ክርስቶስ ሁለት ልደት አለው !?
ኢየሱስ ክርስቶስ ሁለት ልደት አለውን !? #ኢየሱስ ክርስቶስን ተዋህዶች "ሁለት ልደት አለው ብለው" ያስተምራሉ ፤""ቅድመዓለም ከአብ ያለእናት ድኅረ ዓለም ከድንግል ካለአባት ከድንግል የተወለደው ነው። "" በማለት ። ቅብአት የሚባሉት ደግሞ ሦስት ልደት ነው ይላሉ ፣ በሁለት ልደት ዕሳቤ ላይ ፣ " አብ ከድንግል ማርያም ማኅጸን በሥጋ ወለደው " ይህንን ሃሳብ በመጨመር ያምናሉ ። የቅብአቶች አስተምህሮ በግልጽ ውድቅ የሆነ ስለሆነ ትኩረቴን በተዋህዶች አስተምህሮ ላይ አደርጋለሁ ።በተዋህዶች አስተምህሮ ላይ በስፋት የሚያትተው ሃይማኖት አበው መጽሐፍ ነው፤ከቀደምት አባቶች። ይህንን የሚያነብ ሰው ጸሐፊው አባቶችን በስህተትነት ለመፈረጅ ሳይሆን ሰው መሠረታዊ ነገር እንዳይረዳ ያደረገ አገላለጽ ስለሆነ ፣ለማስገንዘብ እና የምናምነው እምነት የተጠቀምነው ቃላት ስለማይገልጹ ልዩ ትርጉም ስለሚሰጡ እርማት ለመስጠት በማሰብ ብቻ ነው ።ሃይማኖት አበው ላይ ብፁዕ ዘሄሬነዎስ ስለኢየሱስ ክርስቶስ እንዲህ ይለናል ፦ "" በሰው ባህሪይ ሰው የሆነ እርሱ ነው ፣ከአብ የተወለደ ፣ ከባህሪይ አምላክ የተገኘ የባህሪይ አምላክ ፣ የዘለዓለም ንጉሥ እርሱ ነው።.."" ከዚህ ክፍል የሚንረዳው ኢየሱስ ፦ ✍️ ሙሉእ ሰው እንደሆነ፣ ✍️ከአብ እንደተወለደ ና ✍️ ከአብ የተገኘ አምላክ እንደሆነ ነው። *ትኩረት የምናደርገው በኢየሱስ ከአብ መወለድ ላይ ነው።ስለዚህም ከአብ "እንዴት ተወለደ ? አምላክ ሆኖ ሳለ " ብባል መልሳቸው ፣ አብ በአፉ ቃል እንደወለደው ከመጽሐፉቱ እንረዳለን ፦ "ቃል ከአብ ያለ ድጋሚ ወጣ ፣ድንግልም ያለ ድካሚ ወለደችው "እን...