ሊቀ ካህናታች ኢየሱስ ክርስቶስ ነው
“እንግዲህ በሰማያት ያለፈ ትልቅ ሊቀ ካህናት የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ስላለን፥ ጸንተን ሃይማኖታችንን እንጠብቅ።” ዕብ 4፥14
☝ በምድር በሰዎች መካከል አልፎ ወደ ቅድስት የገባ ሳይሆን ሰማያትን አልፎ ወደ ቅድስተ ቅዱሳን የገባ ሊቀ ካህናት አለን ፣
☝ ስለዚህም "እርሱ ስላለን" ፥ በነገር ሁሉ ስለእኛ ፦ ይታያል ፣ ይረዳናል ፣ ደግሞም ጠበቃችን ነው ማለት ነው፣
☝ እንግዲህ "ስላለን" ይላል እንጂ "ስላሉን" አይልም ለብዙ ሰው እንደሚናገር ፣ምክንያቱም እርሱ ብቻ ብቸኛ ጠበቃችን ነው፤ሃሌ ሉያ።ኢየሱስ ክርስቶስ አሁን ሊቀ ካህናት ሆኖ በሰማይ ፣ ስለእኛ ያለ እና የተቀመጠ ፣ የእኛ ወካይ ሰው ነው፤ሃሌ ሉያ።
....................
“እንግዲህ ምሕረትን እንድንቀበል በሚያስፈልገንም ጊዜ የሚረዳንን ጸጋ እንድናገኝ ወደ ጸጋው ዙፋን በእምነት እንቅረብ።” ዕብ 4፥16
☝ ወደ እግዚአብሔር መቅረብ እንችላለንንና!
☝ ምከንያቱም በደሙ ተሸፍነናል!
☝ በማንም በምንም በኩል ሳይሆን እርሱ ኢየሱስ ክርስቶስ ስላለን በእርሱ በኩል ወደ እግዚአብሔር እንቅረብ ፣
☝ እርሱ ወደ እግዚአብሔር የሚያቀርብ እና የሚረዳንን ጸጋ ልያሰጥ የሚችል ሊቀ ካህናት ነው ( ሙሉዑ ሰውም ነውና )
...................................
“እርሱም በስጋው ወራት ከሞት ሊያድነው ወደሚችል ከብርቱ ጩኸትና ከእንባ ጋር ጸሎትንና ምልጃን አቀረበ፥ እግዚአብሔርንም ስለ መፍራቱ ተሰማለት፤” ዕብ 5፥7
☝መጽሐፍ እንደሚል ከሥጋው ወራት በፊት ወይንም በኃላ (ከትንሳኤው በኃላ) ምልጃን አቀረበ አይልም ፣
☝ጸሎት እና ምልጃውን ወደ ፉጡር አላቀረበም ፤ወደ አባቱ ብቻ እንጂ ፣
☝ለብ ያለ ምልጃ ሳይሆን ያቀረበው ፣ ልባዊ ልቅሶ እና ጩኸት ያከለ ነው፣
☝ እግዚአብሔርን መፍራት በመታዘዝ ይታወቃልና ፣ እርሱ ፍጹም መታዘዝን ታዘዘ፣አባቱም ሰማ ፣
☝ ከክርስቶስ በፊት ልመና ያቀረቡት በፍጹም እሺታ አልታዘዙም ፣ እርሱ ብቻ ግን አንዳች አለመታዘዝ እና ነቀፋ ሳይኖር ታዘዘ ፣ ተሰማለትም።
[ሌሎቹ ያልተሰማላቸው ሊቀ ካህናት ናቸው፤ኢየሱስ ግን የተሰማለት ብቸኛ ሊቀ ካህናት ነው፤ሃሌ ሉያ።]
..................................
