አምልኮተ ሰብእ ከምንጩ ይነቀል! ለዘማሪ ልዑልሰገድ የቀረበ የኑፋቄ ምንጭ ምላሽ ።
አምልኮተ ሰብእ ከምንጩ ይነቀል!
መግባት ይቻላል !
በዚህ ርዕስ ላይ ለመጻፍ ያነሳሳኝ የሰሞኑ ገጠመኝ ነው።ዘማሪው ነው።ቋንቋው ሰብዒ የሆነለት።ተስፋም እምነቱ እና ትምክቱም ሰብዒ የሆነለት።ከአትሮኖሱ ስሰበክ በመስማቱ ማከፈሉን ብነግረንም ።ከብዙ ተቋውሞ በኃላ ነው ።"መጀመሪያም ሳያምን ነውን!?" ፣ ምክንያቱም አራተ እየደጋገመ "ኢየሱስ ያድናል ማለት ክህደት /ምንfikiና / ነው" ብሏልና።የጥያቄ እና የተቋውሞ ናዳ ስወርድበት ፣ ከቤቷ ሰባክና ከአትሮኖሱ መስማቱን በመንገር "ከደሙ ንፁህ ነኝ" ለማለት አላፈረም ።
ከጎበዛዝቱ የመጣውን ተግሳጽ እንደ ስድብም መቁጠሩ አስገርሞኛል።ከሁሉ በላይ የሚያስገርመኝ በቦታው የሰሙት እና በደብሩ የሞሉቱ በሺዎች የሚቆጠሩ ሕዝቦች ፣ሳይጋጭባቸው 'ኢየሱስ ያድናል ማለት ክህደት ነው' ብለው መቀበላቸው ነው፤ከቦታው ተቋውሞ አልሰማንምና።"ቃለ ሕይወት ያሰማ" አዎን ያሰማ ወዳጄ፤ሄድክኮ።የአስተማረውም 'ሊቀ' ጥላቻ ካልሆነ በስተቀር ፣ በየትኛው መጽሐፍ ክፍል ስለትም ኢየሱስ የሚያድን እንደሆነ መመስከሩ ክህደት ሆኖ አያውቅም፤ጫፍ የወጣ ጥላቻ እና መመረዝ ካልሆነ በስተቀር።ከአንድ 'እውቅ' መምህር የማይጠበቅ ነው።ወንጌል የቋንቋ ማቀነባበሪያ አይደለም ሕይወት ነው።ወንጌል የቃላት ብልጫ ሳይሆን የቃሉ የነጠረ እውነት ነው።
ዘማሪ ባወጣው በእምነት ቃል ፦"ኢየሱስ ያድናል ማለት ክህደት ነው " በሚለው በዚህች ቅጥበት ብቻ "ልክ ነው" ያለው ስንቱ ነው መሰላቹ ? ታዲያ የሚወዱቱ እና የሚያከብሩቱ ቀጥታ ከመምህር የሰሙት እንዴት ተበርዝው ይሁኑ !? ጌታ ይድረስላችሁ።በእኛ ሃገር ውሸት ስደጋገም እውነት ይሆናል ።ምክንያቱም ሞኝ የተከለውን ብልህ አይነቅለውም።ባይነቀልም እንኳን እኛም ከመናገር ዝም አንልም፤የታባቱ ኑፋቄ ደግሞ።
ታዲያ በዚህ ኑፋቄ ላይ ሳይተባበሩቱ በብርቱ በመቃወም ለቃሉ ያላቸውን ፍቅር የገለጹትን ማበረታታትን ወደድኩሁ።ተባረኩ።እውነት በማንም ስነገር ያምራል ።ቃሉ እንደሚል ዋናው የእውነት ቃል በዚህ አጋጣምም መሰበኩ ነው።ምንም እንኳን የቀረበውን ውሃ ዘማሪው እንዴት መጠጣት እንኳን በማያውቅ መልኩ መዋጡ ብያሳዝንም፣ልጅ በሆነው ልቡ።ግን አስድቶኛል።ምክንያቱም እሱ ባያካፍል በደብሩ ከአትሮኖሱ ኑፋቄ ተስብኮ እንደኖረ ማን ያውቅ ነበር።እናም ተባረክ ።እንደዚሁም ማከፈሉን ልመድ ።ለራስህ ግን በብልህነት በመጠንቀቅ ጠጣ።ለዓይን የማታዩ ብዙ ጀርሞች አሉና።ማንም ከተናገረ "ምንጩ ከዬት ነው?" ለማለት ሞክር ።ይህ ሌላው ግዜ ትምህርት ይሆናል ።ደስ ይላል።
እናንተም ያለ መሰላቸት ያለዝምደት እስከመጨረሻው የገሰጻችሁ እግዚአብሔር ይባርካችሁ ።እኝ አባት ለዚህ የተዳረጉት ከምን እንደሆነ ብትገነዘቡ እና እንዴት የቤተክርስቲያን መሠረት የሆነው ትምህርት እንደተዳፈረ ከምንጩ እንድትቦረቡሩ ግብዣዬ ነው።በእውነቱ በመምህሩም በተቀበለው በዘማሪውም አልፈርድም ።ከምውሉበት ቦታ የተነሳ ነውና።እናም "የት እና ምን እያነበቡ ሁለው ነው እንዲህ የዘቀጡቱ?" ብትሉ ፣ "አባታቸውን (መጽሐፍ ቅዱስን) ከማይመስሉ መጻሕፍት ጋር ከርመው ነው" የሚል ነው መልሴ።
እኔም ሸክም እንደሚሰማኝ ሰው ከዚህ ለአንደና ለመጨረሻ ግዜ መውጣት እንድሆንላቸው ይህችን አጋጣሚ በመጠቀም አምልኮተ ሰብዒ ውስጥ እንዳላችሁ ከመጻሕፍታችሁ ላሳያችሁ ወደድኩ።ብዙ የሚዲያ ስብከት አለ።ለሁሉም ግን ቃሉን ማስተማር የመልስ መልስ ነው።ከምንጩ እናድርቅ።
________________
አምልኮተ ሰብእ ከምንጩ (1)
"በእርሷ ላመኑት ድነታቸው ነች " [1] ሌላው ፦ "እመቤታችንን ለዓለም መድኃኒት እንዳደረጋት እወቁ"[2] ደግሞም ፦"ከኀጢአት ታነፃላች "[3] ከብዙ በጥቅቱ ከምንጩ ይህንን ይመስላል።
በዚህ ክፍል ብቻ ተነስተን የዘማሪው እና የመምህሩን ውድቀት ከዚህ እንደሚጀምር መገንዘብ እንችላለን ።"ኢየሱስ ያድናል አይባልም" ለማለት እስከ መድረስ ያበቃቸው እና ያልጎረበጣቸው ለዚህ እንደሆነ ግልጽ ነው፤ ይሆናል።ምንም እንኳን "ከደብሩ ተቋውሞ ለምን አላጋጠማቸውም" ብልም ቀሳውሱቱም የሚያነብቱም ይህንን ስለሆነ ነው፤ተአምረ ማርያምን ።ምክንያቱም ይህን "መጽሐፍ መስማት በራሱ የወንጌል ምትክ ተደርጎ ይቀጠራልና"።ስለዚህ ከምንጩ ተቃወሙት እላለሁ።ግን ሕዝቡን ይቅርታ መጠየቅ ስገባው/ቡ፤ለምን ተወ/ው !?
