስ ስም።አሜን ።ሃሌ ሉያ።
ዋቢ መጽሐፍት
☝የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት
☝መጽሐፍ ቅዱስ የ1954 ዓ.ም (ነባሩ ዕትም)
☝የኢትዮጵያ .ቋንቋችና.ጥናትና ምርምር ማእከል አ.አ የካቲት 1993
☝ ኪዳኔ ወልደ ክፍሌ መዝገበ ቃላት ሐዲስ
Comments
Post a Comment