“ምንም ልጅ ቢሆን፥ ከተቀበለው መከራ መታዘዝን ተማረ፤”— ዕብ 5፥8
☝በተፈጥሮ ልጅነት መጀመሪያ ከማይባልበት ጀምሮ የሚታዘዝ ብሆንም ፣ ግን ሰው ሆኖ ለዚህ ተግባር እንድታዘዝ ስላክ የመጀመሪያው ነው ፣
☝ሰው በመሆኑ አድስ ተፈጥሮ ገንዘቡ ስላደረገ ፣ በዚህ ሰውነቱም በፍጹም መታዘዝ ስለታዘዘ ፣እንደ አድስ መታዘዝ ቆጥሮ "መታዘዝን ተማረ" አለ ፣
☝ "መታዘዝን ተማረ" ማለቱ በአድሱ ተፈጥሮውም በፍጹም መታዘዝ ፥ መታዘዝ መቻሉን ለመግጽ ነው፤ከዚህ በፊት የማይታዘዝ ሆኖ አይደለም ፣
☝ ስለዚህም የመከራው ብዛት አበረታው፣
[[የሊቀ ካህናታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መታዘዝ የማይለወጥ ፣የማይናወጥ፣ፍጹም መታዘዝ ነው]]
...................................
“ከተፈጸመም በኋላ በእግዚአብሔር እንደ መልከ ጼዴቅ ሹመት ሊቀ ካህናት ተብሎ ስለ ተጠራ፥ ለሚታዘዙለት ሁሉ የዘላለም መዳን ምክንያት ሆነላቸው።” ዕብ 5፥9-10
☝ ምልጃው ከተፈፀመ በኃላም ሊቀ ካህናት ነው፤አልተሻረም፤ለዘላለም አይተካም፣
☝ ስለዚህም ለሊቀ ካህናቱ ለኢየሱስ የሚታዘዙት ሁሉ እንዲድኑ ምክንያት ሆነ፤በሠራው ሥራ ፣
☝ስለ ተወሰኑ ብዱኖች እንደሚናገር ሳይሆን ስለሰው ልጆች ሁሉ መዳን ፣ ለዚያውም ለዘላለም መዳን ምክንያት ስለመሆኑ ለመግለጽ "ለሚታዘዙለት ሁሉ" አለ፤ለሁሉም ነውና ፣
☝ ለመዳን ለሊቀ ካህናቱ መታዘዝ፤ሃጥአተኛ መሆኑን ማመን እና መናዘዝ ይጠበቃልና ።
[[ ሊቀ ካህናታችን የሁሉ ሰው የመዳን ብቸኛ ምክንያት ነው፤ሌላ የመዳን ምክንያት የለም ]]
....................................
“እርሱ ራሱ ተፈትኖ መከራን ስለ ተቀበለ የሚፈተኑትን ሊረዳቸው ይችላልና።”— ዕብ 2፥18
☝ ሊቀ ካህናታችን ለራሱ ሳይፈተን መከራ ሳይቀበል እንዲሁ የተቀመጠ ሳይሆን ተፈትኖ መከራ የተቀበለ ነው ፣
☝ የተቀመጠው በድካማችን ልረዳን ነው እንጂ በድካማችን ልፈርድብን አይደለም፤አሁን ፣
☝ የሚረዳን በደሙ ሃጥአታችንን አጥቦ ወደ ዙፋኑ በማቅረብ ነው፤ የሚያስፈልገን ጸጋን (እንደገና የሚያቆመን ጸጋን) በመስጠት ነው ፣
[[ ሊቀ ካህናታችን ልረዳን እንጂ ልፈርድብን የተቀመጠ አይደለም፤አሁን ]]
.....................................
“ስለዚህ..፥ የሃይማኖታችንን ሐዋርያና ሊቀ ካህናት ኢየሱስ ክርስቶስን ተመልከቱ፤” ዕብ 3፥1
☝አብርሃም የእምነት አባት ተብሎ ብቆጠረም ወደ አጋር ገብቷል ፣ ኢየሱስ ግን በፍጹም መታመን የታመነ ነው ዕብ 2፥13 ፣
☝ ሙሴ ትሁት ነው ግን እንደ ኢየሱስ ጉዱለት የሌለበት አይደለም፤ኢየሱስ ብቻ ፍጹም ትሁት ነው ፣
☝ስለዚህም ሰዎች ላይ ጉድለት አለ፤ጉድለት የሌለውን ኢየሱስን ተመልከቱ፤አስቡም ይለናል ፣
☝መምህራንን ተመልክተን ሳይሆን የኢየሱስን መስቀል ሥራ ተመልክተን ልንከተለው ይገባናል።
[[ ሊቀ ካህናታችን እያሰባችሁ ሩጫውን ፈፅሙ ]]
....................................