ከላይ ያስቀመጥኩት ክፍል "የኢየሱስ እናት መሆኗን የሚያምን" አይልም ።እንዳዛ ብል በምን እድል።ምናልባት የኢየሱስ ሥጋ የማርያም ሥጋ(የዳዊት ልጅ ሥጋ) አይደለም የሚሉትን የሚያሳፍር ይሆን ነበር።ግን "መዳን እንደሆነች እመኑ" የሚል ነው።እጅግ የሚከብድ ኑፋቄ ነው።መጽሐፍ ስናገር “ልባችሁ አይታወክ፤ በእግዚአብሔር እመኑ፥ በእኔም ደግሞ እመኑ።”ዮሐንስ 14፥1፣የሚል ነው።ለመዳን ልታመን የሚገባው እርሱ አንድ አምላክ ነው።ምክንያቱም በእርሱ ብቻ የዘላለም ሕይወት እንዳለን እናውቃለንና 1ዮሐ 5፥13።
ስለዚህም "መዳን" አይደለችም፤ሆናም አታውቅም ።ጌታ በምድር ስመላለስ አገልግሎቱን ከጨረሰ በኃላ ማንንም "መድኃኒት አላደረገም" ።የመጣውም “ፈቃዴን ለማድረግ አይደለም እንጂ የላከኝን ፈቃድ ለማድረግ ከሰማይ ወርጃለሁና።”— ዮሐንስ 6፥38 ፣ብሏልና።ስለዚህም የአባቱ ፈቃድ ደግሞ “ልጅንም አይቶ በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወትን እንዲያገኝ የአባቴ ፈቃድ ይህ ነው፥ ..።”ዮሐ 6፥40 ።
ይህ ቃል ትራስ ሆኖ የመብረቅ መከላከያ አድርገን የያዝነው መጽሐፍ ምስክር ነው።ደግሞም ዘማሪው እና መምህሩ ከተናገሩት ኑፋቄ ከምንጩ ስንገመግም የሚገርመው ነገር ኢየሱስ ሰውን "ምስክር" ማድረጉን ነው እንጂ መድኀኒት አለማድረጉን ነው የሚንረዳው።ማርያምን መድኃኒት ለማድረግ አልመጣምና፤አላደረገምም።ግን የመድኃኒት ጠቋሚ መስካሪ አደረጋት እንጂ።
ሌላው ደግሞ ምንም እንኳን ተአምረ ማርያም "ከኃጢአት ታነፃለች" በማለት ኑፋቄ ብዘራም መጽሐፍ ስናገር ግን ከዚህ በኃላ ከኃጢአት መንጻት "በስሙ" እንደሆነ ይመሰክርልናል።መቼስ በስሙ ከመሰከረ "በስሙ ብቻ" አይልም የሚል ድርቅና መንፈስ አዝም አይሆንባችሁም ።ቃሉ እንዲህ ነው የሚለው ፦ሉቃስ 24፥⁴⁷ በስሙም ንስሐና የኃጢአት ስርየት ከኢየሩሳሌም ጀምሮ በአሕዛብ ሁሉ ይሰበካል ተብሎ እንዲሁ ተጽፎአል።⁴⁸ እናንተም ለዚህ ምስክሮች ናችሁ።ስለዚህም ማርያምም ከቅዱሳኑ አንዷ ናትና ለመመስከርም የታደለች የታመነች ናት።ስለራሷ ሳይሆን ስለ አምላኳ እና ስለ መድኀኒቷ መስካሪ ብቻ ነች።ቃሉ የሚለው ይሁኑኑ ነው።
"ኢየሱስ ያድናል ማለት ስህተት ነው" ስባል የተቃወምነው "ሌላው አያድንም" በማለት እንደሆነም ልብ ይሏል።ምክንያቱም እርሱ ከብዙዎች አንደኛው አዳኝ ሳይሆን ብቸኛ አዳኝ ነው።ሃሌ ሉያ።አሁን ነው መቃወም።
አምልኮተ ሰብእ ከምንጩ ይነቀል!
🤸🏼♂️ [1] ተአምረ ማርያም ትንሣኤ ዘጉባኤ ማተሚያ ቤት 1989 ፤ተአምር 63
🤸🏼♂️ [2] ዚኒ ከማሁ ተአምር 12
🤸🏼♂️ [3] ዚኒ ከማሁ ተአምር 12
_______________________
አምልኮተ ሰብእ ከምንጩ (2)
"እመቤቴ ሆይ አንቺ ባትወለጂ ኖሮ ማንም ጻድቅ ባልሆነ ነበር ።"(ዝክረ ቃል 2005 ዓ.ም ዘመስከረም በዓታ)
እንዲህ ያለ አይንን በጨው ያጠበ ኑፋቄ ስሰማ ጆሮ ጭው አለማለቱ የሚደንቅ ነው።የዚህ ሁሉ መንስኤ አዋልድ መጽሐፍት ናቸው ።ለእነዚህ መጻሐፍት ተቀባይነታቸው ጎልቶ እንደ መጽሐፍ ቅዱስ ልክ መቆጠራቸው "ሁሉንም አሜን" ለማለት በር የከፈተ ነው።ምንም እንኳን የቅዱሳት መጽሐፍ ቁጥር "81 ነው" ብሎ ዘርዓ ያዕቆብን ያሳወጀው ማለቂያ የሌለው የደብተራ ተረት እና ተንኮል መሆኑ በክብረ ነገስት ብመዘገብም፣ ከዚያ ጊዜም ጀምሮ በግልጽ የደብተራ ሥራው በቤቷ መኖሩ እየታወቀም ፣ ይህንን ከምንጩ ለመንቀል አሻፈረኝ ማለቷ የሚያስታዝብ ነው።በውኑ መሠረቷን አልለቀቀችምን !? ወይንም በመሠረቷ ላይ በእንጨት አልገነባችምን !? መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር እስትንፋስ ያለበት መጽሐፍ እንደሆነ ሙሁራኑ የምቀበሉት ነው ።ታዲያ ልጆች አባታቸውን መምሰል የለባቸውምን !? ከምንጩ ጋ መጋጨት አለባቸውን !?
