ተአምረ ኢየሱስ የሚባለው መጽሐፍ ተአማኒነት አለው ?
<< ኢየሱስ ከ30 ዓመቱ በፊት ምልክት አድርጎ ነበርን? ተአምረ ኢየሱስ የሚባለው መጽሐፍ ተአማኒነት አለውን !? >>
👉" ተአምረ ኢየሱስ"የሚባለው መጽሐፍ ኢየሱስ ከፅንሰቱ እስከ ትንሳኤው ድረስ የሰራውን ተአምር የመዘገበ መጽሐፍ እንደሆነ ይነገራል፤ደግሞም ተምረናልም።
☝እንደ እግዚአብሔር ቃል <<ኢየሱስ ምልክት ማድረግን መቼ ጀመረ !? በእውነት ከ30 ዓመቱ በፊትም ምልክቶችን ያደርግ ነበርን !? >> የሚለውን ጥያቄ ይዘን ለመፈተሽ ተነስተናል ።
☝በእውነቱ.. ጌታ ከ30 ዓመቱ በፊት ምልክቶችን ያደርግ እንደነበረ የሚያሳይ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ይኖር ይሁን !?
☝በእርግጥም የሚጠቀሰው አይጠፋም ፤ያው ማንም ይጠቅሳልና ፥ ግን "ተአማኒነት አለው ወይ !?" የሚለው ጥያቄ ልነሳ ይገባል።
☝ለዚህ ማስረጃነት የሚጠቀሰው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል የዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 20፥30 ነው።ቃሉ እንዲህ ይላል ፦ “ኢየሱስም በዚህ መጽሐፍ ያልተጻፈ ሌላ ብዙ ምልክት በደቀ መዛሙርቱ ፊት አደረገ፤”
☝ይህ ክፍል 'ኢየሱስ ክርስቶስ ከ30 ዓመቱ በፊት ምልክቶቹን አድርጓል' ስለመባሉ ማስረጃ ልሆን ይችላል ወይ !? የሚለውን እንፈትሽ በጥልቀት ፦
🌱 ኢየሱስ በዮሐንስ ወንጌል ያልተመዘገበ ሌላ ብዙ ምልክቶቹን እንዳደረገ ቃሉ ይገልጽልናል ።ግን ቃሉ የሚለው << ኢየሱስ ሌላ ብዙ ምልክቶችን፣በመጽሐፉ ያልተጻፉትን፣እንዳደረገ ነው፤ እንጂ ከ30 ዓመቱ በፊት ምልክቶችን ስለማድረጉ አይነግረንም፤ይልቁንም ቃሉ የሚለው ፦ኢየሱስ ክርስቶስ ያደረገው ተአምር ሁሉ በቁጥር እንደ ብዛቱ መጠን እንዳልተጻፈ ነው።
🌱ግን የኢየሱስ.. ምልክቶችን፣ ዮሐንስ ሁሉንም አለመዘገቡ በራሱ ሌላ ሰው መመዝገቡን ያሳያልን !?
🌱ደግሞም ምልክቶቹ የተደረጉት ከ30 ዓመቱ በፊት በልጅነቱ ነው ለማለት ያስደፍራል !? አያስደፍርም።ምክንያቱም ዮሐንስ ስመሰክር <<ኢየሱስ ምልክቶቹን በደቀመዛሙርቱ ፊት አደረገ >> እንጂ በልጅነቱም አደረገ አይልም።
🌱ኢየሱስ ምልክቶችን በደቀመዛሙርቱ ፊት ካደረገ ፣ ደቀመዛሙርቱ በ30 ዓመቱ፣ከውሃ ጥምቀት በኃላ መሰብሰቡ ደግሞ የመጽሐፉ እውነታ ነው፤ከዚህ ጋር ደግሞ ይቃረናል፤ትርክቱ።
🌱ስለዚህም ኢየሱስ ብዙ ምልክቶችን በደቀመዛሙርቱ ፊት፣ከ30 ዓመቱ ጀምሮ ምልክትን እንደሰራ እንረዳለን ።በዚህ እውነት መሠረት <<በልጅነቱ ምልክቶቹን አድርጓል>> ለማለት የሚጠቀሰው ይህ የዮሐንስ ወንገል ምዕራፍ 20፥30 አያስከድም እንላለን ።
☝ ሌላው ደግሞ ኢየሱስ ከ30 ዓመቱ በፊት ምልክት እንዳልሰራ የሚያስረዳው ክፍል የዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 2፥11 ነው።ቃሉም እንዲህ የሚል ነው ፦ “ኢየሱስ ይህን የምልክቶች መጀመሪያ በገሊላ ቃና አደረገ፤ ክብሩንም ገለጠ፥ ደቀ መዛሙርቱም በእርሱ አመኑ።”ዮሐ 2፥11
☝በዚህ ክፍል መሠረት በገሊላ ቃና የተደረገው ምልክት ፦
🌱1ኛ.ዮሐንስ እንዳለው በደቀመዛሙርቱ ፊት የተደረገ ምልክት ነው ፣
🌱2ኛ.የመጀመሪያው ምልክትም ነው፣
🌱3ኛ."ክብሩን ገለጠ" እንደሚል ክብሩም የተገለጠበት የመጀመሪያው ምልክት ነው።
☝በዚህ ጊዜ ነው እንጂ ክብሩ የተገለጠው ከ30 ዓመቱ በፊት እንዳልሆነ ግልጽ ነው ።
[ስለዚህም ምክንያት ኢየሱስ በልጅነቱ ምልክት አላደረገም ፤ 'ተአምረ ኢየሱስ' የሚባለው መጽሐፍ ተአማንነት የለውም እንላለን]
የምነቀለው ይነቀላል የምተከለው ይተከላል በኢየሱስ ስም !
#መልስ አለኝ የሚል ሁሉም ይምጣ።
Comments
Post a Comment