“ክህነቱ ሲለወጥ፥ ሕጉ ደግሞ ሊለወጥ የግድ ነውና።”— ዕብ 7፥12
☝ በብሉይ ኪዳን ክህነት ለመቀበል ሕጉ ፦ ወንድ መሆንን ፣ የሌዊ የዘር ሀረግ መሆንን ይጠይቃል፤ኢየሱስ ግን ከይሁዳ ነገድ ነው፤ የክህነቱን ሕግ ተሽሯል፣
☝ሌዋውያን የሚያገለግሉት እስከሚሞቱ ነው፣ኢየሱስ ግን የክህነት ሕጉን ቀይሮ ለዘላለሙ ሳይሻር ፣ ከሞት በኃላም ሊቀ ካህናት ሆኖ እያገለገለ ነው፣
☝ስለዚህም ክህነቱ ከጊዜያዊ ወደ ዘላለማዊ ስለወጥ የክህነት ሕጉም ተቀየረ ፣
☝ የብሉይ ሕግ ሌዋውያን የሆኑትን ደካሞችን ይሾማል፣የተለወጠው ሕግ ደግሞ አንዳች ድካም የሌለውን ይሾማል(ፍጹም የሆነው ይሾማል) ፣
☝ የተለወጠው ሕግ ፍጹም የሆነውን ስለሚሾም ዕብ 7፥28 ፣ ከኢየሱስ ውጭ ፍጹም የለም ፤ከኢየሱስ ውጪ ሌላ የሚሾም አይኖርም የሚተካው ፣
☝ ኢየሱስ ክርስቶስ ወርሶ ሳይሆን ስለሚገባው ተሹሞ ነው ፤ ሃሌ ሉያ።
[[ሊቀ ካህናታችን የክህነትን ሕግ ሽሮታል፤ክህነቱ በፍጹምነት ነው፤ፉጡር ደግሞ ፉጹም አይደለም፤ስለዚህም ፉጡር ሊቀ ካህናት መሆን አይችልም]]
.....................................
“እንግዲህ በምድር ቢኖርስ፥ እንደ ሕግ መባን የሚያቀርቡት ስላሉ፥ ካህን እንኳ ባልሆነም፤”
— ዕብራውያን 8፥4
☝ኢየሱስ ምድራዊ ብቻ ብሆን(ሰው ብቻ ብሆን)የብሉይ ሊቀ ካህናት መሆን አይችልም፤ ምክንያቱም ሕጉ ለሌዋውያን ብቻ የፈቀደ ነው፣
☝ እንደ ብሉይ ሕግም መባን ለማቅረብ የተመረጡ ስላሉ ኢየሱስ በምድራዊ መቅድስ ሊቀ ካህናት ሆኖ ማገልገል አይችልም ፣
☝ ስለዚህም በተቃራኒው ደግሞ በሰማይ መቅደስ ለማገልገል ፍጹም መሆን ያስፈልጋል፤ጉድለት አልባ ፉጡር ደግሞ የለም፣
☝ ስለሆነም በሰማይ መቅደስ ሊቀ ካህናት ለመሆን ሙሉዕ ሰው እና ሙሉዑ መለኮት መሆን ያስፈልጋል፤ይህንን የሆነው ኢየሱስ ብቻ ነው ፣
[ሊቀ ካህናታችን ሰውም መለኮትም ነው]
.....................................