እንደ እውነቱ ከሆነ መጽሐፍ ቅዱስ በጥንት ብቻ ሳይሆን ዛሬም በስደት ላይ ነው።ለራሱ ቤተ-እምነት እንደሚች ተደርጎ እየተበረዘ ነውና።በስውር ጥቃት።ደግሞም "91 ይሁን 81 ይሁን ፣ ልክ በሌለው መልኩ ሁሉም ቅዱስ መጽሐፍ ነው"እየተባለ ነው።መጀመሪያ ከግዑዙ ጋር ተስተካክሎ የተተረጎመው ፣አሁን ለግል ትምህርት አልመች ተብሎ እንደገና አደገኛ ጥቃት ተፈጽሞበታል ። የሚገርመው መጽሐፍ ቅዱስ ድሮ በአሕዛብ ነገስታት ይሰደዳል ዛሬ ግን 'በክርስቲያን' የሚሰደድ መጽሐፍ ነው፤ወዮ ጌታ ሆይ መጥተህ ውሰደን እባክህን።
መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር ቃል እንደሆነ ሥልጣኑን በሙሉ ካላገኘ ይህ አይነቱ ዝቅጠት ይቀጥላል እያልኩ ወደ ርዕሰ እሸጋገራለሁ። ከላይ የተቀመጠው ፣ጥርሱን ያሾለ እና አይኑን በጨው ያጠበ ኑፋቄ ፦ የደብተራ ተንኮል ነው። በማርያም መወለድ ጻድቅ እንደሆንና ያለማርያም መጽደቅ እንደማይቻል ለማስተማር ዓይኑን በጨው ያጠበ ኑፋቄ ነው።ከስር ከመሠረቱ እንተንትነው ፦
ያለ ማርያም መወለድ ማንም ጻድቅ እንደማይሆን የሚናገረው ይህ ኑፋቄ በውስጡ የእግዚአብሔርን ችሎታ በመገፋት እና ለማርያም ስጀመርም እሷ ብቁናት ለማለት የተደፈረ አሽሙር ነው።እስኪ መጻሐፍትን እናገላብጥ "ማርያም ባትወለድ" ብለን እንነሳ ።ማርያም ባትወለድ “በውኑ ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር አለን? ..”ዘፍ 18፥14 ።የለም።ሳራ ልጅ እንኳን መቋጠር የማይችለው ማህፀኗ ፣ልጅ ለመውለድ በእግዚአብሔር ችሎታ ከቻለ ፣እንዴት "ማርያም ባትወለድ ጻድቅ አንሆንም" ይባላል !? ለሳራ በራሱ ችሎታ ብቻ ካደረገ ለማርያምስ እንዴታ !?ለእኛስ እንዴት አይሰራም !?ይሰራል።
በአጭር ቋንቋ ማርያም ባትወለድም እግዚአብሔር ጻድቅ ማድረግ ይችላል።"ማርያም ባትወለድ ጻድቅ አይገኝም" የሚለው የፈጠራ ወሬ ምንጩ የስንፍና ልብ የወለደው የደብተራ ተንኮል ነው።ምክንያቱም "ማርያም በራሷ ስትፈጠር ራሱ ብቁ ናት ፤እሷ የተለየች ናት፤እናት የሆነችው ፍጹምት ጻድቅ ሆና በመገኘቷ ነው" የሚል እሳቤ የፈጠረ ትርክት ነው።እንደ እውነቱ ከሆነ ቅዱስ ያረድ ፍልሰታ ድጓ ላይ መጽሐፈ ኪዳነ ምህረት ላይ "ሥጋዋን አንጽቶ፣እርሷን ቀድሶ፣በእርሷ ላይ አደረ" ማለቱ ማርያም "በራሷ ብቁ ሆና ፣ፍጹምት ሆኖ ስለተገኘች ነው የወለደችው" የሚለውን ትርክት የሚቃወም ነው
በሌላ በኩል "ማርያም ከጥንተ አብሶ ነፃ አይደለችም"[1] ይሏል።በዚህ ደግሞ በሃሳብ እንኳን ሃጥያት ሰሪታ አታውቅም ይሏል።ስለዚህም ጥንተ አብሶ አለባት ማለት ምን ማለት እንደሆነ ማብራሪያ ጠይቄ ማለፍ መልካም ነው።ይሁንና ማርያም በራሷ ብቁ ሆና በመገኘቷ እናት እንደሆነች የሚነግረን አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል የለም።መጽሐፍ ስናገር “መልአኩም እንዲህ አላት፦ ማርያም ሆይ፥ በእግዚአብሔር ፊት ጸጋ አግኝተሻልና አትፍሪ።”ሉቃስ 1፥30 ፣ እንዲህ የሚል ነው።"ጸጋ ማለት አለዋጋ የሚሰጥ እና የሚደረግ ማለት ነው።"(ኪ.ወ.ክ መዝገበ ቃላት)።ስለዚህም ጸጋ ማለት ያለ ዋጋ የሚከፈል እና የሚደረግልን ከሆነ ፣ማርያም ምን ዋጋ ከፈለች !? ቃሉ የሚለው ጸጋ አግኝተሻል እንጂ መሥፈርት አሟልተሻል የሚል አይደለም። ስለዚህም ማርያም ራሷ እናት የሆነችው እግዚአብሔር በቸርነቱ አድሎላት እንጂ ከሌሎች ሰቶች ፍጹም ሆና በመገኘቷ አይደለም።ያረድ እንዳለው ባሪኳት እና ቀድሶ ነው እናት ያደረጋት።ከምን ቀደሳት ? ከጥንተ አብሶ።ስለዚህ የእግዚአብሔርን ቸርነት በስንፍናችሁ አታበላሹ።አምልኮተ ሰብ ከምንጩ! ይድረቅ
🤸🏻♂️ [1] የኢኦተቤክ መሠረተ ሃይማኖት እና የካህናት ተልዕኮ ገጽ 29
_________________________
አምልኮተ ሰብእ ከምንጩ (3)
ኢትዮጵያ ሃገራችን በሁሉም ነገር የታደለች ናት።የተፈጥሮ ሃብታችን ከእኛ ዓልፎ ለዓለም የሚተርፍ ነው።ግን የደሃ ደሃ ነን።በዚህ ዘመንም ቁጭ ብለን የሌሎችን ቴክኖሎጂ ማየት ብቻ ነው ሥራችን።ተክኖሎጂውን እንደው ገዝተን እንኳን ለመጠቀም አቂም የለንም።በየዓመቱ ረሃብ አለ።"በኢትዮጵያ ታርክ ኢትዮጵያ ላይ ረሃብ ሳይከሰት በሃረብ ሰው ሳይመታ የታለፈ ዓመት የለም"።ሁለም በየዓመቱ ረሃብ አለ።ይህ ሁሉ የእርግማን ምንጭ የደብተራ ሥራ ነው።ለራሱ አያድግም ፤የሚሰሩትን አይለውጥም ፤ቅጠል ስበጠብጥ ይኖራል።ሁላችንም ወደ ቃሉ ብንመለስ ፣ይህንን ጠንቁልና ተቋውመን ብንታገል ፣ ዜናችን ከዘይት ወጥቶ አድስ ነገረ ተፈጠረ ይሆን ነበር።እንጠቀምም ነበር።ምን ይፈይዳል ስማችን ሳይቀየር ከረሃብ ሳንወጣ ቅድስት ቅድስት ማለት ? ችግርን ደብቀን መፍትሔ አናገኝ ነገር። ስለዚህም የእግዚአብሔርን የእጁ በረከት ለመቀበል ሃገር በቀል የደብተራ ክርስቲና ሳይሆን እግዚአብሔር በልጁ በኢየሱስ ያቋቋመውን ክርስቲና እንቀበል ።እንደ ቃሉ።እንዲያ ብሆን እኛም ሁለም እንደሰት ነበር ፤ ስደትም ያበቃ ነበር። እያልኩ ወደ ዛሬው "የደብተራ ሥራው ከምንጩ ይነቀል" ጹሑፌ እገባለሁ ።እነሆ ፦
".ስለ አንቺም ከምድር ወደ አርያም ወደ መንግሥተ ሰማያት የቀረብን ሆንን ።በአንቺና በልጅሽ ስም የቀረብን ሆን " (አንቀጸ ብርሃን ዘያሬድ )
እንግዲህ ተመልከቱ ልብን ያደነደነ ጆሮውን እውነትን ከመስማት የከለከለው ይህ ነው።አራተም ፣ሺህ ጊዜም ፣ዕድሜ ልክም "ኢየሱስ ያድናል ማለት ክህደት ነው" ስሉ የማይሰቀጥጠው ለዚህ ነው።በኃላው የተሰለፉ ጋነኖች እንዳሉ ግልጽ ነው።
ብዙ ግዜ "አዋልድ መጻሐፍት አንቀበልም ይላሉ" ይሉናል ፤አዕምሮ ለማደንዘዝ ፤ ልዩነትን ለመስበክ።ለዚህ ኑፋቄ ምንጭም የክርስቶስ የቃሉ ፍቅር ሳይሆን ጥላቻ ነው።የልዩነት ፣ የመከፋፈል መንፈስ ነው።አንድ መጽሐፍ ቅዱስ ይዘን መንጋው አንድ እንዳይሆኑ ፣ለሆዳቸው የተጉት የጥልቁ ሠራውቶች ናቸው ።የተባለው ተብሎ መጽሐፍ ቅዱስን የሚመስሉ የተኛውንም መጽሐፍ ለምክር ለትምህርት እንቀበላለን እንጠቀማለን ።ግን "እንደ መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር እስትንፋስ የሆነ መጽሐፍ ነው፣ ስህተት የለበትም ፣ አይታረምም ብለን አናምንም ነው" ያልነው ።እናም ልዩነትን የሚያጎላ ሳይሆን በክርስቶስ ከዓለም ተለይተው የወጡትን አንድ የሚያደርግ ፣ አንድ መንፈስ እንድኖር የሚያደርገውን ፣የእግዚአብሔርን አፍ ከሆነው ቃሉ ጋር የማይጋጨውን እንቀበላለን ።መዝነን።ምክንያቱም የሰው ሃሳቦች በአልድ መጻሕፍት ላይ አሉ።
ከላይ ያለው ኑፋቄ ከምንጩ ስናጠና የቤቷ ትምህርት በደብተራዎች መበረዙ በግልጽ ይታያል።ልክ እኛ ወንጌላውያን አሁን መንፈሳዊ ቀውስ ውስጥ እንደገባነው[የቃል እምነት ኑፋቄ እና ሃሰተኛ ነቢያት ሕዝቡን ቀፎ እንዳደረጉት ነው]። ተሃድሶ(መመለስ) ለሁላችንም ነው።የሕይወት ልዩነት እጅግ በጣም ትንሽ ነው።በኢኦተቤክ አባላቱ ሰው ስታመም ከጸበል ወደ ጸበል ቦታ እንጂ የግል ጸሎት አይታሰብም፤አንደኛው ጸበል ቦታ ከሌላኛው የሚበልጥ ተደርጎ ይቆጠራልና ፤እግዚአብሔር የሚሰማ አይመስልም።በወንጌላውያን መካከልም ብሽቅ ከሆነው የሚጠቀሰው ልክ እንደ ጸበል ቦታ ወደ ጸበል ቦታ መሮጡ ከነቢይ ወደ ነቢይ መሮጡ እና የግል ጸሎት በአባት ፊት መንበርከክ በአብዛኛው ሕዝብ አለመኖሩ ተመሳሳይ ያደርጋል ። ምናልባት የሰፋ ልዩነት ብንል በመጽሐፍ ተጽፎ ድጋፍ በወንጌላውያን በኩል አለመሰጠቱ ይሆናል፤የደብተራው መጽሐፍ ግን የኢኦተቤክ ገንዘቧ ነው።
በነገራችን ላይ ተሃድሶ ስባል ለተዋህዶ ብቻ ብለው የተነሱ አድርገው ይቆጥራሉ ።አዎ በተዋሕዶ ላይ ብቻ 365 ቀን የሚሰሩ አሉ።ያ ማለት ግን ተሃድሶ ለተዋህዶ እንጂ ለወንጌላዊያን አያስፈልግም ማለት አይደለም ።ተሃድሶ ለእኔ ነው።ከራስ ነው።ለሁሉም ነው።ሁለም ነው።እንደ ቃሉም ነው፤አብረን የምንጠረብም ነን ።
የቤቷ ትምህርት ድብልቅልቅ ያለ ነው እስኪ ሌላኛው አዋልድ መጻሕፍቷ ምን እንደሚል እንመልከተው ፦
"ወደ እርሱ አቀረበን ያለው ርቀን መኖራችንን ያስረዳል የሰው ባህሪይ ከእግዚአብሔር ተለይቶ ነበረና በደጋጎች አበው በነቢያት በኦሪት ከእርሱ አስቀድሞ በነበረው ዘመን ሁሉ አዳምም ከበደለ ጀምሮ ከእነዚህ ሁሉ ወደ እርሱ ሊያቀርበን ማንም ማን አልቻለም[1]።"
ይህ ሃይማኖተ አበው የሚባለው መጽሐፏ በዚህ ክፍል መሠረት "ማንም ወደ እርሱ ሊያቀርበን አልቻለም" በማለት በኢየሱስ ክርስቶስ ብቻና ብቻ ወደ አብ መቅረባችንን ፊንትው አድርጎ ይገልጽልናል ።በሌላ ስፍራም ፦
"ከእርሱ በቀር ራሱ ብቻውን ኀጢአት ማስተስረይ የሚቻለው የታመነ አስታራቂ ማነው? ለማስታረቅ ኀጢአትንም ለማስተስረይ ያቀረበው መሥዋዕትስ ምንድን ነው ? መሥዋዕት ለመሆን የነሣው ሥጋ ብቻ ነው እንጂ " [2] በማለት ይገልጽልናል ።
ከዚህ ክፍል ጸሓፍ ጋር በመተባበር ጥያቄ አቀርባለሁ [ወደ እግዚአብሔር የቀረብነው በእርቅ እስከሆነ ድረስ]።ስለዚህም ከእግዚአብሔር ጋር ያስታረቀው ማነው ? ማርያም ካስታረቀች ያቀረበችው መስዋዕት ምንድነው ? መቼ እና የት አቀረበች ? ምስክር አላትን ? እንደ ምኝ ሰው እጠይቃለሁ እንጂ ማርያም አይደለም ለማስታረቅ ፣ መስዋዕት ለማቅረብም የበቃች አይደለችም ።
ስለዚህም ከእግዚአብሔር ጋር እርቁ የሚፈጸመው በመስዋዕት ነው።ማርያም መስዋዕት ለመሆን ቀርቶ እንደ ሕጋቸው እንኳን መስዋዕት ማቅረብ አትችልም[ለሴት ልጅ አይፈቀድም]።ስለዚህም በማርያም አልቀረብንም ፤በማርያም በኩልም አልታረቅንም እያልኩ የደብተራ ሥራውን በመቃወም የመጽሐፍ ቅዱስ ማስረጃ አቀርባለሁ ።እንደሚከተለው ፦
“ጠላቶች ሳለን ከእግዚአብሔር ጋር በልጁ ሞት ከታረቅን፥ ይልቁንም ከታረቅን በኋላ በሕይወቱ እንድናለን፤”ሮሜ 5፥10 ።እርቁን ያገኘነው በኢየሱስ ሞት ነው።ስለዚህም ሕይወቱን ስለእኛ በመስጠቱ የዘላለም ሕይወት በእርሱ አገኘን ።ስለዚህም እርሱ በሰራው ሥራ “በኢየሱስ ክርስቶስም በሆነው ቤዛነት በኩል እንዲያው በጸጋው ይጸድቃሉ።” ሮሜ 3፥24።