“ፊተኛይቱም ድንኳን በዚህ ገና ቆማ ሳለች፥ ወደ ቅድስት የሚወስደው መንገድ ገና እንዳልተገለጠ መንፈስ ቅዱስ ያሳያል።”ዕብ 9፥8
☝ አሁንም የሙሴ ሥራዓት የሚያገለግል ከሆነ አዲስ ኪዳን አልተገለጠም ፣
☝ የሙሴ ድንኳን ከአዲሱ ኪዳን ጋር ተደምሮ ወይንም ተቀይጦ አይቀጥልም ፣
☝ የሙሴ ድንኳን በራሱ ፍጹም አይደለም፤ሰማያዊ ድንኳን ግን ፍጹም ነው ፣
☝ የሙሴ ድንኳን ከዚህ ፍጥረት የሆነ፤ታላቅ ያይደለ ሲሆን የአዲሱ ኪዳን ድንኳን ግን ታላቅ ነው ዕብ 9፥11፣
☝የሙሴ ድንኳን "ተጠንቅቀ ሥራ" የተባለ ነው ፤ በሰው እጅ ስለሚሰራ፣ የአዲሱ ክዳን ግን ያለማስጠንቀቂያ በራሱ በጌታ የተሰራች ናት ፣
☝ስለዚህም ከሙሴ መቅደስ ወጥታችሁ በኢየሱስ ወደተሰራች መቅደስ ግቡ ፣
☝ አንድ መቅደስ ( ድንኳን ) እና አንድ ሊቀ ካህናት ብቻና ብቻ ነው ያለን ፣
☝ የሙሴ ድንኳን ፦ታቦትን፣መባን፣ቅድስተ ቅዱሳንን፣መቅረዝ.. እናም የመቅደሱ ካህናት ይዞዋል፤አሁንም ይህ እስካለ ድረስ አድስ ኪዳን አልተገለጠም ፤ እንዲያ የሚያደርጉት (ካሉ) የአዲስ ክዳን መጋረጃዎች ናቸው ፣
[[ሊቀ ካህናታችን በተቀየጠ መቅደስ ሥራዓት አይገለጥም፤መቅዱሱም አንድ ብቻ ነው]]
..........................
“ጠላቶቹም የእግሩ መረገጫ እስኪደረጉ ድረስ ወደ ፊት ይጠብቃል።” ዕብ 10፥13
☝ ሊቀ ካህናታችን አንድ ግዜ ቆሜ ፣ ለዘላለሙም ተቀመጠ፤የተቀመጠው በእግዚአብሔር ቀኝ ነው(ስልጣን አለው) ፣
☝ ሊቀ ካህናታችን ፍጹማን ልያደርግ የሚችል መስዕዋት ስላቀረበ ፣ የኀጢአት መታሰቢያ የለበትም ግን የኀጢአት መወገጃ አለ፣
☝ስለዚህም አስቀድሞም እንደተገለጸው አሁን ክርስቶስ አይለምንም፤ደም አያቀርብም፤አንዴ ለምኖ አንድ ግዜ ብቻ ደም አቅርቧልና፤ከበቂ በላይም ሆነ(ነው)፣
☝አሁን ሊፈርደን በአብ ፊት አልተቀመጠም ፣ ልራራልን እና አቂም ለመስጠት ስልጣን ይዞ ተቀመጠ እንጂ፣
☝አሁን ሊቀ ካህናታችን የሚጠብቀው ተቃዋሚዎች ሁሉ እስከ ሚገዙለት ነው ፤አዎ የአሕዛብ መጨረሻ አለ፤መረገጫው የሚሆኑበት ሰዓት።ራዕይ መጽሐፍ ይህንን ትንብት ቃል ከዕብራውያን ጸሓፍ ጋር ይተባበራል ፦ “አሕዛብንም ሁሉ በብረት በትር ይገዛቸው ዘንድ ያለውን ልጅ ወንድ ልጅ ወለደች፤ ልጅዋም ወደ እግዚአብሔርና ወደ ዙፋኑ ተነጠቀ።”— ራእይ 12፥5
☝ይህ ትንቢት ቃል አሕዛብ ሁሉ ስሰግዱለት እና ኢየሱስ ክፍ ብሎ ስታይ ትንቢቱ ይፈፀማል ፣
[[ሊቀ ካህናታችን ተቀምጦ ፣ አሕዛብ ሁሉ የሚበረከኩበት ግዜ ይጥብቃል]]
.....................................
“እርሱ ግን ስለ ኃጢአት አንድን መሥዋዕት ለዘላለም አቅርቦ በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀመጠ፥”ዕብ 10፥12
☝ ሊቀ ካህናታችን አሁን አልቆመም ማለትም እየለመ አይደለም (አባት ሆይ ይቅር በላቸው አይልም፤አሁን)፣
☝ "በቀኙ ነው የተቀመጠው " ማለት ፣ ሊቀ ካህናታችን እየፈረደ ነው ማለት አይደለም ፤ይልቁንም ስልጣን አለው ማለት እንጂ ፣
☝"በቀኙ ከተቀመጠ የሊቀ ካህናታችን ስልጣን አሁን ምንድነው !?" ብንል ፣ ስልጣኑ መራራት ፣ ከመራራቱ የተነሳ ከወደቅን የመነሳት አቂምን መስጠት ነው ዕብ 5፥18፤ዕብ 4፥16 ፤በድካማችን የመፍረድ ሳይሆን የመርዳት ማንነት አለው፣
☝ አስተውሉ "ተቀመጠ " ስለተባለ እየፈረደ ነው ማለት አይደለም ፤በእርግጥም አሁን ግን ያልተቀበሉትን ለመርገጥ እየጠበቀ ነው ፣
☝ስለዚህም "በአብ ቀኝ ተቀምጧል"ስባል ፣ እንደ ክርስቲያን በአዕምሮአችን ማሰብ ያለብን "የሞት ፍርድ" ሳይሆን የሚራራ ፣የሚቀበል ፣የሚያነሳ ፣ የሚያቆም ፣ የእንደገና አምላክ መሆኑን ነው።በእርግጥ አሕዛብ ይፍራ ፣ ይደንገጥ እየተጠባበቀ ያለው እነሱን ለመፍረድ ለመርገጥ ነውና ፣
☝የኢየሱስ ሊቀ ካህናትነት ላመኑት ብቻ ስለሆነ አሕዛብ ዘንዶ ጥቂት ጊዜ መኖሩን አውቆ ብፈራገጥ አይገርምም ፣
[[ሊቀ ካህናታችን ላመኑት ለመመራት ፣አቂምን ለመስጠት የተቀመጠ ሲሆን ላላመኑት ግን ለመርገጥ እየተጠባበቀ የተቀመጠ ነው፤ወዮ]]
...............................
“ቅዱሳን ወንድሞች ሆይ፥ የሃይማኖታችንን ሐዋርያ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።"
☝ ሊቀ ካህናታችን ሐዋሪያ ነው፤የተላከ ነው።ምንም እንኳን የተላከ ብሆንም እርሱ ራሱ ላኪም ነው ፣
☝ሌሎች እንደ ሙሴ በቤቱ የሚያገለግሉ ባሪያዎች ናቸው፤እርሱ ግን የቤቱ ባለሥልጣን ነው፣
☝ሌሎች ክርስቶስ በመሠረተው ቤተክርስቲያን የሚያገለግሉ ናቸው ፣ ሊቀ ካህናታችን ግን ብቸኛ የቤተክርስቲያን መስራች እና ባለሥልጣን ነው ፣
☝ሌሎች "እውነት፣ሕይወት እና መንገድ እርሱ ነው"ብለው ይጠቁሙታል ፣ ሊቀ ካህናታችን ግን ራሱ "እውነት ሕይወት እና መንገድ" መሆኑን ይመሰክራል ፣
☝ሌሎች በእርሱ ሥልጣን አጋንንት ያንቀጠቅጣሉ፣እርሱ ግን በራሱ ስልጣን ያንበረክካል፣
☝ሌሎች ሐዋርያት እርሱ "ብርሃን ነው"ብለው ይመሰክራሉ ፣ እርሱ ግን ብርሃን ነኝ ይላል ፣
[[ሊቀ ካህናታችን ተላኪ ብቻ ሳይሆን ሹዋምም ላኪም ነው፤አምላክ ነውና ]]
....................................