ደግሞም መጽሐፍ ስናገር እንዲህ ይላል ፦
ኤፌሶን 2 ፥ ¹⁴-¹⁵ እርሱ ሰላማችን ነውና፤ ሁለቱን ያዋሐደ በአዋጅ የተነገሩትንም የትእዛዛትን ሕግ ሽሮ በመካከል ያለውን የጥል ግድግዳን በሥጋው ያፈረሰ፤ ይህም ከሁለታቸው አንድን አዲስን ሰው በራሱ ይፈጥር ዘንድ ሰላምንም ያደርግ ዘንድ፥ ¹⁶ ጥልንም በመስቀሉ ገድሎ በእርሱ ሁለታቸውን በአንድ አካል ከእግዚአብሔር ጋር ያስታርቅ ዘንድ ነው። ¹⁷ መጥቶም ርቃችሁ ለነበራችሁ ለእናንተ ሰላምን፥ ቀርበው ለነበሩትም ሰላምን የምስራች ብሎ ሰበከ፤ ¹⁸ በእርሱ ሥራ ሁላችን በአንድ መንፈስ ወደ አብ መግባት አለንና።
አንደ ጌዜ ብቻ አይደለም በክርስቶስ የሚንቀርበው ፣እስከመጨረሻው በክርስቶስ በኩል ወደ እግዚአብሔር እንገባለን።“በዘመን ፍጻሜ ይደረግ ዘንድ ያለው አሳቡም በሰማይና በምድር ያለውን ሁሉ በክርስቶስ ለመጠቅለል ነው።”ኤፌ 1፥10 እንደሚል። ሃሌ ሉያ ላቀረበን።ለብቸኛው አቅራቢያችን።
[1]ሃይማኖት አበው ት.ዘጉባኤ.ማተሚያ ቤት ፣ም.66 ቁ.17 ፣1989 ዕትም
[2]ዝኒ ከማሁ ም.62 ቁ.14
_____________________________
አምልኮተ ሰብእ ከምንጩ (4)
"ኢየሱስ ያድናል ማለት ክህደት ነው" ብለው በሕዝብ ፊት የእግዚአብሔር ቃል እንደሚናገር ፣በቃሉ ላይ ሊቅ መሆኑን ለማሳያት መራቀቁን በዚህ መልኩ መግለጹ የሚደንቅ ነው።ደግሞም ሳይሸማቀቅ በሚዲያ ልክ እንደ ወንጌል ሰባክ ደረቱን ነፍቶ ፣በክህደት ባበጠ ልብ መከሰቱ አጀብ የሚያስብል ነው።ሳያፍር ሳይደነግጥ በሺህዎች ፊት የሆነውን ፎቶ መልቀቁን ስመለከት ፦
“እንግዲህ በነቢዩ በዳንኤል የተባለውን የጥፋትን ርኩሰት በተቀደሰችው ስፍራ ቆሞ ስታዩ፥ አንባቢው ያስተውል፥”ማቴ 24፥15 የሚለው የእግዚአብሔር ቃል በጆሮዬ ይመላለስብኛል።
እንዴት ያለ መታወር ነው? በእውኑ የማያምኑትን ኢየሱስ አያድናቸውምን ? ያመኑትን እስከመጨረሻው ከምንም እየጠበቀ አያድናቸውምን !? ይህንን የሰበከ ልብ ምኑን ተማምኖ እንደሆነ ለማሳየት "ኑፋቄው ከምንጩ ይነቀል" ጹሑፌ ክፍል አራት ብሎ መጀመሩ ነው።እነሆ ቀርቧል፦
"..መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ኃጥዑን በፊቱ አቁሞ የበቀሉን ፍርድ በገለጠ ጊዜ በኃጥዐን ፊት ላይ በቃል ኪዳን ቀለም የተጻፈ 'የድንግልን ስም' ሲጠራ ሰምቶ የአደባባዩን ፍርድ ትቶ በቸርነቱ በኀጥአን መፍረድን ይተዋል "[1]
'ሊቃውንቱ እና ዘማሪው' በዚህ ድርሳንም ተማምኖ እንደሆነም ግልጽ ነው።ሳይቀጥጣቸው "ኢየሱስ ያድናል አይባልም" ለማለት የደረሱት ለዚያ ነው።ይህ ከላይ ያለው ድርሳን የእውነት ከሆነ በኢየሱስ ማመን እና ለስሙ መዘመር እኮ አያስፈልግም ።ደግነቱ ምንጩ ዲያብሎስ መሆኑ ነው።እንደሚትመለከቱት የማርያም ስም በዕለተ ምጽአት ቀን (በጌታ ፍርድ ቀን) ከተጠራ ፣ኢየሱስ ክርስቶስ ፍርዱን እንደሚተው የሚነግረን የፈጠራ "በሬ ወለደ" የሆነ የዲያብሎስ ወሬ ነው።
ስለ እለተ ምጽአት ካነሳን አይቀር እኛ እንደ ቃሉ የሚናምነው "በዚያ ቀን ፍርድ እንጂ እርቅ የለም" ብለን እናምናለን ።ምናልባት እንደዚህ ስለሚያምኑ ይሆናል "ኢየሱስ አሁን በደሙ እያስታረቀ ነው" ስንል ፣ "በእለተ ምጽአትም ያስታርቃል ይላሉ" ብለው እኛን የሚያስቡት።ግን ምልጃ ብሎ ነገር በፍርድ ቀን የለም።እንደስሙም የፍርድ ቀን ነው፤ "ፍርድ ብቻ ነው ያለው" እንላለን ።ምክንያቱም ቃሉ ፥
“የሰው ልጅ ከመላእክቱ ጋር በአባቱ ክብር ይመጣ ዘንድ አለውና፤ ያን ጊዜም ለሁሉ እንደ ሥራው ያስረክበዋል።”ማቴ 16፥27 ፣ ነው የሚለን ።
"ለሁሉም እንደ ሥራው ያስረክባል" ማለት የሚገባውን መስጠትን እንጂ በማንም በምንም የሚቀየር እና የሚቀር ፍርድ አለመኖሩን የሚያሳይ ነው ። ይህ የዲያብሎስ ማስታወሻ የሆነ ትምህርት ለኢትዮጵያ እድገት ማነቆ እና እርግማን ነው።
በተጨማሪም መገንዘብ ያለብን ጉዳይ "በዚያ ቀን ምልጃ አለ" ብሎ ማሰብ የእውነትም የሚያሳዝን ነው።በዚያ ቀን ግን መረከብ እንጂ ምልጃ የለም።ስለሆነም "ምልጃ አለ" ብለው የሚያምኑትን "በማን ነው ምልጃው ያለው?"ብትሉ ፣ የአንበሳውን ድርሻ የሚትወስደዋ የአዋልድ መጻሕፍት ማርያም ናት ።የአዋልድ መጻሕፍት ማርያም በፍርድ ቀን በእግዚአብሔር ቀኝ እንደሚትቆም ይታመናል ።ይህ ወሬ በማርያም ብቻ አይበቃም፤በማርያም እናት ተብላ ለሚትነገረዋም ለሐናም ነው።ስለዚህም ሁለት ፉጡር አገኘን ማለት ነው በቀኙ ከሚቆሙትንi ፤ምናልባት እኔ አላየሁም ይሆናል እንጂ ሌላ ፉጡርም ይኖር ይሆናል ።እኛ ግን አሁን በእጃችን ካሉ እና ካየናቸው መጻሕፍት ማስረጃ አድርገን እንቀጥል ።
በእግዚአብሔር ቀኝ ትቆማለች የሚባለው አስተምህሮ ፍጹም ስህተት ነው።ምክንያቱም "በቀኝ በኩል ያሉቱ" ብባል ከሌሎች ቅዱሳን ጋር መሰለፏን እንረዳለን ፤በእኩል።ግን ልክ ክርስቶስ በእግዚአብሔር ቀኝ እንደተቀመጠ ፣ እሷም ደግሞ በእግዚአብሔር ቀኝ ቆማለች መባሉ ቀላል ነገር አይደለም ። የቃል እምነት ኑፋቄአዊያን እግዚአብሔር ልክ እንደ እኛ ፊት እና ጀርባ ያለው ፣ ዓይን እና ጆሮ ያለው ፣ ቀኝ እና ግራ ያለው አድርገው ያስተምራሉ እንድሁም በቁመትም ከእኛ ጋር እኩል እንደሆነም ይነግሩናል ይከትባሉ።ልክ እንደዚያ ነው ።
በእግዚአብሔር ቀኝ ትቆማለች ኑፋቄው ለእግዚአብሔር ቀኝ እና ግራ በመስጠቱ እግዚአብሔር መንፈስ መሆኑን የሚክድ ነው።እግዚአብሔር መንፈስ ነው።ቀኝም ግራም የለውም።እናም ክርስቶስ "በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀመጠ" ስባል "ሥልጣን አለው" እንደሚንል ነው።በራሱ እኮ "ማርያምም በኢየሱስ ቀኝ ቆማለች" መባሉ ሥልጣን አላት ፣ታስምራለች ለማለት ነው።ከላይ እንዳየነው።ለኀጥዐን ስሟ ስለተጠራ ብቻ ፍርድን የሚታስቀር ፍርደ ገምድል የሆነች ናት።ይህች 'ማርያም' የመጽሐፍ ቅዱሷ ማርያም አይደለችም። ምክንያቱም የመጽሐፍ ቅዱሷ ማርያም የእግዚአብሔር ባህሪ ተካፋይ ናት።ብፅዕት ናት።እግዚአብሔር ሃጥአትን ይቀጣል ልጁን እስከመቅጣት።ስለዚህም የእርሱ የሆኑቱም ሁሉም ከኀጥአት ጋር አይተባበሩም።ይህ ወሬ ኢየሱስ ክርስቶስን ክፉ በማድረግ ፣ሰዎችን በአዋልዷ ማርያም እግር ስሪ የሚጥል ነው።ምክንያቱም እሷ ፍርድ ታዛባለች፤ለወንበዴዎች ታደላለች፤የወንበዴዎችን ዋሻ ነች፤እንዴ ደብተራ ትምህርት ።
እንዲህ ያለ ወሬ ለመስማት ጆሮክ "እህህ" ይበል እንጂ ይቀጥላል ።ማለቂያ የለውም።የደብተራው ተንኮል የኢየሱስን እናት ማርያም በቀኝ ቆማ ፍርድ ማዛባቷን ብቻ ሳይሆን ሐና ራሷ በቀኙ መቆሟን በመጽሐፋቸው ስገልጹ እንዲህ ብለዋል ፦
"ብፅዕት ሐናን በክብር በገናናነት የሰማይና የምድር ንግሥት በሆነች በተባረከች ልጇ ቀኝ ቁማ ባየዋት ጊዜም .." [2]
የተኛውም አካል በሥልጣኑ ፅድቅ የሆነውን ፍርድ እንደ በደል እና ክፉ በማስቆጠር፣ እግዚአብሔርን ከሰዎች ልብ ላይ አስጠቁሮ ፣ሰዎቹን አዛኝ እና ማሪ ማድረጉ ለተንኮል ነው።የደብተራ ሥራው ነው።የእግዚአብሔር ፍርድ እኮ ጽድቅ ነው።ሃሌ ሉያ።መጽሐፍ ስናገር በፍርድ ቀን ፦
ማቴዎስ 25፥ ³⁴ ንጉሡም በቀኙ ያሉትን እንዲህ ይላቸዋል፦ እናንተ የአባቴ ቡሩካን፥ ኑ፤ ዓለም ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ የተዘጋጀላችሁን መንግሥት ውረሱ።… ⁴¹ በዚያን ጊዜ በግራው ያሉትን ደግሞ ይላቸዋል፦ እናንተ ርጉማን፥ ለሰይጣንና ለመላእክቱ ወደ ተዘጋጀ ወደ ዘላለም እሳት ከእኔ ሂዱ።
በግራውም በቀኙ ያሉትን "የሚገባቸውን ቦታ ሂዱ" በማለት ይፈርዳል እንጂ ማንም ፍርድ አያዛባም፤ምልጃም እርቅም በዚያ ቀን የለም።ያለው አንድ ነው "ሂዱ" ነው።አይደለም የአዋልዷ ማርያም እና እናቷ ቀርቶ ሁሉም አዋልድ ዱቁሳን በቀኙ ብግደረደሩም ፍርድ አይዛባም።ፍርዱ ትክክል ለማንም ሰው ፊት የማያዳላ ነው።እግዚአብሔር በሥራው ትክክል ነው።ሃሌ ሉያ።
በእውኑ የኢየሱስ እናት ብፅዕት ማርያም ከአዋልዷ ማርያም ትለያለችን ? አዎን።እንደሚከተለው ከቅዱሱ ቃሉ ቀርቧል፦
ሉቃስ 1 ፥ ⁵¹ በክንዱ ኃይል አድርጎአል፤ ትዕቢተኞችን በልባቸው አሳብ በትኖአል፤ ⁵² ገዥዎችን ከዙፋናቸው አዋርዶአል፤ ትሑታንንም ከፍ አድርጎአል፤ ⁵³ የተራቡትን በበጎ ነገር አጥግቦአል፤ ባለ ጠጎችንም ባዶአቸውን ሰዶአቸዋል።
ስለዚህም እውነተኛው የኢየሱስ እናት የመጽሐፍ ቅዱሷ ማርያም የኃጥዐን ልብ በመበተኑ የተደሰተች፣ ዝቅ ያሉትን ክፍ በማድረጉ በፍርዱም ደስ ያላት፣ በዝባዦችን በማራቆቱ ሐሴት ያደረገች በፍርዱ የሚትጽናና ትሁት ሴት ነች።የተባረከች ናትና።
በመጨረሻም አይደለም ማርያም ኢየሱስ ራሱ አሁን በሕይወተ ሥጋ እያሉ የደከሙትን ለማንሳት እና ምህረት ለመስጠት ሥልጣን አለው እንጂ ከሞት በኃላ "ምህረት ይሰጣል ያሰጣል" የሚል አስተምህሮ የለንም።እንዲያ ያለው ወሬ የደብተራ ተንኮል ነው፤ የመቀየጥ ሥራ ነው፤ሥራው ከመሠረቱ ይነቀል በኢየሱስ ስም ።
🤸🏻♂️[1] ድርሳነ.ኪ.ምህረት ገጽ 26፣2010 ዓ.ም ት.ማተሚያ ቤት
🤸🏻♂️[2]መ.ተስፋ ሚካኤል ታከለ(ትርጓሚ)፣ድርሳነ ኢያቄም ወሐና ዘረቡዕ፣2007፣ቁ.7 ገጽ 46
______________________
አምልኮተ ሰብእ ከምንጩ (5)
እስካሁን ለማሳየት የጣርኩት ከስሪ ከመሠረቱ በመስሪው በዲያብሎስ የተተከለ መርዝ መኖሩን እንድትገነዘቡ ነው።በእውነቱ እነዚህ አዋልድ መጻሕፍት የኢኦተቤክ መጻሕፍት እስከሆኑ ድረስ "ከደሙ ንፁህ ነኝ" ማለት እመቤት ስንዱ ትችላለችን !? ባለፈዉ ሳምንታት ሊቀ ጠበብት ዶክተር ዘሪሁን ሙላቱ "ጸረ ደብተራ ንቅናቄ" ጹሑፍ ስያስነብብ ነበር ። እጅግ በጨከነ ልብ ብዙ ስድብ እየገረፈበት።እናም በዚህ ጹሑፍ ላይ ክብረ ነገሥት የደብተራ ጹሑፍ እንደሆነ መዝኖ "ቻው" ብሎታል።ሌሎችም ሊቃውንት ለሕዝቡ እውነቱን እንዲያሳውቁ አብዝቶ ይጮህ ነበር።ምናልባት የጹሑፍን ፍሬ እናይ ይሆናል ።ይህ "ክፍል አምስት የደብተራ ሥራው ከምንጩ ይነቀል" ጹሑፌ ነው። መልካም ምንባብ ፦