“..፥ የተጠሩት የዘላለምን ርስት የተስፋ ቃል እንዲቀበሉ እርሱ የአዲስ ኪዳን መካከለኛ ነው።” ዕብ 9፥15
☝ሊቀ ካህናታችን መካከለኛ ነው፤ከብዙዎቹ አንደኛው መካከለኛ ሳይሆን ብቸኛ መካከለኛ ነው፣
☝ሊቀ ካህናታችን ሰውም አምላክም ስለሆነ የአምላክነት እና የሰውነት መሃል ነው፣
☝"የአድስ ኪዳኑ መካከለኛ ነው" ማለት እግዚአብሔር እና ሰው የሚገናኙበት "ድልድዩ" እሱ ነው ማለት ነው፣
☝እርሱ ብቻ ብቁ ስለሆነ ፣ ሌላ የሚደመር ወይንም የሚቀየጥ መካከለኛ አላስፈለገውም ፣ ሌላም የመሆን ብቃቱ የለውም ፣
☝እርሱ "መካከለኛ ነው" ማለት የኪዳኑ አስታራቂ ነው ማለት ነው፤ለዚያውም ብቸኛ አስታራቂ ነው፣
☝ያለ እርሱ ወደ እግዚአብሔር መቅረብ ፣ መምጣት የለም፤በዚያ ልክም ያለ እርሱ እግዚአብሔር ራሱ የሚቀርበው ሰውም የለም ፣
☝መጽሐፍ ስናገር “አንድ እግዚአብሔር አለና፥ በእግዚአብሔርና በሰውም መካከል ያለው መካከለኛው ደግሞ አንድ አለ፥ እርሱም ሰው የሆነ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው፤” — 1ኛ ጢ 2፥5
☝እርሱ የአድስ ኪዳን ብቸኛ አስታራቂ ብቻ ሳይሆን ብቸኛ ተያዥም፤ዋስም ነው ( “እንዲሁ ኢየሱስ ለሚሻል ኪዳን ዋስ ሆኖአል።” — ዕብ 7፥22)፤ ሃሌ ሉያ ።
[[ስለዚህም አንድ አስታራቂ አለን፤አንድ እግዚአብሔር አለን፤አንድ ኪዳን አለን፤አንድ ዋስ አለን፤ሃሌ ሉያ]]
..................................
ዕብራውያን 5
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹¹ ስለ እርሱም የምንናገረው ብዙ ነገር አለን፥ ጆሮቻችሁም ስለ ፈዘዙ በቃል ልንተረጕመው ጭንቅ ነው።¹² ከጊዜው የተነሳ አስተማሪዎች ልትሆኑ ሲገባችሁ፥ አንድ ሰው ስለ እግዚአብሔር ቃላት መጀመሪያ ያለውን የሕፃንነትን ትምህርት እንዲያስተምራችሁ እንደ ገና ያስፈልጋችኋልና፤ የሚያስፈልጋችሁም ወተት ነው እንጂ ጠንካራ ምግብ አይደለም።
[[ቃሉ እንደሚል እስካሁን ስለ ሊቀ ካህናትነቱን ያወሳነው የዚህ ዘመን አእምሮ ሕፃንነት የተነሳ ነው]]
....
""በእግዚአብሔር ቀኝ የተቀመጠም ፣
በእግዚአብሔር ፊትም ያለ ነው፤ስለዚህም ኢየሱስ ጻድቅ ፈራጅም አማላጅም ነው""
" በእግዚአብሔር ቀኝ የተቀመጠ ሊቀ ካህናት ነው " ማለቱ አሁን ስለመፍረዱ የሚሳይ ሳይሆን ምህረትን እና ጸጋን ለመስጠት ሥልጣን መኖሩን የሚያሳይ ነው ዕብ 2፥18 ፤ 4፥18 ። በእርግጥም ለመፍረድ ፣ለመርገጥ ነው የተቀመጠው፤ፍርዱ ግን ወደ ፊት ነው እንጂ አሁን አይደለም። [[የሚረግጠው ያላመኑትን ነው]]
ኢየሱስ በእግዚአብሔር ቀኝ መቀመጡ እሙን እንደሆነ ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት መኖሩም እሙን ነው ዕብ 9፥24።በአንደ ሁሉ በሁሉ ሆኖ መገለጡ ድንቅ ነው።በእግዚአብሔር ቀኝም በእግዚአብሔር ፊትም፤ ነው።
*"በእግዚአብሔር ቀኝ መቀመጡ መፍረዱን ብቻ ያሳያል" እንደው እሺ ብንል እንኳን በእግዚአብሔር ፊት መኖሩ አማላጅነቱን እንደሚያሳይ አያጠራጥርም። ስለዚህም ኢየሱስ ጻድቅ ፈራጅም አማላጅም ነው።
ለዚህም ነው መጽሐፍ ስናገር አሁንም ኢየሱስን "አገልጋይ ነው" የሚለው ፦ “እርሱም የመቅደስና የእውነተኛይቱ ድንኳን አገልጋይ ነው፥..።”ዕብ 8፥2 አዎን ኢየሱስ ሳይለምን፥ተቀምጦ፥የሚያስታርቅ ብቸኛ አማላጅ ነው ።ልዩ ነው የእርሱ፤አሰራሩ።
ሃሌ ሉያ
Comments
Post a Comment