".በሐናና በኢያቄም ጸጋና ጽድቅ ተሰጠን ።በሰማይም ቢሆን በምድርም ቢሆን እንደ እርሷ ያለ አልነበረም "[1]
ጽድቅ ማለት እውነት ርግጥ.. ማለት ነው።[2] ሙሴ ከጾም በኃላ ለእስራኤላውያን ሁለት የድንጋይ ሰሌዳ በእጁ ይዞ መጣ ዘፀ 24።ሁሉቱ የድንጋይ ሰሌዳዎች ሕግ የተጻፈባቸው ናቸው ። እናም የእኛ ግንኙነትም ከሕጉ እንጂ ከድንጋዩ አይደለም ።ምክንያቱም ሁለት ድንጋይ ተሰጠን ሳይሆን ሕግ ተሰጠን ነው የተባልነው ። ይህ ሕግ ለእስራኤላውያን ብቻ የተሰጠ የቃል ክዳን ሕግ ነው ።ይህንን ሕግ ከእስራኤላውያን ውጭ የሚጠቀሙት የሉም።ምናልባትም "እኛም ይህንን ሕግ ተሰቶናል እንጠቀማለን" የሚል ብኖር ፦ "ዓላማው ምንድነው !?" የሚለውን መጠየቅ ተገብ ነው። ምክንያቱም ለእስራኤላውያን ሕጉ ስሰጥ የራሱ ዓላማ እና ውል አለው ።መጽሐፍ ስናገር ፦
“.. ሕግ በሙሴ ተሰጥቶ ነበርና፤”ዮሐ 1፥16 እንደሚል ሕጉ በሙሴ ተሰጠ። "ለማን ተሰጠ ?" ብንል ፦
“እነርሱ እስራኤላውያን ናቸውና፥ ልጅነትና ክብር ኪዳንም የሕግም መሰጠት የመቅደስም ሥርዓት የተስፋውም ቃላት ለእነርሱ ናቸውና፤”ሮሜ 9፥4 የሚል ነው።
ስለዚህም ይህ ሁሉ በሙሴ በኩል ለእስራኤላውያን ብቻ ተሰጠ። ደግሞም ፦
“ጸጋና እውነት ግን በኢየሱስ ክርስቶስ ሆነ።” ዮሐ 1፥17
አሁን አስተውሉ ቅዱሱን ቃሉን በግልጥ አዋልድ መጻሕፍቷ ስቃወሙ የቤቷ ዝምታ ይገርማል ። በእውነቱ እኔ በበኩሌ "ደብተራ በርዝል" ብዬ ባምንም ፣ ቤቷ ግን ራሷ "አንቀበልም" እስካላሉ ድረስ ከደብተራዎች ለይቼ አላያትም።በእውነት ይህንን የሚለው በጣም እያዘንኩ እና በድፍረት ነው።ዶክተር ዘሪሁን እንደ ተቃወመ በግልጽ የኢኦተቤክ ይህንን መጽሐፍ እና መሰሎቹን እስካልወገዘች ድረስ "የደብተራዎች ዋሻ እና የሕዝብ እርግማን ምንጭ ናት" ብዬ ሳልሳቀቅ አወራለሁ ። አንዳንድ ጎበዛዝቱንም ይህንን እስካልተቃወሙ ድረስ የዶብተራ ልጅ ጠንቋይ አርገ እንጂ ለየቼ አላያቸውም።እንደ ክርስቲያንም አልቆጥርም ።ይህንን የሚደግፉ ሰዎች ጋር በኮሜንት ይሁን በድምፅ ሳወራ ከጠንቋይ ጋር እንደ ማወራ ነው የሚቆጥረው ።
እናም ወዳጆቼ "ሃሰተኛ ክርስቶስ ይነሳል" ስባል ሃሰተኛውን የምናውቀው "የክርስቶስን ሥራ" ለራሳቸው በማድረጋቸው ነው።ስለዚህም ይህ የደብተራ ሥራ ይህችን ሐና የሚትባውን የፈጠራ ሴትን 'ክርስቶስ አደረጋት' ።ምክንያቱም ጸጋና ጽድቅ በኢየሱስ እንጂ በሌላ በማንም በምንም አልሆነም ።አይሆንምም ።ስለዚህም ይህ ዓይንን በጨው ያጠበ የጠንቋይ ሥራ ነው። ማን ለቃሉ እስከ መጨረሻው እንደሚወግን አሁን እናያለን ።ክርስቶስ ወይ ደብተራ !? መጽሐፍ ቅዱስ ወይ የድበተራ ወሬ !? ለየትኛው እንደምናስቀድም በውስጣችሁ ያለው ሃሳብ ምስክር ነው።የማን ልጅ እንደሆናችሁም ምስክር ነው።
በሕያው እግዚአብሔር ፊት እምላለሁ ጸጋና እውነት በሁለት አካል አልሆነም ።የሆነው በአንዱ ብቻ ነው።በክርስቶስ ብቻ ሆነ።ልንቀበል ብንወድ ጌታ በሐዋርያቱ በተደጋጋሚ ጸጋና እውነት በክርስቶስ መሆኑን ስያስመሰክር ነበር።ተመልከቱ ፦
“አሁን ግን በሕግና በነቢያት የተመሰከረለት የእግዚአብሔር ጽድቅ ያለ ሕግ ተገልጦአል፥” ሮሜ 3፥21
ስለዚህም መጽሐፍ የሚያውቀው ሕጉም ነቢያቱም የመሰከሩለት ጽድቅ በሐና በኩል የመጣ አይደለም ።በጭራሽ።ምክንያቱም የእግዚአብሔር ጽድቅ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።ሃሌ ሉያ።ይህ እውነት ያሳርፈን ።ሌላ አንጨምር ።ምክንያቱም በክርስቶስ የተገለጠው ጸጋ ሰዎችን ሁሉን የሚያድን ነው።መጽሐፍ እንደሚል ፦
“ሰዎችን ሁሉ የሚያድን የእግዚአብሔር ጸጋ ተገልጦአልና፤”ቲቶ 2፥11
ይህ በቂ ነው።ከበቂም በላይ ነው።በኢየሱስ ክርስቶስ ማረፍ ይሁንልን ። የጠንቋይ ልጅ እና ተከታይ ሆናችሁ አትሞቱ የሞት ሞትን ። ካልተቃወማችሁ በምን እናውቃለን !? ልዩነት የለምና።ክርስቲና መለየት ነው። መጽሐፍ ፦
“ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ እርሱም መቀደሳችሁ ነውና፤”1ኛ ተሰ 4፥3 እንደሚል።
ተቀደሱ ፤ተለዩ፤ኮንኑ።አትተባበሩ ።ልዩነትን ማየት እናፍቃለሁ ከጎበዛዝቱ።የድብተራ ሥራ ከሥሩ ይነቀል።
በመጨረሻም የዘማሪው እና የሊቃውንቱ መርዝ ምንጩ ይህም ነው እላለሁ።ምንጩን እናፍርስ።አሜን በኢየሱስ ስም ።ቃሉ ፦
“የሰውንም አሳብ በእግዚአብሔርም እውቀት ላይ የሚነሣውን ከፍ ያለውን ነገር ሁሉ እናፈርሳለን ለክርስቶስም ለመታዘዝ አእምሮን ሁሉ እንማርካለን፥”2ኛ ቆሮ 10፥5 እንደሚል ፦ እናፈርሳለን በክርስቶስ ኀይል። እኔም እመለከተው ይሆናል የደብተራ መርዝ ስወገዝ።
[1]መ.ተስፋ ሚካኤል ታከለ(ትርጓሚ)፣ድርሳነ ኢያቄም ወሐና ዘሰኑይ፣2007፣ቁ.3 ገጽ 3።
[2] ኪ.ወ.ክፍሌ መዝገበ ቃላት
_______________________________
አምልኮተ ሰብእ ከምንጩ (5)
ቅዱሱን መጽሐፍ ታነባላችሁን !? በእውኑ ይህንን እንዴት አያችሁት ? ፦ “ይህም ድንቅ አይደለም፤ ሰይጣን ራሱ የብርሃንን መልአክ እንዲመስል ራሱን ይለውጣልና።”2ኛ ቆሮ 11፥14
ጳውሎስ "ድንቅ አይደለም፤አይገርምም" ይለናል ።ምክንያቱም ጳውሎስ የሰይጣን ሽንገላ ለመቃወም እንድቻለሁ ቃሉን የታጠቀ ሰው ነው ። ስለዚህም "አይገርምም" ይለናል ።ለእኛ ግን ትንግርት ነው።ተለባብሶ ፣ ተግጦ ፣ተውቦ ለዚያውም ቅዱስን ቃሉን በእጁ ከፍ አድርጎ ጨብጦ ፣ ከውጭ ብርሃን ፣ ያማረ ፥ ግን ከውስጥ ጨለማ ፣ከአፉ የሚወጣው መረን፣መርዝ ፣ እርኩሰት የሆነ ነው።
ወዳጆቼ ሰይጣን መንፈስ ነው።አይታይም።የሰይጣን ቀለም ጥቁርም ነጭም አይደለም ።ስለዚህም በግብረ አበሮቹ ይገለጣል ። ልክ እንደዚህ ።እናም ወዳጆቼ የእውነትም ብርሃን የሆነ መላአክ የሚመስል አትጠብቁ።ንቁ።ይህ ነው ባላጋራው።ተጠንቀቁ ። ስለዚህም ከውጭ ባለው ነገር ሳንታለል ፣ከውስጥ "ከሆዱ የሚወጣውን ተመልከቱ! ስሙ!" እያልኩ ሳላስብ ቁጥር ስድስት የደረሰውን "የደብተራ ሥራው ከምንጩ ይነቀል" ጹሔፈን አቀርባለሁ ።እነሆ ተሳንድቷል ሙኩት ሙኩቱን ፦
"በተክለሃይማኖት አጥንት ቦታ ቁርባን የተቀበለ በእውነት ሲኦልን አያይም."[1]
በሌላ ቦታ የተቀበለስ !? እነኚ እና መሰሎቹ 'ሊቃውንት' ከምንጩ ከደብተራ ሥራ ተቀድተው እንደሆነ አያጠራጥርም ።ይህ ገድል በተክለሃይማኖት አጥንት ቦታ ቁርባን የተቀበለ የዘላለም ሕይወት እንደሚያገኝ ያብሰራል።አጀብ ነው።እናም እነኚ ሰዎች በዚህ ገደልም ተማምነው እንደሆነም አያጠራጥርም ።በእውኑ ይህ አጥንት ቦታ የክርስቶስ ደም የዘላለም ሕይወት ለመስጠት ስላልበቃ የተጨመረው ነው!? ወይንም የክርስቶስ ደም ከኃጢአት ሁሉ አያነጻምን !? ብቻውን ደሙ በቂ እና ከበቂ በላይ አይደለምን !? የኢየሱስ ደም ከአጥንት ስፍራ ጋር ተደምሮ ይሰራልን !? ይህ መታወር አይደለምን !?
መጽሐፍ ስናገር እንዲህ ይላል፦ "ወደ ጥፋት የሚወስደው መንገድ ሰፊ ነው" እንደሚል ፣ የእነኚ ሰዎችም መንገድ እንደዛ ነው።ምንም እንኳን በአጥንቱ ስፍራ ቁርባን ለመውሰድ ባይደርስ ሌላ አልጋ በአልጋ የሆነ 'ድንቅ መንገድ አለi' ። ከሰፊው ከጥፋት መንገዶች ከሚጠቀሰው መካከል አንዱ "የገደል መጽሐፋቸውን በአግባቡ መጻፍ እና መያዝም ነው"።እንያ ፦
"..የሐናን ዜና የምትናገር ይህችን መጽሐፍ የጻፈውን በብዙ ትጋት ንቃት ያስጻፈውን ሰው ስም ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስ በማይናወጥ በማይወድቅ የወርቅ ዐምድ በሚያበራና በሚያንጸባርቅ በወርቅ ቀለም ስሙን ይጻም"[2]
እንዲህ የገድል ወይንም የድርሳን መጻሕፍትን "በአግባቡ የያዘ ዋጋ አለው ፣የዘላለም ሕይወት ያገኛል" የሚሉት ጹሑፎች በብዙ ገድላት አሉ [በላሊበላ ገድል፣በተክለሃይማኖት ..ወዘተ)። እናም ወዳጆቼ ይህ ትምህርት እንደሚነግረን ከሆነ አንድ ሰው የአንዱን ሰው መጽሐፍ በእጁ ብኖረው ፣ በትክክል ብይዝ ፣ ምናልባት ብያስጽፍ ብጽፍ፣ "በዘላለም ሕይወት መዝገበ መጽሐፍ እንደሚጻፍ" የሚነግረን ከንቱ ተስፋ ነው።ስለዚህም ምናልባትም እነኚ ኑፋቄአዊያን ከምንጩ በዚህም ተማምኖም እንደሆነም አልጠራጠርም።ከምንጩ ይንቀል!።ወንጌሉ ቦታውን ይረከብ።
በውኑ የጥፋት ደጅ አልጋ ባልጋ የሆነ መንገድ በዚህ ብቻ ያበቃልን !? አንድ ውሸት እንጨምርና ከድርሳነ ሚካኤል እንያ ፦
<< በሚካኤል ቀን ለቤተ ክርስቲያን ዕጣን የሰጠ፣ በሚካኤል ስም የተራበ ያበላ የተጠማ ያጠጣ፣
በሚካኤል ስም የታረዘ ያለበሰ፣
በሚካኤል ስም የታመመውን የጎበኘ፣
ስለ ሚካኤል ስም እስረኛን የጠየቀ ገሃነም አያይም >> [3]
አሁን ተመልከቱ ሰይጣን እንዴት እንደሚሰራ ፣ቃሉን እንዴት እንደሚያዛባ ፣ ከመሠረቱ በሚካኤል ስም እንዲህ ብቻል ጌታ ለምን ይመጣል !? እንደው የደሙን ዋጋ ስያቃልሉ።በነገራችን ላይ "በስሜ የሚትቀበሉትን "መጽሐፍ ስል ምን ማለት እንደሆነ በዚህ ገብተው ያንብቡ ፦ https://t.me/FistumTehadiso/92
"ጭራሽ እጣን ሰጥተ የዘላለም ሕይወት ማገኘት ከታቸለ" ከዚህ በላይ አልጋ በአልጋ የሆነ መንገድ አለን!? ያሳዝናል ። በእውነቱ እነዚህ የተጠቀሱት የዘላለም ሕይወት ለማግኘት ማረጋገጫ ተባሉ እንጂ እውነት ብሆን ሰው በዚህ ብቻ ያርፍ ነበር።ግን ውሸት ስለሆነ አያሳርፍም ሁለም መሮጥ ነው በከንቱ
አንድ የመጨረሻ ብዬ ልጨርስ ፦ ይገርማችኋል እነኚ እኮ አገልጋይ መስሎአችኋል ። ብቻ ከምንጩ ይነቀል ። ኢትዮጵያ ከደብተራ ጥንቁልና ነፃ ሆና ተለውጣ ማየት እናፍቃለሁ ።የኢትዮጵያን በረከትን የቀማው አወላዋይቱ ናት።ከምንጩ ይድርቅ በኢየሱስ ስም።
[1] ገድለ ተክለሃይማኖት ም.62 ቁ.3
[2] መ.ተስፋ ሚካኤል ታከለ(ትርጓሚ)፣ድርሳነ ኢያቄም ወሐና ዘሐሙስ፣2007፣ቁ.27 ገጽ 75።
[3] ድርሳን ሚካኤል ገጽ 5-7
Comments
Post a Comment